ሕዝብ ላለፉት
ሁለት አስርት አመታት እንደአለመታደል ሆኖ ነፃነቱን በመጎናፀፍ ፋንታ ከአብራኩ የተቀፈቀፉ ጎጣዊ የመንደር ስብስብ አምባገነኖች
እየተፈራረቁበት አንዱን ያዘለበት የጀርባው ቁስል ጠፈፍ ሳይል ሌላውን በፈረቃ እያዘለ ዘመኑን ሁለ በዋይታና በሰቆቃ ማሳለፍ ግድ
ሆኖበታል፡፡ ሁሌጊዜም ተስፋን ለሕዝብ ባልሰነቁ ነገር ግን በአፈና ችጋር የታጨቁ ዓመታትን ቀናትን እየቆጠረ ይቀበላል፡፡ ይሸኛል፡፡ አንዱን እኩይ አንባ ገነን በሞት
ሲሽኝ ሌላው ምንደኛ እኩይ ደግሞ ከንጦሮጦስ አምልጦ የመጣው ርዓይ አስፈጻሚ አሻንጉሊት ሆኖ ይተካል፡፡ ያለዲሞክራሲም ሥነስርአት ዲሞክራሲ ይደስኮራል
በተግባር ግን በአገሪቱና በዜጎቹዋ ላይ ሕገዓራዊታዊ ኢስባዊ ብሔራዊ ወንጀልና ይፈጸማል መስሪ በሆነ ዳርጎት አገራዊ
ማንነት ታሪካዊ እሴቶችን ያጠፋል ከአገር ጥቅም ይልቅ ለባእዳን አገራት ጥቅም ይቆማል። ሕዝብንም ከላይ እስከታች በጠርናፊ አስጠርናፊ
ዘለበቶች ሽርቦ በባእዳን አገሮች ቀለብ ስፋሪነት ምጽዋት ብደር ስጭነት
አገርና ሕዝብን እስረኛ በማድረግ ለጥቂት ምድረገነት ለብዙኅኑ ደግሞ ምድረ ሲኦል የሆነ ኑሮን ያስንፋል። ላለፉት
ሁለት አስርት ዓመታት የወያኔያዊ ዘረኛ፣
ፀረ ኢትዮጵያና አምባገነናዊ የሆነውን አገዛዝ
ደሞክራሲያዊ ነኝም በማለት እርሱን የሞካሻል።
"ታማኝ ውሻን ጃስ ይበሉ"
ነውናም ባዕዳንም አገልጋያቸውንና ተላላኪያቸውንም ዴሞክራሲያዊ ብለው ሲያመሰግኑና ሲዋሹ
ታዝበናል። ወያኔና ዴሞክራሲ
እሳትና ውሃ ስልሆኑ የማይዛመዱ የማይታረቁ ባላንጣዎች ናቸው ይህንም የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠንቅቆ ያውቃል።

ከዚህ ጋር ተያያዥ ሆኖ በዋቢነት የሚጠቀሰው የወያኔ ነፃ አውጭ ድረጅት ዘረኛ አምባ ገነን ሥርአት እራሱን በእራሱ ለመደበቅ
አዲስ ጭምብል አጥልቆ ሕዝብን ለማደናገር ኢሃድግ ብሎ እራሱን እንደአዲስ ድርጅትን መፍጠሩ ነው። ምንም እንኩዋን ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ
የሕዝብን የአመለካከት እይታ ለማድበዝ ኢሐድግ የግንባሮች ግንባር አንድነት በማለት ላለፉት ሁለት አስርተ አመታት ቢደስኩርም ዲስኩሩ ከዲስኩረነት የማያልፍ እውነትን
ያልጨበጠ የትግሬ ነፃ አወጭ ድረጅት ወያኔ በሕዝብና በአገር ላይ የሚያደርሰውን የዘረኛ አንባገነናዊ ጭቆናና ብዝበዛ ፍንትው ብሎ
እንዳይታይ በአሳዳሪ ባእዳን አግሮችና በሆደ አደር ወያኔ አደር ልሂቃን ተመክሮ የተደረገ አገረን ለማቆርቆዝ የተዶለት ፍሬ ከርስኪ የአገር ካሕዲያን ብልጣብልጥ
ዱለታ መሆኑ ግልጽ ነው። ይሁንና ግን የግንባሩ ማንነት ሲመረመር
በዚህ
ግንባር ውስጥ የተካተቱትና በዋናነት የሚጠሩት፤ ከራሱ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ሌላ፤ ብሔራዊ የአማራ ዴሞክራሲያው ንቅናቄ
(ብአዴን)፣ የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ)፣ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) ተብዬዎቹ
ናቸው። እነዚህም ወያኔ ሰራሽ ድረጅቶች ከፍጥረታቸው ጀምሮ የወያኔ የከፋፍለህ ግዛ ድራማ ከዋኒዎች በመሆን
በአልጋ ላይ ቀጋ ሆኖው ላለፈው ሁለት አስርት አመታት የምርጫ ሳተን ኮሮጆ ገልባጭ አስገልባጭ አጎንባሽ አፋዳሽ የሃገርን ሃብት
ዘራፊ በዝባዥ አሳለፎ የአገርን ሃብት መሬትን ለባእዳን ለጋሽ አገርን አፍራሽ ታሪክን ቀልባሽ ሕዝብን አስለቃሽ ሃይማኖትን በጎሳ
መትሮ እምነትን ደምሳሽ የሕዝብን አንድነት መራዥ … ከሆነው የትግሬ ነፃ አውጭ ወያኔ ድረጅት አላማ አስፈጻሚነት በላይ፤ አለውክልና እንወክለዋለን የሚሉትን ሕዝብ እንኳ ለስብሰባ መጥራት የማይችሉ ነፃ ያልሆነ የሕዝብ ዓላማን የላነገቡ ሆደ አደር ስብስቦች የወያኔ ምንደኛ እንጅ ግንባርም
ሆነውም አያውቁም አልነብሩም።
በተለይ ደግሞ ደርግ
ከወደቀ በኋላ፤ ወያኔ የፈጠራቸው የድልአጥቢያ የጎሳ ነፃ አውጭ ድርጅት ተብየዎች የግንባርነታቸው ትርጉም በጓዳ በር አፈትልኮ አምልጧል።
ግንባሮች ነፃ እንውጣ ብለው ከተነሱበት ሀገር ነፃ ወጥተዋል ወይንም አሁንም በባርነት ውስጥ ናቸው። ገዥ ሆኖ ባርነት የለም። ገዥ
ሆኖ ነፃ አውጪ ድርጅት መሆን የለም። ስለዚህ ትርጉም የሌለው ነፃ አውጪነት ሆነ። አሁንም የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ወያኔ
ሆኖ የተቀመጠው ገዥ ቡድን፤ ከማን ነፃ ሊወጣ ነው? ደርግ ሲወድቅ፤ መጀመሪያ የህዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ፣ የትግሬዎች ነፃ
አውጪ ግንባርና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አገር አፍራሽ የዘረኛ አምባገነን ርዮት አንግበው መጥተው አገርን ገነጠሉ አስግነጠሉ ሕዝብን
በጎሳ በመፈረጅ ገደሉ ከተወለደበት ካደገበት ቀዬ አባረሩ የአገር ሃብትንም ዘረፉ በመጨረሻም ሌባ ሲካፈል እንጅ ሲሰርቅ አይጣላም
ሆኖ ስምምነታቸውን በተራ በትራ አፈረሱ። እንዲሁ በኢሃድግ ተብዬው ወያኔያዊ ፈጠር ስብስብ ውስጥም የታቀፉ ግንባር ተብዬዎች ለወያኔ
ግልጋሎትነት የተፈጠሩ ስለሆነ፤ ለጎሳዊ አምባገነን የትግሬዎች ነፃ
አውጪ ግንባር መንግሥት የቆሙ ናቸው። ይህም ሃቅ ማንንም አያስገርምም፤ ለዚሁ ነውና የተፈጠሩት። ለዚህ ማጣፊያ የሆነው ደግሞ
“ፌዴራል” የሚል ጌጥ በአስተዳደሩ ላይ መለጠፉ ነው። ይህ ነበር እና ነውም በገዢው ቡድን በኩል የነበረውና ያለው ተጨባጭ የስነ-አስተርዳደር
ሀቅ።
ወያኔ በወሽት ተፈጥሮ ውሽትን መሰረት በማድረግ የአገዛዙን እድሜ
ለማራዘም እንደሚጥር ለማንም ግልጽ ነው። የተለያዩ የሕዝብን አቅጣጫዎች ማሳቻ ምህንድስናዎችም እንደሚቀይስና ግብ ላይ በነማን አጋዥነትና
ተባባሪነት ላለፉት ሁለት አስርት አመታት ሲያደረግ እንደነበረ እንዳል በተለይ የወያኔን ሥነስርአትን ገርስሦ ለመጣል በሚደርገው
የትግል ርብርቦሽ የተሳተፉ የሚሳተፉ ኃይሎችም ስፊው ሕዝባችንም ቢሆን በዋቢ የሚያውቀው ጉዳይ ነው። ሆኖም ይህ የማደናገርና ትኩረት የማስቀየር ስልቱና እንቃስቃሴውም የንቃተ ህሊናቸው ደካማ የሆነውን ብቻ ሳይሆን ነቃን አውቅን፤ ምሁር ልሂቅ፤ ተቃዋሚ የሕዝብ መሪ በሉን የሚሉትንም ሰለባ አድርጎ ለስላቅ ዳርጓቸዋል። በ1997-ኡ ምርጫ ጊዜ የሙት ከተማ አድማን አክሽፈው ከወያኔ ሟቹ ቀጣፊ ጋር የረባ ድርድር ይካሄዳል ብለው የቋመጡት ወደዱም ጠሉም ወያኔን እንደጠቀሙና የሕዝብን ወሳኝ ትግል ግን መቀመቅ እንደከተቱ በምጸት የምናስታውሰው ነው። በዜጎች ሬሳ ላይ ተረማምዶና ማወቅ የሚገባቸውን አደናግሮ፤ ጥቂቶችንም በሆዳቸውና በፓርላማ ወንበር ገዝቶ ባለጌ አገዛዙን በራሳችን ላይ በቀጣይነት ሊጭን ችሏል። የማቹ ዘረኛ የወያኔ ቁንጮ ባለቤት "የባሌ የወር ደሞዝ 4ሺ ብር ነው” ልጆቼን ማስተማሪያ ገንዘብ አጠረኝ ስትል የዋሾ ዋሾ መሆኗን ለማረጋገጥ ፈልጋ ሳይሆን ሕዝብን ሞኝ አድርጋ ወስዳ የወያኔ ማደናገር ሁሌም ይሠራል በሚል እምነት ነው። ወያኔ ሕዝብን መናቁ ደግሞ የአደባባይ ምስጢር መሆኑ አይካድም።
የተነሳውን ተቃውሞ ሁሉ ደም አፍሶ ስለሚያፍን ፤ አርድ አንቀጥቅጥ ሕዝባዊ አመጽ ገና ስላልተከሰተ፤ ቢያፍስ ቢረሽን የሚደርስበት አጸፋ ባለመኖሩ፤ ተለጣፊና አደግዳጊ ማፍራት በመቻሉ፤ በሰርጎ ገቦችና በታኝ- አንጃዎች ድርጅቶችን ማዳከም ስለቻለ፤ የሀገርን መሬት ለሱዳን ሲሸጥ፤ ለቻይና፣ ለህንድና አረቦች ሲቸረችርና ሕዝብን ሲያፈናቅል፤ የሃይማኖት ተቋሞችንና አማኞችን ሲደፍር ሲረግጥ፣ ሲያስር ሲበድል፣ ስነ ምግባር ለጎደለው አረብ ቱጃር ሕዝብን አዋርድ ብሎ ሲፈቅድ፤ ህጻናትንና ወጣት ሴቶችን ሲሸጥ፤ የሀገራችንን መሬት የባዕድ ጦር መስፈሪያ ሲያደርግ አሁንስ በዛ ብሎ የሚያምጽ በማነሱና ይባስ ብለውም ሰላም ሰላም እያሉ የሕዝብ ትግል ላይ ቀዝቃዛ ውሀ የሚቸልሱ በመብዛታቸው የወያኔ ንቀትና እብሪት ከዳሸን ተራራ ተልቋል። ወያኔ ነጋ ጠባ ወይም አስፈላጊ በሆነበት ማደናገሪያውን ይፈለፍላል። ሆኖም ማንም የተሞኝለት የሚሞኝለት
የለም።
በቅርቡ ይዞ የተነሳውን የአባይ ግድብና የሙስና አፈሳ ማደናገሪያዎችም መጥቀስ የሚገባን ነው። የፈረደበትን አማራ በጥላቻ ካፈናቀለ በኋላ ተቃውሞ ሲፋፋም በሙስና እነ እገሌን አፍሰናል ብሎ በመንጫጫት የብዙዎቹን ትኩረት አቅጣጫ ቀየረ። የታገቱት የወያኔ የውስጣዊ ችግርና ቀውስ ሰለባዎች እንዳሉ ሆኖማደናገሪያ/መጠፊያ መሆናቸው ደግሞ ለማንም ግልጽ ነው። ዋናዋ የሙስና እቴጌ እያለች፤ ሀፍረተ ቢስና ይሉኝታ ያጡ በሙስና የተጨማለቁ ዋና ዋና ወያኔዎች እያሉ ድምቢጦችን አፍሶ ጩኸት ማፋፋሙ ግቡ የሕዝብንና የዓለምንም ትኩረት ከአማራው ጥቃት ለማንሳትና ለመቀየር መሆኑ ግልጽ ነበር--በከፊልም ሰርቷል ብንል ስህተት አይሆንም።
የሕዝብ ትኩረት የወያኔን አገዛዝ በማስወገድ ላይ መሆን ያለበት ነው። ተቃዋሚ ድርጅቶችም ዋና ትኩረታቸው ከፋፋዮችንና የወያኔ ሰርጎ ገቦችን አስወግደውና ድክመታቸውን አቸንፈው በጋራ ትግል ላይ መሰማራት ነው። ከዚህ አስፈላጊና ሀገር አድን ትኩረት የሚያግድ ማንኛውም የወያኔ ሴራና እንቅስቃሴ ለወያኔ ወርቅ ነው። በአረብ ሀገሮች/ሰሜን አፍሪካ ዛሬ ቢደናቀፍም የሕዝብ አመጽ ተፋፍሞ እየተስፋፋ ስለነበር ይህም ወደ ኢትዮጵያ እንዳይዘልቅ የፈሩት ወያኔዎች የአባይ ግድብ የሚል ማደናገሪያን ይዘው በመነሳት፤ ለኢትዮጵያ የሚጠቅም እቅድ የሚይዙ አስመስለው በመመጻደቅ ለማደናገር ችለዋል። በግብጽና ሱዳን ሙሉ ድጋፍ ለሥልጣን የበውቃው ወያኔ፤ ሥልጣን እንደያዘም አባይን በተመለከተ ከሙባረክ/ግብጽ ጋር ገጥሞ የነበረው፤ የሀገራችንን መሬት ለሱዳን የሸጠው፤ ለህንድና ቻይና፣ …ወዘተን መረን ለቆ ስንት ሺውን ያፈናቀለው ወያኔ፣ ከመቅጽበት ለሚጠላት ኢትዮጵያ አሳቢ ይሆናል/ሆነ ብሎ መገመት ራሱ ከስህተት በላይ ቅዠት ሆኖ ሳለ አባይም ይገደባል፤ ከወያኔ ጎን ቆመን ደማችን ግብጽን ለመከላከል ይፈሳል የሚሉ ተቃዋሚዎች ወይም ነቃን ባይ ምሁር በሉን ባዮች ብቅ ብቅ ብለዋል። ወያኔ እውን ግድቡን ሊሰራ ካሰበ 4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ድሀ ሕዝባችን ላይ ጭኖ መክራን ከማባባስ ለምንስ ከዘረፈው ገንዝብ ወጪውን አይሸፍንም? ለምንስ ሱዳን ድንበር አጠገብ ሄዶ ግድብ ልስራ ይላል ? ኢትዮጵያ የጥቁር አባይ ምንጭ ብትሆንም ብቸኛ የአባይ ባለቤት አይደለችም-- ውሀ አጠቃቀምን በተመለከተ ዓለም አቀፍ ህጎች ኣሉ--ግብጽም ብትሆን ይህን መካድና መሻር አትችልም። አባይ ከመገደቡ በፊት የወያኔ ፀረ ኢትዮጵያ አገዛዝ ይውደቅ ማለቱ ሲገባ በሌለ አቅምና አላስፈላጊና ጎጂ በሆነ ጎዳና ወደ ግጭት መንጎድ ስህተት ነውነው።
ወያኔ ለሥልጣን ከበቃ በኋላ የኢትዮጵያ መከራና ስቃይ መረን ለቆ መባዛቱ፣ መብዛቱ የሚካድ አይደለም። የሕዝብና የሀገር ጠላት የወያኔ አገዛዝ ነው ። ግብጽ ሆነ ሌላ በመጀመሪያ ደረጃ የሚመደቡ አይደሉም። ዝንጀሮ በቅድሚያ የመቀመጫዬን እንዳለችው የሕዝብ ዋና ትኩረትና ግዳጅ መሆን ያለበት ወያኔ ጠላት መሆኑን አውቆ አምርሮ--ሳይደናገሩ-በመታገል ማሽነፍና መጣል ነው። ይህ ንቃትን፤ ለወያኔ ተንኮል ሰለባ አለመሆንን ይጠይቃል። በተያያዘም ደግሞ የሀገራችን ሕዝብ የቆየ አንድነት ታድሶ መቀጠል እንዳለበትም ጫና ሰጥቶ መገንዘብ ያስፍልጋል።
ትግል ይቀጥላል!!
የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔን ያቸንፋል !!_