Saturday, August 10, 2013

የመጨረሻው ሱባኤ ክፍል አንድ፡-ንግርት፣ የመጨረሻው መጀመሪያ ሱባኤና የመንግስት ትንቅንቅ

ክፍል አንድ፡-ንግርት፣ የመጨረሻው መጀመሪያ ሱባኤና የመንግስት ትንቅንቅ

በታላላቅ የበቁ የቤተ-ክርስቲያን አባቶች ዘንድ ዘመን የተቆጠረለት የኢትዮጵያን መጻኢ እድል የሚተነብይ ጥንታዊ ንግርት አለ። ኢትዮጵያ እግዚአብሔርን በካዱ ጨቋኝ መንግስታት ለአርባ አመታት ወድቃ እንደምትገዛ በታላላቆቹ የኢትዮጵያ ገዳማት አባቶች በለሆሳስ ሲነገር ከርሟል። ይህ ዘመን የሚቆጠረው ጃንሆይ ከተፈናቀሉበት ዘመን ጀምሮ ነው። ይህም ሲሰላ መነሻው 1966 .. መሆኑ ነው። አዎን አርባ አመት ከዛ ላይ
ስትጨምሩ የዘመን ባቡር በፍጥነት የፊታችን መስከረም 2006 .. ላይ ያደርሰናል። ይህ ትንቢት ይተገበር ዘንድ ግን በግድ መፈጸም ያለበት በመጨረሻዎቹ ሁለት አመታት ከታላላቅ የኢትዮጵያ ገዳማት የተውጣጡ አባቶች በሕብረት ሱባኤ መያዝ አለባቸው። ይህን ብርቱ ሚስጥር በየገዳማቱ አስርጎ በሰገሰጋቸው የበግ ለምድ በለበሱትካድሬመነኮሳት አማካኝነት ቀድሞ ያወቀው መንግስት ከፍተኛ የሰውና የገንዘብ ሃይል በመመደብ ሱባኤውን የማክሸፍ ዘመቻ ከፈተ።

በኢትዮጵያ ገዳማትና አብያተክርስቲያናት ዘመን የሚቆጠረው በሱባኤ እየተጠቀለለ ሲሆን፣ አበይት በሆኑ አጽዋማት ወቅት ልዩ ሱባኤ ስለሃገር፣ ስለሕዝብ፣ ስለሰላም፣ ይያዛል። በነዚህ ሁለት አመታት የተያዙት ሱባኤዎች ግን እጅግ ፈተና የበዛባቸው ሆነዋል። ሰርጎገብ የመንግስትካድሬመነኮሳት ባቀረቡት መረጃ የተደናገጠው መንግስት ሱባኤዎቹን ለማደናቀፍ ሰፊ እቅድና ዘመቻ ይዞ ከተነሳ አንድ አመት አለፈው። ለዚህ እቅዱ ማስፈጸሚያ ይረዳው ዘንድ ሽፋን መጠቀም ነበረበት። ለዚህም ነው በታላቁ ዋልድባ ገዳም ክልል ውስጥ የስኳር ፋብሪካ እክፍታለሁ የሚል አደናጋሪ ፕሮጀክት የጀመረው። መንግስት ተጠናክሮ በደረሰው መረጃ መሰረት የሱባኤ መያዣ ታላቁ የዋልድባ ገዳም ነው ብሎ አምኗል።

በተባለው የስኳር ፋብሪካ ሽፋን አማካኝነት የዋልድባጠፍመሬቶችን በስፋት ለመቆጣጠር ሲያቅድ፤ በተለያዮ የገዳሙ አብያተክርስትያናት የተያዙትን ቦታዎች ደግሞ በመረጣቸውካድሬመነኮሳት አማካኝነት ይቆጣጠራል። በዚህ እኩይ ምግባር የተነሳ ከታላላቅ የኢትዮጵያ ገዳማት ተጉዘው ዋልድባ ገዳም ለሱባኤ የደረሱ አባቶች ፈተና ላይ ወደቁ። በነዚህ መንፈሳዊያን ላይ ብዙ ስቃይ ደረሰባቸው። ብዙዎች ተደበደቡ፣ ብዙዎች ለእስር ተዳረጉ፣ ብዙዎች ተፈናቀሉ።ከመንግስት ቁጥጥር ውጭ የሆኑ መገናኛ ብዙሃን የመንኮሳቱን እንግልትና የህዝቡን ተቃውሞ በተከታታይ ሲዘግቡት ቆይተዋል። እስካሁን ግልጽ ሆኖ ያልወጣው ጉዳይ ግን የመንግስት ድብቅ ሱባኤ ማስተጓጎያ ዘመቻ ነው። አዎን ለመንግስት በደረሰው የካድሬ መነኮሳት መረጃ መሰረት ትንቢቱ የሚሰምረው ሱባኤዎቹ ሲፈጸሙ ነው። እናም የግዛት ዘመናቸውን ለማራዘም በሰውኛ የማይፈነቅሉት ድንጋይ አይኖርም።

ክፍል ሁለት፡- የተረሱ መቋሚያዎች

ሰዎች ወደንስሃ እንዲገቡና እንዲድኑ የሚወደው አምላክ መላእክተኞቹን በትእቢት ለታወሩት እንኳ ይልካል።ሰዎች ግን በክፉ ምርጫቸው መጥፊያቸውን ሲመርጡ በመጽሃፍ ደጋግመን አይተናል። ለሱባኤ ዋልድባ ገዳም የተሰባሰቡ መነኮሳት መንግስት የከፈተባቸውን መጠነሰፊ የጥፋት ዘመቻ በመገንዘብ የእግዚአብሔርን የንስሃና የድህነት መልእክት አስይዘው ተወካዮቻቸውን ወደቤተ-ክህነት እና ወደ ቤተ-መንግስት ላኩ። እንደፈርኦን ልባቸው በትእቢት የታወሩት የቤተ- ክርስቲያን እና የመንግስት መሪዎች ለሰላምና ለምህረት የተዘረጋላቸውን እድል አበላሹ።

የቀድሞው ጳጳስ አቡነ ጳውሎስ እና ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በይፋና በአደባባይ ስለዋልድባ መነኮሳት እንግልት ሽምጥጥ አድርገው ካዱ። ተወካይ መነኮሳቱ መጀመሪያ ያመሩት ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ መለስ ዜናዊ ጽህፈት ቤት ነበር። አራት ኪሎ ቤተ-መንግት ድረስ ለመሄድ ድፍረት ማግኘታቸው ያስገረማቸው የስርአቱ ባለስልጣናት በለመዱት አይን ያወጣ ብልጣብልጥነት መነኮሳቱን ሊደልሉና ሊያግባቡ አልሆን ሲልም በሃይል አስገድደው መንግስትን ደግፈው በቴሌቪዥን እንዲቀረጹ ከባድ ትንቅንቅ አደረጉ። ፍርሃትን ያሸነፉት መነኮሳት የተቀረጹት ቃል ግን ለመንግስት የተሰጠውን የመጨረሻ እድል ነበር። እናም ይህ ቃላቸው በልዮ ሚስጥር እንዲጠበቅ ታዘዘ። ይህንን ተመሳሳይ ጥሪ ለአቡነ ጳውሎስ ይዘው የሄዱት መነኮሳት እዛም የእብሪትና የእምቢታ መልስ ጠበቃቸው። ነገር ግን አንድ አስደንጋጭ ክስተት ተፈጠረ።

ለሰላም መልእክት ወደ አቡነ ጳውሎስ ቅጽረ-ጊቢ የተጓዙት መነኮሳት አንድ ነገርእረስተውመሄዳቸው የተነገራቸው አቡነ ጳውሎስ ልባቸው ተንጠልጥሎ ምንነቱን ይጠይቃሉ። የጉዳዩን ክብደት ያልተረዱት አገልጋዮቻቸው ነገሩን አቅለውመቋሚያእረስተው መሄዳቸውን ሲነግሯቸው አቡኑ በድንጋጤ ወደመሬት ይወርዳሉ። አገልጋዮቻቸው የደረስባቸውቅስፈትአስደንግጧቸውና ግራ ገብቷቸው አፋፍሰው ወደ ሃኪም ያደርሷቸዋል። አባ ጳውሎስ ሃኪም ዘንድ ደርሰው ነፍሳቸውን ሲያውቁ አንድ ነገር ይከነክናቸውና በጥድፊያ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ደውለው ስለመነኮሳቱ ቆይታ ይጠያይቁ ገቡ። ጊዜ ሲከዳ ከባድ ነውና የሚፈሩትን ዜና መስማት ግድ ሆነባቸው።

አዎን እነዚያ መነኮሳት በዛም ሰፈርመቋሚያ እረስተዋል”! ይህንን እንደ ክፉ መርዶ የተረዱት አባ ጳውሎስ እየደጋገሙተቀሰፍን” “ተቀሰፍንእያሉ በታላቅ ድምጽ ሲጮሁ ያረፉበትን ሃኪም ቤት ሰራተኞችና እረዳቶቻቸውን ድንጋጤ ላይ እንደጣሉ ይታወቃል። ጥንታዊ በሆነው የቤተ-ክርስቲያን ልማድ፣ የንስሃና የድህነት መልእክታቸው የተገፋባቸው መነኮሳት መቋሚያ ጥለው ከሄዱ እንደመርገምት ይቆጠራል። ውድ አንባቢያን እንደምታውቁት ልክ የዛሬ አመት የሆነውና እንደ ተአምር የተቆጠረው ጣምራ ሞት የጣምራ መቅሰፍት እዝ እንደሆነ ከዚህ መረዳት ይቻላል። ከዚህ መለኮታዊ መልስ ውጭ ቤተ-ክርስቲያንን እና ህዝቡን በጋራ አስጨንቀው የሚገዙት ሁለት የስርአቱ ቁንጮዎች በአንድ ላይ ላይ ለቅስፈት ሲዳረጉ ሌላ ምን ሊባል ይቻላል!

ክፍል ሶስት፡-ደረስጌ ማርያም

ይህች ታሪካዊት ቤተ-ክርስቲያን የምትገኘው በጎንደር ክፍለ ሃገር፣ በወገራ አውራጃ፣ ዳባትን አልፎ የወቅን ተራራን ተሻግሮ የዳሸን ተራራ እግርጌ በሆነቸው በደባርቅ ከተማ አቅራቢያ ነው። ታሪካዊ የሚያደርጋት ጥንታዊት መሆኗ ብቻ ሳይሆን የዘመናዊ ኢትዮጵያ መስራች የሆኑት አባ ታጠቅ ካሳ፤ አጼ ቴዎድሮስ ተብለው በአቡነ ሰላማ ተቀብተው የነገሱባት ሚስጥር የተቋጠረባት ደብር ናት። አምና ደግሞ ሌላ ታሪካዊ ጉባኤ አስተናገደች። ዋልድባ ገዳም ሱባኤ እንዳያደርጉ እጅግ ውስብስብ መሰናክል የተጋረጠባቸው መነኮሳት በአካባቢው የሚገኝ ተለዋጭ፣ የማይገመት እና አሳቻ ቦታ መፈለግ ነበረባቸው። ሽሚያቸውም ከሰአት ጭምር ነበር። የመጨረሻው-መጀመሪያ ሱባኤ መፈጸም የነበረበት የፍልሰታን ጾም ተንተርሶ ነው። ስለሆነም አዲስ አበባ የመጡበት የሰላም ጉዞ እንደተደናቀፈ ባስቸኳይ ሱባኤው መጀመር ስለነበረበት ቀሪዎቹ መነኮሳት መርጠው በቆዩት የደረስጌ ማርያም ተከናወነ።

የደብሯ ምእመናን እና ቀሳውስት ከተለመደው ውጭ በርከት ብለው የሚገኙት መነኮሳት ጉዳይ ግር ቢላቸውም ክርስቲያናዊ እንክብካቤያቸውን ግን አልነፈጓቸውም። መነኮሳቱም ራቅ ወዳለ ገዳም እየተጓዙ እያለ በማሃሉ የፍልሰታ ሱባኤ እንዳይስተጓጎል በአቅራቢያው ካገኘናት ደብር ተጠጋን ብለው ሚስጥሩን ቀበሩት ጥርጣሬንም አጠፉ። እንዲያውም ህዝበ- ክርስቲያኑ ከበረከታቸው ለመሳተፍ ልባዊ አገልግሎት አቅርቧል። የእግዚአብሔርም ልዮ ሚስጥር በዚህች ታሪካዊት ደብር ተገልጾ ደረስጌ ማርያም ዳግም ታሪክ ተፈጸመባት። የመጨረሻው-መጀመሪያ ሱባኤ በዚህ መልኩ በአምላክ ፈቃድ ተፈጸመ። ያ ሱባኤ የትንቢቱ ፍጻሜ መዳረሻ የሆኑ አበይት ክስተቶች ታዮበት። በገዥው መደብ መደናገጥን ፈጠረ። የስርአቱም ሹማምንት እንደባቢሎን ሰዎች አልሰማማ ብለዋል። ከክርስቲያኑ ከተቆራረጡ ቆዮ፣ ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ከተካረሩ አመት አለፋቸው፣ አንቀላፍተው የነበሩት ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንኳ እረፍት በሚነሳ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፎች አጨናንቀዋቸዋል። ታዲያ ቀጣዮ ምን ይሆን? ትንቢቱ እና የአርባ አመቱ ቀጠሮስ ደርሶ ይሆን? ለዚህ ቁልፍ የሆነው የመጨረሻው ሱባኤስ እክል ይገጥመው ይሆን ወይስ የተስፋይቱ ቀን ሳናስበው ጎበኘችን!

ክፍል አራት፡- የተስፋው ምእራፍ፣ የአርባ አመት ቀጠሮ

ከባዱ እና ውስብስቡ የመጨረሻው-መፈጸሚያ ሱባኤ የተያዘው ደግሞ በዚህችው የእመቤታችን የመታሰቢያ ጾመ-ፍልሰታ ላይ ነው። ለመሆኑ ከብዙ ገዳማት የተውጣጡት እነዚያ መነኮሳት የመጨረሻውን ሱባኤ የት እያደረጉ ነው?
የመንግስት ሴራስ እንዴት ይታለፋል?

በመላ ኢትዮጵያ የሚገኙ ብዙ አብያተ ክርስቲያናት በዘንድሮ ፍልሰታ ለየት ያሉ ገዳማውያን መነኮሳትን ማስተናገዳቸውን በውል ሳይገነዘቡት እጅግ የበቁ አባቶች ከህዝበ ክርስቲያኑ ጋር ተመሳስለው ሱባኤውን ይፈጽማሉ። ለመጨረሻው ሱባኤ የተመረጡ የታላላቅ ገዳማት አባቶች በሁለት አበይት ምክንያቶች በአብያተክርስቲያናት ተበትነው እንዲያሳልፉ ወስነዋል። የመጀመሪያው ምክንያት ከመንግስት ውስብስብ መሰናክል እና እይታ ውጭ ለመሆን ይጠቅማል።
በዋናነት ግን መላ ሕዝበ ክርስቲያኑ ለትንቢቱ ስምረት በግድ የሱባኤው ተሳታፊ መሆን ስላለበት ነው። ይህን የአርባ አመት የጦርነት፣ የአፈና፣ የርሃብ፣ የስደት፣ የውርደት፣ የግድያ እና የመለያየት ዘመን አልፎ የፍቅር፣ የደስታ፣ የሰላም፣ የብልጽግና፣ የአንድነትና የተስፋ ሃገር ለመድረስ ይህችን የመጨረሻ ሱባኤ ከእግዚአብሔር ጋር ተገናኝቶና ፈቃዱን ፈጽሞ መገኘት ግድ ይላል። ማነው አይኑን የገለጠ?

ምን እንደ ሙሴ ለፈጣሪ የቀረብን ብንሆን በዚህች የመጨረሻ ሱባኤ ፍጹም ታዛዥ ካልሆንን የምንጓጓላትን የተስፋይቱን ምድር እንኳን ልንረከባት ላናያትም እንችላለን። ታዲያ በእኛ አመጸኛ ልብ እንዴት ይህ ሊሆን ይችላል?

ግን ለአምላክ የሚሳነው አለን! እንኳን እንደ አሸዋ የሞሎ የበቁ አባቶች ላላት ኢትዮጵያ ለአንድ ጻድቅ ሲል እንኳ ሰዶምና ገሞራን አላተረፈም! በጻድቁ ኖህ መርከብ ፍጥረትን ለዘር አልታደገም! ግን ግን የአምላክ ልዩ ትእዛዝ በኢትዮጵያ ላይ በተለየ መልኩ መጥታለች። ሕዝበ ክርስቲያኑ ከገዳማውያን፣ መናንያን ጋር የመጨረሻውን የሃገር ሱባኤ እንዲያደርሱ በላካቸው መልእክተኞቹ በየምኩራቡ ሲነገር ከርሟል። ጆሮዎችያድምጡ፣ አይንም ተገልጦ ይይ፣ ልቦናም ያስተውል። የመጨረሻው ምእራፍ ላይ ደርሳቹሃልና ተግታቹህ ጸልዮ። ስለቤተክርስቲያን ጸልዮ። ስለኢትዮጵያ ጸልዮ። ስለህዝቡ ጸልዮ። የተስፋይቱን ምድር አጥብቃቹህ እሿት ታገኟትማላቹህ።

ማስገንዘቢያ

ይህ ጽሁፍ ከምናብ ነው ከእውን፣ ከታሪክ ነው ከንግርት፣ ከምኞት ነው ከተጨባጭ፣ ከእምነት ነው ከፍላጎት፣ ከሸክም ነውከተስፋ፣ እያላቹህ እንዳነበባቹህት እገምታለሁ። ልቦናችሁ እንደተቀበለው ተቀበሉት።

ሙሉነህ ዮሃንስ
ከሲያትል ዋሽንግተን
የፍልሰታ ልደታ ቀን 2005 .. ተጻፈ



ሃሳብ መለዋወጥ ከፈለጋቹህ muleur@yahoo.com

Thursday, August 8, 2013

Amnesty International: Ethiopian repression of Muslim protests must stop

The Ethiopian government must end its use of repressive tactics against demonstrators, following initial reports of widespread arrests of Muslim protestors during this morning’s Eid al-Fitr celebrations, said Amnesty International today.

“We are extremely concerned at reports coming out of Ethiopia this morning of further widespread arrests of Muslim protesters. The Ethiopian government’s ongoing repressive crackdown on freedom of speech and the right to peacefully protest has to end now,” said Claire Beston, Amnesty International’s Ethiopia researcher.

Last week, another incident related to the protests reportedly ended in the deaths of an unconfirmed number of people in the town of Kofele in Oromia region.

During the 18 month-long protest movement against alleged government interference in Islamic affairs, the vast majority of demonstrations have been peaceful. However, there have been at least four incidents involving serious allegations of the excessive use of force by security forces against demonstrators in the long-running movement.  While a few isolated incidents of violence involving protestors have occurred, these have taken place during episodes where excessive police force is alleged.

“These reports of further deaths in the context of the Muslim protest movement are deeply worrying. There must be an immediate, independent and impartial investigation into the events in Kofele, as well as into the four incidents last year which resulted in the deaths and injuries of protestors,” said Claire Beston.

“With further protests planned, it is imperative that the behaviour of the security forces is scrutinised and if enough admissible evidence of crimes is found, suspected perpetrators should be prosecuted in trial proceedings that meet international standards.”
Accounts of last week’s incident in Kofele from the protestors and the government differ widely.

Protestors report that the security forces opened fire on unarmed people who were protesting against the arrests of members of the local Muslim community. One resident of Kofele told Amnesty International that 14 people were shot dead by the army, including at least three children. Another said that 11 people had been killed.

According to media reports, the authorities have said that the protestors were armed, leading to an outbreak of violence which resulted in the deaths of three protestors and injuries to a number of police officers. Government representatives refused to respond to Amnesty International’s queries about the incident.

There are also reports of large numbers of arrests in and around Kofele, Oromia, and further arrests in Addis Ababa over the last week.
Those arrested included two journalists – Darsema Sori and Khalid Mohamed – detained early last week in Addis Ababa.

The two men were working for Radio Bilal, which has regularly reported on the protest movement. Darsema Sori had also previously worked for the publication Ye’Muslimoch Guday (Muslim Affairs), from which two employees have already been arrested during the protest movement, and who are currently being prosecuted under the Anti-Terrorism Proclamation.

According to information received by Amnesty International Darema Sori and Khalid Mohamed are being held at Sostegna (third) police station in Addis Ababa and are not being permitted visitors. They have reportedly been taken to court and were remanded in custody while the police continue their investigation.

Reports of arrests and detentions of peaceful protestors and people suspected of involvement in organising the protests have continued throughout 18-months of demonstrations.

Despite many months of large-scale, peaceful protests, the government has repeatedly attempted to paint the protest movement as violent and terrorist-related in statements to the media and in parliament. Amnesty International has received a number of reports of messages aired via the state media over the last week, warning that the authorities would take firm action against anyone who attempted to take part in further demonstrations.

“This is a violation of people’s right to peacefully protest, as protected in Ethiopia’s Constitution,” said Claire Beston. “The government continues to respond to the grievances of the Muslim community with violence, arbitrary arrests and the use of the overly-broad Anti-Terrorism Proclamation to prosecute the movements’ leaders and other individuals.”

As demonstrations continue, Amnesty International is concerned that the response of the authorities will also continue to involve human rights violations, including arbitrary arrests of peaceful protestors and possible further bloodshed.

The organization urges the Ethiopian government to respect the right of its citizens to peacefully protest and urges an immediate end to heavy-handed tactics in response to the protests. Anyone arrested solely for exercising their right to peaceful protest must be released immediately.

Background
The trial continues of 29 figures related to the protest movement including nine members of a committee of representatives selected by the Muslim community to represent their grievances to the government, and one journalist, Yusuf Getachew, of the publication Ye’Muslimoch Guday. The trial has already been marred by a number of fair trial concerns, including the airing on state-run Ethiopian Television (ETV) of a programme called “Jihadawi Harakat.” It painted the Muslim protest movement and some of the individuals on trial as having connections with Islamic extremist groups, seriously jeopardising the right of the defendants to be presumed innocent until proven guilty.

The trial is now taking place in closed proceedings, increasing fears that the defendants will not receive a fair trial. Amnesty International believes that the individuals on trial are being prosecuted because of their participation in a peaceful protest movement.

Solomon Kebede, another journalist working for Ye’Muslimoch Guday was recently charged under the Anti-Terrorism Proclamation along with 27 other people, according to information received by Amnesty International.

During 2012 there were at least four incidents in which the security forces were alleged to have used excessive force during the dispersal and arrest of protestors. At least two of these incidents – in the towns of Gerba in the Amhara region, and Asasa in the Oromia region – resulted in the deaths of protestors.

Two further incidents in Addis Ababa reportedly resulted in many injuries to protestors. Amnesty International called for independent investigations to be conducted into these incidents, but according to available information, no such investigation has taken place.

Other protests have also been affected by the government’s pervasive intolerance of dissent. The opposition Unity for Democracy and Justice Party has reported arrests of its members in a number of locations around the country in recent weeks. They were engaged in organising demonstrations, handing out leaflets for demonstrations and calling on people to sign a petition calling for the revocation of the Anti-Terrorism Legislation and the release of political prisoners.