የምትገድሉት ደስታን ስለሚሰጣችሁ ነው።
ሰውን መግደል በፉልም እንደምናየው አይነት ትሽ፤ ትሽ፤ አይነት ቀላል ነገር በጭራሽ አይደለም። በእዚህ ጉዳይ ላይ የተደረጉ ጥልቅ የሆኑ ጥናቶች በሙሉ የሚያሳዩት ሆነ አጥኚዎቹ የሚስማሙበት እጅግ በጣም በጣም ከባድ ነገር ያዘለ መሆኑን ነው። ይህን አይነት ገጠመኝ ያላቸው ሰዎች በሙሉ ህጋዊ ፖሊስ ሆነ ወታደር፤ ነብሰ ገዳ ወይ እራስን ለመከላከል ብሎ የፈፀመው ሁለም ተመኩሯቸው ሲናገሩ ዘግናኝና እጅግ አስፈሪ ጉዲይ እንደሆነ ነው። ብዙዎች ተመልሰው የድሮ ማንነታቸውን ማግኘት እንዳልቻሉ ነው የሚመሰክሩት። አባቶቻችን ደም ያለበት ሰው የሚለት ከመሬት ተነስተው አይደለም።
የብዙዎች ገለፃ ሰውነትህ ውስጥ ያለው ደም በሙለ አይምሮህ ላይ ይሰባሰባል። ልብህ በርጥሶ የሚወጣ አይነት ነው የሚሰማህ። አይንህ በድም ይሞላል ማየት አትችልም። ብዥ ይልብሀል። አይምሮህ ማሰብ ያቆማል። የት እንዳለህ ይጠፊብሀል። የሚለ አይነት ናቸው። ለረጅም ጊዜ የሚያስከትለው ጦስም በጣም ቀላል እንዳልሆነ ነው የሚናገሩት። ይህ ሁለ ግን ለመጀመርያ ጊዜ ነው። እንደሁለም ነገር ሲደጋገም መላመድ ይኖራል። ለተላመዱት እልም ያለ አውሬ፤ ለዛውም እብድ አውሬ ነው የሚሆኑት።
የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያንን ከዛሬ በሗላ ብሶታቸውን ባደባባይ ካሰሙ እንገላለን ብለው መንግስት ነን የሚሉ ግለሰቦች መግለጫ በዜና አውታራቸው አሳልፍው ሰማው። መንግስት ነን ስላሉ ብቻ መንግስት ናቸው ብዬ መቀበል የለብኝም። ላለፉት ሀያ ሁለት አመታት ኢትዮጵያ ውስጥ መንግስት የሚባል ነገር መኖሩን ለመቀበል ከሚቸገሩት ውስጥ ነኝ። የተለመደውን አይነት የለየላቸው አንባገነን መንግስት ለሚለውም ነው የምትሞሉልኝ። እኔ ብቻ ግን አይደለሁም “መንግስት የለም ወይ” የሚሉት ድምፆች እየበዙና ጎልተው መሰማት መጨመራቸው ያለ በቂ ምክንያት በጭራሽ አይደለም። ዛሬ ነን ብትሉም። መንግስት ናቸው የሚልም ቢኖሩ። ያገር ክህደትት ስለፈፀማችሁ።ለዛውም በተደጋጋሚ። ንፁሀን ዜጎችን በጅምላ የፈጃችሁ ስለሆናችሁ። ነገ ከነገ ወዲያ ደግሞ እንፈጃለን ብላችሁ እየፎከራችሁ ስለሆነ።ዛሬም ባይሆን ጊዜው ሲደርስና ህግ ፉት ስትቆሙ በረከት ስምኦን፤ አዳኅኖምና ብዙ ተጋዳላይ ተክላይ ተኩልዎች እንዲሁ ሀይለማርያም ደስ አለኝ፤ አባዱላና ደመቀ ምን አለበት ሀይሌም አስገቡኝ እያለ ነው ካስገባችሁት እራጩ ሀይሌ ጀሌ ሆነው እንደ አስተዋጿቸሁ እንደሚሆን አያወዛግበንም።
ግን መንግስት ሆናችሁስ ቢሆን። እንደውም በአግባቡ ውክልና ያላችሁ ህዝብ ምሩን ብሎ ድምጽ የሰጣቸሁ። መንግስት ስለሆናችሁ በጅምላ ለመግደልም፤ ለማሰርም ሆነ ለመደብደብ መብት ተሰጥቷል ብሎ የነገራችሁ ማን ነው?። በአለም ላይ ካለም ከነበሩም መንግስታት በጅምላ የመግደልና የማሰር መብት የነበራቸው አሉንስ?። የተጨፍጨፈ ቢኖሩም መብት ነበረን ብለው የሞኝ ክርክር ያቀረቡስ?። አቅርበውስ?። ፍቃድ ነበራቸው ተብለው በህግ ፉት ነጻ የወጡ ?። ወይስ መቼ ነው ከመረጣችሁን በሰኘንና ባማረን ጊዜ ሴት፤ ህፃን፤ ጎረምሳ ሳንል በጅምላ እንጨፈጭፊችሗለን፤ እናስራችሗለን ብላችሁ ነግራችሁን ዜጋች ማለፉያ ነው ያልነው። ታዲያ በምን መሰረት ነው ትክክል የሆናችሁ ወይ መብታችሁ መስሎ የተሰማቸሁ?።
“መንግስት እርምጃ ይወስዳል”። ዘረኛ ውላጅ ነብሰ ገዳይ ሁሉ። እውነት እውነት እላችሗለው በምንም መመዘኛ ሆነ የህግ አንጻር በጅምላ ለመግደልና ለማሰር ማሰባችሁ በራሱ ወንጀል ነው። በጅምላ ንፁሀንን መግደል ሁላም ትክክል ተደርጎ ተወስዶ አያውቅም አይደለምም። ሁሌም ማንም ያደረገው ማን ጥርት ያለ ወንጀል ነው።
ግነ ካልጨፈጨፍን የምትሉ ምን አደረጓችሁ?፤ ምን ጥፊት ፈጸሙ ቢሉዋችሁ ነው? ። እምነታችሁን ቀይሩ አትበሉን ስላሉ። ድርጅቶቻችን ከኛ ውስጥ በተውጣጣ ቦርድ ይተዳደር ስላሉ?። ምርጫችን በመስጊዳችን ስላሉ?። ወይስ እንደመሩን የመረጥናቸውን በማን አለበኝነት ማሰራችሁ ትክክል አይደለም ስላሉ ተደፈርን ብላችሁ ነው?።
ለሁለት አመት ሙለ ደግመው ደጋግመው ያሉት ይህንኑ ነው። ይህንኑ ቅሬታቸውን ደግሞ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ መስጊዳቸው ውስጥ ሆነው ነው ያሰሙት። መቶ ጊዜ በሚጠጋ አቤቱታቸውን ሲያቀርቡ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ነው። ታዲያ የትኛው ሃሳባቸው ወይ ድርጊታቸው ነው በገፍ ከልገደልናችሁ፤ ሰብስበን ካላሰርናችሁ ተኝተን አናድርም እንድትሉ ያደረጋችሁ። ይህ በዘረኝነት ላልታወረ ዜጋ በሙላ፤ አለምም የታዘበው የሚመሰከርው እውነት ነው። ታሪክም የዘገበው ይህንኑ ነው። ታዲ ታዲያ ለምን በጅምላ ልተገሉና ልታሰቃዩ ፈለጋችሁ?።
ይህ መልስ የሚሻ በጣም ትልቁ ጥያቄ ነው። ሁሉም ዜጋ አፅኖት ሰጥቶ ሊመረምረው የሚገባም ጉዳይ ነው። ለምን በጅምላ ፍጅት ለመፈጸም አሰቡ?። በትክክልም ዝግጅታችሁ ብዙ ይናገራል። ስትቋምጡ ነበር። ከሁለት አመት በሗላ አሁን ልትፈፅሙት የምትችሉ ጉዳይ ሆኖ ለምን ተሰማቸሁ? እነዚህ ጥያቄዎች መመለስ አለባቸው። አስገዳጅ ሁኔታ ውስጥ ስላይደላችሁ ለጊዜው ከናንተ መልስ አናገኝም። እኛ ግን አግባብ ያለው መልስ ልንሰጥበት ይገባል። እውነተኛውን የውስጥ የአይምሯችሁን ፍርጥርጥ አድርገን ማስቀመጥ አለብን።
ዋንኛው መልስ ያለው እነማናችሁ የሚለው ላይ ነው። ስበሀት፤ በረከት፤ ሳሞራ፤ አቦይ ፀሀይዬ፤ አለማየው አቶምሳ፤ አዲሱ ለገሰ፤ ሀይለማርያም የመሳሰሉ አጫፊሪዎች ጋር አይደላችሁም?። እናንተ ናችሁ እንግዲ እርምጃ ለመውሰድ የወሰናችሁት። እርምጃ ስትሉ በገፍ ልትፈጁ ነው?። በገፍ ልታስሩና ልታሰቃዩ ነው። አሸባሪና መንግስትን በሀይል ለመጣል ስትሉ በደረደራችሁት ምክንያቶች ተነስተን የስላምንእምነት ተከታዮች ችግራቸው ከመንግስታችሁ ጋር እንደሆነ እንድናስብ ትፈልጋላችሁ አይደል?። መንግስታችሁን ለማቆየት ዜጎችን መግደል በራሱ ወንጀል ነው። በእኩል የሚያስቆጣን የምንቃወመውም ቢሆንም መግስታቸውን ለመከላከል ነው ብለን እስካሰብን ግን ችግር የለውም አይደል?። ደም ናፊቂ ልክስክስ ወሾች።
ታዲያ የምንግስታችሁ ጉዳይ ከሆነ የስላምና እምነት ተከታይ ዜጎች ባደባባይ የጠየቋችሁ ጥያቄዎች በጣም ቀላሎች ነበሩ። ጥያቄዎቹን መመለስ በደንብ ትችለ ነበር። ብትመልሱ መንግስታችን የምትለት ጉዳይ ላይ በየትኛውም አቅጣጫ የሚያመጣው ምንም ጉዳትም አልነበረም። ጥያቄዎቹ ቀላልና ወሳኝ ስላልነበሩ ለጊዜው መልሳችሁ ያጣችሁትን ቁጥጥርና የበላይነት በሂደት የነበረበት ማድረግስ ጠፍቷችሁ ነው?። ቀጥተኛ ባልሆን ሁኔታ ለጥሩ የሚችሉት ተጽኖዎች ቢኖሩ እንኳ ለጊዜው ለዚህ እልባት ሰጥቶ በሗላ ተያያዥ ችግር ካስከተለ መፍትሄ መስራትን የምታውቁት አሰራር አይደለም። በድጋሚ ታዲያ ለምን ደም ያለበትን ምርጫ አደረጋችሁ?።
መንግስታችሁን ለመከላከል ከሆነ ሌሎችም ብዙ አማራጮች ነበሩ። የውጪ አማካሪዎቻችሁም የተሻሉትን ሌሎች አማራጮች በርግጠኛነት ነግረዋችሗል። ድሮም ሲያማክሯችሁ የነበሩ የናንተ ቅርብ የሆኑ ሰዎች በአደባባይ አማራጮችን አሳይተዋችሗል። ሙስሉም ዜጎቻችንን እምነታችሁን ቀይሩ ነው እያልችሗቸው ያላችሁት። ይህ በቀላል እንደማይሆን ታውቃላችሁ። ለምን ብዙ ንፁሀንን መግደል፤ ብዙ ንፁሀንን ማሰቃየትን የሚል ሌላውን መንገድ መረጣችሁ?።
ኢቲቪን ለሚያዳምጥ፤ ሰለጉዳዩ በተለያየ ጊዜ የተናገራችሁትን የሰማን፤ ጀሀዲዊ ሀረካት፤ የአባታችንን የኑሩ ሁሴን ግድያ የተቀናበረበትን ሁኔታ። የሰጣችሁትን ያየር ሽፊን፤ የተቀደደ ባንዱራ ቡትለካ፤ ቀድሞውንም ምርጫ ያደረጋችሁት መንገድ ደም ያለበትን መፍጀት የሚያስችሎችሁን መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው። ሌሎችም ብዙ ጠቋሚ መረጃዎች የሚያረጋግጡት ይህንኑ ነው። ለምን ግን?።
የሰው ልጅ ስልጣን ላይ ሰለወጣ ብቻ የሰው ህይወት ቁብ የማይሰጠውና ፍጅት ፈፃሚ አይሆንም። ሁሌም የሚኖሩትን ተቀናቃኞችን ማስወገጃው መንገድ ግድያ ነው ብለው የሚያስቡ ብዙ መሪዎች በርግጥ አሉም ነበሩም ። ሙት አመቱ እየተከበረበት ያለውን ሰውዬ ጨምሮ የኛዎቹ ተጋዳላይ ገዳዮች ንፁሀንን የምትፈጁበት
ምክንያት ግን ለስልጣን እጦት ስጋት በጭራሽ አይደለም።
ነብስ እንዳወቃችሁ ለትግል ጨካ ገባችሁ። ላለፈት አርባና ሀምሳ አመታት ሞት ስቃይና ሰቆቃ የበዛበት ሁኔታዎች ውስጥ ነበራችሁ። ሁላችሁም ማለት በሚቻል ሞትና ስቃይ ቀንደኛ ፈጣሪዎችም ነበራችሁ።
በዚህ ጊዜ ውስጥ ምን ያህል የሞተ ሰው ነው ያያችሁት፤ ስንቶቹ ጭንቅላታቸው ፈርሶ ነበር።
ስንቶቹስ ደረታቸው ተከፍቶ ነበር። ስንት የተቆረጠ እግር፤የተቆረጠ እጅ ወይ የወጣ አንጎል ነበር ያያችሁት። ሰንቶቹ
የምታውቋቸው ነበሩ። ስንት ሰው ተኩሳችሁ ገድላችሗል። ከገደላችሗቸው ስንቶቹ ትዋጓቸው የነበሩ ወገኖቻችሁ ናቸው። ስንቶቹ የምታውቋቸው
አጋሮቻችሁ፤ ጓደኞቻችሁ፤ ዘመድቻችሁ ነበሩ። ብዛታቸው በርግጥ በቁጥር ልታስቀምጧቸው የሚቻላችሁ ነው። የሰው ልጅ ለመሞት ሲያጣጥር ምን ይመስላል?። የሰው ልጅ ስቃይና ህመም ሲበዛበት ምን አይነት ባህሪ ነው ያለው?። ስንት የሰውን ልጅ ስቃይ መቋቋም አቅቶት እስኪሞት ድረስ አሰቃይታችሗል?።
አንባቢ ማወቅ ያለበት ወያኔዎች
እያንዳንዳቸው ለነዚህና ይህን ለመሰለች ጥያቄዎች ማስታወስ የቻሉትን ብቻ እንኳ ቢናገሩ ብዙ ደርዘን ገጠመኞችን መናገር የሚችሉ ናቸው። ተስማማንም አልተስማማን እነዚህ ሰዎች የተለዩ ናቸው። ጤናማ አይምሮ ለሆን በአገራችን እየሆነ ላልው ነገር ሁለ ትርጉም የሚሰጥ መረዳት ለመያዝ የሚቸግረን ወናው ምክንያት ይህ ይመስኛል።
የመግደል፤ ሰቆቃ
የመፈፀም፤ በጅምላ የመፍጀት ልምዳቸው የተጋድሎ ጊዜ ከሚሉት የሚነሳና እያደገ እየዳበረ የሄደ የመግደል፤ ሰቆቃ የማሰፈስፀም፤ በጅምላ
የመፍጀት ልምዳቸው የተጋድሎ ጊዜ ከሚለት የሚነሳና እያደገ እየዳበረ የሄደ ነው። ቤተመንግስቱን ከተቆጣጠሩ በሗላ የፈጸሟቸው ንፁሗንን መፍጀት በሙሉ አንድ በአንድ አውጥተን ብንመረምር አንዳቸውም እነሱ ለክፉ ድርጊታቸው የሰጡት ምክንያት አይደለም እኛ በተለያየ ጊዜ ለፍጅአቸው ልንሰጣቸው የሞከርናቸው ምክንያቶች በበቂ ሊያስረዱት ወይ ትርጉም እንዲሰጥ ሊያደርጉት የሚችሉት አይደለም። ለምን?።
በበደኖ፤ በሀረር፤
በአርሲ፤ በጋንቤላ እንዲሁ የጎንደር የኦርቶድክስ እምነት ተከታዮች ላይ። የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ።
በምርጫ 97 በሗላ በመላው አገሪቱ በይበልጥም በአዲስ አበባ የተፈጸሙትን ፍጅቶች ሌሎችም አንባቢ አንድ በአንድ እያወጣ እንዚህ ግለሰቦች ፍጅትና ደም ያለበትን ምርጫ ሲያደርጉ እንዲያደርጉ የሚያስገድድ
ሁኔታ በርግጥ ነበር ወይ ብሎ እስቲ ይጠይቅ?። ነበሩ የሚባሉት ችግሮች ለስልጣናቸው ወይ በግላቸው
በርግጥ የሚያሰጋቸውና የዚህ አይነት ጭፍጨፋ እንዲፈፅሙ የሚያደርጋቸው ነበር
ወይ?። ሌሎች አማራጮችስ አልነበራቸውም ወይ? የመሳሰለትን ጥያቄዎች አንስቶ መልስ እራስን በነሱ ቦታ አድርጎ ለመስጠት ይሞክር። የሚደረስበት እውነታ የሚገሉት ስለሚያስደስታቸው ልምድ
ስላረጉት ነው የሚል መደምደሚያ ላይ ነው። በተራ በተራ እያነሳው በስፊት ያሌሄዴኩበት ፀሁፈን
ላለማንዛዛት ነው።
ካስፈለገ ትናንሽ
ሊሰኙ ነገር ግን ስለነዚህ ግለሰቦች በጣም ብዙ ሊነግሩን ከሚችለ አስረጅ ምክንያቶችን መጨመር ይቻላል።
መለስ ዜናዊን ጨምሮ ዛሬ መንግሰታችን የሚለት ብዙዎች ከምርጫ 97 በሗላ የፈፀሙት ፍጅት ላይ በመጀመርያ የቅንጅት መሪዎች በሗላ ላይ ደግሞ ብርቱካን
ነች ንፁሃንን የፈጀችው ብለው አተካራ ካለባቸው ሲገጥሙ እናስታውሳለን። ግራ ግብት እስኪለን። በረከት ስምኦን ቅንድቡ እንኳ ሳይርገበገብ ዜናዊ አልሞተም አይኔን
ግንባር ያድርገው ብሎ ሲናግርስ። እኔን ጨምሮ እርግጠኛ ነኝ ብዙዎቻችንን ይህ ሰው አልሞተ ይሆን እንዴ ብለን እንድንጠራጠር አድርጎናል። በደንብ የሚያውቁትን
የቀድሞ ባልንጅሮቹን ጨመሮ ብዙዎችን የበረከት የመዋሸት ችልታ አስምኗቸዋል። የዚህ አይነት ያልተለመደና አስገራሚ ድርቅና፤ ወሸት፤ ሽምጥጥ አድርጎ የመካድ ባህሪ ከየት መጣ። እጠይቃለሁ ለምንድነው
በጅምላ ሁላችሁም በጣም በተለየ ሁኔታ ልትካኑበት የተቻላችሁ?።
ኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ ሰልፍ በቦንብ ተበትኑ ነበር፤ እስረኛ በአውሬ
ታስበሉ ነበር፤ ታክሲ ላይ ወይ ጋዝ ማድያ ላይ ቦንብ አፈንድታችሁ
ንፁሀንን ፈጅታችሗል። ንፁሀንን
አስራችሁ የመጨረሻው ድረስ ስቃይ ትፍፅሙና ውስጣዊ ጥንካሬያቸውን ሲሰባበር እያናዘዛችሁ ተሳልቃችዋል?። ያልተለመደ አይነት የሆነው የፍቶት ፍላጎታችሁስ?። ይህን የመሰለ ሌሎችም
ብዙ ታምር ሊሰኙ የሚችሉ ጉዶችን ደራርባችሁ
አሳይታችሁናል።፡ እንዴት አንድ ጤናማ አይምሮ ያለው ሰው ይህን
አይነት ዘግናኝና አስገራሚ ድርጊቶችን ሊፈፅም ይችላል። ለኔ መልሱ
በሽተኞች ናችሁ። የምትገሉት ደስታን ስለሚሰጣችሁ ነው።
መግደልን ልምድ አድርጋችሗል።በሆነ መንገድ ልናስቆማችሁ ካልቻልን በጭራሽ እየባሰባችሁ ይሄዳል እንጂ አታቆሙም።
እራሱ በመግደል የተለከፈ አስገዳይ ሲሆን እንዴትም አድርጎ ስብእና ሊስማው አይችልም። ምኑስ ሊከብደውና ቆም ብሎ እነዲያስብ ያደርገዋል?።
ለመጀመርያም ለመጨረሻም ጊዜ እሬሳ ያሳያችሁኝ እናንተ ናችሁ። እንደገባችሁ ሰዎች እየገደላችሁ እሬሳ አይነሳ በምትሉበት ጊዜ ነው። እውነት እላችሗለው ጤናማ አይምሮ ለምን ማየቱ በራሱ በጣም ይረብሻል። የእህቴ ልጅ ከካናዳ ከናቱ ጋር
አገር ቤት ይሄዲል። ጊዜው የፊሲጋ በአል የሚከበረብት አካባቢ ነበር። ለበአለ ሁለት ቀን ቀደም ብል በግ ተገዝቶ ነበር። ልጁ ከበጉ ጋር ጓድኝነት መስርቶ ኗራል። የበአለ ቀን ጠዋት ከንቅልፈ ስነሳ በጉ ሲታረድ ያያል። የአስራ ሁለት አመት ልጅ ነው። አምርሮ አለቀሰ፤ አምርሮ
አዘነ። ደግሞ ደጋግሞ ለምን ትገሉታላችሁ፤ ምን አደረጋችሁ ብሎ ነበር ሲጠይቅ የነበረው። ሰጋ መብላት የጀመረው ከብዙ ጥረትና አመታት በሗላ ነው። አዬ ሌጄ
ያኔ እንዳይሰማ በአማርኛ ያለው እዚህ አገር ላይ ሲያሰኛቸው ሰው የሚያርዱ የነገሱበት መሆኑን
አላወክ ነበር።
ይህን ፅሁፍ የፃፍኩት ቀድሞ ሌሊት ነበር። ሳላበጃጀው እሁድ ከሰአት
የሱሳቸውን እንዳደረሱ አነበበኩ። እስከሚቀጥለው አርብ ይጀምራለ የሚል ግምት አልነበረኝም። አላስቻለቸውም ወገኖቼን
ቅዳሜ እለት ፈጆቸው። ከሰማሁበት ጊዜ አንስቶ ከፍተኛ ሀዘንና ቁጭት እየተሰማኝ ነው።
ጮህን እንኳ ይውጣልን። ድምፅችንን የምናሰማበት ሁኔታ ይፈጠር። ለምን በዚህ ጊዜ አሁን ደግሞ ለምን አርሲ የሚለውም በቅዳሜ ዝግጅት ለመደረጉ አስረጅ
ስለሆነ አመችቶኝ ብሄዴበት ደስ ይለል።
ዲዊት ዲባ።