Friday, October 18, 2013

ኢትዮጵያ፡ በፖለቲካ እስረኞች ላይ የማሰቃየት ድርጊት ይፈጸማል

በግዳጅ የእምነት ቃል እንዲሰጡ ለማድረግ ፖሊስ በጋዜጠኞች እና በተቃዋሚዎች ላይ በደሎችን ይፈጽማል።


(ናይሮቢ፣ ጥቅምት 7 ቀን 2006 .) የኢትዮጵያ ባለስልጣናት አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው ዋና የማሰሪያና የምርመራ ጣቢያ ውስጥ በፖለቲካ ሳቢያ የተያዙ  እስረኞችን እንደሚያሰቃዩ እና ለጎጂ አያያዝ እንደሚያጋለጡ ሂዩማን ራይትስ ዎች ዛሬ ይፋ ባደረገው ሪፖርት  አስታወቀ፡፡ ማዕከላዊ በመባል በሚታወቀው የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዘርፍ የሚፈጸሙ ህገ ወጥ ተግባራትን ለማስቆም እንዲሁም የሚፈጸሙትን በደሎች በተመለከተ የሚቀርቡ ቅሬታዎች በገለልተኛ ወገን እንዲመረመሩ እና አጥፊዎቹንም ተጠያቂ ለማድረግ የኢትዮጵያ መንግስት አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ አለበት፡፡

74 ገፆች ያሉት እና “ ‘የሚፈልጉት የእምነት ቃል ነው ማሰቃየት እና ጎጂ አያያዝ በኢትዮጵያ ማዕከላዊ ፖሊስ ጣቢያበሚል ርዕስ የወጣው ይኸው ሪፖርት  2002 . ጀምሮ በማዕከላዊ የተፈፀሙ ከባድ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች፣ በህገ ወጥ መንገድ የሚካሄድ ምርመራን እና በዚያ ያለውን አስከፊ የእስር  ሁኔታ ይዘረዝራል። በማዕከላዊ ከሚታሰሩት መካከል ተቃዋሚ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ የተቃውሞ ሰልፍ አስተባባሪዎች እና ጎሳን መሰረት ያደረገ ትግል የሚያካሂዱ አማፂያንን ይደግፋሉ የሚባሉ ሰዎች ይገኙበታል፡፡ ሂዩማን ራይትስ ዎች 35 የሚበልጡ የቀድሞ ታሳሪዎችን እና ቤተሰቦቻቸውን ያነጋገረ ሲሆን እነሱም የማዕከላዊ ሃላፊዎች መረጃ እና የእምነት ቃል ለማግኘት ሲሉ እንዴት መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውን እንደከለከሏቸው፣ እንዳሰቃዩአቸው፣ በተለያየ መልኩ ያልተገባ አያያዝ እንደፈጸሙባቸው እና የቤተሰብ አባላትን እና የሕግ ጠበቃ እንዳያገኙ እንደከለከሏቸው በዝርዝር ገልጸዋል፡፡

በሂዩማን ራይትስ ዎች የአፍሪካ ምክትል ዳይሬክተር ሌስሊ ሌፍኮመረጃ ለማግኘት ሲሉ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በዋና ከተማዋ እምብርት በየጊዜው ጥቃት ይፈፅማሉብለዋል፡፡ ሌፍኮ እንዳሉትድብደባ፣ ማሰቃየት እና በማስገደድ ቃል መቀበል ለጋዜጠኞች እና ተቃዋሚ ፖለቲከኞች የተገባ አይደለም።

ሂዩማን ራይትስ ዎች እንዳለው በኢትዮጵያ 1997 አወዛጋቢ ምርጫ በኋላ በሰላማዊ ተቃዎሞ ላይ የሚደረገው ጫና ተባብሷል። በማዕከላዊ  ተይዘው  ምርመራ የሚካሄድባቸው የመንግስት ተቃዋሚ ናቸው ተብለው የሚታሰቡ ሰዎች ጥብቅ በሆነው የሀገሪቱ የፀረ ሽብርተኝነት ሕግ መሠረት መከሰስን ጨምሮ የዘፈቀደ  እስር እና ፖለቲካን መሠረት ያደረገ ማሳደድ ይፈጸምባቸዋል።የማዕከላዊ ሃላፊዎች በዋናነትም መርማሪ ፖሊሶች እስረኞቹን በተለያየ መንገድ ያሰቃያሉ፤ ጎጂ አያያዝም ይፈጽማሉ፡፡ በተለይ በምርመራ ጊዜ ታሳሪዎቹ በጥፊ፣ በእርግጫ እንዲሁም በብትር እና በሰደፍ በተደጋጋሚ እንደተመቱ ለሂዩማን ራይትስ ዎች ገልጸዋል፡፡ እስረኞቹ ሰውነታቸውን ለህመም በሚዳርግ ሁኔታ እንዲሆኑና በተለይም እጆቻቸውን ከግድግዳ ጋር ታስረው እንዲንጠለጠሉ ተደርጎ ለረጅም ሰዓታት ያለማቋረጥ እንደሚደበደቡ ተናግረዋል። ከኦሮሚያ ክልል የመጣ አንድ ተማሪ  ብቻውን ተነጥሎና በሰንሰለት ታስሮ ለበርካታ ወራት እንዲቆይ እንደተደረገ ተናግሯል፡፡ለመቆም ስሞክር እቸገራለሁ፡ ለመቆም ጭንቅላቴን፣ እግሮቼን እና ግድግዳውን መጠቀም ነበረብኝ ፡፡ ምግብ ስመገብ እንኳ በሰንሰለት ታስሬ ነበር። ስመገብ እጆቼ  በፊት ለፊት በኩል እንዲታሰሩ ይደረጋል ስጨርስ ደግሞ መልሰው ወደ ኋላ ያስሩኛል።

በማዕከላዊ በሚገኙት አራቱ  ዋና የማሰሪያ ብሎኮች ያለው ሁኔታ አስከፊ ነው። ሆኖም በየብሎኩ ያለው ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ ይለያያል፡፡ጨለማ ቤትበመባል በሚታወቀው በጣም የከፋ ብሎክ የቀን ብርሃን እና የመፀዳጃ አገልግሎት ማግኘት በእጅጉ የተገደበ መሆኑን የቀድሞ ታሳሪዎች የገለጹ ሲሆን  ጣውላ ቤትበሚባለው ብሎክ የታሰሩት ደግሞ ወደ ደጃፍ ለመውጣት ያለውን ገደብ እና የክፍሎቹን በተባይ መወረር ገለጸዋል።  እስረኞቹ ለመርማሪዎቹ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በሚያደርጉት ትብብር መሰረት በቅጣት  ወይም በማበረታቻ መልኩ መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውንና ሌሎች  የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ሊከለከሉ ወይም ሊፈቀዱላቸው ይችላል፡፡ ይህም ታሳሪዎቹን ከአንዱ ብሎክ ወደ ሌላ ማዘዋወርን ይጨምራል፡፡ ከዓለማቀፉ ሆቴል ስያሜውን ወዳገኘው እናሸራተንበመባል ወደሚታወቀው ብሎክ መዛወር የተሻለ የመንቀሳቀስ እድል ስለሚያስገኝ ከመፈታት ቀጥሎ እስረኞች እጅግ የሚናፍቁት ነገር ነው።

በጨለማ ቤት እና በጣውላ ቤት የሚታሰሩ እስረኞች በተለይ በመጀመሪያዎቹ የእስር ወቅቶች የህግ ጠበቃ እና ዘመዶቻቸውን እንዲያገኙ አይፈቀድላቸውም፡፡  የታሰሩ ዘመዶቻቸውን ለመጠየቅ በየቀኑ ወደ ማዕከላዊ ቢሄዱም  ምርመራው እስኪያልቅ በሚል ለተራዘመ ጊዜ ከእስረኞቹ ጋር ለመገናኘት ሃላፊዎቹ እንደማይቅዱላቸው በርካታ የቤተሰብ አባላት ለሂዩማን ራይትስ ዎች ገልፀዋል፡፡ በምርመራ ወቅት የህግ ጠበቃ አለመኖሩ ታሳሪዎቹ ላይ የሚፈፀመውን በደል እንዲጨምር ያደርጋል፣ በመርማሪዎቹ የሚፈጸሙ ጎጂ አያያዞችና ማሰቃየትን የሚመለከቱ መረጃዎች እንዳይመዘገቡ ያደርጋል፤ እንዲሁም ፍርድ ቤት ይህ ያልተገባ አያያዝ እንዲሻሻል መፍትሔ ሊሰጥ የሚችልበትን እድል ይገድባል ሲል ሂዩማን ራይትስ ዎች ገልጿል።

እስረኞች ከጠበቆቻቸው እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዳይገናኙ ማድረግ በደል ሊፈጸም የሚችልበትን ዕድል ከመጨመሩም በላይ እስረኞች የመርማሪዎቹን ፍላጎት በሚያሟላ መልኩ ብቻ እንዲሄዱ ከፍተኛ ጫና ይፈጥርባቸዋልያሉት ሌፍኮበማዕከላዊ የሚገኙ እስረኞች በምርመራ ወቅት ጠበቆቻቸው እንዲገኙላቸው፣ከዘመዶቻቸው ጋር እንዲገናኙ እንዲሁም በፍጥነት ክስ ተመስርቶ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ መደረግ ይኖርበታልብለዋል።

መርማሪዎች ድብደባ፣ ማስፈራራትና  ሃይል በመጠቀም እስረኞች የሰጡት የእምነት ቃል ላይ እንዲፈርሙ እንደሚያደርጓቸው ሂዩማን ራይትስ ዎች መረዳት ችሏል፡፡ አንዳንድ ጊዜ የፈረሟቸውን ጽሁፎች እንደማስፈራሪያነት በመጠቀም ከተፈቱ በኋላ ከመንግስት ጋር እንዲሰሩ ጫና ለመፍጠር የሚያውሏቸው ሲሆን  በፍርድ ቤት ማስረጃ ሆነውም እንዲቀርቡ ይደረጋል፡፡

2004. በማዕከላዊ ታስሮ የነበረው ስዊድናዊ ጋዜጠኛ ማርቲን ሽብዬ ታሳሪዎች የእምነት ቃል እንዲሰጡ ለማድረግ ስለሚደረገው ጫና ሲናገርአብዛኞቹን ማዕከላዊ የሚገኙ ሰዎች ተስፋ ቆርጠው የእምነት ቃል እስኪሰጡ ድረስ ያቆዩአቸዋል። ቃለመጠይቅ ሳይደረግልህ ለሶስት ሳምንታት ልትቆይ ትችላለህ። የእምነት ቃል እስኪገኝ ድረስ ብቻ ነው የሚጠብቁት።ሁሉ ነገር የእምነት ቃል ማግኘት ላይ ብቻ የሚያጠነጥን ነው።ፖሊስ ጉዳዩ ፍርድ ቤት ሲቀርብ መላ ያገኛል ይላል ነገርግን ፍርድ ቤት ሲኬድ አንድም የሚገኝ ነገር የለምብሏል፡፡

ሂዩማን ራይትስ ዎች እንዳለው ታሳሪዎች ለተፈጸመባቸው ጎጂ አያያዝ መፍትሔ ሊያገኙ የሚችሉባቸው መንገዶች ውሱን ናቸው። በተለይ ፖለቲካ ነክ  በሆኑ ጉዳዮች ላይ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ገለልተኝነት አይንጸባረቅባቸውም፡፡ በጸረ-ሽብርተኝነት ህጉ  መሰረት የተያዙ ሰዎችን ጨምሮ እስረኞች ስለሚፈጸምባቸው ጥቃት በርካታ ቅሬታ ቢያቀርቡም ቅሬታዎቹ አንዲመረመሩ ወይም ቅሬታ ያቀረቡ እስረኞች  የበቀል  ጥቃት እንዳይፈጸምባቸው ክትትል እንዲደረግ ፍርድ ቤቶች የወሰዱት በቂ  እርምጃ የለም፡፡

ያልተገባ አያያዝን በተመለከተ ለሚቀርቡ ቅሬታዎች ፍርድ ቤቶች በንቃት ምላሽ መስጠት አለባቸው።  ይህም ሊሆን የሚችለው መንግስት በነፃነት እንዲሰሩ ሲፈቅድ እና የሚሰጧቸውን ውሳኔዎች ሲያከብር ብቻ ነው። ሲል ሂዩማን ራይትስ ዎች ገልጿል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ኢትዮጵያ በነፃ አካላት የሚደረግን የሰብአዊ መብቶች ምርመራ እና ሪፖርት የማድረግ ሥራ በእጅጉ ገድባለች። ይህም በማዕከላዊ ያለው የእስር  ሁኔታ ክትትል እንዳይደረግበት አድርጓል። መንግስታዊው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን 2002 . ጀምሮ ማዕከላዊን ሶስት ጊዜ የጎበኘ ሲሆን ከሰዎች ጋር ግንኙነት እንዳይኖራቸው ተነጥለው የሚታሰሩ ሰዎችን አስመልክቶ ያለውን ስጋት በይፋ አስታውቋል፡፡ ይሁንና የቀድሞ እስረኞች ለሂዩማን ራይትስ ዎች እንደገለጹት በጉብኝቱ ወቅት የማዕከላዊ ሃላፊዎች ከኮሚሽኑ ከመጡት ጎብኚዎች ጋር ስለነበሩ የኮሚሽኑን አባላት በግል ለማነጋገር ሳይችሉ ቀርተዋል። ጉብኝቱን ተከትሎ የመጣ ለውጥ ስለመኖሩም እርግጠኞች አይደሉም፡፡

ሂዩማን ራይትስ ዎች እንደሚለው በማዕከላዊ እና በሌሎች ማሰሪያ ቦታዎች የሚደረገው የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል እንዲሻሻል የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት አዋጅ እና የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ የተሰኙት ሁለት አፋኝ ህጎች መሻሻል አለባቸው፡፡ በሁለቱ ህጎች ምክንያት ገለልተኛ የሰብዓዊ መብቶች ክትትል ሥራ በእጅጉ ቀንሷል እንዲሁም ማሰቃየት እና ጎጂ አያያዝን ለመከላከል የሚያስችሉ መሠረታዊ የሕግ ጥበቃዎች ተሰርዘዋል።

የኢትዮጵያ ህገ መንግስት እና ሀገሪቱ የገባችባቸው ዓለማቀፍ ግዴታዎች ባለስልጣናት በእስረኞች ላይ ያልተገባ አያያዝ እንዳይፈጸም እንዲከላከሉ የሚያስገድዱ ሲሆን  በሁሉም ደረጃ የሚገኙ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በደል የመፈጸም አሰራሮችን የማስቆም እና ፈጻሚዎችም በሕግ እንዲጠየቁ የማድረግ ሃላፊነት  አለባቸው ብሏል ሂዩማን ራይትስ ዎች፡፡ መንግስት የነደፈው የሦስት ዓመታት የሰብአዊ መብቶች የድርጊት መርሀ ግብር የታሳሪዎች አያያዝ መሻሻል ያለበት መሆኑን የሚገልጽ ቢሆንም  መርሃ ግብሩ በአካል ላይ የሚፈጸም ጥቃትን እና ማሰቃየትን አይዳስስም። በስፋት የሚፈፀመውን በደል ለማስቆም መወሰድ ያለበትን ተጨባጭ ፖለቲካዊ እርምጃ ከመግለጽ ይልቅ የአቅም ግንባታ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል።


ተጨማሪ ገንዘብ እና የአቅም ግንባታ ስራ ብቻውን በማዕከላዊ እና በሌሎች የኢትዮጵያ ማሰሪያ ቦታዎች  በስፋት የሚፈጸመውን ያልተገባ አያያዝ አያስቆምምያሉት ሌፍኮእውነተኛ ለውጥ የሚመጣው በደሎቹን የሚፈጽሙት ሰዎች ላይ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት እርምጃ ሲወስዱ እና ጥፋተኞች ተጠያቂ እንዳይሆኑ የሚያደርገው የአሰራር ባሕል እንዲወገድ ሲያደርጉ ነው።ብለዋል።

Ethiopia: Political Detainees Tortured Police Abuse Journalists, Opponents to Extract Confessions

(Nairobi) – Ethiopian authorities have subjected political detainees to torture and other ill-treatment at the main detention centre in Addis Ababa. The Ethiopian government should take urgent steps to curb illegal practices in the Federal Police Crime Investigation Sector, known as Maekelawi, impartially investigate allegations of abuse, and hold those responsible to account.

The 70-page report, “‘They Want a Confession’: Torture and Ill-Treatment in Ethiopia’s Maekelawi Police Station, ”documents serious human rights abuses, unlawful interrogation tactics, and poor detention conditions in Maekelawi since 2010. Those detained in Maekelawi include scores of opposition politicians, journalists, protest organizers, and alleged supporters of ethnic insurgencies. Human Rights Watch interviewed more than 35 former Maekelawi detainees and their relatives who described how officials had denied their basic needs, tortured, and otherwise mistreated them to extract information and confessions, and refused
them access to legal counsel and their relatives.


“Ethiopian authorities right in the heart of the capital regularly use abuse to gather information,” said Leslie Lefkow, deputy Africa director. “Beatings, torture, and coerced confessions are no way to deal with journalists or the political opposition.”

Since the disputed elections of 2005, Ethiopia has intensified its clampdown on peaceful dissent. Arbitrary arrest and political prosecutions, including under the country’s restrictive anti-terrorism law, have frequently been used against perceived opponents of the government who have been detained and interrogated at Maekelawi.

Maekelawi officials, primarily police investigators, have used various methods of torture and ill-treatment against those in their custody. Former detainees described to Human Rights Watch being slapped, kicked, and beaten with various objects, including sticks and gun butts, primarily during interrogations. Detainees also described being held in painful stress positions for hours upon end, hung from the wall by their wrists, often while being beaten.

A student from Oromiya described being shackled for several months in solitary confinement: “When I wanted to stand up it was hard: I had to use my head, legs, and the walls to stand up. I was still chained when I was eating. They would chain my hands in front of me while I ate and then chain them behind me again afterward.”

Detention conditions in Maekelawi’s four primary detention blocks are poor but vary considerably. In the worst block, known as “Chalama Bet” (dark house in Amharic), former detainees said their access to daylight and to a toilet were severely restricted, and some were held in solitary confinement. Those in “Tawla Bet” (wooden house) complained of limited access to the courtyard outside their cells and flea infestations. Investigators use access to basic needs and facilities to punish or reward detainees for their compliance with their demands, including by transferring them between blocks. Short of release, many yearn to be transferred to the block known as “Sheraton,” named for the international hotel, where movement is freer.           

Detainees held in Chalama Bet and Tawla Bet were routinely denied access to their lawyers and relatives, particularly in the initial phase of detention. Several family members told Human Rights Watch that they had visited Maekelawi daily but that officials denied them access to their detained relative until the lengthy investigation phase was over. The absence of a lawyer during interrogations increases the likelihood of abuse, and limits the chances for documenting abuse and obtaining redress.


“Cutting detainees off from their lawyers and relatives not only heightens the risk of abuse but creates enormous pressure to comply with the investigators’ demands,” Lefkow said. “Those in custody in Maekelawi need lawyers at their interrogations and access to their relatives, and
should be promptly charged before a judge.”

Human Rights Watch found that investigators used coercive methods, including beatings and threats of violence, to compel detainees to sign statements and confessions. These statements have sometimes been used to exert pressure on people to work with the authorities after they are released, or used as evidence in court.

Martin Schibbye, a Swedish journalist held in Maekelawi in 2011, described the pressure used to extract confessions: “For most people in Maekelawi, they keep them until they give up and confess, you can spend three weeks with no interviews, it’s just waiting for a confession, it’s all built around confession. Police say it will be sorted in court, but nothing will be sorted out in court.”   

Detainees have limited channels for redress for ill-treatment.  Ethiopia’s courts lack independence, particularly in politically sensitive cases. Despite numerous allegations of abuse by defendants, including people held under the anti-terrorism law, the courts have taken inadequate steps to investigate these allegations or to protect defendants complaining of mistreatment from reprisals.

The courts should be more proactive in responding to complaints of mistreatment, but that can happen only if the government allows the courts to act independently and respects their decisions Human Rights Watch said.

Ethiopia has severely restricted independent human rights investigation and reporting in recent years, hampering monitoring of detention conditions in Maekelawi. The governmental Ethiopian Human Rights Commission has visited Maekelawi three times since 2010 and publicly raised concerns about incommunicado detention. However, former detainees told Human Rights Watch that Maekelawi officials were present during those visits, preventing them from talking with commission members privately, and questioned their impact.

Improved human rights monitoring in Maekelawi and other detention facilities requires revision of two repressive laws, the Charities and Societies Proclamation and the Anti-Terrorism Proclamation. These laws have significantly reduced independent human rights monitoring and removed basic legal safeguards against torture and ill-treatment in detention.

Ethiopia’s constitution and international legal commitments require officials to protect all detainees from mistreatment, and the Ethiopian authorities at all levels have a responsibility both to end abusive practices and to prosecute those responsible. While the Ethiopian government has developed a three-year human rights action plan that acknowledges the need to improve the treatment of detainees, the plan does not address physical abuse and torture; it focuses on capacity building rather than on the concrete political action needed to end the routine abuse.


“More funds and capacity building alone will not end the widespread mistreatment in Maekelawi and other Ethiopian detention centers,” Lefkow said. “Real change demands action from the highest levels of government against all those responsible to root out the underlying culture of impunity.”