Friday, December 13, 2013

ዛሬም አንደ ጥንቱ ባርነትና የሰው ንግድ

በሰዎች መካከል በጥቅም ላይ በሚደረግ ግጭት ጦርነት ከተደረገበት ጊዜ አንሥቶ ተሸናፊዎች በባርነት እንደተገዙ የታወቀ ሲሆን ሰውን እንደ ዕቃ የመሸጥ-መለወጥ ሥራ የተጀመረው በአረብ ነጋዴዎች ነበር። “Hugh Thomas” የሚባል መጽሐፍ ፀሐፊ “The Slave Trade and Robin Blackburn’s The Making of the New slavery“ በሚል ርዕስ በጻፈው መጽሐፍ ላይ እንዳስቀመጠው ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮ እሰከ 869 (ኢኤአ) አረቦች ሸቀጥ ይዘው ወደ አፍሪካ ሲወስዱ የአፍሪካ መሪዎች በገዛ ሕዝባቸው ሸቀጣቸውን ይለውጧቸው ነበር ብሏል። ከዚህ በታች
ከመጽሐፉ በቀጥታ የተጠቀሰውን ይመለከቷል፦

 “…it [slave trade] was pioneered by Arabs, its economic mechanism was invented by the Italian and Portuguese, it mostly run by Western Europeans, and it was conducted with the full cooperation of many African kings.” ¹

ጎርዶን ሙሬይ ስለባሪያ ንግድ ከሬጂናልድ ኮፕላንድ ሥራ ጋር በማገናዘብ ያጠናቀረውን ጥናት እንደሚከተለው ገልጾታል፦

Now the European Slave Trade did not begin till the 16th  century, it did not reach its full volume till the 18th, and in the course of the 18th, and in the course of the nineteenth it was suppressed. But the Arab Slave Trade, as has been seen, began before the Christian era, and did not stop till some fifty years ago; and though its output in any single year can never have reached the highest figures of the European trade, the total number of Africans it exported from first to last through all those centuries have been prodigious. (Reginald 137)

በአውሮፓ ኢንደስትሪ እያደገ ሲሄድ የሰው ጉልበት በማስፈለጉ የባሪያ ንግድ ተስፋፋ። በመፈንገልና በማስፈንገል አረቦች የባሪያ ገበያው ስለደራላቸው ከአፍሪካ ወደ አውሮፓና ወደ አዲሱ አሜሪካ፣ ብራዚልና ወደ ካረቢያን ደሴቶች ጭምር ንግዱ ስለተስፋፋላቸው ለነዚህ አገሮች ከአፍሪካ በዓመት እስከ 80,000 ሰው ያቀርቡ ነበር። ለአውሮፓና አሜሪካ እርሻና ሌሎች ኢንደስትሪዎች መሠረት በመሆን ከፍተኛ ኃይል ሆኖ ያገለገለው ከመላው ዓለም በተለይም ከአፍሪካ በባርነት ተሸጦ የተወሰደው ሰው ነው። 19ኛውና 20ኛው መቶ ክፍለ ዘመናት ፖርቱጋሎችና አውሮፓውያንን ተከትለው የአረብ ነጋዴዎች በመካከለኛው ምሥርቅ የባሪያ ንግድ ቱጃሮች ሆኑ። እስከ 1900 . ድረስ እስከ 18 ሚሊዮን የአፍሪካ ዜጎች ተፈንግለው እንደ ኢራቅ፣ ኩዌት፣ ኢራን ቱርክ በመሣሰሉት አረብ አገሮች እስከ ሕንድ ድረስ ለባርነት ተልከዋል።ወንዶቸ ባሪያዎች የአረቡን ዘር እንዳይበርዙ ተብሎ ይኮላሹ ነበር። በሳኡዲ አረቢያ 1930ዎቹ ዓመታት የባሪያዎች ቁጥር 700,000 1,960ዎቹ ዓመታት 450,000 የነበረ ሲሆን፤ ይህ ከአገሩ ሕዝብ ውስጥ 32% እና 20% ነበር። (Gordon 225-234)

የታሪክ ምሁራን ያደረጉትን ጥናታዊ መረጃዎች በመጠነኛ ዝርዝር ለመገንዘብ የሚከተሉትን የታሪክ ሰኖዶች በተጨማሪ ይመለከቷል፦

ክርስትያኔ በርድ በመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ተዘዋውራ ካደረገችው ጥናት በመነሣት በጻፈችው መጽሐፍ በመካከለኛው ዘመን አረቦች ስላቮችን እየፈነገሉ ይሸጡ አንደነበረና “slave” የሚባለው ቃል የተገኘውም ከነዚሁ ከእስላቮች ስም እንደሆነ ገልጻ፤ አረቦች አፍረካን በባርነት መግዛት መሸጥ የጀመሩት 1,000 ዓመታት ከምእራባውያን በፊት ሲሆን ምእራባውያን የባሪያ ንግድ ካቆሙ በኋላም ንግዱን እንደቀጠሉበት አስረድታለች። ... እስከ 2000 .. ድረስ የቀይ ባህርን ተሻግረው ወደ ኦማን ብቻ በዓመት 7,200 ባሮች ይሻገሩ እንደነበርና ባርነት ከእስልምና ሃይማኖት በፊት የነበረ ሲሆን ሃይማኖቱ በተለይ የወንድ እስላሞችን መሸጥ መለወጥ እንዲቀር የደነገገ ቢሆንም በተለይ የእምነቱ ተከታይ ባልሆኑት ላይ ሕጉ ትግባራዊ ያልሆነና፤ ያደረገው ነገር ቢኖር ጭካኔ የተሞላበት የባሪያ አያያዝ እንዲሻሻል ነው ብላለች። ሆኖም ወንዱም ቢሆን ጥፋት ከተገኘበት ግድያ እንደማይቀርለትና ለሙሉ ሰው የሚሠራ ሕግ ለባሪያ እንደማይሠራ ገልጻለች። (Christiane 27-31) ሮሞሎ . ፓሻ የሚባል አውሮፓዊ አገር አሣሸ 1,892 .. በጻፈው መጽሐፍ እንደገለጸው፣ አረቦች ጥቁሮችን ብቻ ሳይሆን ስላቮችንም ይሸጡ እንደነበረና በሰሜን አፍሪካ 20,000 በባሪያ ንግድ የተሠማሩ የአረብ ነጋዴዎች በዓመት 180,000 ሰዎችን ከአፍሪካ ወደ ግብፅ፣ ቱርክ፣ ኢራቅና ፋርስ ገዝተው ወይም ፈንግለው ይወስዱ ነበር። በአፍሪካ ቀንድ ለባሪያ ንግድ ኬላነት ሲያገለግሉ የቆዩት ባጋምዩ፣ ዛንዚባር እና ኪቱራ በታንዛኒያ፣ ሶፋልያ በሞዛምቢክ፣ አሰብ፣ ምፅዋ፣ ነፋሲት፣ ዘይላ፣ ታጁራ፣ ሞቃዲሾ፣ በረበራ፣ ኪስማዩ ሆብዮ (ሶማሊያ) ነበሩ። 1860ዎቹ ውስጥ በሱዳን በኩል ወደ አረብ አገሮች ይደረግ የነበረው የባሪያ ነግድ 14 ዓመታት ውስጥ ውስጥ ነጋዴዎቹን የባለሚሊዮን የአሜሪካን ደላር ቱጃር ሊያደርጋቸው እንደቻለ የሮሞሎ ጥናት (Romolo 2, 386)

ያመለክታል። ሬጂናልድ ኮፕላን የሚባል ሌላ የታሪክ ምርምር እንደሚያመለክተው የባሪያ ንግድ በአረቦች አንደተጀመረና በኦማን (አረቢያ) ቅኝ ግዛት ሥር በነበረችበት 200 ዓመታት ውስጥ ዛንዚባር በምሥራቅ አፍሪካ ዋና የባሪያ ንግድ መናኸሪያ ነበረች። ሁለት እጆቻቸው ከኋላ እየታሠረ አፋቸው ተለጉሞ፣ 200 የሚሆኑት ተፈንጋዮች እርስበርሳቸው ተሣሥረው እየተነዱ ተወስደው ምድር ቤት ውስጥ በተገነባና በአንድ ጊዜ ብዙ ሰዎችን በሚይዝ መጋዘን ውስጥ ወደውጭ በመርከብ እስከሚጫኑ ድረስ ታጉረው ይጠባበቁ ነበር። በዚህ ሂደት ውስጥ ብዙዎች ሲሞቱ የተረፉት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ቀይባህርን ተሻግረው በመሸጥ 60% እስከ 100% ድረስ ትርፍ ይገኝባቸው ነበር። (Couplan 138 146) በዓለም-አቀፍ ኢኮኖሚክስ ዋጋ ጥናት ፕሮፌሰርና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በፋይናንስ ሙያ የሠሩት እና ከሐረቫርድ በዶክትሬት ተመርቀው በመካከለኛው ምሥራቅ ከሠሩ በኋላ በለንደን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ፕሮፌሰር ከሆኑት ከልጃቸው አላን .. ፊሸር ጋር በጋራ በጻፉት መጽሐፍ ላይ እንደገለጹት ደግሞ 1,870 ዎቹ ዓመታት ናይጄሪያ ውስጥ በቦርኖ ክፍለ ሀገር በኩካ ገበያ ላይ የአንድ ሰው ዋጋ $4.00 እስ $80.00 እንደነበርና ዝቅተኛ ዋጋ ከሚያወጣ ሽማግሌ ከፍተኛ ዋጋ እስከሚያወጣው የተኮላሽ ወንድ ልጅ ያለውን የመገበያያ ዋጋ ዘርዝረው በሰንጠረዥ አስቀምጠዋል (197) ከምሥራቅ አፍሪካ 1,839 . . ብቻ 30,000 ሰዎች ወደመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች እንደተሸጡ፤ ሳይሞቱ ከደረሱ 300% እስከ 500% ትርፍ ይገኝባቸው እንደነበረ (74) ባሮች ከማርያ ትሬዛ ቀጥሎ ለውጭ ምንዛሪ መለዋወጫነት (currency) ያገለግሉ አንደነበረም ትሪፖሊ ከሚገኘው የእንግሊዝ ካውንስል ጋር የጉዞ መረጃዎችን ጭምር በማገናዘብና ከመካከለኛው አፍሪካ አህጉር ምሥራቅ አፍሪካን አቋርጦ እስከመካከለኛው ምሥራቅ ድርስ የሚያሳየውን በካርታ የተደገፈ የባሪያ ንግድ መነሻና መድረሻ አስረድተዋል (Allan 73, 74, 188,197) ጎርዶን ሙሬይ በጻፈው መጽሐፍ ላይ እንደገለጸው በአረቦች ዘንድ ለባርነት ሁለት ዋና ምክንያቶች እንዳሉት፤ ይኸውም አንዱ በጂሐድ ምርኮኛ መሆንና በእስልምና አለማመን ናቸው ብሎ፤ ሐበሻ የሚለውን ስያሜ ለኢትዮጵያውያን የሰጡት አረቦች ሲሆኑ 19ኛው መቶ ክፍለዘመን ሁለተኛው አጋማሽ ሐበሻ ልጃገረዶች በሜካ ገበያ ላይ ከፍተኛ ትርፍ ያስገኙ እንደነበረ እና በምሥራቅ አፍሪካ በሚደረግ የንግድ ትርኢት ላይ እንደሸቀጥ ተኮልኩለው ይታዩ እንደነበረም ገልጿል። አላን ፊሸር በመጽሐፉ ሲገልጽ ባሮች ከአራዊት ጋር ፍልሚያ በማድረግ ሕይወታቸውን በማጣት ጭምር ትርኢት በማሳየት የአረብ ሀብታሞችን ያዝናኑ ነበር። በአንዳንድ አገሮች ደግሞ በአምልኮታቸው ወቅት ለመስዋዕት ይገደሉ እንደነበር ገልጿል (19) ጊዜ የሴቶች ባሮች ለግብረሥጋ ግንኙነትና ለቁባትነት መመረጥን እንደትልቅ ዕድል ይቆጥሩት ነበር (126)

አውሮፓውያን አፍርካን በቅኝ ለመያዝ ሃይማኖትን እና ሥልጣኔ የማምጣትን ምክንያት እንደተጠቀሙ ሁሉ፣ የአረብ ባሪያ ነጋዴዎችና የመንግሥት መሪዎቻቸው ቁራን ባሪያ ማሳደርን ይፈቅዳል በማለት ሕጋዊ ቅርጽ (legitimacy) ለመስጠት ሞክረዋል። ቁራን ሙካታባ በሚባል ስምምነት አንድ ባሪያ የራሱን ዋጋ ገዝቶ ነፃ መውጣት እንደሚችል ቢገልፅም በትክክል ተግባራዊ የተደረገበት የአረብ አገር አልነበረም፤ አባቱ ዳኛ ልጁ መልከኛ እንደሚባለው ሕጉም የአስገዳጅነት ኃይል አልነበረውም። በተለይ የሺያ ፈለግ በሚከተሉት ውስጥ ነፃ መውጣት የሚችሉት የእስልምና ተከታይ ባሮች መሆናቸው ቢገለፅም ተፅዕኖው በተለይ በሴቶች ላይ ከፍቶ ቆይቷል

የባሪያ ንግድ ሕጋዊ በነበረበት በዚያ አስከፊ ዘመን ፍንገላ ሲደረግ የባላገር መንደሮች ስለሚወረሩ የቤት እንሰሳት ጭምር እተየዘረፉ ቤት ንብረታቸውም ይቃጠል ስለነበር፤ ሰላም ስለሌለ ልማት የሚባል ነገር ስለሚቆም ሕይወት እንደነበረች አትቀጥልም። በአጋጣሚ የሚተርፉት የመኖር ዋስትና ስለሚያጡ ሌላ ምርጫ በማጣት እጃቸውን ለፈንጋዮች በመስጠት በገዛ ፈቃዳቸው ባሪያ ለመሆን ይገደዱ እንደነበር የክርስትያኔ ጥናት ያመለክታል(144) ይህን ነገር አሁን እየተደረገ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ስናስተያየው ከ30 ዓመት በላይ (አንድ ትውልድ) ንብረት አፍርተው ከኅብረተሰቡ ጋር ተጋብተውና በማኅበራዊ ኑሮ ተስማምተው ከሚኖሩበት አካባቢ ከሌላ ዘር ናችሁ በሚል ብቻ ቤትንብረታቸውን ተወርሰው ያለምንም መድረሻ በግፍ ከደቡብ የአገራችን ክፍል እንዲፈናቀሉ የተደረጉ፤ በሰሜን የአገራችን ክፍል ቤት ንብረታቸው ተቃጥሎና መኖሪያቸውን ጥለው እንዲሰደዱ የተገደዱ ዜጎቻችን እጣ ፈንታ ቀድሞ ለባርነት ከተዳረጉት ሕዝቦች እንዳልተለየ ይመለከቷል። በተለይ ከአፍሪካ የተገዙ ባሮች ንዳድ በሚኖርባቸውና ለኑሮ አስቸጋረ በሆኑት የተምር፣ የጥጥና ስኳር እርሻ ቦታዎች፣ በባስራ ባነዳር፣ አባስ፣ ምናብ፣ ሂጃዝ አንዲሁም በባህሬን በሐር እርሻ ላይ እንደሚሠሩ ታውቋል። (ሙሬይ 19፤24፤49)

እንዲሁም “Arabs and Slave Trade” በሚል ርእስ Shirley Madany የተሰኙ ፀሐፊ ባወጡት ጽሑፍ ያስቀመጡትን እንደሚከተለው ያነቧል፦

Arabia was another major centre for the slave trade. The flow of slaves from Africa into Arabia and through the Gulf into Iran continued for a long time. The extension of British, France, and Italian control around the Horn of Africa deprived the slave traders of their main ports of embarkation …The way in which slavery was practiced in Islamic countries had both bright and dark sides. What is regrettable now is that this practice among Muslims is seldom openly discussed – as if slavery was exclusively a Western phenomenon. This deliberate silence enables Islamic propagandists in America to represent Muslims as liberators of the people of African origin, contrary to historical fact [2]
.
. . . በሚዚያ 1998 Le Monde diplomatique ላይ ኤሊክያ ምቦኮሎ ባወጣው ጽሑፍ በየተኛውም ኬላ እንደ አፍሪካ ክፍለ አህጉር የሰው ልጅ የተፈነገለበት አልነበረም ብሏል። ይኸውም በሳሃራ፣ ቀይ ባህር፣ ሕንድ ውቅያኖስንና አትላንቲክ ውቅያኖስን በመሻገር ንግዱ የደራ ነበር። በምሥራቅ አፍሪካ የቀይ ባህርና ሕንድ ዳርቻ የአረብ ባርያ ፈንጋዮች ምፅዋንና ደህላክን ጭምር በመጠቀም ከኢትዮጵያ ሲነግዱ እንደነበር Periplus of the Erythraean  Sea የሚባል በግሪክ የሚታተም የባህር ጉዞና ንግድ መመሪያ /travel guide/ በተደጋጋሚ ዘግቦ ተገኝቷል። በተለይ 19ኛው መቶ ክፍለዘመን ለፖርቹጋልና ፈረንሳይ ጋር በባሪያ ንግድ የአረቦች ተሳትፎ ከፍተኛ ነበር።

ግራኝ ሞሐመድ 1520 እስከ 1535 .. በቱርኮች ተረድቶ የእስላም መንግሥት በኢትዮጵያ ሊመሠርት ሲሞክር በጦርነቱ ወቅት በብዙ የሚቆጠሩ ዜጎች ወደ አረቢያ ተግዘዋል። . . 1453 ኮንስታንቲኖፕልን በመያዝ አውሮፓን በተቆጣጠሩበት ዘመናት ኦቶማኖች ነጮችን በብዛት በባርነት ሸጠዋል፤ ለውጠዋል። የኦቶማን ቱርክ ግብጽን ይዞ ሲገዛ በተለይም 1,821 ..ጀምሮ በሞሐመድ አሊ ፓሻ እየተመራ ሱዳንን በቅኝ በያዘ ጊዜ ብዙ የሱዳንና የኑብያ ዜጎች ለባርነት ቀይባህርን ተሻግረው ተሸጠዋል።

ዶክተር ዓለማየሁ ገብረማርያም የተባሉት ምሁር “Masters of African Slavery since Antiquity” በሚል መስተአምር/article/ ያጠናቀሩት ጽሑፍ በባርነት ወደ አሜሪካ የገቡት የተለያዩ ዜጎች ከአውሮፓ ከመጡት ዜጎች ቁጥር ጋር ሲነፃፀር የባሪያዎቹ አምስት ጊዜ እንደሚበልጥ ዘግበዋል [3] ይኸው ጽሑፍ ቀደም ሲል በአረቦች ሲፈጸም የነበረው የባሪያ ንግድ አሁን ከሚፈጸመው ፍለሳ ጋር የታሪክ ተመሣሣይነት እንዳለው ያረጋግጣል።

ከብዙ መቶ ዓመታት በኋላ ታሪክ በያዝነው ዘመን ውስጥ በአዲስ መልክ ቀጥሎ ማየት ይቻላል። በቅርብ ጊዜ በየመን በተፈጠረው የመንግሥት አለመረጋጋት የተነሣ 12,000 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መካከል ልዩ ልዩ ጥቃት ደረሶባቸዋል፣ በግብረሥጋ ተደፈረዋል፣ ይህን አስከፊ ሁኔታ ለማምለጥ ጥቂቶቹ ወዳልታወቀ ቦታ ጠፍተዋል፤ የሞቱም ይገኙበታል። እንዲሁም ከሦስት ወራት በፊት 700 የሚሆኑ ጥገኝነትን የጠየቁ ኢትዮጵየውያን በሮርዌይ መንግሥት ጥያቄያቸው ተቀባይነት በማጣቱ በግዳጅ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ከነ አቶ መለስ ዜናዊ አስተዳደር ጋር ሲደራደሩ የነበረ ሲሆን ከእነዚህ አብዛኛዎቹ በፖሊቲካ ምክንያት ከአገራቸው የወጡና 15 ዓመታት በላይ በኖርዌይ የኖሩ ሲሆን፤ ሕጋዊ የይለፍ ወይም የመኖሪያ ፈቃድ ስለሌላቸው ተገደው ከመመለስ ወደ ሌላ አገር ጠፍተው ሰብአዊ ክብራቸውንና መብታቸውን አዋርደው ሊኖሩ እንደሚችሉ እና የዘመኑ ፈንጋዮች ሰለባ ለመሆን የሚገደዱ ብዙዎች እንደሚሆኑ መገመት ይቻላል[i] [4]

በአረብ አገሮች የቤት ሠራተኞች ከባሪያ ያልተሻለ አያያዝ እንዳላቸው የሚያመለክቱ ሁለት ምሳሌዎችን ማየት ይቻላል፦ የሊቢያው ሞአመር ጋዳፊ ከሥልጣን ከመውረዳቸው ጥቂት ቀናት በፊት ለእንጀራ ልጃቸው ተቀጥራ ታገለግል የነበረች ተስፋ እንጂ ደሞዝ የሚባል ነገር የማተውቅ አንድ ኢትዮጵያዊት ኢሰብአዊ የሆነ ትእዛዝ ለመቀበል ስላመነታች እጅ እገሯ ታሥሮ የፈላ ውሀ በመላ አከላቷ ላይ እንዲፈስ በማድረግ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባት ታውቋል። እንዲሁም ዓለም ደቻሳ የምትባል ሌላ ኢትዮጵያዊት የቤት አገልጋይ አቤቱታ የማቅረብም ሆነ የመንቀሳቀስ ዕድል ተነፍጓት፣ በቤሩት የኢትዮጵያ ቆንስል ጽሕፈት ቤት ፊት-ለፊት መንገድ ላይ እየተጎተተችና እየተደበደበች ተገፍታ እንደ ዕቃ መኪና ውስጥ ስትጫን በአደባባይ የታየ ሲሆን ከሁለት ቀን በኋላ ተሰቅላ ሞታለች።

በአንድ አገር ውስጥ የሚደረግ የእርስበርሰ ጦርነት ለዜጎቹ ሰብአዊ መብት የማይቆረቀር መንግሥት በሌለበት አገር የባሪያ ፍንገላ ሕጋዊ ወይም ሕገወጥ በሆነ መንገድ ሲፈጸም ቆይቷል። “Internal Displacements in Ethiopia” በሚል ርዕሰ Chemin de Balexert የሚባል ”Norwegian Refugee Council/Global IDP Project” [5] የሚሠራ ባለሙያ በጻፈው ላይ እንዳመለከተው 2,003 እስከ 2005 . . ድረስ ከግማሽ ሚሊዮን ሕዝብ በላይ በአገራችን ውስጥ ተፈናቅለዋል። ይህ መፈናቀል የቀጠለ ሲሆን በተለይም ኢሕአዴግ በሚያራምደው በዘር የተከፋፈለ አመራር ባስከተለው መዘዝ ብዙ ዜጎች በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት፣ በኦጋዴን፣ ባሌ፣ ወለጋ፣ ሸዋ፣ ጅማ፣ ጋምቤላ፣ ወዘተ በተፈጠረባቸው የእርስ በርስ ግጭት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕዝቦች ተፈናቅለዋል። በአንድ በኩል እንደኮሚኒስቶች መሬትን ተቆጣጥሮ ገበሬውን የመንግሥት ጭሰኛ ሆኖ አልምቶ እንዳያድግ በማድረግ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ዝንታለም የኖሩበትንና የእርሻ መሬታቸውን ነጥቆ በልማት ካባ ለአረቦችና ሌሎች የውጭ ነጋዴዎች ሸጧል። አያቶቻቸው በደማቸው ያቆዩትን የኢትዮጵያ ግዛትና መሬታቸውን ለፖሊቲካ መሣሪያነት ከጎንደር ቆርሶ ለሱዳን፣ ከትግራይና አፋር ቆርሶ ለኤርትራ የተሰጠባቸው ኢትዮጵያውያን፣ እንዲሁም በየጊዜው በእምነታቸው ምክንያት ጠብ የተለኮሰባቸውና ሲያመልኩበት የኖሩበት ቤተክርስትያን እየተቃጠለ የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በሚሊዮኖች የሚቆጠር ነው። ለእልፍ አዕላፍ ዘመናት የቆየውን የአገሪቷን ታሪክ በመካድ 100 ዓመት ወዲህ በተፈጸመ ወረራ የተገኘ በማሰመሰል የገዛ አገሩን ልዕልና የሚያቃልል የአገር መሪ ሊባል አይችልም። እስላሙን ከክርስትያኑ ሆን ብሎ በማጋጨት ሕዝቡን የመንግሥት ያለህ እንዲል አድርጎታል። እነዚህ የመፈናቀል ክስተቶች ዜጎችን ቀቢፀ ተስፋ ያደርጓቸዋል፤ ከተስፋ ማጣት የተነሣ ለኅልውና ሲሉ ሰብአዊ ክብራቸውን አዋርደው መብታቸውን ተነጥቀው ከአገር ተሰደው ለመሄድ ይገደዳሉ። ሕገወጥ በሆነ ጉዞ በዕቃ መጫኛ የብረት ሣጥን (container) በኮንተሮባንድ ጀልባ ተጭነው ከቀይባህር ማዶ ለምሳሌ ወደየመን ለመግባት ሁለት ኪሎሜትር ያህል ዋኝተው በሞትና ሕይወት መካከል የሞቱት ሞተው፣ በዕድል የተረፉት የሚጠብቃቸው እሥር፣ በሽታና ረሀብ ነው። ወደ የመን ብቻ በዓመት እስከ 45,000 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ይገባሉ። “Yemen Times” በሚባለው ሳምንታዊ የየመን ጋዜጣ ላይ ... ግንቦት 7 ቀን 2012 እንደተመለከተው 2001 . 65,000 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ የመን የገቡ ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ /ቤትን ጠቅሶ እንዳመለከተው 37,333 በሕገወጥ መንገድ የገቡ ሲሆን 616 ሚሆኑት የሞቱ ወይም ምን እንደደረሰባቸው ያልታወቀ መሆኑን ገልጿል። ይህን ሁሉ አበሳ ካዩ በኋላ ምርጫ ስለሌላቸው ከባርነት ባላነሰ መልኩ ሰብአዊ ክብራቸውን ቀንሰው ባይተዋር በሆኑባቸው አገሮች ከሰው በታች ሆነው ያገኙትን ሥራ ተብዬ ሠርተው ይኖራሉ፤ የሚገርመው አንደዚህ ከሚጉላሉት ስደተኞች መካከል ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መገደዳቸው ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት በየወሩ በብዙ የሚቆጠሩ ሴት ሠራተኞችን ለሳዑዲ አረቢያ ለመስጠት ከሳዑዲዎች ጋር ስምምነት ያደረገ ሲሆን በየወሩ 13000 ሴት ሠራተኞች ብቻ ወደሳዑዲ አረቢያ በሕጋው መንገድ እንደሚገቡና ከዚህ በተጨማሪ ያለፈቃድ የሚገቡት ቁጥር በብዙ ሺዎች እንደሚቆጠር ብሉምበርግ የሚባል የዜና አገልግሎት በያዝነው ዓመት ጥር ወር ላይ ዘግቧል። ድህነትን ለመሸሽ ወደ ኢጣሊያ ሲጓዙ ከነበሩ 470 የአድሪቃ ቀንድ ስደተኞች መካከል ሲሲሊ ደሴት ለመድረስ ትንሽ ሲቀራቸው የተሳፈሩበት ጀልባ ተገልብጦ ሲሰጥም 155 ብቻ መትረፋቸውን አልጀዚራ አሜሪካ ጥቅምት 4- 2013 ዓም ዘግቧል። ባለፈው ሰኔ ወርም 43 ኢትዮጵያውያንና የሶማሌ ዜጎች በተመሣሣይ ሁኔት ድህነትን ለመሸሽ ባደረጉት ሙከራ በዕቃ ማጓጓዣ የብረት ሣጥን ውስት እንዳሉ ታፍነው ሞተዋል።

በሕገወጥ መንገድ ከአገር ወጥተው ምናልባትም የፖሊቲካ ነገር ተጨምሮበት የሚጠብቃቸው ሌላ አበሳ መሆኑን ስለሚያውቁ በማይታወቁበት አገር ሁኔታው አስገድዷቸው ባርነት ውስጥ ይወድቃሉ። መታወቅ ያለበት አንድ ዜጋ እትብቱ የተቀበረበትንና ባህሉ፣ ወጉና በአጠቃላይ ማንነቱ ታውቆና ተከብሮ ከሚኖርበት አገር ቤተሰቦቹንና ወገኖቹን ጥሎ ለመሰደድ የሚገደደው ቢቸገረው እንጂ በቅንጦት አለመሆኑን ነው።

በሌላ በኩል ከሳዑዲ አረቢያ ሕዝብ መካክል 23% የሚሆኑት የውጭ ዜጎች ሲሆኑ፣ ከሠራተኛው ቁጥር ውስጥ ደግሞ 66% የሚሆነው ላቡን አንጠፍጥፎ በምንዳ የሳዑዲዎችን አኮኖሚ የሚገነባው የውጭ ዜጋ ነው።

ባርነት በዓለምአቀፍ ሕግ እንዲቀር ከተደረገ በኋላ ዛሬም 21ኛው መቶ ክፍለዘመንበ ዘመናዊ መልኩ ቀጥሏል። ዛሬ የውጭ ጠላት ሳይመጣብን ፍትሕ በመጓደሉና ድህነትን ለመሸሽ ከአገር የተሰደዱ ዜጎቻችን ቢመለሱ የሚጠብቃቸውን ስለሚያውቁ ከመሞት መሰንበት በሚል ሰብአዊ ክብራቸውን ቀንስው በባርት መኖርን በነዚያው የአረብ አገሮች ኮንትራት ፈርመው በዘመናዊ ባርነት በኢሰብአዊ አያያዝ ስለመከፈሉም ዋስትና በሌለው ምንዳ እያገለገሉ ይገኛሉ። የጉዞ ወኪል በሚል ሽፋን ላልታወቁ ሰዎችና ባልታወቁ አድራሻዎች ለምሳሌ ኢትየጵያውያን ሴት ልጆች ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ይተላለፋሉ፤ ከአገር ሲወጡ የሚፈርሙት ኮንትራት መብታቸውን ሙሉ በሙሉ የሚከለክላቸው ሲሆን፤ በአንፃሩ ተቀባዩ ሰው ባለሙሉ መብት ስለሚሆን ከቤት ወጥተው እንዳይጠፉ የብዙ ወራት ደሞዛቸው ይያዝባቸዋል። የይለፍ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት በተቀባቀዮቻቸው እጅ ሰለሚያዝና እንደልብ የመዘዋወር ነፃነት ስሌላቸው ፈርመው የገቡላቸውን አሳዳሪዎቻቸውን ፈቃድ ከመፈጸም ሌላ አማረራጭ የላቸውም። ታዲያ ባርነት ቦቃ አለው? ሴቶች ዜጎቻችን በነዚሁ የድሮ ጌቶች አገር በቤት ሠራተኛነት ስም እየተቀጠሩ በተመሣሣይ ሁኔታ አካላቸውን የሚያስደፍሩበት ሕይወት ላይ መገኘታቸው ብቻ ሳይሆን ይህንኑ ጉድ እመቤቶቻቸው ካወቁ እጅእግራቸው ታሥሮ ከሕንፃ የሚወረወሩና ወደባህር የሚጣሉት ሲታይ ባርነት ቅርጹን ቀየረ እንጂ በይዘቱ እንዳልተለወጠ መገንዘብ ይቻላል። በኅዳር 2006 ዓም እንደተከታተልነው የዘመናዊ ባርነት መገለጫ ከሆነው ውል ጋር በተያያዘ ሁኔታ 50,000 የሚበልጡ በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኛ ሠራተኞች መብታቸው እንዲከበርላቸው በሰላማዊ ሠልፍ ጥያቄ ሲያቀርቡ በሳዑዲ አረቢያ ያጋጠማቸው እንደ አውሬ ቤት ለቤት እየተዳኑ መደብደብ፣ መዘረፍ፣ በገሃድ መደፈርና እስከግድያ የደረሰ ወንጀል መንግሥት ባሠማራቸው ፖሊሶች ጭምር መፈጸሙ የአደባባይ ወሬ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግሥት ዝምታ ለሰብአዊ መብት ጥሰቱ ተባባሪ ከሚያደርገው በስተቀር ምን ሊባል ይችላል?

እንግዲህ እንዳየነው 3,000 ዓመታት ገናና ታሪክ በኋላም በአገራችን ባርነት አለ፤ አንድ ድርጅት የሁሉም የበላይ ጌታ ፈላጭ ቆራጭ ነው፤ የሕዝቡን ሃይማኖቱንና የግል ሕይወቱን ጭምር መቆጣጠር ይዟል፤ የተለወጠው ቅርጹ ነው እንጂ ይዘቱ አይደለም። ጥቂቶችን ለማበልጸግ የሰው ልጅ ተወልዶ እትብቱ ከተቀበረበት አያት ቅድመ አያቶቹ በደማቸው ካቆዩበት አገርና ቀበሌ ቤት ንብረቱን ጥሎ ለስደት ከተዳረገ፣ ሰብአዊ ክብሩን ቀንሶ የጎዳና ተዳዳሪ ከሆነ፣ ከመሞት ለመሰንበት የሚያሳድረውን ጌታ የሚፈልግ ከሆነ፣ ዘመናዊ ባርነት አንጂ ነፃነት አይባልም። ባርነት ሰብአዊ ጭቆና ነው፤ ሰብአዊ ጭቆናም ባርነት ነው።

ነፃነት በስጦታ ወይም በቸርነት ስለማይገኝ ባርነትን ለማስቀረት የባሪያ ቤተሰብ የሆነው ሕዝብ በጋራ ለነፃነት መነሣት አለበት። ገዥውን ማስወገድ ባሮችን ነፃ እንደሚያወጣ ይታመናል፤ ባርነትን ጨርሶ ለማጥፋት ግን የባህል ለውጥ ማድረግ ያስፈልጋል፤ ምክንያቱም ገዥው ተገዥ፣ ተገዥው በተራ ገዥ የሚሆንበት ራዕይ ወይም መንፈስ ካልጠፋ ባርነት እንደገና ቅርጹን ለውጦ ሊመላለስ ይችላል፤ መራሹ ኢሕአዴግ እንደ ባእዴንና ኦሕዴድ ያሉትን አሻንጉሊቶች አስከትሎ ሲመጣፍትሕ፣ ዲሞክራሲ፣ ሰላምየሚሉ የሚያማልሉ ተስፋዎችን ይዞ ነበር የገባው፤ በጠመንጃ፣ ኃይል ሕዝባዊ መፈክሮችን ለብሶ መጣ አንጂ ሕዝባዊ ውክልና አልነበረውም። ገዥው መንግሥት ሥልጣን ላይ ከመውጣቱ በፊት እኩልነትንና ፍትሕን በመከተል አንዲየውም በሶሽያሊስት ርዕዮተ ዓለም የጋራ ሀብት የሚበለጽግበትን መርህ በመፈክር ይዞ ቆይቶ ሥልጣን ላይ ከወጣ በኋላ እንደመንግሥትም እንደሞኖፖልም ሆኖ የአገሪቱን ሀብት ለጥቂት ቡድኖች የግል መጠቀሚያ እያደረገ ነው። ዲሞክራሲን ፍትሕ የጠማውን ሕዝባችንን በስሙ ተጠቀመበት እንጂ አንጀቱን አላራሰውም። ከሃያ ሁለት ዓመታት በኋላም ለሆዳቸው ያደሩ አጫፋሪዎቻቸውም የኋላ ኋላ ጌቶቻቸው ሲጥሏቸው ከሕዝብ ፍርድ ባያመልጡም ለዚያው ገዥ ቡድን ታማኝ ሆነው እያጀቡ ነው እንጂ የሕዝቡን ልዕልና አላስከበሩም። እንዲሁም በአገራችን እንደ አሸን የፈሉት ድርጅቶች መሪዎች እያንዳንዳቸው የመንገሥ ራዕይ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ከሆነ በዚህ ሂደት የሚገኘው ለውጥ አንዱን ጌታ በሌላ ጌታ ወይም ብዙ ጌቶች የመቀየር ህልም፣ ድህነትንና ዘመናዊ ባርነትን አንጂ ነፃነትን አያስገኝም። የሚያስፈልገው በመራሽነት ጠመንጃን ተማምኖ ወደሥልጣን መሮጥ ወይም ሥልጥንን የሙጥኝ ብሎ በሕዝባዊ መፈክር የቡድን ዓላማን ማራመድ ሳይሆን ሕዝቦች ተባብረው ልዕልናቸውን በጋራ እንዲያስከብሩ የማስተባበር አገልግሎት በመስጠት ፈቃዳቸውን መፈጸም ነው። ሆኖም ለሕዝብ አንታገላለን በማለት የሥልጣንና ጥቅም ራዕይ ይዘው የሚንቀሳቀሱ መሪዎችም ለሆዳቸው የተገዙ ባሮች ስለሚሆኑ የሩቅ ግብ ስለሌላቸው ለአገራችን ኋላቀርነት መፍትሔ ሳይሆን ችግር የሚጨምሩ ናቸው። ግለኝነትን ያላስወገደ መሪ ለሕዝብ ልዕልና ሊቆም አይችልም።

እኤአ 1950 እስከ 1970 ባሉት 20 ዓመታት ኢትዮጵያ አግኝታ የነበረው የውጭ አገር እርዳታ $600 ሚሊዮን ነበር፤ በደርግ ዘመን ከግብረሰናይ ድርጅቶች ከተቀበለችው እንደ እህል፣ መድሐኒት፣ ወዘተ በስተቀር የውጭ እርዳታ ቆሞ ነበር። የሰላም፣ ዲሞክራሲ፣ እኩልነት፣ ፍትሕና ነፃነት ዓላማ ይዣለሁ በሚለው የኢሕአደግ መንግሥት ዘመናት ደግሞ በእርዳታ ብቻ ከውጭ በያመቱ በአማካይ $3.5 ቢሊዎን እየተገኘ የሥራ-አጡ ሕዝብ ቁጥር እየጨመረ መሄድና ሕዝባችን በድህነት ምክንያት ለዘመናዊ ባርነት መዳረግ የማይጣጣሙ ነገሮች ናቸው። የአገሪቷ የነፍስ ወከፍ ምርታማነት (GDP) ማደጉንና እኤአ 2012 ዓም $1,200 የነፍስወከፍ የመግዛት አቅም $1,167 እንደሆነ የተዘገበ መሆኑን አይ ኤም ኤፍም አረጋግጧል (Ethiopia Economy Profile 2103) ሆኖም ዘገባው የባለፀጎችን ገቢ ለደሀውም በማካፈል የሚገኝ ቁጥር ስለሆነ አሳሳች ነው።ትክክለኛው የነፍስ ወከፍ ገቢ በግልዕ አልተቀመጠም። ምክንያቱም የበለፅጉት ጥቂቶች ስለሆኑና የብዙሐኑ ቁጥር ለሥሌት የሚገባ እንጂ የጥቅሙን ተቋዳሽ ስለማያሳይ ነው። የአገሪቷን ጥቅም ተቋዳሾች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እስከሆኑ ድረስ 90 ሚሊዮን ሕዝብ የራሱ ባልሆነ ገቢ በስሌት ብቻ ምን ይጠቀማል?

ስለሆነም ዲሞክራሲንና ፍትሕን ለማግኘት በንድፈ-ሐሳብ ወይም ሥራ ላይ በማይተረጎም መፈክር ሳይሆን በትክክለኛ የሕዝብ ውክልና አገራችን ነፃ እስካልወጣች ድረስ እውነተኛ ነፃነት፣ እኩልነት ወይም ፍትሕ አይኖረንም። በየዋህነትም ቢሆን ከኛ በላይ ለሕዝብ አዋቂ የለም የሚሉ መሪዎች ጭልጥ ካሉ አምባገነኖች ስለማይለዩ አፉን ለጉመው የሥልጣን ኮርቻ ላይ ተቆናጠው እኛ እናውቅልሃለን በማለት ሕዝባዊ ከበሮ እየደለቁ ሕዝብን እንደፈረስ ከነዱ ወይም ከጎትቱ አመራራቸው በቅርጹም ሆነ በውጤቱ ጭቆና ሰለሚሆን በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባለች ሦስተኛ ዓለም ሀገር የብዙኃኑ መረገጥ የከፋ ውጤት ያመጣል። የጥንት ባሪያ አሳዳሪዎች ሰውን መሸጥ መለወጥ የቻሉት ሕዝቦችን ነጣጥለው በመውረር ነው። ዛሬም ያልተባበረ ሕዝብ እጩ ባሪያ ከሚሆን በስተቀር ነፃነት ሊኖረው አይችልም። የጥቂት አምባገነኖች ቡድን እንደ ተራ ወንበዴ ያገራችንን ቅሪት ሙልጭ አደርጎ በመበዝበዝ ሕዝቦቻችንን ነጣጥሎ ግዞተኛ ሲያደርገው ጭቆናውን ተቀብሎ እየተረገጠ መኖር የሕዝባችን ምርጫ ሊሆን አይችልም። ሆኖም ይዋል ይደር እንጂ ፍትሕ የጠማው ሕዝብ ሲወስን ከፍርዱ ማምለጥ ስለማይቻል በትግል ውስጥ ያሉ መሪዎች የራሳቸውን ግላዊ ህልም ትተውና ለሕዝብ ፈቃድ ተገዥ በመሆን በወቅቱ ሕዝብን ለማገልገል አቋማቸውን ማስተካከል ይጠበቅባቸዋል።

በማጠቃለል ዛሬ ዓለም ቤተሰብ እየሆነች በሄደችበት ዘመን በግላዊ ራዕይ እንደዝንጀሮ ተነጣጥሎ መሮጥ ለዘመኑ ትናንሽና ትላልቅ ተኩላዎች ከመመቸት በስተቀር ሌላ የረባ ፋይዳ አያመጣም። እውነተኛ ግላዊ እርካታ የሚገኘው የአገር ጉዳይ አስተማማኝ መፍትሔ ሲያገኝ ብቻ ነው። ምክንያቱም ዛሬ እየተከሠተ ያለው ብዙሐኑን ደሀ የሚያደርግ አቅጣጫ በወቅቱ መፍተሔ ካላገኘ የሚቀጥለው ትውልድ የሚጠብቀው የበለጠ ስደትና ባርነት ብቻ ነውና። አገር ደግሞ በተለያየ ቋንቋ፣ ሃይማኖት፣ ባህላዊና ማኅበራዊ አኗኗር የሚገለፅ የሕዝቦች ውህደት ሲሆን በየትኛውም አካባቢ የሚታይ መሠረታዊ ሰብአዊ ችግር እየተስፋፋ ብዙ ወገኖችን መጉዳቱ ስለማይቀር ሁሉም እስከሚጎዳ መጠበቅ የሚመረጥ አይደለም። ስለሆነም ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከፖሊቲከኞች ብቻ ተአምርን መጠበቅ የለበትም። አሁንም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ድርጅቶች በአንድ በኩል እንወክለዋለን የሚሉትን ሕዝብ በሚገባ ሳያቅፉ በሌላ በኩል ደግሞ ተባብረው በጋራ አለመሥራታቸው የሚያያመለክተው ለሥልጣን የሚደረግ ግላዊ ሩጫን ወይም አምባገነንነትን ስለሆነ ለሕዝቡ መሠረታዊ ችግር መፍትሔ የሚያመጣ አቅጣጫን አይደለም። ዛሬ በአብዛኛው የፖሊቲካ ድርጅቶች የሚታወቁት ካላቸው ሕዝባዊ ፕሮግራም ይልቅ በታዋቂ መሪዎቻቸው ነው፤ ከነዚህ መሪዎችም አብዛኛዎቹ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የተወሰኑ የሕዝብ ወገኖችን ብቻ እንወክላለን የሚሉ ናቸው። ሆኖም ዛሬ በትግል ወቅት የተለያየ ፍላጎት ያላቸውን የሕዝቦቻችንን ቤተሰቦች ለጋራ ዓላማ በማስተባበር ተሞክሮ አርዓያነትነት ያላሳዩ መሪዎች እንዴትስ ፌዴራላዊ አመራር ይከተላሉ ተብሎ ሊታመኑ ይችላሉ?

የስሞች መቀያየር ነፃነትን አያመጣም፤ ስለሆነም ተስፋ ማድረግ የሚገባው ከጠንካራ መሪዎች ይልቅ በጠንካራ ሕዝባዊ ድርጅት ላይ ነው። ምንጊዜም ሕዝባዊ መሠረት የሌለውና ሕዝቡ የማይቆጣጠረው ድርጅት ለአምባገነኖች ክፍተት ስለአለው ሕዝቡ በስሙ የተቋቋሙ ድርጅቶችን ሊቆጣጠር ይገባል። ስለሆነም ምንም በማያለያያው የአገሩ ጉዳይ ሃይማኖት፣ ጎሣ፣ ቋንቋ፣ ወዘተ ሳይወስነው ከሌሎች ወንድሞች - እህቶቹ ጋር በመወያየት የጋራ መፍትሔ መፈለግ አለበት።እውነተኛ የሕዝብ መሪዎች ለይስሙላ የዲሞክራሲ ካባ የሚለብሱ ሳይሆን ለሕዝቦች ፈቃድ ተገዥ ሆነው፤ ቋንቋን ለመለያያ ሳይሆን ለመግባቢያነት ብቻ በመጠቀም፤ ብሔርተኝነትንና ጎጠኝነትን አስቀርተው፤ ከሁሉ ሕዝቦችና የሕዝብ ወገኖች ጋር በጋራ በመቆም ሕዝቦችን ማገለገል ይጠበቅባቸዋል። ምሁራን ፋና ወጊ የሚሆኑበት፤ አገር ወዳዱ ሁሉ ከባርነት ለመውጣት እጅ ለጅ ተያይዞ ከእግዜር የተሰጠውን ሰብአዊ ክብር በኃይሉ ለመመለስ “United We Stand, Divided We Fall” ወይምድር ቢያብር አንበሳን ያሥርእንደሚባለው ለጋራ ነፃነት፣ እኩልነት፣ ሰብአዊ፣ዲሞክራሲያዊና ፍትሐዊ ግብ ሕዝቦች በጋራ እንዲሰለፉ የሕዝባዊ ድርጅት መሪዎች ሚና በሕዝብ ፈቃድ በመመራት ሕዝብን ማስተባብር ነው፤ ሕዝብ ደግሞ በጋራ ሲቆም በተለያየ ቅርጽ የሚገለጽን ባርነት እስከነአካቴው አጥፍቶ ልዕልናውን ሊያሰፍን ይችላል።

(ተፈራ ድንበሩ)


References
[1] http:..www.Scaruffi.com/Politics/slavetra.html.
[2] www.answering-Islam.org/ReachOut/slavetrade.html
[3] http://www.ethiomedia.com/broad/3656.html
[4] http://www.mmo.gr/pdf/news/Migration_in_the_Middle_East_and_Mediterranean.pdf
[i] http://www.nytimes.com/2013/10/04/world/europe/scores-die-in-shipwreck-off-sicily.html?_r=0
[5] http://reliefweb.int/node/77505

Works Cited

  • Al-Maamiry, Ahmed Hamoud. Oman and East Africa. New Delhi: Lancers Publishers, 1980.
  • Arab Slave Trade: “African Holocaust society. http://www.arabslavetrade.com.
  • Bird, Christiane. The Sultan’s Shadow: One Family’s Rule at the Crossroads of East
  • and West. New York: Random House, 2010.
  • Coupland, Reginald. The Exploitation of East Africa 1856-1890 the Slave Trade and the Scramble. London: Faber and Faber Limited, 1939
  • Davis, Robert C. Christian Slaves, Muslim Masters: White Slavery in the Mediterranean, the Barbary Coast, and Italy, 1500-1800 (Palgrave Macmillan, London 2003) ISBN 978-1-4039-4551
  • Dugard, Martin. Into Africa: The Epic Adventures of Stanley & Livingstone. New York: Broadway Books, 2003.
  • Ethiopian Refugees in Norway: Stop Helping the Dictatore Meles Zenwai. http://www.ethiopianreview.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=37660
  • Fisher, Allan G. B., Humphrey J. Fisher. Slavery and Muslim Society in Africa. New York: Doubleday & Company, INC., 1971.  
  • Gordon, Murray. Slavery in the Arab World. New York: New Amsterdam Books, 1989.
  • Huntingford, G. W. B. The Galla of Ethiopia: The Kingdom of Kafa and Janjero. Ethnographic Survey of Africa part II. Ed. Daryll Forde. London: International African Institute, 1955.
  • Huntingford, G. W. B. The Galla of Ethiopia: The Kingdom of Kafa and Janjero. Ethnographic Survey of Africa part II. Ed. Daryll Forde. London: International African Institute, 1955.
  • Lewis S. Herbert. A Galla Monarchy: Jimma Abba Jifar, Ethiopia 1830-1932.
  • Madison and Milwaukee: The University of Wisconsin Press, 1965.
  • Manning, Patrick. Slavery and African Life: Occidental, Oriental, and African Slave Trades. Cambridge 1990.
  • Masters of African Slavery since Antiquity. http://www.ethiomedia.com/broad/3656.html
  • Pankhurst, Richard. The Ethiopian Borderlands: Essays in Regional History from Ancient Times to the End of the 18th Century, Asmara: Red Sea Press Inc., 1997.
  • Pankhurst, Richard. The Ethiopian Borderlands: Essays in Regional History from Ancient Times to the End of the 18th Century, Asmara: Red Sea Press Inc., 1997.
  • Pasha, Romolo, G. Seven Years in the Sudan: Exploitations, Adventures, and Campaigns against the Arab Slave Hunters. Ed. Fellin Gessi. London: Samson Low, Marston & Company Limited, 1892.
  • Segal, Ronald. Islam’s Black Slaves: The Other Black Diaspora. New York: Farrar, Straus and Giroux, 2001.
Yemen Turns into hell for Ethiopians. http://www.ethiopianreview.com/con

Tuesday, December 10, 2013

Welcome to Ethiopia, let me have your bag.

I hope you are sitting down while reading the story I am about to tell you. Unfortunately it is a true story and it couldn’t have happened anywhere but in good old Ethiopia. When it comes to laying down like a doormat and letting everyone walk all over us we Ethiopians wrote the manual. We cannot repeat this story to any outsider because they would look at us in a strange way and walk away not understanding this kind of convoluted humor. In fact most of us will deny it happened. Some of us would have to come up with some kind of explanation to make the story go down smooth to avoid getting choked with our shame.


As you all know the Saudis mostly but all the Middle Eastern Arabs have not been kind to us for quite a while. Three weeks ago the Saudis decided to tighten the collective noose around our neck by a notch. It was not pleasant. I mean due to the Internet and ubiquity of mobile technology the whole world witnessed their barbarity. For those that got killed, raped, beaten and humiliated may the creator have mercy on their soul.

It even angered the so called Diaspora or economic and political refugee from their motherland. The abuse of Ethiopians in the Middle East is common knowledge. The news of some little girl hanging herself, taking household detergent as poison, being driven out of her mind has become an everyday news. Normally we read the news then we shrug, swallow hard make that hissing sound and move on. This time it was different. Instead of trickled down abuse they decided to do it wholesale style to us. Hunt them down and throw them in the desert was what the King declared. The security force and vigilantes were more than happy to comply.

Now the Ethiopian government was true to its nature of being the fire starter and the fire fighter at the same time. This game has been refined by the late nameless warlord that all the new guys have to do was go on auto pilot and let us do all the heavy lifting. Thus they activated their cadres to take us on a rampage and get the world to notice the crime. We complied beautifully. I am not saying we should not have protested but the heart of the matter lies protest against who and why and to what end. Woyane answered those questions for us.

If you look closely at all the rallying cry since the problem started you will notice all our ire was directed at ‘Saudis, Arabs, Muslims’ and other phantom enemies. The Ethiopian government unable to take care of its people willingly exports them to the Middle East, turn its face away when they are abused, closes Conciliates to deny them shelter and we curse the ‘Arabs’ for not being humane to the those with no place to go. One thing our cry did was help Woyane spin a new version of the sad story.

This is where Woyane excels- snatching victory out of defeat. Sure enough the Foreign Minister that seems to be void of diplomatic language using such memorable words such as ‘depressed, bugged etc.’ to explain tragic events that happened to his people was the lead sent out to calm us down. A blind leading the blind is what comes to mind.

However you sneer at it, it worked. Before you know it the international conscience we were able to wake up and take notice was what Woyane was anticipating. All of a sudden the urgency of the situation was magnified by Woyane. The numbers kept climbing from one day to another. The Foreign Minister on training set up what he called ‘command center’ to collect money in an orderly manner. The Saudi Government paid for the trip, the Red Cross facilitated the camp, the UN refugee organization poured money into the bucket and good old Woyane opened their pockets.

This is where I am going to tell you more of what happened. I ask you again if you are sitting down. You see the Saudis started flying around the clock bringing the Habesha home. So you would think people will be lined up to welcome the traumatized, abused and weak from being kept in a desert tent back to their mother land. One would hope it would be a joys day where families embrace their loved ones and thank their Gods for their safe return.

I am afraid none of that happened. The government did not want the people to be involved in this happy moment. Furthermore our dear old government came up with a brilliant scheme to make money of already beaten people. New regulations went into effect. Only two bags, two mobile phones, no electronic items and gold has to be weighed before entering the country. All excess amounts will be confiscated.

Thus the Saudis kicked our people from their country, they killed some, raped a few but in the end allowed them to gather their belongings and transported them home. The Ethiopian government waited with open hands and robbed them of their last shred of dignity as a welcome gesture.

I am glad some of our people were rescued from this hell on earth. I am happy we their brethren did not ignore their plight. No matter what a few tried to use this sad situation to line their pockets, show loyalty to their handlers, secretly betray their people and country most of us with good heart did what we have to do. What I am saying here is that it is not enough. A band aid solution is not the way to go. What we have done is postpone the problem for another day.

Our halfhearted gesture ultimately ends up hurting us. We are present at the start of the problem but we do not wait around to solve it. We raise the issue and someone else comes around and sticks a useless defanged solution that we have to go back and try to solve again. Let us see when the Emirates, or Lebanon or Kuwait gets tired of our people and starts the deportations are we going to go out and scream again? What would those that see us with our banner again think of us? Let alone foreigners even some of us are getting tired of this crap. Let us pay attention to what Henry David Thoreau said ‘There are a thousand hacking at the branches of evil to one who is striking at the root.’ Strike at the root, hit Woyane!


By Yilma Bekele

Thursday, December 5, 2013

ፈይሳ ጃታ… ብሄራዊ ውርደትን ያልተቀበለ ጀግና!!

ሰሞኑን ስለብሄራዊ ውርደት ብዙ ይባላል። ብዙ ስለሚባለው ነገር መልሼ ከማውራት ይልቅ፤ አንድ ሰው ላስተዋውቃቹሁ። ፈይሳ ጃታ ይባላሉ። ሀረር ውስጥ ለብዙ አመታት የኖሩ ናቸው። ጣልያን የጫነብንን ብሄራዊ ውርደት ያልተቀበሉ፤ የሱማሌ ወረራን ተከትሎ የመጣውን ሽንፈት፤ “እምቢኝ” ያሉ ጀግና ነበሩ።

የሀረሩን ፈይሳ ጃታ ያለ ምክንያት አላነሳሁዋቸውም።ብሄራዊ ውርደትብለን በምንጠራቸው ዘመኖች፤ እንደሳቸው አይነት ያለተዘመረላቸውና ምንም ያልተባለላቸው ሰዎች መኖራቸውን ለማስታወስ፤ ከዚያም አልፎ ሁሌ ብሄራዊ ውርደትን ያሸነፉ፤ ጀግኖች መኖራቸውን ማውሳት አስፈላጊ ስለሆነ ነው።

ለነገሩ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በበርካታ የታሪክ ምዕራፎች ብሄራዊ ውርደትን አስተናግደናል። አንደኛውና ሁላችንም የምናውቀው በጣልያን ወረራ ወቅት፤ በራሳችን ባንዳዎች የተፈጸመብን ውርደት ነው። ሁለተኛውን ውርደት ተከናነብነው በቀይና በነጭ ሸብር ዘመን ወንድም ወንድሙን ገድሎ ወንድም በየጎራው ተሰልፎ የፎከረበት ወቅት ሲሆን፤ ሶስተኛው ብሄራዊ ውርደት ደግሞ፤ አሁን በአገራችን ያለው ስርአት ያከናነበን የቅሌት ቡሉኮ ነው። በመግቢያዬ ላይ እንደገለጽኩት ስለያንዳንዱ ዘመን ብሄራዊ ውርደት ለመተንተን አይደለም - የዛሬ መነሻዬ። ይልቁንም በእንደዚህ አይነት የውርደት ዘመናት አንገታቸውን ቀና አድርገው፤ ሰንደቅ አላማችንን ከፍ ስላደረጉ አንድ ግለሰብ ጥቂት ለማለት ፈልጌ ነው።

እንደገና ላስተዋውቃቹህ። ፈይሳ ጃታ ይባላሉ። ፊታቸው ሁሌም ሙሉ ጺም ያለው፣ ቀጭን፣ ቁመታም፣ ሁሌ ቁምጣ የሚያደርጉ ቆፍጣና ሰው ናቸው። በጣልያን ዘመን ገና ወጣት ልጅ ነበሩ። የተወለዱት ሰላሌ አውራጃ ሲሆን፤ ኩሩ ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ ናቸው። በወቅቱ የአርበኝነት ዘመን የአካባቢው ወጣቶች ይሰለፉበት በነበረው የጃጋማ ኬሎ ጦር ስር ሆነው ለአገራቸው ክብር ከቆሙት መካከል አንዱ ነበሩ።

በዚህ የአርበኝነት ዘመን እሳቸው የነበሩበት ጦር፤ ጣልያንን ለመምታት እና ግዳጁን ለመወጣት ወደ ሰላሌ ያመራል። እዚያ ሲደርሱ ግን፤ የሰላሌ አካባቢ ዋና ሃላፊ ወይም ባንዳ ሆነው ለጣልያን አገልግሎት ይሰጡ የነበሩት የእናታቸው ወንድም፤ አጎታቸው መሆኑን ይሰማሉ። ቀጥሎም ወደ ከተማ ገብተው ይህንኑ በአይናቸው አይተው ያረጋግጣሉ። የአካባቢው ኦሮሞዎች ከጣልያን ጦር ባልተናነሰ፤ የፈይሳ አጎት ይፈጽሙባቸው የነበረው በደል ከባድ መሆኑን ተመለከቱ። በሁኔታው አዝነው፤ ከአጎታቸው ጋር ጦርነት ላለመግጠም ብለው፤ እንዳዘኑ ያቺን መንደር ለቀው ወጡና በሌላ መስመር
በአርበኝነት አገለገሉ።

ጣልያን ድል ከተመታ በኋላ አርበኞች ወደ አገራቸው ሲመለሱ፤ አጎታቸው የባንዳነት ቡሽ ኮፍያቸውን አውልቀው፤ ጃንሆይ የሰጧቸውን አዲስ የስልጣን ካባ ደርበውአሁንም ከድል በኋላ ህዝቡን ሲያተራምሱት ተመለከቱ። በጣልያን ጊዜ የነበረው ብሄራዊ ውርደት ሳያንስ፤ ከድል በኋላም ተጨማሪ ውርደትን ለመሸከም ትከሻቸው አልቻለም፤ ከህሊናቸው ጋር ሙግት ገጠሙ። በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያሉ አንድ ቀን፤ አጎታቸው እንደተለመደው በቅሎ ላይ ሆነው ገበያተኛውን ሲያምሱት፤ የሚታሰረውን ሲያስሩና ሲያሳስሩ አይተው አዘኑ። በዚህን ጊዜሁለት ጊዜ አንዋረድም! ሞትም አንዴ ነው!” ብለው፤ የራሳቸውን አጎት በጥይት መትተው ገደሏቸው።

ከዚህ በኋላ ፈይሳ ጃታ ሰላሌን ለመጨረሻ ጊዜ ለቀው ወጡ። የሰላሌው የታሪክ ምዕራፍ ተዘጋና ሌላኛው የታሪካቸው ምዕራፍ ሀረር እና ጅጅጋ ላይ ተጀመረ። በኋላ ላይ ብሄራዊ እርቀ ሰላም ለማውረድ ሲባል መንግስት የምህረት አዋጅ አወጀ። “ነፍስ ያጠፋህ በሙሉ፤ እጅህን ሰጥተህ ታርቀህ በሰላም ኑር።” ተባለ። ፈይሳ ጃታም አዋጁን ተከትለው፤ ምህረት ተደርጎላቸው እንደማንኛውም ሰው ከጅጅጋ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት በሚገኘው ፋፈም ላይ መሬት ተመርተው መኖር ጀመሩ።

ከጊዜ በኋላ ግን… ፈይሳ ጃታ የተመሩበት መሬትት ውስጥ ለውስጥ የፋፈም ወንዝ ይሄድበት ኖሮ፤ ሚስጥሩ ሲታወቅ የወቅቱ ባለስልጣናት ይዞታው ላይ አይናቸውን ጣሉ። ከነዚያ ባለስልጣናት መካከል አሁን ስማቸውን መጥቀስ የማልፈልጋቸው፤ ፖሊስን ማዘዝ የሚችሉ ጄነራል ነበሩ። ጄነራሉ ፈይሳ ጃታ መሬቱን እንዲለቁ ቢያስጠይቋቸው “አሻፈረኝ” አሉ። ሽማግሌዎች ቢላኩም፤ “ሬሳዬን ተሻግሮ ይውሰድ” ብለው መለሷቸው። በኋላ ላይ እንዲያዙ ፖሊስ
ተላከ።

ፈይሳ ጃታም፤ “በህግ አምላክ፤ ይዞታዬ ውስጥ አትግቡ!” ብለው አስጠነቀቁ። ፖሊሶቹ ግን የሚሰሙ አልሆነም። በመጨረሻ ሁለቱን ፖሊሶች ገደሉ። ፈይሳ ጃታ ፖሊሶቹን ገድለው፤ ለተወሰነ ግዜ ከፖሊስ ጋር ድብብቆሽ ይጫወቱ ጀመር። የአጋጣሚ ነገር ሆነና፤ በ1953 ዓ.ም. ጄነራሉ በጃንሆይ ላይ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ በማድረግ ጥፋት ተወንጅለው ተገደሉ። ከጄነራሉ ሞት በኋላ… ለፈይሳ ጃታ ለሁለተኛ ጊዜ ምህረት ተደረገላቸው።

በዚህ መሃል ያለውን ታሪክ እንለፈውና ወደ ሱማሊያ ወረራ ዘመን ልውሰዳቹህ። በየካቲት ወር 1969 ዓ.ም. የሱማሊያ ወረራ ወቅት፤ ሱማሌዎች ጎዴ፣ ቀላፎ፣ ቀብሪዳሃር፣ ደገሃቡር፣ ዋርዴር የሚባሉት ከተሞችን ያዙ። ሃምሌ ላይ ደግሞ ጅጅጋን ለመያዝ ትልቅ ጦርነት ተከፈተ። በወቅቱ ፈይሳ ጃታ እድሜያቸው ወደ እርጅናው ተጠግቶ ነበር። እንደዚያም ሆኖ ህዝቡን ለማስተባበር ጉልበታቸው አልደከመም፤ አንደበታቸው አልታሰረም።

ሃምሌ 8 ቀን፣ “ከሱማሌ ጋር ተባብራችኋል” የተባሉ ሰዎች ተገደሉና በጅጅጋ ትልቅ ፍጅት ሆነ። በሳምንቱ የሱማሌ ጦር እየገፋ ሲመጣ፤ ህዝቡ ተስፋውን በኢትዮጵያ የጦር ሰራዊት ላይ ጥሎ ነበር። ሆኖም የጅጅጋ ከተማ ከመያዟ አንድ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ከየወረዳው አፈግፍጎ የመጣው የጦር ሰራዊት አባላት፤ ለሊቱን ቤተሰባቸውን ይዘው አካባቢውን ለቀው፤ ጉዟቸውን በመኪና እና በእግር ወደ ሃረር አደረጉ። በንጋታው ጠዋት የጅጅጋ ህዝብ ከእንቅልፉ ሲነሳ፤ ከተማው ዙሪያውን በሱማሌ ታንክ ተከቦ ተመለከተ። በየጋራው ላይ በርካታ የሱማሌ ታንክ አፈ ሙዙን ወደ ከተማው አድርጎ ቆሟል። የጅጅጋ ህዝብ በሁኔታው ተደናገረ። ለሊቱን ሲከናወን ስለነበረው ሁኔታ ብዙም የሚያውቀው ነገር አልነበረም። የኢትዮጵያ ጦር አካባቢውን ለቅቆ ስለመሄዱም የሚያውቁት ነገር አልነበረም። ከነዋሪው በቀር ጅጅጋ ባዶዋን ናት። ማንም የሚጠብቃት ሰው አልነበረም።

የሱማሌ ታንከኛ ጦርም በኢትዮጵያ አየር ኃይል እንዳይመታ በመስጋት በቀን ወደ ከተማው ለመግባት አልደፈረም። ከአምላኳ በቀር ሌላ ጠባቂ ያልተረፈላት የጅጅጋ ከተማ እስከ ምሽት ድረስ፤ አጭር እድሜ አላት። የመንግስት ባለስልጣና እና ወታደሩ አካባቢውን ለቅቆ ወጥቷል።

ጀንበር ስትጠልቅ፤ የሱማሌ ጦር ወደ ጅጅጋ ገብቶ የነበረው እንዳልነበረ ይሆናል። በዚህ የመጨረሻ የጭንቅ ሰዓት አንዳንድ ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ ጦር ሰፈር ገብተው የቻሉትን ያህል መሳሪያ ወስደው ራሳቸውን ለመከላከል ታጠቁ። የኢትዮጵያ ጦር የሚለብሰውን የወታደር ልብስ ለብሰው፤ ጠመንጃቸውን አንግተው… በታንክ የመጣውን የሱማሌ ጦር ለመዋጋት ተዘጋጁ። ፈይሳ ጃታ በዚህ ሁኔታ የጅጅጋን ህዝብ የሚያስተባብሩ ብቻ ሳይሆን፤ ለዚያን ቀን ከመንግስት ያልተሾሙ፤ የጅጅጋ ህዝብ መሪ ሆኑ።


ፈይሳ ጃታ… በዚያች ቀውጢ ወቅት መሪነታቸውን አስመሰከሩ። በኢትዮጵያውያን ዘንድ ከሰው ባልተናነሰ መልክ፤ ሰንደቅ አላማ ትልቅ ክብር ስለሚሰጠው “ሰንደቅ አላማ በጠላት እጅ መውደቅ የለበትም።” በማለት፤ በቅድሚያ በጅጅጋ አስረኛው ሜካናይዝድ ብርጌድ ግቢ ውስጥ የተሰቀለውን የኢትዮጵያ ባንዲራ አወረዱ። ለአገራቸው ክብር የኢትዮጵያ ወታደር ልብስ የለበሱት ፈይሳ ጃታ ይህችን ሰንደቅ አላማ ይዘው፤ ህዝቡን እያረጋጉ፣ ወጣቱን እያስተባበሩ ወደ ሃረር ጉዞ ጀመሩ። ሆኖም የሃረር መንገድ ተዘግቷል። ከሃረር አንድ መቶ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ… ከመቶ ሺህ ህዝብ በላይ ከካራማራ ተራራ ጀርባ፤ ሀደው ከተማ ላይ ሰፍሯል።

ከሃደው ከተማ የተነሳው ህዝብ ቀስ በቀስ ወደ ሃረር መሄድ ቢጀምርም፤ የሚደረገው ጉዞ አስቸጋሪ ነበር። በየጋራው ላይ የመሸገውን የሱማሌ ጦር እየተዋጉ መሄድ ግድ ይላል። ፈይሳ ጃታ እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ጦር መትረየሳቸውንደግነው፤ እየተኮሱና እየተዋጉ ጉዞ ወደ ሀረር ሆነ። ከጅጅጋ ወደ ሃረር የነበረው ጉዞ ከ25 ቀናት በላይ ፈጀ። የኢትዮጵያ አየር ኃይል በሰማይ ሲያንዣብብ፤ የሱማሌ ጦር የሚገባበት ስለሚጠፋው… በዚያች አጋጣሚ ህዝቡ ከየመሸገበት እየወጣ ወደ ሃረር የሚያደርገውን ጉዞ በፍጥነት ይቀጥል ነበር።

የሃረር ህዝብ እንዳይደነግጥ ስለተሰጋ፤ ከጅጅጋ እና ከኦጋዴን ከተሞች የፈለሰው ህዝብ ወደከተማው እንዲገባ የተደረገው ለሊት ላይ ነበር። የሃረር ህዝብ ግን ቀደም ብሎ መስማቱ አልቀረም። ፈይሳ ጃታ ሃረር ወደሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ሲሄዱ፤ ልጆቻቸው የደርግ ተቃዋሚ ተብለው ቀበሌ እንዳሰራቸው ይሰማሉ። በሱማሌ ወረራ ጅጅጋ ላይ የተመለከቱት ውርደት ሳያንስ፤ ሃረር ውስጥ ልጆቻቸው መታሰራቸውን ሲሰሙ በቀጥታ ወደ ቀበሌ ሄደው አብዮት ጠባቂውና ሊቀመንበሩ ላይ አነጣጥረው፤ “ሱማሌ 45 ኪሎ ሜትር ላይ ቁጭ ብሏል። እናንተ መንደር ለለመንደር ትበጠብጣላቹህ። ፍቷቸው!” ብለው ሲጮሁ ሚስታቸው፤ “አረ ይተዉ። የታሰሩት የርስዎ ብቻ አይደሉም፤ የሁሉም ልጆች ናቸው እኮ” ቢሏቸው… “አሁን የአገር ጉዳይ ነው። አገር እየተገደለች እና እየተዋረደች ልጆቻችን እንደገና በእስር አይንገላቱም። ፍቷቸው!” በማለት ሁሉም ታሳሪ እንዲፈቱ አደረጉ። (በወቅቱ ከታሰሩት ልጆቻቸው መካከል አንዳንዶቹ አውሮፓ ውስጥ ናቸው)

ፈይሳ ጃታ በዚህ አይነት ሃረር ላይ ከቆዩ በኋላ፤ አንድ ቀን ሌላ ችግር ገጠማቸው። የወታደር ልብስ፣ ጫማ ወይም መለዮ መልበስ በአዋጅ ተከልክሏል። ሆኖም ፈይሳ ጃታ አላግባብ የወታደሩን ልብስ በመልበሳቸው ታሰሩ።፡ ታስረም የሃረር ክፍለ አገር አስተዳዳሪ ከነበረው ኮሎኔል ዘለቀ በየነ ዘንድ ቀረቡ። እዚያም ቀርበው፤ የወታደሩን ልብስ
መልበሳቸው ትክክል እንዳልሆነ እና ወንጀል የፈጸሙ መሆኑ ተነገራቸው።

ፈይሳ ጃታም የባለስልጣናቱን ውንጀላ ከሰሙ በኋላ፤ “ይህን የወታደር ልብስ እኔ ብቻ አይደለም የለበስኩት። ይህንን መለዮ እና ልብስ ትታችሁ የሸሻችሁት እናንተ ናቹህ፤ ይህን ልብስ በየቦታው በመተዋቹህ የሱማሌ ጦር ጭምር ለብሶታል። እኔ እናንተ ትታችሁ የሄዳችሁትን ልብስ በመልበሴ እወነጀል ይሆናል። እናንተ ደግሞ ልብስ እና መሳሪያዎችን ትታችሁ ሱማሌ እንዲወስደው በማድረጋቹህ፤ አንድ ቀን ትጠየቃላቹህ።” አሏቸው።

በዚህ ጉዳይ አንድ ሁለት እያሉ ሲከራከሩ፤ ፈይሳ ጃታ በመጨረሻ የሰንደቅ አላማውንም ጉዳይ ነገሯቸው። “እናንተ የልብሱ ጉዳይ ለምን ይገርማችኋል? ከ10ኛ ሜካናይዝድ ብርጌድ ግቢ የተዋችሁትን ሰንደቅ አላማ ጭምር፤ በስርአት አውርጄ ይዤው መትቻለሁ።” አሏቸው። ይህ አባባል ሁሉንም ዝም አሰኘ። ማንም መልስ ለመስጠት አልሞከረም። ኮሎኔል ዘለቀ በየነም፤ የፈይሳ ጃታን ጀግንነት አድንቀው እንዲፈቱ ትዕዛዝ ከመስጠት ውጪ ምንም አላሉም።

ጊዜው በግርግር እና በጦርነት እሳት ተወጥሯል። የኢትዮጵያ ጦር ተጠናክሮ እንደገና ማጥቃት ጀመረ። ከአስር ወራት በኋላ፤ የሱማሌ ጦር ከአካባቢው ሙሉ ለሙሉ ተደምስሶ ጅጅጋ እንደገና በኢትዮጵያ አስተዳደር ስር ወደቀች። ሀረር ላይ ሰፍሮ የነበረው ህዝብ እንደገና ወደ ጅጅጋ ከተማ ተመለሰ። እነሆ የድል ምስራች ከዳር እስከ ዳር አስተጋባ።

ፈይሳ ጃታ እና ተከታዮቻቸው ወደ ጅጅጋ ከተማ ሲመለሱ፤ ህዝቡ እንዳጀባቸው በቀጥታ ያመሩት ወደ ቤታቸው አልነበረም። ከአስር ወራት በፊት በክብር ያወረዱትን ሰንደቅ አላማ በክብር መልሰው ለመስቀል ወደ 10ኛው ሜካናይዝድ ብርጌድ ግቢ አመሩ። ወታደሩም አስተዳደሩም፣ ህዝቡም አጀባቸው። የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማን በታላቅ ክብር፤ በደስታና በሆታ መልሰው ሰቀሉ።

ከዚህ በኋላ ፈይሳ ጃታ ወደ ቤታቸው ተመልሰው የወታደር ልብሳቸውን አወለቁ። የዚህ ታሪክ ተራኪም ከጥቂት ቀናት በኋላ ኢትዮጵያን ለቅቆ ስለወጣ፤ ስለፈይሳ ጃታ በወሬ በወሬ ከሚሰማው በቀር፤ ቀሪ ታሪካቸውን አያውቅም። ሆኖም በታሪክ ስማቸውን ከፍ የሚያደርግ ብሄራዊ ውርደትን አልቀበል ብለው እንደተፋለሙ ጠንቅቆ ያውቃል። በመጨረሻም በእርጅና ቆይተው አስከሬናቸው ሃረር ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በክብር ማረፉን ሲያወራ፤ ለሱም ክብር ይሰማዋል። ዛሬ የምንሰማው “ብሄራዊ ውርደት” በየትኛውም ዘመን እና ወቅት፤ በየትኛውም መንደር እና አገር ሊያጋጥም ይቻላል። ዋናው ቁም ነገር… ይህንን ውርደት የሚሸከም ህሊና የሌለን መሆኑን ማረጋገጡ ላይ ነው። ይህንን የምናረጋግጠው ደግሞ በወሬ ብቻ ሳይሆን፤ እንደ ፈይሳ ጃታ ለኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ እና ለህዝብ ክብር በመቆም ነው!!

ተራኪ - ተስፋ ጥ ዑመ-ልሣን

ጸሃፊ - ዳዊት ከበደ ወየሳ

Saturday, November 30, 2013

Such inhuman and shameful treatment of Ethiopian migrants living in Saudi Arabia and other Gulf States should be stopped immediately.

Such inhuman and shameful treatment of Ethiopian migrants living in Saudi Arabia and other Gulf States should be stopped immediately.

 I am a fourth generation Ethiopian-Armenian and, like many Armenians who lived in Ethiopia, my grandparents took refuge in Ethiopia after the Armenian Genocide. Those Armenians who were fortunate enough to have escaped the Turkish atrocities and mass murders of the early 20th century repatriated to different countries around the world.

Ethiopia was a country that provided unconditional support and welcomed Armenians with open arms. We lived and prospered in Ethiopia where we maintained our institutions such as our churches, schools and community centers without any interference from the Government of Ethiopia and its citizens. We were treated as brothers and sisters and lived a good life. Although I now live in Canada, I still have a lot of love for Ethiopia and the Garbis Korajian people. Therefore, I find it necessary to say a few words about the current mistreatment of Ethiopians in the Gulf States including Saudi Arabia which has been the focus of despicable mistreatment of Ethiopians. For various reasons, mostly economic, oday’s young Ethiopians are traveling abroad looking for better opportunities of life through employment. For women, this is mostly domestic help and for men, it would be construction or any other job they can find.

Needless to say, life for Ethiopians looking for work and to survive in these countries is not easy. On top of these hardships, the Ethiopians who are law abiding and hard working members of society are facing persecution beyond anyone’s imagination.

There is no justification for such cruel behavior. It is important to remember that one day, the citizens and its descendants from the countries that are committing such atrocities on helpless Ethiopians may very well seek refuge in Ethiopia as was done 1500 years ago. As always, what goes around always comes around. Do not forget your history vis-a-vis Ethiopia and stop mistreating our Ethiopian brothers and sisters living in your country. Start treating them with decency and respect.



Garbis Korajian