Friday, June 14, 2013

ሕዝብን ለጦረነት አገርን ለጥቃት አሳልፎ ከሚስጥ ጋር መተባባር አገራዊ [ብሔራዊ] ወንጀል ነው።

የአንድ አምባ ገነን ሥራዓት ማንንት ባሕርይም ሆነ ተግባር ሊታይና ሊገመገም የሚገባው ሥራአቱ በአገሪቱና በዜጎች ላይ ከሚፈጽመው ብሔራዊ ወንጀልና ከሚያደርስው አገራዊ ጉዳት አኩያ ነው።
እንደሚታወቅው ወያኔ  ከአፈጣጠሩ ጀምሮ በካሃዲ በጸረ ኢትዮጵያውያን የመንደር ስብስቦች ጥላቻ ተረግዞ፤ በግራ ቀደም ፖለቲካ ስንኩል ትርኪምርኪ አመለካከት ተጠምቆ ወንድሞቹን ሲያርድ ሲያሳረድ የኖረ፤ የአባቶቹን የእናቶቹን የአያቶቹን የወንድሞቹን የልጆቹን የዘመዶቹን በርሃብ ማለቅ ግድ ያላለው፣ የማይለው፣ ስብዓዊነት የማይስማው፣ ለርሃብተኞች የመጣውን እርዳታ ቀምቶ ከሱዳን እስከ ሊቢያ ሲቸረችር የኖረ ፤ የኢትዮጵያን ታሪካዊ ማንነቷን ሕልውናዋን ስንደቃላማዋን የካደ፤  አገር አስገንጣይ፤  በኢትዮጵያ ጠላቶች ያደገ የተመነደገ ፤ አገርና ሕዝብን ዘርፎ የሚያዘርፍ፤  በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነ ግን አጥፍቶ ጠፊ መሰሪ፤  በፋሽቱ ቪኒቶ ሞሶሎኒ የከፋፍለህ ግዛ አስተምህሮ፤  በሂትለርና በስታሊን የድርጅታዊ የፕሮፓጋንዳና ቅስቀሳ ብሂሎችን እራሱን የካነ፤ እራሱ ደንቁሮ አገርንና ሕዝብን፤ የሚያደነቁር፤ የሃገሪቱን ዋና ዋና መሠረታዊ መንግስታዊ መዋቅሮችን በቁጥጥር ስር አድረጎ ፤ በአባሪ ተባባሪዎቹ የሆድ አደር አጋሰስ አጋርነት፤ በባእድ አገር የፖለቲካና የገንዘብ ለጋሲነት እርዳታ ብድር ሰጭነት፤ አማካሪነት እየታገዘ፤ ሕዝብን ሃገርን በንቅዘት በምዝበራ አደህይቶ አገርን ለመበታተን ቆርጦ የተነሳ እኩይ ስብስብ ለመሆኑ፤ ከሆድ አደሮቹ፣ከአባሪ ተባባሪዎቹ በስተቀር ማንም ኢትዮጵያዊ በጥሞና የሚያውቀው ማስረጃዎች በዋቪነት የያዙት፤ በታሪክ መሓደር ተረቆ ያለ የማይታበል ሃቅ ነው ።

የተዚህ ቀደሙ ወንጀል ሳያንስ ዛሬ ደግሞ ወያኔ በቡኅ ላይ ቆረቆር ሆኖ ሕዝብን ለጦርነት፤ ሀገርን ለጥቃት ለማዘጋጀት ህዳሴ ግድብ በሚለው ማታለያ በአድርባይ ሆድ አደር ጠርናፊ አስጠርናፊ ስብስብ አቀንቃኝ  ሊቀመኩዋሶች ታዳሚዎች  እየታጀበ ግብጽን እየተነኮስና እየቀሰቀስ በመቀጠሉ የአባይ ውሀ አንድም ጠብታ አይቀነሰብኝም ከምትለው ከስግብግቧ ግብጽ ጋር ጦርነትን እየጋበዘን ነው።

አገራችን ኢትዮጵያና ሌሎች ሀገሮች በነጭና ጥቁር አባይ የመጠቀም መብታቸው የተጠበቀ መሆኑ አያክራክርም በአለም አቀፍ ህግ መሰረትም ሌሎች ከወንዞቹ ተጠቃሚ ሀገሮች ውሃ እንዳያገኙ ማድረግ የሚፈቀድ አይደለም። አባይን በተመለከተ ተንኮለኛው አጋብሶ አደር የእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ ሱዳንና ግብጽን ብቻ ይዞ የወሰነው የውሀ ድርሻ/ክፍፍል ትክክለኛ አለመሆኑም አከራራክሪ ኣይደለም-- ግብጽና ሱዳን አሌ ቢሉም። ግብጽ በረሀዋን ልታለማና ሚሊዮኖችን ልታሰፍር በመፈለግ የአባይን ውሀ በተጨማሪ ደረጃ መፈለጓና የተፋሰስ ሀገሮችን ጥቅም ከቶም አላዳምጥ ማለቷም የሚደገፍ አይደለም ወያኔ በአሁኑ ጊዜ ትልቅ ግድብ በሌለ ገንዘብ እሰራለሁ ብሎ የተነሳው ለኢትዮጵያ አስቦ (ወያኔና የኢትዮጵያ ጥቅም ሆድና ጀርባ ናቸውና) ሳይሆን የሕዝባዊ አመጽ ነፋስ ወደ ሀገራችንም እንዳይነፍስ በሚል የህዝብን እይታ ለማደናገር የሸረበው ተንኮል መሆኑ ክርክርን አይጠይቅም በኢትዮጵያ እስከዛሬ የተሰሩት ግድቦችና ገና ያላለቀው ግልገል ጊቤ ቁጥር ሶስትንም ጨምሮ ለሀገሪቷ የመብራት ሀይል ፍጆታ ከበቂ በላይ ሆነው ሳለ ዛሬም በብዙ ከተሞች መብራት በፈረቃ እየተሰጠ እንዳለ ሕዝባችን የሚያውቀው ነው። ግዙፍ ግድብ ለመገንባት መነሳትና ይህንንም ግብጽ እንደምትቃወም እየታወቀ በስልት ጉዳዩን በመያዝ ፈንታ ድንፋታና ፕሮፓጋንዳን ማስቀደሙ፤ ቦንድ ብሎ ሕዝብን ማስጨነቁና ማስገደዱ፤ ሀገር ወዳድ መስሎ ለመቅረብ መፍጨርጨሩ ሕዝብን ሊያደናግር የሚችል አይደለም። የለመዳባቸው የወያኔ የገደል ማሚቴዎችና አደናጋሪዎች --በባድሜ ጦርነት እንዳየነው ሁሉ-- ሀገር ልትጠቃ ነው ኡኡ በሚል ወያኔን በመታገል ፈንታ ሕዝብ እንዲደግፍና ከጎኑ እንዲሰለፍ ለማድረግ ከወዲሁ የተንኮል ቅስቀሳ፤የማደራጀት ስራና ጫጫታ ጀምረዋል። ሁሉም ሀገር ወዳድ ዜጋ ይህንን በሚገባ ተገንዝቦ ውጉዝ ከመ አርዮስ መባል አለባቸው።

የግብጽ ሕዝብ ጠላታችን አይደለም። አንዋር ሳዳት የአባይ ወንዝ ከተገደበብን ጦርነት የግድ ይሆናል ያለውንም አንረሳውም--ዛሬም የግብጽ መሪ ተመሳሳይ አቅዋም በመውሰድ እሱም በበኩሉ ልክ እንደ ወያኔ ውስጣዊ ውጥረቱን ዘወር ለማድረግ ይፈልጋል። ተጨባጭ ሁኔታውንና አቅምን ሳያውቁ ሳይመዝኑ ህዳሴ ግድብ ይሰራል ብለው ጫጫታ ላይ ያሉት ክፍሎች ቅዠት ላይ ናቸው
ከግብጽ ጋር ጦርነት ቢነሳ ይህ የኢትዮጵያ ሳይሆን የወያኔ ነው። ልክ እንደ ባድሜ። 130 ዜጋ አልቆ ምን ተገኘ ? ወያኔና አጫፋሪዎቹ--አንዳንዶቹ ደግሞ ተቃዋሚ ነን ሊሉም ኢትዮጵያ በአባይ ልትጠቀም ስትነሳ በግብጽ ተጠቃች ወይም ልትጠቃ ነው በሚል ሀገር ወዳድ ሁሉ ተነሳ ለማለትና ለማደናገር አቅደዋል። የሚሞኝላቸው አይኖርም ማለትም አይቻልም። ለነገሩ ግብጽ ኢትዮጵያን ሊወር አይችልም-- አይሮጵላኖች አስነስቶ ግድብ ተብየውን ሊደበድብ ይችላል። የሚያቆመውም አይኖርም ። ዕድሜ ለወያኔ ስንት ሚሊዮን ብር የፈሰሰበትን አየር ሃይል በትኖ በጀሌዎቹ ሞልቶት ይቀልዳል። መካላከያ ተብየው ሆኖ ሕዝብንም ከፋፍሎና አሽመድምዶ ይገኛል ።

ኢትዮጵያ መብቷን ለማስከበር አቅም የላትም። ወያኔ የአሜሪካ ሎሌና ተገዢ ነው-- አሜሪካ ደግሞ ግጭት ከተነሳ ግብጽን መቃወም ኣንችልም/ ብላ ለወያኔ አስጠንቅቃለች። የወያኔ አገዛዝ ከድጡ ወደ ማጡ ሊከተን ነው እየጣረ ያለው። ይህን መቃወም ደግሞ ለሀገራችን ደህንነት ወሳኝ ነውና ወያኔና ቅጥረኞቹን ወግዱ እረፉ ማለት ግድ ነው።ዛሬ ባለንበት ሁኔታ ከግብጽ ጋር ግጭቱ ለኢትዮጵያ የሚጠቅማት አይደለም። የኢትዮጵያ መንግሥት የለም ። አገርም በመንግስት ስም የሚገዙዋት ሕዝብን ለጦረነት አገርን ለጥቃት አሳልፎ የስጠ የሚሰጥ በአገራዊ [በብሔራዊ] ክህደት ወንጀለ የሚጠየቅ የወያኔ ስብስብና ተባባሪዎጩ ናቸው። 

ወያኔ ስልጣን ሲይዝ ከግብጽ ጋር ተፈራርሞ የሀገርን ጥቅም መሽጡንም መርሳት አንችልም። ወያኔ ጫካ ሳለም በግብጽ መረዳቱንና የተከዜ ድልድይን ሊያፈርስ መሞከሩንም የምንረሳው አይደለም። ወያኔ ከስረ መሰረቱ ፀረ ኢትዮጵያዊ ጥላቻን መስረት በማድረግ ከባንዳ አያቱና፤  አባቱ፤  ዘመድ አዝማዶቹ፤  የባኤላ አሹቅ እየቃመ፤ቂጣ እየገመጠ፤በለስ እየጋጠ፤ ጥሕሎ እየዋጠ፤  እሳት ዳር ተኮልኩሎ፤  በባላባታዊ የስልጣን ትንንቅ አባዜ የወደቁ ለጠላት ያደሩ ቅድመ አያቶቹ፤ አባቶቹ  ያወረሱትን ቂም በቀል የጎሳ ጥላቻ አፈታሪክ አንግቦ፤ በስነልቦና የበታችነት ማንነት በሽታ ተጠምዶ ያደገበትን ማንነት ባሕሪ መሰረት በማድረግ፤ኢትዮጵያ የቅኝ ገዥ አገር ናት፤ ትግሬን ነፃ አገር እናደርጋለን፤ትግሬ ለትግራዊ  የሚል ፋሽታዊ ብሂል አንገቦ ፈጣሪውን ሻቢያን ተገን አድርጎ በባእዳን አገራት አጋርነት አደራጅነት አማካሪነት የፖለቲካና የዲፕሎማቲክ፣ የእርዳታ ገንዘብ ለጋሲነት፤ በወገን ደም ሰክሮ ስልጣንን በመጨበጥ፤ የኢትዮጵያ ታሪክ የመቶ አመት ታሪክ ነው በሚል ጸረ ኢትዮጵያዊነት ቅዥት ውስጥ ተዘፍቆ ፤በመላው ኢትዮጵያውያን አንድነትና ትብብር አጥንታቸውን ከስክሰው ደማቸውን አፍስሰው አባቶች እናቶች ያቆዩንን ታሪክ፤ የአማራ ገዥዎች የጻፉት ተረት ተረት ነው በሚል ስንኩል ቱሪናፋ ዲስኩር ፕሮፓጋንዳ፤ የሽግግር መንግስት፤ነፃነት ውይንም ባርነት፤ብሔር ብሔረስቦች፤ የብሔር ብሔረስቦች እስከመገንጠል በሚል፤በወንድሞቹ ደም የተጠመቀውን ጠብመንጃ በሕዝብና በአገር ላይ ወድሮ፤ ያላንዳች ሕዝባዊ ውክልና፤አገርን አስገንጥሎ፤ አገርን ያለባሕር በር ያስቀረ፤ ትውልደ ኢትዮጵያን የባእዳን ቅጥረኛ ምሁራንን በፋሽስቱ ቪኒቶ ሞሶሎኒ መርዝ የተለወስ ወያኔያዊ ሕገመንግስት እራሱ አስረቅቆ እራሱ በአምሳሉ በፈጠራቸው የጎሳ አቀንቃኝ ድርጅቶችና ሆድ አደር ስብስቦች በማስወስን፤ አገርን በአስራ አንድ ጎሳንና ቛንቛን መአከል ያደረገ በ1928 በፋሽት የኢጣሊያ የአምስት አመቱ ወረራ ጊዜያዊ አገዛዝ ቻርታ የተነደፈውን የቅኝ አገዛዝ ሥነስርዓት አማካኝ ያደረገ፤ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በኋላ ከተቀበረበት ጕድጒድ አውጥቶ የአፍሪቃ የነጻነት ተምሳሌት የሆነችዋን ውድ ሃገራችንን በጎሳ በቋንቋ ተከፍላ በጥቂት ወያኔ ግርቢጦች፣ የውጭ ቅጥረኛ ጎስኞች መዳፍ ውስጥ ገብታ በሃያ አንደኛው ክፍለዘመን፤ አገር የጎሳ ባላባታዊ አንባ ገነን ሥነመንግሥታዊ አገዛዝ ሥር እንድትወድቅ የመከረ ያስመከረ የተገበረ፤ ሕዝብና አገርን የካደ፤ የሃገርና የሕዝብን ጥቀም አሳልፎ የሰጠ የሚሰጥ፤ አጥፊ፣ መስሪ ስብስብ፤ ትላንትም ሆነ ዛሬ ምግባሩ ሥራውም በጥፋት ላይ ጥፋትን ያነጣጠረ መሆኑ ለማንም አገር ወዳድ ግልጽ ነው። ወያኔ ገርን ለባዕድ ሻጭ ጸረ ኢትዮጵያ ሀይል ነበረ--አሁንም ነው። ለዚህም ነው ከባዕድ ጋር የፍጥጫን ጎዳና መርጦ ሀገራችንን ለጥቃት ሊያጋልጥ እየተፍጨረጨረ ያለው። በመሆኑም ነው ሕዝብን ለጦረነት አገርን ለጥቃት አሳልፎ ከሚስጥ አገራዊ [ብሔራዊ] ወንጀለኛ አገርና ሕዝብ ገዳይ አንባገነን ስነስርአት ጋር አገራዊ ትብብር ሊኖር የሚያስችል ምንም ጉዳይ የሌለው በአባይ ስም  ሕዝብን በጦርነት ለመማገድ  አገርን ለጥቃት አሳልፎ ለመስጠት ከሚያሴሩ ጠርናፊ አስጠርናፊ የወያኔ ቅጥረኞች ተንኮል እራሳችንን አውጥተን ሕዝብና አገርን በጋራ እንታደግ ለነጻነት ትግል በጋራ በመቆም አምርረን እንነሳ።


ድል ለኢትዮጵያ !!!

Sunday, June 9, 2013

Voice from the grave.

By Yilma Bekele

Meles Zenawi is dead. Meles Zenawi is alive. I am afraid in our case both statements are true. We saw the tyrant being buried or placed six foot under and the extraordinary send off orchestrated by his politburo in living colour. The whole country was on stand still for a week or so to bury the warlord who was in the freezer for a month or so. We witnessed the bullying power of the TPLF party that forced every department, every Keble and every household to send a representative and show sorrow for a person hated and reviled by all living Ethiopians.

Well he is not really gone. He is still directing the show from hell or wherever evil resides. It has been said that he vowed to leave us with the seeds of conflict, hate and chaos for a long time after he is gone. It looks like he is right. There is no escaping his presence. I don’t mean the life size posters of his ugly face in every corner of our country. I am referring to his toxic and useless ideas including his insane and childish plans that are trying to drive our politics and economy without him.

I am not talking about his ever chameleon Constitution that is still used to whip the opposition. I am not pointing out to the Kilil system that is creating a country of strangers. There is no need to mention the Keble system that is making every household an extension of the security service. Today I am focused on the use of the king of kings of all rivers, the great nurturer of ancient civilizations the one and only Abay River and its unfortunate use by the evil one to hurt our poor country.

The last week all the talk has been about Abay. We are fortunate to have so many rivers flowing out of our high escarpments that if you look at Google map of Africa you marvel and see how God has favoured our ancient country. Our high mountains kept us isolated and free from invaders while nurturing our people when all around us suffered from lack of water. The great Wabishebele, the giving Awash, the beautiful Genalle, the fierce Tekeze and Mereb the homily Gibe are but just a few of our mothers milk flowing to keep us and our neighbours happy and strong.

What can be said about the great Abay? The mighty Abay is not just an Ethiopian phenomenon. Good old Abay is the mother of the Pharaohs and the great Egyptian civilization. The wonder of the world owes its existence to the highlands of Ethiopia that made it possible for such a civilization to flourish. The Pyramids of Giza wouldn’t exist without the wealth made possible by the river Nile. Our Abay contributes two thirds of the Nile water supply.

Mount Gishe at 10,000 feet floats on a lake according to the priests that bless the spring that gives birth to the mighty Abay. It is here Abay starts its thousands of miles journey until it empties into the Mediterranean Sea. Abay with its deep gorges numerous waterfalls protected our land from European colonialists, Turkish invaders, Italian fascists and all those that wished ill to our Fairland. From mount Gishe to the Sudanese border alone Abay meanders along for over 500 miles (800kM) never in a straight line like most rivers but encircling and hugging our land as if it does not want to leave. Our music and literature is full of praise for the mighty Abay and its force is recognized by all those who come near it and its power felt all over our country.

It is none other than this historic river that today is tossed around like a beach ball by Woyane bastards for their own useless dream and close your eyes lets us fool you story. This what Meles Zenawi planed before his death and this is what he is witnessing from the grave. When Woyane pulled the dam on Abay plan three years ago their leader knew it was his last goodbye wish to our nation that would seal his legacy of evil. It was never mentioned in the five year transformation blueprint they are so proud of. It was never discussed because the idea is so ridiculous any governing body will laugh it off. Thus Meles and company brought it out the last minute and claimed it was kept a secret. Why and from whom is not clear yet. But they damn well knew it was a crazy idea and no one will take it seriously.

Why do you think it is such an insane idea and not even worth refuting? Very simple, our nation is poor and living on welfare even for the food we eat we rely on alms thus no big and complex project like building a dam is possible without the help of outsiders whether the West or the East. No outside Bank or foreign government will finance such a project without adequate studies. Building a dam on a river that crosses an international border complicates the situation in a very big way.

Thus when the warlord came up with the idea that this humongous project was going to be financed by local resources it was time to appreciate the size of his balls for such bravado and empty jive. The claim is so bizarre there is no need to refute such bold face stupidity other than shaking ones’ head and keeping our collective mouth shut. People that survive on a few dollars a day, that look for outsiders to feed them and watch their young and able fleeing their home in droves facing unknown danger are going to save enough to finance a multimillion dollar project is not a good idea to put forward and wait for contributions to pour in. Logic says it ain’t going to happen even when hell freezes over.

Why do you think the dictator pulled this crap out of his hat knowing his days are numbered? He was focused on three important aspects of the future of our country after he is gone and both are shaping as he planned. One is harvesting more enemies for our poor land. Alive he has already managed to get our country entangled into two costly wars. The war with Eritrea that should not have happened has already cost us dearly in both money and lives. Over eighty thousand Ethiopians died and over twenty thousand suffered major injuries. Ethiopia emptied all its foreign reserve buying arms with cash since no weapon dealer accepts credit. For all that investment we won a barren piece of territory that today sits in no mans’ land.

The incursion into Somalia was a no win situation and it was not even in our national interest at all. The dictator to solidify his standing as a ‘terrorist fighter’ and use the situation to clobber the opposition at home had no qualms using Ethiopian lives for his selfish means in order to stay in power. Our solders committed so many war crimes in Somalia the bad felling between the two peoples will take years to wash away. Neighbours that will live for generations in close proximity do not normally engage in such activity that will create animosity and hate between our two people but our great leader was not concerned about that and he showed it by his callous decision.

The second reason for Abay dam madness is to shop for more enemies for our country. You see the idea of building a dam on Abay is not an original idea. Both the Imperial government and the Military regime have exhaustively studied the subject. There are plenty of documents to show their efforts for the project. They have reason why they did not pursue the matter. Today the Woyane regime propaganda makes it look like Meles came up with an original idea and they even coined a catchy phrase ‘Abayen yedefere jegna’ to hype the silly project. So what did he do? He came out with a dam project without asking the rest of Ethiopia or our experts to sit down and define what exactly needs to be done in our nation’s interest. We did not see Ethiopian engineers, hydrologist, geologists, economists, and environmental scientists, political and diplomatic experts being consulted before the ‘secret’ plan was presented in a take it or shut up situation.

Logically a dam on Abay River is a concern to all those upstream countries that rely on the river for survival. Of course the Egyptians did not take the news kindly. Is that a surprise? Put yourself in their shoes would you like it if someone decides to curtail your life line? Our country is not so strong and mighty that it could unilaterally take actions that would negatively affect the lives of so many millions. It was only yesterday in the news that the USA and Mexico signed a negotiated deal on the use of the Colorado River that starts in the rocky mountains of Wyoming and empties into the Baja California in Mexico. It is a shared river and the two governments consult each other on its use. That is what the Egyptians are asking us to do. That is what international treaties require us to do. This political chest thumping and arrogance behaviour is not a sign of a great nation that wants to live in peace and harmony with its neighbours far and close. Meles Zenawi planted the seeds of this conflict before his exit.

The third and important reason for this hasty project is all about a Ponzi scheme to gather more money for our Woyane warriors. Where do you think the recently disclosed three billion dollars net worth of the war lord came from? In a nutshell it is all about EFFORT and its continuing quest to amass more money at the expense of our people and country. Mesfin Engineering and the privately held Italian outfit Salini Construction are the two main contractors on the Abay dam project. If you remember Salini is the same no bid winner on the Gibe dam project that had the tunnel collapse exactly one month upon completion. Salini is also the contractor that at the moment is involved building a dam on Tekeze River affecting Waldeba Gedam. Salini does not bode well for Ethiopia.

The current wild talk by the spooked Egyptian regime is creating a stressful and ugly situation to our Ethiopian citizens that are stuck in Egypt. Every ill-conceived idea by the Woyane regime always creates a backlash against our immigrants that are escaping the dire situation in their homeland. It is obvious Woyane cannot stay in power without drama. They always are creating enemies both at home and outside to deflect our attention away from their failure to build a sustainable economy, a peaceful nation and a just society. It is also a little depressing to see Ethiopians venting their anger at the Egyptians instead of questioning their own dictators why they are always creating havoc both at home and with our neighbours. Our creator in his/her infinite wisdom has recalled one of his defective product to spare our country from further destruction but we in our feeble ways are refusing to bury his toxic ideas and burn the memory one and forever. We should pray for the strength to say no, leave us alone. I urge you to watch a wonderful conversation on ESAT with Dr. Getachew Bagashaw regarding the Abay dam project. You can also read a beautiful analysis by the relentless Professor Mesfin WoldeMariam on Abay.

http://soilandwater.bee.cornell.edu/research/international/eth_pubs.htm
http://www.ethiofreedom.com/dr-getachew-begashaw-on-esat-discussing-the-abay-dam-issue/
http://www.ethiofreedom.com/%E1%8D%95%E1%88%AD-%E1%88%98%E1%88%B5%E1%8D%8D%E1%8A%95-

%E1%8B%88%E1%88%9B%E1%88%AD%E1%8B%AB%E1%88%9D-%E1%89%A0%E1%8A%A0%E1%89%A3%E1%8B%AD-%E1%8C%89%E1%8B%B3%E1%8B%AD-%E1%88%8B%E1%8B%AD/

Saturday, June 8, 2013

Development without Human Rights

The word patriotism comes from a Greek word meaning fatherland. For most of history, love of fatherland or motherland was an attachment to the physical features of the land. But that notion changed in the eighteenth century, when the ideals of democracy, socialism, and communism strongly emerged into political thought. Patriotism was still a love of one's country that included connections to the land and people, but then also included its customs and traditions, pride in its history, and devotion to its welfare. A true patriot speaks out when convinced that their country is following an unwise or unjust action.  

Wednesday, June 5, 2013

ዛሬ ደግሞ…

ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም
ጦርነት እንኳን ገና በልቶ ላልጠገበ ሕዝብና ለጥጋበኞቹም አይመችም፤ የተራበ ሕዝብ በጠገቡ መሪዎች ሲነዳ ግን ጦርነት ለአጉል ጀብደኛነት ዝና የሚጠቅም መስሎ ይታያቸዋል፤ ከኤርትራ ጋር ጦርነት ለመግጠም በሚያሰፈስፉበት ጊዜ በርቱ እያሉ የሚያቅራሩ ሞልተው ነበር፤ ዛሬ አቀራሪዎቹም ሆኑ ጀብደኖቹ በኤርትራ ጦርነት ያለቀባሪ ስለቀሩት ሰዎች፣ ጠዋሪ ስላጡ እናቶችና አባቶች፣ አሳዳጊ ስለሌላቸው ልጆችና አካለ-ጎደሎ ለሆኑት የሚያስብላቸው አለ ወይ? የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት መነሣትና በኢጣልያ የግራዚያኒ ሐውልት እንዳይሠራ የተጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ከልክሎ ለሰልፍ የወጡትን አስሮ ያሳደረ አገዛዝ ለአገራቸው ለሞቱት ኢትዮጵያውያን የሚሰጠውን ዋጋ በመጠኑም ቢሆን ያሳያል፤ ስለዚህም ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ሲወዱ ራሳቸው በልጽገው ለልጆቻቸው ብልጽግናን እንዲያወርሱ ሕይወታቸውን ቢጠብቁ ለአገራቸውም ክብር ይሆናሉ፡፡

ለፍቅር መተዋወቅ እንደሚያስፈልግ ሁሉ ለጠብም መተዋወቅ ያስፈልጋል፤ የተሟላ መረጃ ቢኖረን የጥንት ታሪክ እየጠቀስን ሰዎችን ለጦርነት እንቀሰቅስም ነበር ብዬ አምናለሁ፤ ስለዚህም አንዳንድ አስፈላጊ መረጃዎችን ላቅርብ፤ —
1. የግብጽ የጦር ኃይል በዓለም አሥረኛ ነው፣ በአፍሪካና በመሀከለኛው ምሥራቅ የሚወዳደረው የለም፤ አንድ ሚልዮን ተኩል ያህል የጦር ኃይል አለው፤ በዓየር ኃይልም ከዓለም አሥራ አራተኛ ነው፤ በታንክ ብዛት አራተኛ ነው፤ በባሕር ኃይል ሰባተኛ ነው፤ በጦር በጀት አርባ ሦስተኛ ነው፤
2. በኢትዮጵያ ዙሪያ ጂቡቲ፣ ሶማልያ፣ ሱዳን የአረብ ማኅበር አባሎች በመሆናቸው ለግብጽ ማኅበረተኞች ናቸው፤ በወያኔ ፈቃድ የተገፋችው ኤርትራም የዚሁ ማኅበር ታዛቢ አባል ነች፤ ከቀይ ባሕር ማዶ ያሉት አገሮች ሁሉ ሀብታሙንና ኃይለኛውን ሳኡዲ አረብያንም ጨምሮ የግብጽ ማኅበርተኞች ናቸው፤ በዚህ ሁሉ መሀከል የተከታተፈች ኢትዮጵያ ብቻዋን ነች፤
3. የቤንዚን ሀብትና ከሀብቱም ጋር የሚገኘውን ወዳጅና ጡንቻ አንርሳ፤
ይህ ማስታወሻ ለማስፈራራት አይደለም፤ ማስፈራራትን አላውቅበትም፤ እንዲያውም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ‹‹አትፍሩ›› ብሏቸዋል ተብዬ ተከስሼ ታስሬአለሁ፤ ስለዚህ አላስፈራራም፤ ጦርነት ከመጣብን ልናስቀረው እንሞክር፤ ሌላው ቢቀር እንድንዘጋጅ ጊዜ እናገኛለን፤ ገፍቶ ከመጣ ግን እንቋቋመዋለን፤ ለጦርነት አንቸኩል፤ ለኤርትራም ጊዜ ተናግሬ ነበር፤ የሰማኝ የለም፤ ጥጋብ ላይ ያሉ የሚርባቸው ዝና ነው፤ የሚያገኙት ግን ውርደትን ነው፡፡