Friday, September 20, 2013

ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን ለነፃነት መታገል ያስፈልጋል !!

እኔ እምለው ኢትዮጵያውያን አንድ እንዳይሆኑ ተረግመዋል እንዴ?

Ethnic Politics Split US Ethiopians እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ በመላው አለም በተለይ በአሜሪካ፣ እንደገና በተለይ በዋሽንግተን የሚኖሩ ብዙ ዜጎች አሎዋት፡፡ ከትግራይ ይሁን ከሶማላ፤ ከኦሮሚያ ይሁን ከአማራ፣አፋር፣ደቡብ፣ቤን ሻንጉል፣ ድሬ፣ ሸገርብቻ ከየትም ይሂደ ከየት የሁለም ኢትዮጵያውያን የስደት መነሾበፖለቲካ አልያም የተሻለ ህይወትፍልጋ ከመሆን አይዘልም፡፡

(በሀገሩ መኖርማ ማን ይጠላል …)
ብዙ ጊዜ የማስበው ታዲያ ኢትዮጵያውያኑ በሰው ሀገር ሲኖሩ እንዴውም ከሀገር ውስጥ የበለጠ አንድነትና መግባባት ወይም አብሮ የመኖር ስሜት ይኖራቸዋል ብዬ ነው፡፡ በሰው ሀገር የመኖርን የህይወት ትግል ለመልመድና ለማሸነፍም ከሀገር ልጅ የበለጠ አለኝታ፣ አይዞህ/ ባይ እና አጋዥ የለምና፡፡ በተለያዩ አጋጣሚዎች የምሰማው ግን ከዚህ በተቃራኒው የሆኑ እውነታዎችን ነው፡፡ በጥርጣሬ መተያየት፣ የብሔርና የፖለቲካ ክፍፍልሌላም ሌላም፡፡ እርግጥ ነው ሁላችንም አንድ አይነት አቋም ሉኖረን አይችሌም፤ ከመሰረታዊ ጉዳዮች በስተቀር በእያንዲንደ ጉዲይ ሊይ የግድ ተመሳሳይ ሀሳብ እንዱኖረንም አይጠበቅም፡፡

የተለያየ የፖለቲካ አቋም ሉኖረን ይችላል፣ የተለያዩ ብሔሮች ልጆችም ልንሆን እንችላለን፤ ኢትዮጵያውያን በመሆናችን ግን እነዚህ ሁለ ነገሮች በህልውናችን ላይ አንደጥላ ማጥላት የለባቸውም፡፡ ደግሞም ከተቀራረብን እነዚህ ሁለ ነገሮች ሊታረቁና ሁላችንንም የሚያስማሙ ሀሳቦችን ለመፍጠር ይቻላል። የአፍሪካ የነፃነት ምሳሌ የሆንን ዜጎች ህብረ ብሔራዊ ውበታችንን በእያንዳንዳችን ፓስፖርት ላይ ካለው ኢትዮጵያዊነታችን ጋር የተጣበቁ የጋራ ተቀፅሊዎቻችንን (stereotypes) በማጥፋት የትም ቦታ አንገታችንን ቀና አድርገን ለመኖር ምቹ ሁኔታዎችን ልንፈጥርበት ይገባል፡፡

ልዩነቶቻችንን በማቻቻል የትም ይሁን የት በአንድነት መስራቱ ለዜጎቿና ለኑሮ ምቹ የሆነች ኢትዮጵያን ለመፍጠርና ዳግም ኢትዮጵያን ታላቅ ለማድረግ ያስችለናል፡፡ ይሄም በቅርቡ እውን እንደሚሆን ተስፋ አለኝ!

ይኧዉ ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያስተዳድረዉ ወያኔ/ህውሃት የህዝብ መብት በመንቀፍ ፣ዘረኝነትን በማስፋፋት ፣ሃገርን በመከፋፈል ፣ጎሰኝነትን በማስተማር፣ አገር በመዝረፍ ፣አገርን በመሽጥ፣ ሰዉን ከሚኖርበት ቀ በማፈናቀል፣ በመቻቻል እንዳይኖር በማድረግ፣ ዘር ከዘር ጥሊቻን ማስፈን፣ ቀጥሎበት ሃያ ሁለት ዓመታትን አስቆጠረ። እስከመቸ ይኧን ነገር ዝምብለን ማየት እንችላለን

እዚህ ጋር የሌለች ሀገራት ዜጎችን በሚያስቀና መልኩ አብሮ የመኖርና የመተባበር ባህልና ማህበራዊ ህይወት ያላቸው ባህር ማዶ አገር ኢትዮጵያውያን እንዳሉ መዘንጋት የለበትም፡፡ ይሁንና እነሱም ቢሆን እነዚህንና መሰል በኢትዮጵያውያን እህትና ወንድማማቾች መካከል እየተፈጠሩ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት መንቀሳቀስ ይኖርባቸዋል፡፡

ነጻነታችንን የቀሙን የወያኔ ዘረኞች ነጻነታችንን እንደቀሙን ለረጂም አመታት ለመግዛት እንዲመቻቸዉ በዘር፤ በቋንቋ፤ በክልልና በሃይማኖት ከፋፍለዉን ከሃያ አንድ ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የጀመሩትን እስራት፤ እግልት፤ ግድያና ዝርፍያ አሁንም እንደቀጠለ ነዉ። የወያኔ ዘረኞች ነጻነታችንን ቀምተዉ እየገዙን ቢሆንም ገዛናቸዉ ብለዉ እጃቸዉን አጣጥፈዉ አልተቀመጡም። ዜጎች ነጻነታቸዉንና መብታቸዉን እንዳይጠይቁ አፋቸዉን ያዘጋሉ፤ ለሌላዉ አንዳይቆም አገር፤ ስንደቅና ኢትዮጵያዊነት የሚባለ ትልልቆቹን የጋራ እሴቶቻችንን በየቀኑ ያፈርሳለ። ይህ የሚያሳየን ዜጎች ትልቅ ተስፋ ይዘዉ ቤተሰብ መስርተዉ ለራሳቸዉና ለአገራቸዉ የሚኖሩበት ግዜ እየጠፋ ተስፋ መቁረጥ፤ ስልትና የመከራ ኑሮ ዘመን እየከበበን መምጣቱን ነዉ። ይህ ከሆነ የነገዋን የነጻነት፣ የፍትህ፣ የዳሞክራሲ ባለጸጋ ኢትዮጵያን ለማየት እያንዳንዱ ዜጋ በቻለው አቅሙ ሁለ ጠንክሮ በመታገል እና ከራሱ ባለፈ ለሌላው ዜጋ የነጻነት ትግለን ጎራ እንዲቀላቀል ብልም የዚህ ትግሌ ባለቤት እንድሆን ያስፈልጋል፡፡የሀገራችን ህዝብ የነጻነት ችቦአቀጣጣይ የትግለ አካል በመሆን መስራት እንጅ፣ ከቶ ሌላ አካል፣ ሌላ ኃይል መጦ ነጻ ያወጣኛል በሚል በባርነት እየተገዛ መጠበቅ የለበትም። ነጻነትና ዳሞክራሲ በችሮታ አልያም ከሰማይ እንደሚወርድ መና የሚጠበቅ ስጦታ አይደለም። ነጻነት የራስን መሰዋእትነት ይጠይቃል። አለበለዚያላም አለኝ በሰማይ ወተትዋንም አላይእንዳይሆን ያስፈልጋል።

ነጻነት እኛ ሰዎች በቀደመት ወደዚህ አለም ስንመጣ አብሮን የሚመጣ የተፈጥሮ ፀጋ ነዉ። ነጻነት ከሌሎች የምንጠብቀዉ ወይም ማንንም ስጠን ብለን የማንጠይቀዉ ፈጣሪ ለእያንዳንዳችን ያደለንን፤ በዚህ አለም ቆይታችን ለደቂቃም ቢሆን እንዲነፍገን መፍቀድ የሌለብን ኃብት ነዉ። ነጻነታችን እጃችን ላይ ሲኖር በግለሰብ ለረጃ የምንደሰትበት፤ እንድንቀማ በጋራ የምንጠብቀዉና እንደ ወያኔ አይነቱ ፀረ ህዝብ ኃይል ሲቀማን ደግሞ በጋራ ታግልን ማስመለስ የሚገባን የግልና የጋራ ኃብት ነዉ። ዛሬ 22 የወያኔ አመታት በኋሊ እኛ ኢትዮጵያዉያን በድህነትና በረሀብ የምንጠቃዉ፤ በዘረኝነት አለንጋ የምንገረፈዉ፤ የምንሰደደዉ፤ የምንታሰረዉና የምንገደለዉ ይህንን ፈጣሪ ያደለንን ነጻነት የሚባል ኃብት ወያኔ አንድ፤ ሁለትና ሦስት እያለ ሲቀማን አፋችንን ዘግተንና እጃችንን አጥፈን ስለተመለከትን ነዉ። መፈናቀላችን፤ስደታችን፤ ዉርደታችንና በገዛ አገራችን ሁለተኛ ዜጋ ሆኖ መኖራችን እንዲያበቃ ለማድረግ ያለን ብቸኛ አማራጭ ሌሎች መጥተዉ ነጻ ያወጡናል ከሚለዉ አመለካከት ተላቅቀን ነጻነታችንን ለማስመለስ ህዝባዊ ትግለን መቀላቀል ብቻ ነዉ።

የኢትዮጵያ ህዝብ በወያኔ የዘር በትር አለንጋ የሚደርስበት ግርፋት፣ ስቃይ፣ ርሃብ፣ ስደት፣ እንግልት በራሱ በህዝቡ ላይ ነው። ስለዚህ ህዝቡ ራሱ ለራሱ ነጻነት፣ በእምቢ አልገዛም ባይነት የሚነሳበት ጊዜው አሁን ነው። ነጻነትን ከነጻ አውጭዎች በመጠበቅ እስከመቼ የወያኔ የጥይት ሰለባዎች እንሆናለን?

ወገን ሁለ ለራሱ ነጻነት፣ ህልውና ሲል የለውጡ እንቅስቃሴ ታጋይ የመሆን ኢትዮጵያዊ ግዴታውን እንዲፈጽም ጥሪ ማድረግ ይገባል ፡፡ ለአገሩ፣ለማንነነቱ መሰዋእትነት ለመሆን እንደሚኮራ ሁለ አገሩም በሱ ትኮራለች ፡፡

ወያኔ 22 ዓመት ውስጥ የሰራው ወንጀል በወገናችን ላይ እንዲህ በቃላት ተዘርዘሮ አያልቅም።ይህ አልበቃ ብሎን። ታድያ ምንድን ነው አንድ ሆነን ከመታገል ፈንታ መለያየትን መረጥን!

ኢትዮጵያውያን አንድ እንዲይሆኑ ተረግመዋል እንዴ?


ከቃልኪዳን ካሳሁን


kassahun.kalkidan@yahoo.n