Monday, September 23, 2013

ወያኔ በባሕርይው ጅብና ውሻ ነው

አውሬ አውሬነቱን አይረሳምአለ ልበል ተወልደ (ተቦርነ) ስለአንበሣው ቀላቢውን መግደል ሲያወራ አሁን? አዎ፣ ብሏል፡፡ እውነት ነው አውሬ አውሬነቱን አይረሳም፡፡ ወያኔም ወያኔነቱን አይረሳም - እባብ የትምና መቼም ቢሆን እባብነቱንና የወጣበትን ጉድጓድ እንደማይረሣ ሁሉ፡፡ ወያኔ ፀረ-ኢትዮጵያ ነው፤ ወያኔ ፀረ-አማራ ነው፤ ወያኔ ፀረ-ሃይማኖት ነው፤ ወያኔ ፀረ-ሰላምና ፀረ- ዴምክራሲ ነው፡፡ ወያኔ ኢትዮጵያንና ትውፊቶቿን ለማጥፋት የተነሱ የውጭ ኃይላት ብቸኛ ወኪል ነው - ‹የአድኅሮት ኃይላት ተላላኪ፣ የኢምፔሪያሊዝምና የቢሮክራሲያዊ ካፒታሊዝም አራማጅ ቅጥረኛልበልና የደርግን ዘመን አብዮታዊ ትዝታ ልቀስቅስባችሁ ይሆን? ወያኔ እነኚህን መሰሎቹን የተፈጥሮ ሣይሆን የተጋቦት ባሕርያቱን መቼም አይረሳም - ቢጠግብም - ቢወፍርም -አገርና አካባቢ ቢለውጥም - እርስ በርሱ ቢጣላም - በሎሚ ተራ ተራ አንዱ አንዱን ቢያስርና ቢገርፍም - በማንኛውም ረገድ ወያኔ የተነሣበትን የወያኔነት ጠባይና ምግባሩን አይረሳም፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ ሰውን ጨምሮ በብዙ እንስሳት የማይታይ አንድ እጅግ አስገራሚ ጠባይ አለው፤ ያምአህያ ለአህያ ቢራገጥ ጥርስ አይሳበርም
እንዲሉ በወያኔዎች መካከል ደም እስከመቃባት የደረሰ ጠብና ቅራኔ በነሣም እንደቃል ኪዳን ሆኖ ወያኔ ወያኔን ለሌላ አካል አጋልጦ የማይሠጥ መሆኑ ነው፤ ለዚህም ነው አቶ ስዬ አብርሃ ለአሳሪው ለአቶ መለስ ዜናዊ ሞት ፍራሽ አንጥፎ ከነቤተሰቡ ልቅሶ ተቀምጦ እንደነበር መስማት የቻልነው - መቼም ስዬ እንደክርስቶስ መሓሪ ወይም እንደእግዚአብሔር ሁሉን ታጋሽና ቻይ ሆኖ ነው ብንል ራሱ ስዬ ይታዘበናል - ይህ አስገራሚ ክስተት ከዘረኝነትና ከጎጠኝነትጋር የተያያዘ መሆን አለበት፡፡ ይቅርታ ይደረግልኝና ያን ሁሉ ግፍና በደል በኔና በቤተሰቤ ያደረሰብኝ ደብረታቦሬ ሀገር መሪቢሞት ከሞራልና ከሃይማኖት እንዲሁም ከባህል አንጻር በደስታ ጮቤ መርገጡ ቢቀርብኝ ማቅ መልበሱና ሀዘን መቀመጡ ግን በሟቹ የመቀለድ ያህል እንደሚያስመስልብኝ እገምታለሁና የምሞክረው አይመስለኝም፡፡ የነእንትና ነገር ግንአታሃዛዚቡናእንደተባለው ነው፡፡ እያልኩ ያለሁት በመለስም ሆነ በሌሎች ወያኔዎች የተበደሉ ወያኔዎች አይዘኑ አይደለም፡፡ ከፈለጉ ቅጥ ባለው መንገድ ማዘን ይችላሉ፤ በይሉኝታቢስነታቸው ቀጥለውበት ትዝብት ውስጥ መግባትን ከቁብ ካልጣፉት ደግሞ ፊታቸውን መንጨትና ሰባትም ዐሥራ አራትም ዓመት ከል መልበስ ይችላሉ፡፡ መጠቆም የፈለግሁት የነሱን ጠብ በውኃ እንደሚፀዳ ተራ ነገር የሚቆጥሩ ሲሆኑ፣ በሌሎች ላይ ቂምና የነገር ቁርሾ ከቋጠሩ ግን ባላጋራዎቻችን ናቸው ብለው የፈረጇቸውን ዕድለቢስ ወገኖች መቀመቅ ካላስገቡ በቀላሉ የማይለቁ እጅግ ሲበዛ መርዘኛ መሆናቸውን ነው፡፡
አለመለከፍ ማለት ቀድሞውን ወያኔን አለመሆን ወይም ወያኔን ሆኖ አለመፈጠር ነው እንጂ አንዴውኑ በወያኔነት ልምሻ ከተኮደኮዱ በኋላ የፈውሱ ነገር አዳጋች ነው - በተለይ እንዳሁኑ ዘመን ጊዜ እየነጎደ በሄደ መጠን የተፈጠሩበትን ዕለት እስከመራገም ለሚያደርስ አሰቃቂ የመጨረሻ ዕጣ ይዳርጋል፡፡ ከዚህ ከወያኔው ዓይነት የዘረኝነት ልክፍት የሚፈወሱና ጤነኛ ሰው የሚሆኑ - ጤነኛ ሆነውም አውቀው አምነውበትም ይሁን ሳያውቁ ተታልለው የበደሉትን ሀገርና ሕዝብ ለመካስ የሚተጉ እጅግ ጥቂቶች ናቸው - ያም እንደገና የመወለድ ያህል መታደል ነው - ለነሱም ለሀገርም፡፡ እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች ደግሞ የዕንቁ ያህል ውድ ናቸው፤ በቀላሉና የትም አናገኛቸውም፡፡ እናም እንግባባ - ወያኔ ወያኔነትን የትም ሆኖና በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ለአፍታም አይዘነጋትም፡፡ መዘንጋት ለኅልውናው አደጋ እንደሆነ ያህል ስለሚቆጥረው ይመስለኛል፡፡ አንዲት ማረሚያ ቤት የምትገኝ የወያኔ ወታደር ሰሞኑን በርዕዮት ዓለሙ ላይ ፈጸመቺው የተባለው አስነዋሪ የዘረኝነት ድርጊትም ከዚህ ጋር በቀጥታ የሚገናኝ ነው - ለዚህች ደንቆሮእሥረኛ›  ወያኔነት ማለት የገነትም የመንግሥተ ሰማይም ገዢ ነው - ‹እሥር ቤቱና አሣሪዎቹ እኛው እስከሆን ድረስ፣ ገዢዎቹ እኛው እስከሆን ድረስ ይበልጥ እሥረኞች ሌሎች እንጂ እኛ አይደለንምብላ ሳታምን አልቀረችም(ይህ ዓይነቱ ከፍተኛ ሞኝነት የሚነበብበት የወያኔዎች አካሄድ የጆርጅ ኦርዌልን “All animals are equal, but some animals are more equal than the others.” የሚለውን ያስታውሰኛል፡፡) የብዙዎቹ ወያኔዎች መርሆ እነዚህ ብሂሎች ልብ እንድንል ያደርጉናል፡- “የዘሬን ብተው ያንዘርዝረኝትንሽ ሥጋ እንደመርፌ ትወጋየሥጋ ትል የዘመድ ጥል በእንግሊዝኛው ደግሞ “Blood is thicker than water.” ይህ የወያዎችየዋህነትየሚያሳየን ግን የእግዚአብሔርን መንገድና ትክክለኛውን ማኅበረሰብኣዊ የዕድገት ደረጃን ሣይሆን በዝቅተኛ የንቃትና የዕውቀት ደረጃ የሚገኙ የሌሎች እንስሳትን ነሲባዊ የመሳሳብ ጠባይ ነው፡፡ ሰው ከሰውነት ደረጃ ወርዶ እንዲህ ያለ የደምና የአጥንት ማነፍነፍ ቅሌት ውስጥ ሲገባ ማየት ደግሞ በማኅበረሰብም ይሁን በሀገር ደረጃ ከፍተኛ አለመታደልና የሀፍረት ምንጭም ነው፡፡
የተወልደ በየነ ንግግር እንደዐረብ ጣቢያ ድንገት ጣልቃ ገብቶብኝ በርሱ አባባል ጀመርኩ እንጂ አነሳሴ ቲቪ እያየሁ ሳለ በተጓዳኝ እያነበብኩት በነበረውና አሁን በጨረስኩት አንድ ድንቅ መጣጥፍ ላይ ተመርኩዤ የበኩሌን ጥቂት ለማት ነበረ፡፡ይህ ግሩም ጽሑፍ የቀረበው ከአንድ በስደት ላይ እንደሚገኝ የገለጸ የቀድሞ የመንግሥት ሚዲያ ዘጋቢና የኮሚኒኬሽን ባለሙያ ነው፡፡ ጽሑፉ የሚያትተው ወደፊት መጽሐፍ ሆኖ ይወጣል ከተባለና አንድ የወያኔ ከፍተኛ ባለሥልጣን ይሄው የመንግሥት ሚዲያ ዘጋቢ ከሀገር ሊወጣ ሲል ለሰባት ሰዓታት ያህል በመቅረፀ ድምጽ አጋዥነት ሰጠው ከተባለው የኑዛዜ ቃል ተቀንጭቦ የቀረበ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡ ርዕሱበሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ ከሚገኝ የልብ ወዳጄ ጋር በአገራዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያደረግሁት ምሥጢራዊ ውይይትይላል፡፡ ትንሽ ረዘም ቢልም መነበብ ያለበት ማለፊያ ጽሑፍ ነውና እባካችሁ አንብቡት - ሀገር በጣር ላይ እያለች ለማንበብ መድከም የለብንም፡፡ በተፋፋመ ጦርነት ውስጥ ገብቶ ለሀገር መዋደቅስ አለ አይደል? እየቀነጨብኩ ለፈርጥ ያህል በዚች መጣጥፍ ውስጥ በመጠኑ እንዳልጠቅስላችሁ ጽሑፉን ከፒዲኤፍ ወደወርድ ስለውጠው አንዳንድ ሆሄያት ቅርጻቸው እየተንሻፈፈብኝ ተቸገርኩ፡፡ ወያኔ ኢትዮጵያን ለማጥፋት የሚተገብራቸውን ሥልቶች ብዙዎቹን ታገኙበታላችሁ፡፡ ወያኔ የቱን ተመርኩዞ የቱን እንደሚያጠፋናቀጥሎም አንዱን ለማጥፋት የተጠቀመበትን ምርኩዝ ሰባብሮ የትም እንደሚጥል - ባጭሩ ሕወሓት አስብቶ አራጅ መሆኑን ትረዱበታላችሁ፡፡ በምታምኑት ይሁንባችሁና ግዴላችሁም አንብቡት!
ወያኔ በባሕርይው እንደጅብም፣ እንደውሻም፣ እንደዓሣማም፣ እንደእስስትም፣ እንደእባብምነው፡፡ ለወያኔ የባሕርይ መግለጫነት የማይሆኑ ርግብን የመሳሰሉ የዋሃን ፍጡራን ብቻ ናቸው፡፡ በተረፈ ወያኔ ማለት የክፋት ተምሳሌት የሆኑ የተፈጥሮም ይሁኑ ሰው ሠራሽ ነገሮች ውሁድ ሥሪት ነው፡፡ የክፋት አድማሱ ደግሞ ወሰን የለውም፡፡ ድንበር የለሽ ክፋት ደግሞ ድንበርን ተሻግሮ ብዙ ዘመናትን የማጣቀስ ጠባይ አለው፡፡ ለዚህ ነው የክፋት አምባሳደሩ ወያኔም ሞተ ሲሉት እየተነሳ በአፈ ታሪክ ዘጠኝ ነፍስ ያላት መሆኗ እንደሚወራላት ድመት እስካሁኒቷ ቅጽበት ድረስ በአፀደ ሕይወት ሊገኝ የቻለው፡፡
የወያኔ ውሻዊ ባሕርይ፡፡ ውሾች እርስ በርስ ሊዋደዱም ላይዋደዱም ይችላሉ፡፡ ግን ግን እነሱም ልክ እንደብዙዎቹ እንስሳት ዘር መንጣሪና ”species”ኣቸው ውጪ ከሌሎች ጋር እምብዝም አይቀላቀሉምና በአደንም ሆነ በሥሮት ወቅት አይለያዩም፡፡ ወያኔዎች ከውሻ የወሰዱት ጠባይ ታዲያ ውሾች በግላቸው የፈለጉትን ያህል ይጣላሉ፣ ይነካከሳሉም እንጂ የውጪ ጠላትና የአደጋ ሥጋት ከተደቀነባቸው ቂጣቸውን ይገጥሙና ያን ጠላት በጋራ ይከላከላሉ፤ በክፉ ቀን በመካከላቸው ንፋስ አይገባም፡፡ አጥንት ላይ የተፋጠጡና የሰገሌን ጦርነት በውሻኛ “version” ሊደግሙት የተዘጋጁ ውሾች ሳይቀሩ ያን ሆድ-ተኮር ጠብ በጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት አቁመው የመጣባቸውን የጋራ ጠላት በጋራ ይጋፈጣሉ፤ በውነቱ ይህ መልካም ጠባይ ነው፡፡ በወያኔዎች ላይ ብቻ ተወስኖ መቅረቱና በሰባና ሰማንያ ሚሊዮን በሚገመተው አጠቃላዩ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲሁም በሌሎች የፖለቲካና ማኅበረሰብኣዊ ስብስቦች ዘንድ አለመሥራቱ ግን ያሳዝናል፤ ይቆጭማል፡፡ እነሱ ብልጥ ሲሆኑ ሌላው ጅላንፎ ሆኖ እስከወዲያናው በሚመስል ሁኔታ ሲጃጃል መታዘብ ትልቅ ቁጭት ነው፡፡ ከውሻ እንኳን መማር ያቃታቸው ኢትዮጵያውያን ተቃዋሚዎች ወያኔ በቀደዳለቸው የልዩነት መስመር
እየተመሙ ለወያኔው ዕድሜ መራዘም ጠንክረው በመሥራት ላይ ይገኛሉ፡፡ መቼ ነፍስ እንደሚያውቁና ለከርታታውሕዝባቸውመሢሕነታቸውን እንደሚያሳዩ አናውቅም፡፡ ውሻ በበጎም ሆነ በክፉ ብዙ ተጠቃሽ ባሕርያት ቢኖሩትም ለጊዜው ይህ በቂየ ነው፡፡
የወያኔ ጅባዊ ጠባይ፡፡ ጅብ ፈሪ ነው፡- ወያኔም በጣም ፈሪ ነው፡፡ ገደልኩት ብሎ የሚያምነውንጠላቱንእንኳን የሚፈራና መቃብር ውስጥም ገብቶ ዐፅምን በምናባዊ የስድብና የምፀት ጅራፍ የሚገርፍ፣ በሙታንም ላይ የሚሣለቅና የሚቀልድ ነው - ወያኔ፡፡ ለምሳሌ አማራንና ኦርቶዶክስን ገድሎ እንደቀበራቸው በወያኔዊ መድረኮች ካላንዳች ሀፍረትና ይሉኝታ እየተደሰኮረ ነው፡፡ ግዴለም ሞቱ እንበል፡፡ በሕይወት ያሉ እየመሰለው ታዲያን በባነነ ቁጥር በሚናገራቸው የዕብሪት ቃላቱና በሚያከናውናቸው ፀረ-ሕዝብ ተግባራቱ ለትዝብት እንደተዳረገ አለ ፡፡ ፍርሀት በራስ የመተማመን ችሎታን ያሳጣል፤ ፍርሀት ቤቱን የሠራበት ሰው እንደመለስ ተሳዳቢና አሽሟጣጭ ይሆናል፡፡ ፍርሀት ያሸነፉትን ጠላት እንዳላሸነፉት በማስቆጠር ቀን በእውን ሌት በውን እያስባተተና እያስቃዠ ወንጀለኛና ኃጢኣተኛ ያደርጋል፡፡ የወያኔ ወንጀል እየተቆለለ ሄዶ ለፍርድ አስቸጋሪ እስኪሆንበት ድረስ ፈጣሪን እያስጨነቀ ያለው እንግዲህ ከዚህ መሠረታዊ ምክንያት በመነጨ መሆን አለበት፡፡ እንዲያ ባይሆንስ ቁናው ከሞላ ሰንብቷል፡፡

ጅብ ሆዳም ነው፡፡ የጅብ ሆድ ደግሞ የሚመርጠው የለም፡፡ ያገኘውን እየሰለቀጠ ወደጎሬው ይገባል፡፡ የነጋበት ጅብ በተለይ አይጣል ነው፡፡ ወያኔ እንደዛሬው ሳይነጋበትም ሆነ እንደዱሮው በጊዜ ያገኘውን ሁሉ ማግበስበስ መነሻና መድረሻ ዋና ጠባዩ ነው፡፡ ወያኔ አይጠግብም - እምብርት የለውምና፡፡ ከመሰል ሰብኣዊ ጅቦች ጋር ሆኖ ኢትዮጵያን ራቁቷን እያስቀራት ያለ ወያኔ ነው፡፡ ጅብ ሆዳም ብቻ አይደለም፡፡ የብዙ ብልሹ ምግባራት ተምሳሌት ነው፡፡ ለአብነት እርስ በርሱ አይተማመንም፡፡ ከዚያም የተነሣ ሲሄድ እንኳን ፊትና ኋላ ሆኖ ሳይሆን ጎን ለጎን ሆኖ ነው ይባላል፤ በተለይ የቆሰለ ጅብ በመንጋው ውስጥ ካለ በጣም ካልተጠነቀቀ በስተቀር ከአህያ ያልተናነሰ ዕድል እንደሚገጥመው ይነገራል - በቁሙ ነው አሉ እሚዘረጥጡት፡፡ ወያኔም እንደዚሁ ነው፡፡ አይተማመኑም፤ እርስ በርስ ይበላላሉ፡፡ ተባልተው ተባልተው መጨረሻቸው ደርሷል እየተባለ ነው አሁን፡፡ ለሰው ማን እንዲህ ሹክ እንደሚለው አላውቅም፤ ግንመዥገሩ ወያኔ በደም አብጦና በደም ሰክሮ ሊፈርጥና ሊበታተን ነውእየተባለ በየቦታው ሲወራ እሰማለሁ - ወፍ ትሆናለችእንዲህ እያለች ምሥጢር እያወጣች  ያለች - እንዳፏ ያድርግልን፡፡ ለመሆኑ ግና - መለስ ብለን መለስን ስናስታውስ የወዲ ዜናዊ ሠይፍ ያልቀላው ትላልቅና ትናንሽ ወያኔ አለ ወይ? እንዴ፣ ያልተቆረጠመ ሰው እኮ የለም፤ የመለስ ነዲድና ፍላጻ ሞኛሞኙንና ቅን ታዛዡን ብቻ መርጦ ትቷል፡፡ በልዩ ወርቃማ ዕድል ከዐይኑ የተሠወሩበት ጥቂት ብልጣብልጦችና አድርባዮች ለዘር እንዲተርፉ የመለስ ውቃቢ አምላክ ምሯቸው እንደሆነ እንጂ መለስ የፈጀው ሕዝብ እኮ በውነቱ ከግምት በላይ ነው፤ መለስ ዜናዊ? ኧሯ! በጊዜ መሰብሰቡ በጄ(/-ኣቸው(?)) እንጂ ከርሱ ሾተል ማን ሊተርፍ ይቻለው ነበር? በተለይ እሱ የወያኔ ባለሥልጣን ከሆነበት የብረት ትግሉ የመጀመሪያ ዓመታት ጀምሮ በዚህ ሰውዬ ሥውርና ግልጽ ትዕዛዝ እንዲሁም የሽርና የተንኮል ሤራ በመርዝና በጥይት ብዙ የወያኔ ታጋይ እንዳለቀ ለጉዳዩ ቅርበት ባላቸው ሃቀኛ ወገኖች የተጻፉ ድርሳናት ይመሰክራሉ - የገብረ መድኅን አርአያ ጽሑፎችን ያነቧል፡፡ ይሄ ሁሉ እየታወቀ ግን መለስን እስከማምለክ ተደርሷል - ምክንያቱም መለስን መቃወምና መንቀፍ ማለት ከጥቅምና ከጋርዮሽ ዘውጋዊ ቁርኝት ጋር ይጣረሳላ! ምክንያቱም መለስን መቃወም ማለት አሁን የተደረሰበትን የአንድ ብሔር ሸፋፋና ቅጥየለሽየበላይነትሊያሳጣ እንደሚችል ይታመናላ! ድንቄም የበላይነት! የበላይ የሆኑትስ እየተበደሉና እየተረገጡ የሚገኙት በርካታ ሚሊዮን ወገኖች ናቸው፡፡ የበላይ የሆኑትስ እየተራቡና እየተጠሙ፣ እየታረዙና እየታመሙ፣ እየተጋዙና እየተገደሉ፣ በእሥርና በስደት አሰቃቂ ሕይወትም መከራቸውን እየበሉ ያሉት ምሥኪኖች ናቸው፡፡ የበላይ የሆኑትስ በገዛ ሀገራቸው እንደሦስተኛና አራተኛ ዜጋ ተቆጥረው የማንኛውም የኢኮኖሚና የፖለቲካ መብታቸው ሳይከበርላቸው እንደከብት እንዲኖሩ የተገደዱ ትግሬውን ጨምሮ የየትኛውም ዘውግ አባላት ናቸው፡፡ የበላይ የሆኑትስ ለኅሊናቸው ያደሩና ሀገራቸውን ከወያኔ ጋር ተባብረው ያልሸጡ የሁሉም ዘውግ አባላት ወገኖቻችን ናቸው፡፡ ማን የበላይ ማን ደግሞ የበታች እንደሆነ በጊዜ ሂደት የምናየው ይሆናል፡፡ በጮማ ግሣትና በውስኪ ብስናት ሕዝብ ላይ እያቀረሹመኖር የበላይነት መገለጫ ሳይሆን የአውሬነትና የእንስሳነት ጠባይ ማሳያ ነው፡፡ ኤዲያበቃኝ እባክሽ፤ አናጋሪዎች!

ይነጋል በላቸው

Sunday, September 22, 2013

New Video Semaywi Party


Ethiopian regime repression

They speak of democracy but act violently to suppress dissenting voices and control the people through the inculcation of fear. They ignore human rights and trample on the people. They are tyrannical wolves in democratic sheep’s clothing, causing suffering and misery to thousands of people throughout Ethiopia.


The right to protest
The Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) government repeatedly scoffs at international law and consistently acts in violation of its own federal constitution – a liberal document written by the regime to please and deceive its foreign supporters. It has enacted laws of repression: the widely condemned Charities and Societies Law and the Anti-Terrorism Proclamation – the main tool of political control – together with the Mass Media and Freedom of Information Proclamation form a formidable and unjust arsenal of government control. Freedom of the media (which is largely “state-owned”) is denied and political dissent is all but outlawed.

Against this repressive backdrop, the Semayawi (Blue) Party, a new opposition group, organized peaceful protests on 2 June in Addis Ababa. Ten thousand or so people marched through the capital demanding the release of political prisoners, “respect for the constitution” and justice. It was, Reuters news agency reported, an “anti-government procession… the first large-scale protest since a disputed 2005 election ended in street violence that killed 200 people” – a “disputed election” result that was discredited totally by European Union observers and denounced by opposition groups and large swathes of the population.

The chairman of the Semayawi Party, Yilekal Getachew, told Reuters: “We have repeatedly asked the government to release political leaders, journalists and those who asked the government not to intervene in religious affairs.” In keeping with the recent worldwide movement for freedom and social justice, he stated that, “if these questions are not resolved and no progress is made in the next three months, we will organize more protests. It is the beginning of our struggle.”

To the disappointment of many and the surprise of nobody, the government has made no attempt to resolve the questions raised and, true to their word, a second demonstration was planned for 1 September in Addis Ababa. In the event, as the BBC reported, around “100 members of Ethiopia’s opposition Semayawi Party were arrested and some badly beaten”, and “equipment such as sound systems were confiscated”, ahead of the planned rally, which was banned by the EPRDF. A government cock-and-bull story was duly constructed with Communication Minister Shimeles Kemal stating: “The venue [for Semayawi’s event] had already been booked by a pro-government group condemning religious extremism.”

Non-interference in religious affairs is one of the key demands of the Semayawi Party, a demand based on the constitutional commitment of religious independence from the state, which Muslim groups claim the government has violated. Enraged by government interference in all matters religious, the Muslim community has organized regular small-scale protests and sit-ins in the capital for the last two years. In early August, Reuters reported that demonstrators chanted God is great and hoisted banners that read “Respect the constitution”, referring to allegations that the government has tried to influence the highest Muslim affairs body, the Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council.

Around 40 per cent of Ethiopia’s population (about 85 million) are Muslim. For generations they have lived amicably with their Orthodox Christian neighbours, who make up the majority of the population. The Muslim community is generally regarded as moderate in its beliefs and peaceful in its ways. The EPRDF, in contrast, is violent, intolerant and ideologically driven, “Revolutionary Democracy” being the particular tune to which the democratic dictatorship hums and drums its partisan rule.

Name calling
The government’s response to the peaceful demonstrations has been intolerant and dismissive, describing the demonstrators as foreign-funded Muslim extremists seeking to set up an Islamic state.

Characteristically, it has also imprisoned Muslims, prompting Amnesty International to voice extreme concern and to demand an end to the widespread arrest of Muslim protesters and the repressive crackdown on freedom of speech and the right to peacefully protest.

Meanwhile, protests in Kofele in the Oromia region on 8 August ended in “the deaths of an unconfirmed number”. There have also been reports of large numbers of people being arrested in Kofele and Addis Ababa, including two journalists.

The EPRDF does not tolerate any independent media coverage within the country. It does all it can to control the flow of information out of Ethiopia and restricts totally dissenting voices.
Nor does the EPRDF care who the journalists it represses work for. In October 2012 a reporter from the Voice of America (VOA) covering a protest in Anwar Mosque in Addis was arrested and told to erase her recorded interviews, the Committee to Protect Journalists (CPJ) reported. This was not the first time a VOA journalist had been detained. “They are criminalizing journalism,” said Martin Schibbye, a Swedish freelance journalist who, together with another colleague, was jailed for more than 14 months in 2011 for entering the Ogaden region.

The Ogaden is a heavily militarized area where wide ranging human rights violations constituting crimes against humanity are taking place – violations which have been hidden from the international media and aid organizations since 2007.

Unjust laws of control
In July last year, hundreds of protesting Muslims peacefully demanding that the government stop interfering in their religious affairs and allow them to vote freely for representatives on the Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council were arrested. Most were released, but 29 members of the protest committee were charged on 29October under the universally criticized Anti-Terrorism Proclamation, accused of “intending to advance a political, religious or ideological cause” by force, and of the “planning, preparation, conspiracy, incitement and attempt of terrorist acts”. Their arrest has been slammed by human rights groups as well as by the United States Commission on Religious Freedom, which said it was “deeply concerned that Ethiopia’s government is seeking to silence peaceful religious freedom proponents by detaining and trying them in secret under trumped-up terrorism charges”. Those, who are detained, claim to have been tortured and experienced other ill-treatment in detention.

The ambiguous Anti-Terrorism Proclamation was introduced in 2009 and has been used by the Ethiopian government “to severely restrict basic rights of freedom of expression, association and assembly”, Human Rights Watch states. It violates dues process which, like a raft of other internationally recognized and legally binding rights, is enshrined in the Ethiopian constitution.

The proclamation allows for long-term imprisonment and the death penalty for so-called crimes that meet the EPRDF’s definition of terrorism, and in some cases it denies a defendant’s right to be presumed innocent – the bedrock of the international judicial system. Torture is used without restraint by the military and police. Under the Anti-Terrorism Proclamation evidence obtained while a prisoner is being beaten, hanged, whipped or drowned is admissible in court, which contravenes Article 15 of the United Nations Convention Against Torture (ratified by Ethiopia in 1994).

Ethiopia’s donors and international friends are primarily the US and Britain – have other, larger fish on their minds. Even though they give the country over a third of its federal budget, they seem unconcerned by the criminality being committed by the regime, much of which is taking place under the cloak of development.

Violent rule, however, is a storm that is imploding throughout the world. The people who have suffered long enough are sensing their collective strength and are awakening.

Need for unity
Contrary to the EPRDF’s pledge of ethical federalism, divide-and-rule is its methodology of choice. In a country with dozens of tribal and ethnic groups, and different religious beliefs, unity is the key to any popular social revolution. We are witnessing a worldwide protest movement for change. Age-old values of freedom, equality and social justice, brotherhood and peace are the clarion call of many marching and protesting people.

And so it is in Ethiopia. The Semayawi Party and other opposition groups, the Muslim community and the students are on the street demanding justice. Out of step and blind to the needs of the people and their rightful demands, the ruling party acts with violence to drown out their voices and suppress their rights: in Addis Ababa, where thousands marched in June; in Oromia and the Ogaden, where the people seek autonomy; in Amhara, where thousands have been displaced; and in Gambella and the Lower Omo Valley, where native people are being driven off their ancestral land into state-created villages, women raped and men beaten.


Unity is the song of the day. All steps need to be taken to remove the obstacle to the realization of unity throughout the country – ethnic prejudices and tribal differences must be laid aside. The Ethiopian regime may succeed in subduing the movement for change that is simmering throughout the country, but with sustained, unified action, peacefully undertaken and relentlessly expressed, freedom and social justice will surely come.

Grahm Peebles