Friday, October 4, 2013

መሬት የማን ነው?

መሬት የማን ነው?
(ክፍል አንድ)
መስፍን ወልደ ማርያም

አገር ማለት በአባቶች፣ በአያቶችና በቅድማያቶች አጥንትና ተገንብቶ የታጠረ መሬት ነው፤ የዶር. በድሉ ዋቅጅራን ዋይታ እየኮረኮረ የሚያወጣውና የሚያስተጋባው የፍቅር ስሜት ምንጭ ነው።

የተከሰከሰውና ተፈረካክሶ አፈር የሆነው አጥንትና የወረደው የአያቶችና የቅድማያቶች እየፈሰሰ መሬቱ በሚገኙ ወንዞች ውስጥ ሁለ ገብቶአል፤ እንዲያውም እነዚህ ወንዞች ወስደው በቀይ ባሕር፣ በሜዱቴራንያን ባሕርና በሕንድ ውቅያኖስ ጨምረውታል፤

ይህ በአጥንትና በደም የታጠረ መሬት የማን ነው? በመሬቱ የባለቤትነት መብትንማስከበር ከውጭ ኃይልች ጋር የተጋደሉት ጥንታውያን ነፍጠኞች ቅድሚያን የሚያገኙ ይመስለኛል፤ እነዚህ ጥንታውያን ነፍጠኞች ብቻቸውን አልነበሩም፤ ለምግብ የሚሆናቸውን ሁለ የሚያመርቱ ገበሬዎች ነበሩ፤ ለልብስ የሚያስፈልጋቸውን ሁለ የሚፈትሉና የሚሸምኑ ባለሙያዎች ነበሩ፤ጆቻቸውን የሚንከባከቡና የሚያሳድጉምዘማቹ ምግብ የሚያቀብሉ እናቶች ነበሩ፤ በአጠቃሊይ የሕዝቡን መንፈሳዊ ጤንነትመጠበቅ በቤተ ክርስቲያኖችና በመስጊዶች የሚጸልዩ ሰዎች ነበሩ፤ ሰላምን የሚያስከብሩና የሚያስተዳድሩ ሰዎች ነበሩ፤አንድ ማኅበረሰብተለያዩ  የመደጋገፍ ሥራዎች የሚያስፈልጉት የሰዎች ዓይነት ሁለ ነበሩ፤ እነዚህ ሰዎች ሁለ በአንድ አጥሩንመገንባት አስተዋጽኦ አድርገዋል፤ ስለዚህ መሬቱ የእነዚህ ሰዎች ሁለ ነው።

ታሪካችንን በተግባር በኩል ስንመረምረው ግን መሬቱን እኩል እንዳልተካፈሉት እናያለን፤ ዛሬ ነፍጠኛ የሚባለት መሣሪያ የታጠቁት ሰዎችራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ እንደሚባለው ሰፋፊ መሬት የመያዝ ዝንባሌ ነበራቸው፤ ነገር ግንማረስ የነበራቸው የሰው ጉልበትና የጥንድ በሬ ቁጥር የተወሰነ በመሆኑ ራሱንና ቤተሰቡንማስተዳደር ብቻሚፈልገው ገበሬ በቂ መሬት ይደርሰው ነበር፤ ሰፋፊ መሬት የያዙት ጉልበት አጥሮአቸው ሲቸገሩና ትናንሽ ማሳ ያለው ገበሬ ሰብለ ቀንሶበት
ሲቸገር በመጋዞ በማረስ ይረዳዳ ነበር (ገበሬዎችና ከብት አርቢዎችምሚቱ ስትወልድ ሴት ከሆነችከብት አርቢው፣ የከብት አርቢው ወንድ ስትወልድገበሬው እየተሰጣጡ ይረዳዱ ነበር፤) ሰፋፊ መሬት የያዙትም በጉልበት እጥረት ምክንያት፣ ትናንሽ ማሳ የያዙትም በትንሽነታቸው ምክንያት ከአስፈሊጊው በላይ ስለማያመርቱ ትርፍ ምርት ቢኖርም በጣም ትንሽ ነበር፤ ከላይ እሰከታች ያለው ሰው ሁለ የሚተዳደረው በመሬት ስለነበረ በጣም ጥቂትሆኑ ሰዎች (ቀጥቃጮች፣
አንጣሪዎች፣ ሸክሊ ሠሪዎች፣ ሸማኔዎችወዘተ.) ለጉልበት ዋጋ ከሚከፈልውናአስተዳዳሪዎች ከሚከፈለው ግብር በቀር አብዛኛው ምርትቤት ፍጆታ ነበር።

እዚህ ሊይ በመሬት ጉዳይመታረም ያስቸገሩ ሁለት ስሕተቶችን ሳላመለክትማለፍ አልፈልግም፤ ብዙ ጊዜ እንዲታረሙ ብጥርም ፈረንጆች በብዙ ሰዎች አእምሮ ውስጥ በሙጫ አጣብቀውትፋቅ አልቻለም፤ አንደኛ ገባር ማለት ባለመሬት ማለት ነው እንጂ ጪሰኛ ወይም መሬት የሌለው ሰው ማለት አይደለም፤ መሬት የሌለው ገባር አይባልም፤ መገበር ማለት የባለመሬት ግዳጅ ነው፤ ገባር ማለት ግብር ወይም ታክስ የሚከፍል ባለመሬት ነው፤ ጉዳዩን አጣርተው ያልተገነዘቡት ፈረንጆች በራሳቸው አገር የመሬት ስሪት ዓይነት እንደተረጎሙትኢትዮጵያውያን ወጣቶች አስተማሩ፤ እነዚያም ያንኑ እንደገደል ማሚቶ እያስተጋቡ ስሕተቱን አራቡት፤ ‹‹ፊውዲሊዝም›› የሚለው ቃልም ከዚህ ስሕተት ጋር የተያያዘ ነው፤ አውሮፓ የነበረው ፊውዲሊዝም የሚባል ነገር በኢትዮጵያ ኖሮም አያውቅ።

ሁለተኛው ከመሬት ጋር የተያያዘ ቃል ጉልት ነው፤ ጉልት በመሬት ላይ ያለ መብት ሳይሆን በመሬቱ ከፊል ምርት ላይ የተሰጠ መብት ነው፤ ደሮ ገንዘብ አልነበረምና በጥሬ ገንዘብ የሚከፈል ዋጋ አልነበረም፤ ለወታደሮችም ቢሆን በደመወዝ ፈንታ የሚሰጣቸው ገባሮች ነበሩ፤ ዛሬ ባለመሬቶች በጥሬ ገንዘብ ለመንግሥት ይከፍልና ገንዘቡ ተሰብስቦ ለወታደሮችም ሆነ ለሌሎ የመንግሥት ሠራተኞች ይከፈላል፤ ጥንት ግን ግብር ከፋዩን (ማለ ገባሩን) በቀጥታ ከመንግሥት አገልጋዩ ጋር ያገኛኙትና በእህል እንደቀለበውና በጉልበት እንዲረዳው ይደረግ ነበር፤ ይህ ሥርዓት አልተበላሸም ለማለት አይቻልም፤ ሆኖም የመንግሥት አገልጋዮች በገባሩ መሬት ላይ ምንም መብት አልነበራቸውም፤ እንዱሁም ጉልት የተሰጣቸው የመንግሥት ባለውለታ የሆኑ መሳፍንትና መኳንንት፣ ሴት ወይዘሮዎችም በመሬቱ ላይ ሳይሆን ለመሬቱ በሚከፈለ ግብር ላይ ነበር፤ የጉልት ሥርዓት እያለ የሚጽፉ ወይም የሚናገሩ ሰዎች አለማወቃቸውን እያራቡ ነው።
የኢትዮጵያን የመሬት ስሪት ውስብስብነት በትንሹም ቢሆንመረዳት ቢቀር የብላቴን ጌታ ማኅተመ ሥሊሴን ዝክረ ነገር ይመልከቱት፤ የጥንቱን እንተወውና በቅርብ ዓመታት ኢትዮጵያ ከሶማሌያ ጋር ቢያንስ ሁለት ጊዜ ተዋግታለች፤ ከኤርትራ ጋር የተደረገውን ጦርነትግሞ ብዙ ወጣቶችም የሚያውቁት ነው፤ እነዚህ ጦርነቶች የተደረጉት በመሬት ምክንያት ነበር፤ ምናልባትም ከሶማሌያ ጋር ሁለት ጊዜ ከተደረጉት ጦርነቶች ይልቅ ከኤርትራ ጋር በተደረገው ጦርነት የተገደሉት የኢትዮጵያውያን ቁጥር በጣም የላቀ ሳይሆን አይቀርም፤ ከዚያም በላይ ከኤርትራ ጋር ጦርነት የተደረገበት ምክንያት ከሶማሌያ ጋር ከተደረጉት ጦርነቶች ምክንያት በጣም ያነሰ ነው፤ በአጠቃሊይ አገሪቱን በሙለመውረር የመጣውንም ሆነ አንዲት ትንሽ መንደር የወረረውን እኩል በመዋጋት ሀብትንና የሰው ሕይወትን ማቃጠል የማሰብ ችግር ውጤት ነው፤ጊዜው ዋናው ነጥባችን በነዚህ ጦርነቶች የሞቱት ሰዎች መሬቱ የኛ ነው፤ አንሰጥም፤ በማለት ነው፤ በሌላ አነጋገር የመሬቱ ባለቤት፣ የመሬቱ ባለመብት እኛ በመሆናችን ያለፈቃዳችን አይወስደውም በማለት ነው።


ባለቤትና ባለመብት ሆኖ የሞተውና በየሜዳው ሬሳው ወድቆ ሳይቀበርጅብናአሞራ ምግብ የሆነው ኢትዮጵያዊ መሬትን እንኳንኑሮመቃብርም አላገኘም፤ በሆነው ባልሆነው መጫወቻ የሆነው መስዋእት የሚባል ቃል ትክክለኛ ትርጉሙ ይህ ነው፤ እንግዲህ ይህ ሰው መስዋእት የሆነውምን ዓላማ? ለማን ዓላማ ነው? የሚለው ጥያቄ መሠረታዊ ነው፤ ማንም ሰውመሞት በቆረጠበት ጊዜ ‹‹የምሞተውምን ዓላማ ነው?›› ብሎ መጠየቅ አለበት።