Monday, November 12, 2012

መቻቻል ምንድነው?


ብዙ አንገብጋቢ የሆኑ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች አሉ፡፡ የቱን ጥለን የቱን እንደምናነሳ ራሱ ይቸገራል፡፡ ወዲህ ስንል በፖለቲካው መድረክ የዴሞክራሲው አፈናና እመቃ ገዝፎ ይታያል ብቻ ሳይሆን የማፊያው ሥርዓት - አልባ የወያኔ ሥርዓት መፈናፈኛ አሳጥቶን ይገኛል፡፡ ወዲያ ስንል የኑሮ ውድነቱ ከጥቂት ዘመነኞችና አጭበርባሪ ተውሳኮች በስተቀር አብዛኞቻችንን በቁማችን ገድሎ ቀብሮናል፡፡ እንዲያ ወዲያ ስንል ደግሞ በቂ የእህል ምርት ያለመኖር፣ ሥራ አጥነት እንዲሁም በዬጊዜው በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ በሚሄድ የሕዝብ ብዛት ምክንያት እየተባባሰ የመጣው የምግብ ዕጥረት እያስከተለው ያለው ርሀብ በቀላል ሊድኑ ከሚችሉ በሽታዎች ሳይቀር እየተባበረ ሕዝብን እየፈጀ ነው፡፡ በጥቅሉ እንደ አንድ ማኅበረሰብ በመኖርና ባለመኖር አስቸጋሪ ምርጫዎች ውስጥ ተቀርቅረን የአንድዬን መልስ ብቻ እየተጠባበቅን እንገኛለን፡፡ ከሁሉም በባሰ ደግሞ በሃይማኖት ሰበብ የገባብን ችግር የተግዳሮቶቻችንን ጡዘት በብዙ እርከን ከፍ አድርጎት ባልጠፋ ችግር አላስፈላጊ መሰናክል እየፈጠርን አንዳችን አንዳችንን የጎሪጥ በማየትነገ ደግሞ ምን ይፈጠር ይሆን?› በሚል ሥጋት ተወጥረን እንደነገሩ ይመሻል ይነጋል፡፡ በመሀሉ ግን ለዚህ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ውጥንቅጡ የወጣ ቀውስ የዳረጉን የውስጥ ምንደኞችና የውጪ ጌቶቻቸው በኛ የማያባራ ሥቃይ እየተዝናኑ ለነሱ የተመደበው መከራ እስኪደርስ ለጊዜው በሰው ደምና ወዝ በተፈጠረ ሀብት በመዘፈቅ በፈንጠዝያና በደስታ ይኖራሉ፡፡

ጆሮ የማይሰማው የለም፡፡ በቀደምለት 97 የወያኔ ዳግማዊ ቀይ ሽብር ለማጣራት በወያኔው መንግሥት ተቋቁሞ በነበረው ኮሚሽን ከነበሩት 10 አባላት የሁለቱን አቋምና የመንግሥት ወገንተኝነት በኢሣት ቴሌቪዥን ተከታተልኩ፡፡ እነዚህ የታሪክ ጉድፎችሼህኤሊያስናዶክተርመኮንን ዲልጋሳ የሚባሉት ናቸው፡፡ የነዚህሰዎችየሃሳብ ልዩነት መሠረት መንግሥት በወቅቱ ሕገ መንግሥቱን ጎዳና ነውጠኞችለመከላከል ባደረገው ጥረት የተጠቀመው ኃይል በእጅጉ ተመጣጣኝ እንደሆነና እንዲያውም እንደሼካው ከሆነ ተቃዋሚዎች 16 ሺህ ሰው መስዋዕትነት መንግሥትን እንገለብጣለን በማለታቸውና የሞተው ሰው ቁጥር አንድ ሺህ እንኳን ባለመሙላቱ ከተመጣጣኝም በታች መሆኑን ገልጸዋል - እንደሳቸው እሳቤ መንግሥት ዜጎችን በመጨፍጨፍ ረገድ ገና ሊያወራርደው የሚገባው 97. የሚወራረስ ቀሪ ሒሳብ አለው የሚሉ ይመስላል፡፡ እነዚህሰዎችእንደሰውም እንደሀገር ዜግነትም እንደመሬታዊ ነዋሪነትም በጣም ያሳፍራሉ፡፡ በጊዜው እዚህችው ሀገር ውስጥ አብረን ስለነበርን ያን የመሰለ የተቃዋሚዎች 10 እና 16 ሺህ ሰው የደም ግብር እሳቤ ሼካው ከየት እንዳገኙት አላወቅሁም፤ በወቅቱም ይህን መሰል ነገር ከማንም አልሰማሁም፡፡ ይህን መሰል ነገር ቢናገሩ ልሰማ እችል እንደነበር እገምታለሁ፡፡ ግን ሼሁ የአላህ ሰው ሳይሆኑ በግድያና በጭፍጨፋ የሚደሰተውና ካለነዚህም የማይኖረው የሸይጣን ልዑክ ስለሚመስሉኝ ከወያኔው በልጠው ወያኔን ሆነው ማየታችን ብዙም ሊያስደንቅን አይችልም፡፡ በዚያ ላይ እንደሰማሁት የዘር ጉዳይም እየሳባቸው ሃይማኖታቸውን ያስከዳቸው መስሎኛል፡፡ እንጂ እርግጠኛ ነኝ በእስልምና ሃይማኖት ውስጥ መብቱን የጠየቀን ዜጋ እንደዐይጥ ጨፍጭፍ የሚል ጥቅስ አይኖርም፡፡

በዚያ ኮሚሽን ውስጥ ሰብሳቢውን አቶ ፍሬሕይወትን ጨምሮ ስምንቱ ዕንቁ ዜጎች እውነትን አከበሯት፤ ለሥጋቸው ሳይሳሱ ለማተባቸው አድረውና ለወጡበት ሕዝብ ወግነው ነፍሳቸውን በፈጣሪ ዘንድ ትልቁን ቦታ አስሰጡ፡፡ ኤሊያስ የተባሉት ለሥጋቸው ያደሉ ሃይማኖተኛ ነኝ የሚሉ ሰው ግን በሰው ሃይማኖት እያላገጡ ቀላልነታቸውንና ግብዝነታቸውን በኩራት አጋለጡ፤ እንደዚያ በትዕቢት እየተወጣጠሩ የሰውን ሃይማኖት ለማሽሟጠጥ መሞከሩ ግን አለማወቅን እንጂ ብልህነትን አያመለክትም፡፡ ደግሞም በዘወርዋራም ይሁን በቀጥታ መንገድ ኢየሱስ(ዒሣ) ላይ የማሸሞር የሞራል ብቃት ያላቸው አይመስለኝም፡፡ ከእዳሪ በማያልፍ አንድ እንጀራና ከመሬት በማያልፍ የዘረኝነት ልክፍት የተሸነፉት የዚህ ሰው ስም በታሪክ ዐምድ በጥቁር ቀለም ተጻፈ፡፡ ያሳዝናል፡፡በኔ ሃይማኖትግራህን ሲመቱህ ቀኝህን አዙርለትየሚል ነገር የለም፡፡ በዚህ እኔ አላምንም…” እያሉ ሰይጣናዊ ጥቅሳቸውን ሲደረድሩ እኔ አዘውትሬ በምከታተለው የእስላማዊ ‘Peace TV’ በስብከቱ ከልብ የምወደው የዶክተር ናይክ ዛኪር ሃይማኖታዊ የመቻቻል ስብከትና አስተምህሮ በአእምሮየ ብልጭ አለብኝ፡፡ እኙህ ሰው ከጀሃነም እንጂ ከእስላማዊ ልሂቃን መንደር እንዳልመጡም ወዲያውኑ አመንኩ፡፡ አንድ የሃይማኖት አባት እንዲህ ያለ ንግግር በፍጹም አይናገርም - ሼህ ኤሊያስንና እሳቸውን መሰል የነፍስንና የሥጋን መንገድ ለይቶ የማያውቅ ካልሆነ በስተቀር፡፡ የኢጣሊያንን የቅኝ ገዢ ወታደር ባርከውና ቀድሰው ወደኢትዮጵያ የላኩት የሮማው (ሊቀ?) ጳጳስ ትዝ አሉኝ፡፡ በየሃይማኖቱ እኚህን መሰል ማፈሪያ ሰዎች መኖራቸውን ሳስብ በሃይማኖት ካባ ውስጥ የሚሠራው ወንጀልና ደባ ቁልጭ ብሎ ታየኝ፡፡ ምን ይሻለን ይሆን? ለጊዜው እኔ እንጃ!እያደር ግን ሁሉም እየጠራ ይሄድና እያንዳንዳችን የየመክሊታችንን እንደምናገኝ ጥርጥር የለውም፡

በኢትዮጵያ እንደሚታየው ያለ የሃይማኖቶች በተለይም የክርስትናና እስልምና እምነት ተከታዮች ተሳስቦና ተፈቃቅዶ መኖር የትም የለም ቢባል ማጋነን አይደለም፡፡ በዚህን የመሰለ የጋራ ኅላዌ ላይ ይህን የኤሊያስን የመሰለ ቆርፋዳ ንግግር መቸለስ ምን ዓይነት ቅሬታን ሊፈጥር እንደሚችል መገመት አይከብድም፡፡ ለራሳቸው የማያውቁ ገልቱ ግለሰብ ሆነው ሳሉ በፍቅርና በመተሳሰብ በሚኖሩ የሃይማኖት ተቋማት ላይ ሊዘሩት የተነሱትው ወያኔያዊ የጠብ ዘር ግን ሊታረም ይገባዋልና ሌሎቻችን ከኚህ በቁም የሞቱ ሰው ንግግር ተነስተን ልንማር የሚቻለንን ቁም ነገር እንማር፡፡ መማር ደግሞዕድሜም ሆነ የሃይማኖት ድንበር አይገድቡትም፡፡

ከስሙ ብንነሳ የተማሩቱ እንደሚነግሩን እስላም ማለት ሰላም ማለት ነው፡፡ ሰላም ማለት ደግሞ ለፍቅር ሲባል ሁለት ወገኖች ልዩነቶቻቸውን በመተው መሀል ድረስ በመምጣት የሚተቃቀፉበት እንጂ አንደኛው አንድ ጠርዝ ላይ ቆሞ ሌላኛው መጥቶ እንዲያቅፈው የሚጠብቅበት የትምክህት ዐውድ አይደለም፡፡ የሚሰበከውና በተግባር የሚገለጠው እስካልተለያየ ድረስ በእስልምናም ሆነ በክርስትና ተቻችሎ መኖር ዋነኛው የሕይወት ምሰሶ እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ነብዩ መሀመድ(..) በሀገራቸው ተከታዮቻቸው ሲገደሉና ሲሰቃዩ፣ ሰውን አክባሪ እንግዳን ተቀባይ የክርስቲያኖች ንጉሥ የሆነ በኢትዮጵያ መኖሩን ገልጸው ወደዚያች ሀገር እንዲሄዱ፣ ካልነኳቸውም እንዳይነኳቸው በጥብቅ አስጠንቅቀው ነበር ወደዚች ቅድስት ሀገር እንዲሰደዱ የመከሯቸው፡፡ ይሄ በታሪክ ተመዝግቦ ያለ ነገር ነው፡፡ ዛሬ ዓለም ዘወርዋራ ናትና አሁን በምንገኝበት ውሉ የጠፋበት አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ብንሆንም የጥንቱ ሊረሳ አይገባም፡፡ የሀገራችን መመሪያ ደግሞሀገር የጋራ ሃይማኖት የግልበመሆኑ የፈለጉትን ሃይማኖት እየተከተሉ መኖር ያልተከለከለ ብቻ ሳይሆን የተፈቀደም መብት ስለሆነ ከዚያ ማፈንገጥ ተገቢ አይደለም፡፡ የሌለ ችግርን እየፈጠሩ በሃይማኖት ሰበብ ምድርን ጦር አምጪ ማለት ደግሞ አይገባም፤ ፈጣሪም የለመኑትን የማይነሣ የነገሩትንም የማይረሣ ነውና ይህ ዓይነቱ ቅብጠት ቢቀርብን የተሻለ ነው፡፡ ዘመናችን 21 መቶ ክፍለ ዘመን የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ምጥቀት እየተመዘገበበት ያለ እንጂ የመካከለኛው መቶ ክፍለ ዘመን የክሩሴድና የጂሃድ ዘመነ ድንቁርና ባለመሆኑ ሁላችን በፍቅርና በውዴታ ተስማምተን መኖሩ ነው የሚያዋጣን፡፡ የፉክክር ደጃፍ ሊኖር አይገባም - ሳይዘጋ ማደሩ ለሁላችን ስለማይበጅ፤ ተባብረን በሮችንና ብርድ ወይም ንፋስ የሚገባባቸው ቀዳዳዎችን ሁላችን እየተሸቀዳደምን በፍቅር ስለፍቅር መዝጋት ይኖርብናል፡፡ እልህና ባለፈ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ብቀላና የቂም ቋጠሮ ደግሞ አንዱን ወገን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ይጎዳል፡፡ ያላጠፋን ወገን መበቀልሞ ላም ባልዋለበት ዓይነት ስለሆነ ከጅምሩ ሊታሰብም አይገባም፡፡ የየትኛውም ጠርዝ የለቀቀ አመለካከት ሰለባዎች ብንሆን ተጎጂዎቹ እኛና ቀጣዩ ትውልዳችን ብቻ   ነን፡፡

በአማርኛ አንድ ጥሩ አባባል አለ፡፡ያንቺ ልጅ የኔን ልጅ መትቶት ከሆነ ምች ይምታው፤ የኔ ልጅ ያንቺን ልጅ መትቶት ከሆነ ግን መቼምአለች አሉ አንዷ ፍርደ ገምድል፡፡ ማሰብ ያለብንእኔስ ብሆን? ይሄ ነገር ለኔስ ቢመጣ?...” ብለን ነው፡፡ የኅሊና ፍርድና እውነት ደግሞ ጉልበት ሲሰማን የሚጨቆኑ፣ ገንዘብ ስናገኝ የሚታፈኑ፣ ሥልጣን ሲኖር የሚደፈጠጡ፣ የሰው ምልዓት ሲታይ የሚረሱ ሊሆኑ አይገባም፤ የእውነት አምላክ ስላለ ሁሉን ያያልና፡፡

በግልጽ እንነጋገር፡፡ መሸፋፈን ይቅር፡፡ ሁሉም በጊዜው ይገለጣልና ሃቅን ተመርኩዘን ከአንጀት መነጋገሩ ቅሬታን ለማስወገድ የመጀመሪያ እርምጃ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያን በአንደኛው አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አንድ ሙስሊም ወይም አንድ የፕሮቴስታንት የክርስትና እምነት ተከታይ ገብቶ ካህናትና ምዕመናን በሚመስጥ የስብከት አገልግሎት ላይ እያሉ ይህ ሰውማርያም እንትን ነበረች! እንኳን ልታማልድ ለራሷም አልዳነችም! ከአላህ በቀር እግዚሃር የሚባል የለም! ሁላችሁም …› ቢሉ - በርግጠኝነት ነው የምነግራችሁ - ይህን መሰሉ ሰው እንዳበደ ተቆጥሮ ይታዘንለታል ይጸለይለታልም እንጂ ማንም ዝንቡን እሽ አይለውም፡፡ ምዕመናን በከዘራ ቀሳውስት በመቋሚያ ጨፍጭፈው ይገድሉታል የምትሉ ካላችሁ ተሳስታችኋል፤ ቢያንስ በዚህ ዘመን እንዲህ ያለ ሞኝነት የለም፡፡ የዚህ ዓይነት አጋጣሚዎችን እኔ ራሴ በተገኘሁባቸው የአምልኮት ጊዜዎች ስለታዘብኩ ሰው ከንፈሩን እየመጠጠ ሲያዝን እንጂምናባቱንና ይሄን እንትን ደብድበህ አባርልኝ፤ ወደዚያ አንገቱን ቀንጥስና ገላግልልኝ!› የሚል አንድም ሰው አላየሁም፡፡ ባይሆን ድምጹ የሚረብሽና ፕሮግራምን የሚያሰናክል ከሆነ ዘበኞች ተጠርተው ገፋፍተው እንዲያስወጡት ይደረጋል፡፡

ይህ ለምን ሆነ ስንል አንደኛ ምዕመናን በፈጣሪ ፍርድ መግባት እንደሌለባቸውና መቅጣትም መግደልም ማዳንም መኮነንም የእግዚአብሄር ተግባራት እንደሆኑ ይረዳሉ፤ ሁለተኛ የመጻሕፍት አስተምህሮ ሼህ ኤሊያስ ያላገጡበት ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚያስተምረን ጠላትህን ውደድ፣ ክፉን በክፉ አትቃወም፣ አትግደል፣መጎናጸፊያህን ቢጠይቅ እጀ ጠባብህን ጨምርለትስለሚሉ በነዚህ ተገቢ ሕግጋት አማካይነት ሕዝቡ በፈጣሪ ሥራ እንዳይገባ የለዘበ ስብዕናን ተላብሶኣል፤ ሦስተኛ የመንግሥትን ሕግ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ያም ሕግ ተጠርጣሪ ወንጀለኛንና ጥፋተኛን ይዞ ወደ ሕግ ማቅረብ እንጅ በኦሪታዊ የሀሙራቢዐይንን ለዐይንጥርስን ለጥርስወይም እንደዘመነ ጻፎችና ፈሪሣውያን ስቅሎ፣ ስቅሎየወል ሥርዓተ አልበኝነት አንድ ሰው እንደዐይጥ አይጨፈጭፍም፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ኋላ ቀር ፍርድ እጅግ አደገኛና ኃላፊነት የሚወስድን ሰው ደብዛ የሚያጠፋ ከትክክለኛ ስብዕናም የማይመነጭ ደመ ቁጡነት ነው፡፡
እዚህ ላይ አንድ የቆዬ ታሪክ እንይ፡፡ በጥንት ዘመን በግሪክ ሀገር ሁለት ሴና የሚባሉ ታዋቂ ሰዎች ነበሩ፡፡ አንዱ ፈላስፋና ባለቅኔ ነው፡፡ ሌላው የፖለቲካ አማካሪ ነው፡፡

የፖለቲካ አማካሪው ጥፋት አጠፋ ይባልና ሕዝቡ ሊገድለው በስሙ አማካይነት ሲያፈላልግ ያኛውን ሲና ይይዙታል፡፡እንዴ! እኔ እኮ ባለቅኔው ሴና ነኝ!› ቢላቸውግዴለም፣ ሴና በመሆንህ ብቻ እንገድልሃለን!› ብለው ያለጥፋቱ በስሙ ብቻ ገደሉት ይባላል፡፡ ይህ እንግዲህ ማኅበረሰብኣዊ ዕብደት ካልሆነ ሌላ ስም ሊሰጠው አይችልም፡፡ ሞብአደገኛነት እዚህ ላይ ነው፡፡ሞብደግሞ ያውሞብነው - ከሳሽ ተከሳሽ - ዳኛ ጠበቃ ሕግ ፍርድ ቤትየሌለው እጅግ አደገኛ የሀገርና የኅብረተሰብ ጠንቅ ነው፡፡ ይህን መሰሉን ነቀርሣ የሚጠቀሙበት ተንኮለኞችና ሥውር የጥፋት ተልዕኮ የሚያራምዱ ወገኖች ናቸው፡፡ በዚህ ረገድ የሚታየውን አደጋ ለመቀነስና በሂደትም ለማጥፋት ታዲያ ከየሃይማኖት ተቋማቱና ከምሁራን አካባቢ ራሳቸው ቀድመው የነቁ አብቂዎች ያስፈልጉናል - ዐይንን ገላጭ አንቂዎች፡፡ በሀገራችንም ሆነ በመላው ዓለም ይህን መሰሎች የዕብደት ምልክቶች ሞልተዋል፡፡ በጅምላ መፍረድ፣ በጅምላ እያሉ ንጹሓንን መፍጀት፣ በቅድመ አእምሮ ፍርድ በጥላቻ በመሞላት በአንዱ ወገን ላይ መዝመት፣በሃይማኖትና በዘር በቋንቋ ሰበብ ወገንን ማግለል፣እነዚህ ሁሉ ከእውነተኛው የፈጣሪ መንገድ የወጡ ናቸው፡፡  

ከፍ ሲል በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቢገኙ ብዬ እንደጠቆምኩት ዓይነት ከጤናማ አካሄድ የወጣ አሠራር በመስጊድ ውስጥ ቢገኝስ ብለን እንጠይቅ፡፡ የምናገኘው ምስል አያስደስተንም፡፡ መናገሩም ይቅርብኝ፡፡ ይሁንና በሀገራችን ይህን መሰሉ አዝማሚያ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ አይስተዋልም ነበር፡፡መቻቻልና በኔ ይቅር ባንተ ይቅር ነግሦ ይታይ ነበር፤ አንዱ የአምልኮ ቤት ሲሠራ ሌላኛው ይረዳው ነበር፡፡ በሩቅ የምንሰማውና የምንታዘበው ክስተት ወደ ሀገራችን እንዳይገባና ሥር እንዳይሰድ ተባብረን ከአሁኑ እናጨንግፈው፡፡ ነገሩ ያደረች ባቄላ ከመሆኑ በፊት ወደቀድሞው ለዘብተኛ አቋማችን እንመለስና ቆም ብለን እንተያይ፡፡ ሌላው ሁሉ ቀርቶ በየትም የሌለ የምግብ ልዩነት ያለው እንኳን እኛ ሀገር ውስጥ ነው፡፡ ይህም ልዩነት የተተከለው ባለማወቅ እንጂ በማወቅ አይመስለኝም - ለነገሩ ብዙም አልለያየንም፡፡

በእምነት ብቻ ሳይሆን በአኗኗርም ብዙ የባህልና የትውፊት መስተጋብሮች ያሉን ሕዝብ ስለሆንን ከፍ ሲል በድርበቡ የገለጥኩትን የመሰለ ከውጪ የመጣ ተፅዕኖ አያዋጣንም ብዬ በሙሉ ልብ ልናገር እወዳለሁ፡፡ የሚያዋጣን እንደስከዛሬው አንዱ ሲያጠፋ ሌላው እየገሰጸና እየመከረ ተግባብቶና ተነፋፍቆ መኖሩ ብቻ ነው፡፡ ይህን የምለው ብዙ ነገር በአእምሮዬ እየተመላለሰ ስለሚያስጨንቀኝ ነው፡፤ የአንዳንድ መጤ አክራሪዎች አካሄድ አላማረኝም፡፡ እነዚህ አክራሪዎች ደግሞ ሳይናገሩ ያስታውቃሉ፡፡ ኢትዮጵያዊውን እስላምና አክራሪውን እስላም በዐይነ ውኃቸው መለየት እንችላለን፡፡ አክራሪው ከፈሱ ጋር የተጣላ ነው፡፡ ከርሱ ጋር ለአንድ ደቂቃ እንኳን መነጋገር አይቻልም፤ የሚቀናው በኪሱ የወተፋትን ጩቤ አውጥቶአላሁዋክበር!› ማለትና ሬሣን አጋድሞ መፎከር ነው፡፡ ይህን መሰሉን አውሬነት በአልቃኢዳ የዩቲዩብ ዘግናኝ ምስል ስለተመለከትኩ ከዚህ ዓይነቱ ዐረመኔ ተግባር ሀገራችንን እንዲጠብቅ በበኩሌ በገራገሮቹ የእስላምና የክርስቲያን የጥንቶቹ አባቶችና እናቶች ስም አምላክን እለምነዋለሁ፤ እናንተም የበኩላችሁን ጸልዩ፡፡

ብዙዎቻችን ወያኔ የሚለውን ሁሉ ላለማመን ቃል አለብን፡፡ የእረኛው ቢጤ እንዳይሆን ግን እሰጋለሁ፡፡ ለዚያ ደግሞ ማስተማመኛ በተለይ ከልሂቃን ሙስሊሞች ብዙ እንጠብቃለን፡፡ እረኛው በጎቹን ቀበሮ እንደበላበት እያስመሰለ ሲጮህና ሰዎቹ እንዲደርሱለት በውሸት ሲያታልል ቆይቶ በመጨረሻው የምር ቀበሮዎች መጥተው ዘነጣጥለውለት ሲሄዱ ቢጮህ አንድም የሚመጣለት ሰው አጣ፡፡ እኛም እንደዚያ እንዳንሆን እፈራለሁ፡፡ ለዚህ መድሓኒቱ ርስ በርስ እንድንፈራራ ያደረገንን ብልሹ የወያኔ ሥርዓት በጋራ አስወግደን የጋራ መተማመን የሚፈጠርበትና አንዱ በሌላው ላይ ሸክም የማይጭንበትን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የመሠረትን እንደሆነ ነው፡፡

ኤሎሄ እንበል፡፡የኢትዮጵያ አምላክ ሆይ ጸሎታችንን ስማ፣ በመከራችን ቀን ፊትህን ከኛ አትመልስ፡፡ይህን ደግሞ ልብ እንበል! ሳዑዲ ኢትዮጵያ ውስጥ ከገባች ወዮ ለኛ! ኢራን ኢትዮጵያ ውስጥ ከገባች ወዮ ለኛ! ሦርያ ኢትዮጵያ ውስጥ ከገባች ወዮ ለኛ! አፍጋኒስታን ኢትዮጵያ ውስጥ ከገባች ወዮ ለኛ! ፓኪስታን ኢትዮጵያ ውስጥ ከገባች ወዮ ለኛ! አልሻባብና አልቃኢዳ አል ምናምን ሁላ ተጠራርታ ኢትዮጵያ ውስጥ ከገባች ወዮ ለኛ! “ስለዚህእንበልና ጸሎታችንን እንቋጭ - “ስለዚህ፣ አምላክ ሆይ ለጥፋት ያቆበቆቡ ፀረ - ኢትዮጵያ ኃይሎችን አስታግስልን፤ እስካሁን በደርግና በወያኔ ያየነው አበሳ ከበቂ በላይ ነውና ከአሁን በኋላ ምሕረትህን ላክልን፤ አሜን፡፡

እስላምም ክርስቲያንም ሰላማዊ ሕይወትን ይፈልጋሉ፤ አፈንጋጮችና በአክራሪነት የተሠለፉ ጥቂቶች ብቻ ናቸው በዕልቂትና በመሠያየፍ የሚያምኑ - ደግሞም እነሱ አይደሉም እየሞቱ ያሉት፤ ለዕኩይ ዓላማቸው የሚሞቱላቸውን ንጹሓን ዜጎች ከየሀገሩ እየለቀሙ ያዘጋጃሉ እንጂ እነሱ በምቹ ሥፍራ ተቀምጠው ነው በገንዘባቸው የሚፈልጉትን ሁከት የሚፈጥሩት፡፡ እነሱን የማያውቅ ማን አለ?  አንዷ ሀበሻ ከአንገቷ በስህተት የወጣን የወርቅ መስቀል በጣጥሶ መሬት ላይ በመጣል የሚረጋግጥ መንግሥታዊና ሕገ መንግሥታዊ ድጋፍ ያለው ፖሊስና ወታደር ነው የሚኖርባት - ሳዑዲ! ሌላ ቃል ብትተነፍስማ የሐሙሱ ጎራዴ ነው ተስሎ የሚጠብቃት፡፡ በውኃ ቀጠነ ሰዎች በሚታረዱባት ሀገር አራጆች ከሕግ በላይ እንደሆኑም ይነገራል፤ በዊስኪ መጠጥ ፍጆታ ሳዑዲ ከዓለም ስንተኛ ትሆን? አላውቅም ግን ከደረጃ ሰንጠረዥ እንደማትወጣ እገምታለሁ - ዋናው ነገር ቀን አይጉደልብህ - ድሃ አትሁን፤ ወፍራም ሥልጣንም ይኑርህ፤ ያኔ ዓለም ያንተና የቢጤዎችህ ብቻ ትሆናለች፤ መገደልና መታሠር አንተ በምትጠላቸው ላይ እንጂ ወዳንተ አካባቢ ዝር አይሉም፤ ያሻህን ብትሠራ እንኳን! ብትገድል ሌላ ገዳይ ትሰይማለህ - እንዳስፈላጊነቱ የሚቀጣልህ ወይም የሚወቀስልህ፡፡ ብታጭበረብር ሌላ ምትክ ተጠያቂ ይኖርሃል - ያንተን አበሳ በሙሉም ሆነ በከፊል ወስዶ ዕዳህን የሚከፍልልህ - ሊያውስ ተጠያቂ ስትሆን አይደል? አንተ በቀን 24 ጊዜ የምታደርገው ተራ ነገር ድሃው በአሥር ዓመት አንዴ ቢያደርግ እሱ ወንጀለኛ ነውና ይገደላል ወይ ይታሰራል፤ አንተ ግን ንጹሕ መልአክ ነህ፡፡ አየሃት የዚህችን ዓለም ነገር? ያልተማርክና በጭካኔህ የለየለት ዐውሬ ብትሆንም እንኳን ባለክብር ዶክትሬትና ሩህሩህ ባለራዕይ የሀገር አለኝታ ነህ፡፡ ባጭሩ ካለህ አለህ፤ ከሌለህ የለህም፡፡ ይህች ምድርና ነዋሪዎቿ እጅግ ያሳዝናሉ፡፡ የፊጥኝ ታስረው የተያዙት በማን እንደሆነ ስንገምተውና ስንረዳው ደግሞ ይበልጥ ስፍስፍ ልንልላቸው እንገደዳለን፤ ሁላችን በአንድ ወይ በሌላ አስቀያሚ ሁኔታ የታሠርንባት የመከራና የሥቃይ ዓለም ናት፡፡ ማንኛችንም መረዳት ያለብን ነገር ኢትዮጵያ የሁሉም መሆኗን ነው፡፡ የሁሉ እንዳትሆን የሚሠሩ ካሉ ፈጣሪ ሤራቸውን ያክሽፍባቸው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በደምሳሳው የዋህና እንግዳ ተቀባይ ነው፤ ይህ ባሕርይው ግን ሊያስጠቃው አይገባም፡፡ በደካማ ጎኑ ገብተው ሊጎዱት የሚፈልጉ የውጭ ኃይሎች ይኖራሉና ፈጣሪ የሥራቸውን ይስጣቸው - ከውስጥ ተባባሪዎቻቸው ጭምር፡፡  

ሃይማኖትን ማስፋፋት በራሱ መጥፎ አይደለም፡፡ ነገር ግን የምታስፋፋበት መንገድ ነው ሊፈተሸና የአካሄድ እርምት ሊደረግለት የሚገባ፡፡ በራስ ሀገር ቤተ ክርስቲያን ቀርቶ በቤትህ ውስጥ ማምለክ እንዳትችል እየተከለከልክና በሞት እየተቀጣህ በሰው ሀገር ገብተህ በሠይፍና በጎራዴ ሃይማኖትን ለማስፋፋት መሞከር ሰይጣናዊነት እንጂ የደግ መንፈስ ውጤት ሊሆን አይችልም፡፡ በዓለም ብዙ ፍርደገምድልነት ይታያል፡፡ ብዙ ያናግራል፤ ግን ለአንድዬ እንተወው፡፡ ዛሬ ዛሬን ይመስላል፡፡ ነገ ግን የተለዬ ይሆናል፡፡ ሁሉም እንደሥራው ማግኘቱ ቀድሞ የተነገረ ነውና ክፉም ለራስ ደግም ለራስ የሚለውን አንዘንጋ፡፡ ፈጣሪ ለኢትዮጵያ የሚበጀውን ያምጣልን፤ ሰላም፡፡


ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

Friday, November 9, 2012

Who are China's new strong men? Beijing - The Communist Party of China leads on her 18th Congress might change a one. The current Vice-President Xi Jinping will take over from President Hu Jintao in the party leadership. The assumption of the presidency in March, is then only a matter of form. Also the head of government is changed. Who are the two new leaders in China?



For Xi Jinping is the 18th Congress of the CPC, the last important stage on the way to the head of state. The 59-year-old, who has worked patiently over the decades in the Communist Party up, will take on the practices of the People's Republic on the five-yearly meeting of Hu Jintao as party leader. The National People's Congress in March 2013, the current Vice President Hu's successor will then compete in the highest state office. Thus it would determine the next ten years, China's fortunes considerably.  


Final takeover in March


In June 1953, the Beijing-born son of a revolutionary hero is considered conservative and not very charismatic. His father, Xi Zhongxun had founded the communist guerrillas in Shaanxi Province and on the side of Mao Zedong fought, which he served after the founding of the People's Republic as a Deputy Prime Minister. When, during the Cultural Revolution (1966-1976) as a counterrevolutionary landed in jail, was also his son Jinping - like millions of other young people - sent to the countryside for re-education 
Occurred in 1974 in the Communist Party, Xi was allowed to return a year later to study at Tsinghua University in Beijing - a known hotbed of talent, which was also his mentor Hu was trained. After studying a degree in chemistry and the rehabilitation of his father by the reforms of Deng Xiaoping in the early 1980s Xi climbed into the ranks of the party quickly upwards. 

massive man with a neat side parting 

Xi took over the years items in Shaanxi, Hebei, Fujian and Zhejiang. During his tenure as governor of Fujian, he was one of the few party leaders who were not implicated in a corruption scandal, the then shook the coastal province. In 2007 he was summoned by Hu Jintao to be party chief of Shanghai, after his predecessor had hopelessly entangled in a financial scandal. Since 2008, the hulking man with the accurate side parting Vice President of China.Glamour is on the otherwise brittle Xi by his wife Peng Liyuan. Ten years younger than her husband, Peng is a nationally renowned singer. While Xi as yet unknown party official filed in his career, the soprano was already a star. Her career she had begun as a simple soldier in the Army before going through her performances in the New Year's Gala, which will be broadcast nationwide on television, came to national fame. Today she holds the rank of General of the Army. 

Glamour by wife

As Peng in 2008 after 25 years passed from the New Year's Gala, was rumored that she was her husband, not compete. This was in October 2007, namely elected to the influential Standing Committee of the Politburo. Initially only number six of nine members, he soon rose to continue and was named in March 2008 as Vice President. In October 2010, when he also deputy chairman of the powerful Central Military Commission ascended, his rise to number one in the most populous country in the world was predestined.International Xi made a speech in Mexico in 2009 caused a sensation. He castigated apparently overlooking the West 'foreigners with full bellies that do not otherwise, as to criticize'. Most Chinese people expect but no significant change of course from him, especially in the party the most important decisions are made by consensus of the leadership group.'He is a team player', says China analyst Will Lam. 'He has played by the rules of the party and not on risk.' By unveiling portal WikiLeaks published U.S. diplomat end Peschen Xi describe as pragmatic, ambitious and willing to change his attitude when the political wind changes.

Deputy Prime Minister Li as 'Grandpa Wen' heritageNow it's not far to the very top: China's Deputy Prime Minister Li Keqiang, a bureaucrat lächelwilliger always will be on Thursday at the beginning of the Party of Communists in the squad hierarchy conveyed upward. It is certain that Li in March officially the political daily business of yet-Premier Wen Jiabao takes.Wen has been guided in recent years to a kind stylize friendly face of communism, which earned him the nickname "Grandpa Wen ': He called for political reforms in the People's Republic, and donated to the victims of natural disasters consolation. And again sentenced Wen corruption in the country - but only just reported the New York Times', Wen clan since 1992, secretly amassed $ 2.7 billion (2.1 billion euros).

Youthful and modern



                                                                    Chinese Deputy Prime Minister Li Keqiang

The 57-year-old Li has a similarly affable charisma as 'Grandpa Wen'. With its flowing English language and his demeanor but Li is youthful and modern so often stiff acting as his comrades. Lis Promote economic reforms met with a positive response to many economists - China did these innovations urgently needed, they argue.Li, who comes from the poor eastern province of Anhui, worked in his young years in the youth organization of the Communist Party up. Even in China's President Hu Jintao, who was in the 1980s, head of the organization, he was an influential patron. With his law degree from the prestigious Peking University and a Ph.D. in Agricultural Economics Li maintains today's image as someone who works hard for the Chinese middle class


Before he ascended to the Deputy Prime Minister of the People's Republic, Li was party chief in Henan in central China, and Liaoning in the northeast of the country - and both provinces flourished under his reign. Already, however, doubts about Lis political clout are loud, especially after a never-ending series of scandals in the health sector: Li stands as Deputy Prime Minister just before a commission to prevent just these scandals.

Involved in scandals

During his tenure as party chief of Henan Li looked sharp criticism for his handling of a wave of infections exposed to the AIDS virus: through sloppiness in a government-sponsored blood donation program is infected the inhabitants of entire villages. Lis provincial government responded to protests with harsh crackdown on critics.
The main task of the new government will be to Li, China's economic growth a boost. Since the People's Republic wirtschaftet export oriented pronounced flattens the growth from the global crisis - as demand from the U.S. and Europe is flat. According to observers, makes Li felt powerful, domestic demand in China to stimulate and guide it out of the country so dependent on exports. 

boost economy

Li had 'a good understanding of economics - that's for sure, "says Willy Lam, an expert on Chinese politics at the
Chinese University of Hong Kong:' He could, however, lack strength of character or charisma. ' Some people in Beijing is concerned that Li was cut from the same cloth as his predecessor Wen and his political goals can not prevail against the resistance in ministries and provinces.
As for Li's private life, there is little official information - a typical phenomenon with prominent personnel of the Communist Party. Chinese media reported that Li is married to Cheng Hong, a literary scholar at a Beijing university. The couple has a daughter who is studying in the U.S..

Source dpa



Tuesday, November 6, 2012

The struggle for Freedom

በኢትዮጵያ የአመባገነኖች አዙሪት ሳይውል ሳያድር መደምስስ ይገባዋል፡፡ በምትኩም ለሃገር አንድንት ለፍትህ ለዲሞክራቲ ለሃገር ልማትና ዕድገት ዘብ የሚቆም በኀዝብ ፈቃድና ምርጫ ሃገርና ሕዝብን የሚያስተዳደር  መንግሥት ይኖረው ዘንድ ግድ ይላል፡፡