Friday, March 7, 2014

አውደ ታሪከ ኢመማና የካቲት፣ የማህበሩ ውጣውረድ በጨረፍታ።

አውደ ታሪከ
ኢመማና የካቲት፣ የማህበሩ ውጣውረድ በጨረፍታ።

ዘመን በመቁጠር ሂደት የወርና የሁኔታ ግጥምጥሞሽ ይከሰታል። በሰነድ የተያዘ ማስረጃ እንደሚያሳየው የካቲት 14 ቀን 1941.የመምህራን ኅብረትበደግማዊ ምንልክ /ቤት በአዲስ አበባ ተቋቋመ። የወቅቱ የኅብረቱ ሊቀመንበርም አቶ ሚሊዮን ነቅነቅ ነበሩ። ይህ የመምህራን ኅብረት ስያሜውን እንደያዛ እስከ 1954 . ድረስ ቀጥሏል። ኅብረቱ ከየትኛውም አካል መንግሥትን ጨምሮ አደናቃፊ ኃይል ሳይገጥመው እንዲያውም ድጋፍ እየተደረገለት ነበር እዚህ ወቅት ድረስ የቀየው። ምዝገባ በሕግ የመታወቅና ያለመታወቅ ጥያቄም አልተነሳም ነበር። ኅብረቱ 1953 . የዕውቅናና የምዝገባ ጥያቄ ተነስቶ በዚያውም አፈናና የመንግሥት ጣልቃገብነት ተጨምሮበት ጉዞው አስቸጋሪ ሆነ።

ከላይ የተጠቀሰው ሁኔታ እንዳለ ሆኖ 12ኛው በፈረንሳይ አገር ተደርጎ የነበረው የዓለም መምህራን ማህበር ጉባኤ 13ኛው ጉባኤ በአፍሪካ ውስጥ እንዲደረግ ወስኖ ስለነበር በወቅቱ የትምህርት ሚኒስትር ውስጥ ከፍተኛ ሥልጣን የነበራቸውና ቀደም ብሎም መምህርና በመምህራን ማህበር አመራር ላይ የነበሩት አቶ መኮንን ዶሪ ትምህርት ሚኒስትርን በመወከል 13ኛው የዓለም መምህራን ማህበር ጉባኤ 1957 . በኢትዮጵያ እንዲካሄድ ጋበዙ። ነገር ግን ማህበሩ በአገር አቀፍ ደረጃ ባለመቋቋሙና ሕጋዊ ሰውነት የሌለው መሆኑ አወዛጋቢ ሆነ። ወዲያውኑ ጉዳዩ ለንጉሡ ቀርቦና ፈቅደው የመምህራን ኅብረት 1953 . ጀምሮ አቅርቦት የነበረው የምዝገባና ሕጋዊነት ጥያቄ በመጋቢት 14 ቀን 1957 . ሕጋዊ ሰውነት አግኝቶኢመማበሚል ስያሜ ተመዘገበ። ንጉሡ ይህ ድርጊት የፈጸሙት የዓለም አቀፍ ዝናን ለመግኘት ሲሉና የዓለም መምህራን ማህበርም የአሜሪካን መንግሥት ድጋፍ ስለነበረው መጋፋቱን ባለመፈለግ እንደሆነ ይነገራል። ከዚያም በየጠቅላይ ግዛቶቹ የማህበሩ ቅርንጫፍ /ቤቶች ተቋቁመው ወኪሎቻቸውን መላክ በመቻላቸው 35 አባላት ነሐሴ ወር 1957 . በአፍሪካ አዳራሽ በተካሄደው 13 የዓለም መምህራን ማህበር ጉባኤ ላይ ተሳታፉ። ከእነዚህ ተሳታፊዎች / ጥቀሄር ኃይሉ አቶ ይልማ ወርቅነህ አቶ ኪሮስ ሐብቱና አቶ ደምሴ በላይ ዋና ተውካዮች ነበሩ። ይህ የመምህራን የትግልና የመስዋእትነት ውጤት መሆኑን ሲያመለክት 1953- 1957 በነበረው ጊዜ በአገር ውስጥና በውጪ የኢመማ ግንኙነት ተዳክሞ የመታየቱ ሰበብ 1953 የመፈንቅለ መንሥሥት ማህበሩ ድጋፍ ሰጥቷል የሚል እንደነበረ ይታወቃል። ከዚሁ ጋር ተያይዞም 1958 . ላይ የወጣው የመምህራን የደመወዝ እስኬል በመምህራን በኩል ተቀባይነት በማጣቱ 1960 . በአቶ ከበደ ደስታ ይመራ የነበረው የአዲሰ አበባ መምህራን ማህበር መምህራንን አስተባብሮ መንግሥት ያልጠበቀው የሥራ ማቆም አድማ ማድረጋቸው ሌላ የመንግሥት ጣልቃገብነት የአፈናና እንዳሁኑ የከፋ ባይሆንም የመከፋፈል እርምጃ መከሰቱ አልቀረም። ቀደም ሲል በመምህራን የቀረቡት የደመወዝ እስኬል ጥያቄዎች ምላሽ ሳያገኙ የትምህርት ዘርፍ ክለሳ (Education Sector Review) ወጥቶ ይፋ ሆነ። ይህም የትምህርት ዘርፍ ክለሳ በሚከተሉት ነጥቦች ላይ የተመሰረቱ ተቃውሞ ገጠመው፡-

·         የሴክተር ሪቪው ተግባራዊነትና ውጤቱ ለመምህራን ሳይገለጽ በሚስጢር መያዙ፣
·         መምህራን ወላጆችና ተማሪዎች ተሳትፈው አስተያየት ያልሰጡበት መሆኑ፣
·         በሙከራ ሳይታይ በአገሪቱ በሙሉ በሥራ ለማዋል መሞከሩ፣
·         ለከፍተኛ ትምህርት ገንዘብ እንዲከፈልበት መጠየቁ፣
·         ለመምህራን የታሰበው መነሻ ደመወዝ ብር 153 መሆኑ
·         በገጠር የመሬት ይዞታ ለውጥ ሳይደረግበት የገበሬውን ኑሮ ያሻሽላል መባሉና ሌሎች


በዚህም መሰረት 1966 . ከታሕሣሥ 12 እስከ 15 የዘለቀ ልዩ ጠቅላላ የማህበሩ ጉባኤ ተጠርቶ የሴክተር ሪቪውና የመምህራን ደመውዝ እስኬል መጠን ወስኖ ከሌሎች ተዛማጅ ጥያቄዎች ጋር መልስ እንዲሰጣቸው ተስማምቶና ወስኖ ተነሳ። እስከ የካቲት 11 ቀን 1966 . ድረስ ለጥያቄዎቹ መልስ ሳይሰጥና የመምህራን ድምፅ በወኪሎቻቸው አማካይነት ቀርቦ ሳይሰማ ቢቀር ማህበሩ ሁኔታው እንዲቃና የተቻለውን ሁሉ ስለፈጸመ የመሰላቸውን እርምጃ ቢወስዱ በኃላፊነት እንደማይጠየቅም አሳወቀ። የመምህራን ጥያቄ መሰረታዊና ሥር የሰደደ መሆኑን ያልተገነዘበው ትምህርት ሚኒስቴር ግን በራሱ አካሄድ የወሰነውን ፕሮግራሙን ተግባራዊ ማድረግ ስለጀመረ አፈጻጸሙ ማህበሩንም ሆነ  ምህራንን ይበልጡን ለተቃውሞ አነሳሳ። ዘግይቶም ቢሆን ትምህርት ሚኒስቴር የሠራተኛ ማስተዳደሪያ ኮሚሽንና የኢመማ መሪዎች በአንድነት ለድርድር በያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ሰብሰባ ቢያደርጉም ስምምነት ላይ አልተደረሰም። ጉዳዩን ስንመለከተው የዘውዱ ሥርዓት ባለሥልጣናት በውይይትና በመደራደር ረገድ ከደርግና ከወያኔ ተሿሚዎች በተሻለ ደረጃ መሆናቸውን ነው። ከላይ ለማስታወስ እንደሞከርነው የማህበሩ የታሕሣሥ 1966 ልዩ ጠቅላላ ጉባኤ ባሳወቀውና በማስጠንቀቂያው መሠረት የካቲት 11 ቀን 1966 . መምህራን በመላው አገሪቱ የሥራ ማቆም አድማ መቱ። ታክሲ ነጂዎች በአዲሰ አበባ የካቲት 13 ቀን 1966 . ሥራ በማቆም ከመምህራን ጎን ቆሙ፤ ሥራ ባላቆሙት ታክሲ ነጂዎች ላይም እርምጃ ወሰዱ። የሠራተኛ ማህበራት አባላትም ሥራ ለማቆም ማቀዳቸው ታወቀ። ይህ ሥርዓት ለውጥ አማጭ የኢትዮጵያ አብዮት ዋዜማ መሆኑ ለኢመማ የሕዝብ አለኝታነት አሌ የማይባል ነው። መምህራን ሥራ ማቆማቸውን ሲሰሙ ንጉሡ፡-

·         አስፈላጊ ሁኔታዎች እስኪሟሉ ሴክተር ሪቪው ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ፣
·         የደመወዝ ጉዳይ ተጠንቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ውሳኔ ስለሚደረግ መምህራን ይህን አውቀው ሥራ እንዲጀምሩ የካቲት 16 ቀን 1966 . አስታወቁ። በዚህም ተባለ በዚያ የጥያቄው ዓይነትና ብዛት አገር አቀፍና ሕዝባዊ ይዛት ተላብሶ ሕዝባዊ አመጽ( አብዮት) አስነስቶ የዘውዱን ሥርዓት አስወገደ። በወቅቱ የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ጥያቄዎች ከነበሩት ጥቂቶቹና ጎላ ብለው ይታዩ የነበሩት የሚከተሉት ናቸው፡-“ መሬት ላራሹየድሃ ልጅ ይማርዲሞክራሲያዊ መብቶች ያለገደብ ይከበሩየመምህራን የደመወዝ እስኬል ይሻሻልበጋዝ ላይ የተደረገው ጭማሪ ይነሳየሃይማኖት እኩልነት ይከበርሕዝባዊ መንግሥት ይቋቋምየሴቶች ድርብ ጭቆና ይወገድየሴቶች የእኩልነት መብት ይከበርፊውዳልዝም ይውደምኢምፔሪያሊዝም ይውደምየሠራተኞች የሥራ ሰዓት በቀን 8 ሰዓት ይሁንየብሔረሰቦች የእኩልነት መብት ይከበር “ --- ወዘተ።

ኢመማ በአብዮቱ ወቅት የተጫወተው ሚና በዋዛ የሚታይ አልነበረም። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ልጅ እንዳልካቸው መኮንን ውጥረቱን ለማስታገስ የኢመማ አመራር አባላትን ጠቅላይ ፖስታ ቤት ቢሮአቸው አስጠርተው መምህራንን እንዲያስታግሱላቸው ትብብር ጠይቀው እንደነበር ይታወሳል። የጦር ኃይሎች የፖሊስ ሠራዊትና የብሔራዊ ጦር ሰኔ 21 ቀን 1966 . እንደተቋቋመ አንድ ቡድን ኢመማ /ቤት መጥቶ አነጋግሯል፤ የትብብር ጥያቄም አቅርቧል። ሐምሌ 3 ቀን 1966 . ኮሚቴው ለኢመማ በጻፈው ደብዳቤ መነሻነት ከሐምሌ 3-5 ቀን 1966 . የተሰበሰበው የኢመማ ሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ በሰጠው መልስ ላይኮሚቴየሚለውንደርግበሚል ስለተካው ወታደራዊ ኮሚቴው ከኢመማ በወሰደውደርግብሎ እራሱን እንደሰየመ ይታወሳል።

የኢመማ //ኮሚቴ ለአገሪቱ ጠቃሚ ነው ብሎ ያመነበትን የመፍትሔ ሐሳብ 4 ገጽ ጽፎ ለደርግ አቅርቦ ነበር። ሕዝቡ ምን ዓይነት መንግሥት ቢቋቋም እንደሚፈልግ እንዲጠየቅ ሌላ ሕገ መንግሥት ከየክፍሎቹ በሚወከሉ ጠበብት እንዲዘጋጅ እስከዚያው ድረስ ደርግ ከሕዝባዊ ማህበራትና ከመሳሰሉት ጋር በመካከርና በመደጋገፍ መሠረታዊ የሐሳብ መግለጽ ነፃነትና ሰብአዊ መብቶች ተጠብቀው ለተወሰነ ጊዜ አገሪቱ በጊዜያዊ ሕገ መንግሥትና አዋጆች እንዲትተዳደር ያለውን ሐሳብና ድጋፍ ገልጾ ነበር፤ በሂደቱም የራሱን ርቱዕ አስተዋጽኦ አድርጓል። ውሎ አድሮ ግን የወታደራዊ ቡድን (ደርግ ) ክንዱን እያፈረጠመ በጠመንጃ የመግዛት አባዜ እየተጠናወተው በመምጣቱ ኢመማና ደርግ ዓይንና ናጫ ሆኑ። በተለይ ጳጉሜ 1967. በጅማ የማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የሥርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ከዚሁ ጋር አስታኮ የወታደራዊውን መንግሥት አካሄድ በመቃወም የኢኮኖሚና የመብት ጥያቄዎችን አቅርቦ መልስ የማይሰጥ ከሆነ ሕዳር 7 ቀን 1968 . መምህራን የሥራ ማቆም አድማ እንደሚያደርጉ ወስኖ ተበተነ። አድማውም አልተሳካም ስብሰባም አልተቻለም ምክንያቱም ደርግ ለጥያቄዎቹ መልስ ለመስጠት በመወያየትና በመደራደር ፋንታ የኃይል እርምጃና አፈናን በመምረጡ ነበር። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የኢመማ መሪዎች ታደኑ ታሠሩ ተገደሉ ተሰወሩ ለሰደት ተዳረጉ እስከ1971. ድረስ ዋናው ማህበር ሥራ በማቋረጡ የኢመማ /ቤት ሠራተኞች እንኳ ደመወዝ የሚከፈላቸው አጥተው በብድር ስም የወሎ መምህራን ማህበር እየከፈላቸው እንደቆየ የማህበሩ ታሪክ ያስረዳል።ከዚያ በኋላ አፋኙ ደርግ አንድ ጊዜ በኢማሌድኅ ( የኢትዮጵያ ማርክሳዊ ሌንናዊ ድርጅቶች ኅብረት) አንዴ በኢሠፓአኮ( የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ አደራጅ ኮሚሽን) በሌላ  ጊዜ በኢሠፓ ( የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ) አመራር ሥር እያለ ማህበሩን ምርኮኛ አባላቱን ጥገት አድርጎ እስከ 1983 . ድረስ ባተ።
1983 ዓም በውስጥ ቦርቧሪዎች ቅጥረኝነትና በውጪ ጠላቶቻችን አስተባባሪነት ወያኔ/ኢህአዴግ የአገሪቱን ጦር በሻጥር አተራምሶ፣ ደርግ አገሪቱ ያፈራቻቸውን እውቅ የጦር ጄኔራሎች ማጥፋቱን ተጠቅሞ አገሪቱን በመላ ከተቆጣጠረ በኋላ የሕዝባዊ ማህበራትን እያፈረሰ ንብረታቸውን እየወረሰና /ቤቶቻቸውን ሲዘጋ ምክንያቱ በውል ባልታወቀ ሁኔታ በኢመማ ላይ ተመሳሳይ እርምጃ አልወሰደም ይሁን እንጂ የማህበሩን አመራር ይዘው የቆዩት መሪዎች አዲሱ ክስተት ውስጥ በነፃነት መሥራት የማይችሉ መሆናቸው ስለገባቸውና የማህበሩ ቆይታም በኢሠፓ ቅኝት የታጠረ ስለነበር ከመምህራንም ተቃውሞ ስለገጠማቸው ሌላ ምርጫ ተካሄዶ ለአዲስ መሪዎች አስረክበው ለመውጣት በመንግሥት ስም የተቀመጠውን ቡድን ጠይቀው ተፈቀደላቸው። ወቅቱ ዝብርቅርቅ ሁኔታ የተፈጠሩበት ስለነበር በመላው ኢትዮጵያ ምርጫ እንዲካሄድ የሚያደርግ አካል ባለመኖሩ በትምህርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት ማህበሩን እንደገና የሚያደራጅና ጉባኤ ጠርቶ ምርጫ የሚያካሄድ አስተባባሪ ኮሚቴ እንዲቋቋም ሁኔታዎች ተመቻችተው ሰኔ 21 ቀን 1984. ልዩ የምክር ቤት ስብሰባ ኮሚቴው ተመረጠ። መምህራን በተወካዮቻቸው በኩል አዲስ ለተቋቋመው የአስተባባሪ ኮሚቴው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በርካታ ጥያቄዎችን ልከው ኮሚቴው ከተላኩት ሁሉ ጨምቆ 20 ጥያቄዎችን ለሽግግር መንግሥቱ አቀረበ ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳእንዲሉ ነውና ወያኔ/ኢህአዴግ የአውሬነት ተፈጥሮው አይሎ ወጣና በጥፍሩ መቧጠጥ በጡጫውም መርገጥ ፍትሕንም መደፍጠጥ ገና በጥዋቱ በሥልጣን ማሟሻው ጀመረ። በተለይኢትዮጵያየሚል ስም ለመስማትም ሆነ ለመናገር ይጠየፍ ስለነበር ማህበሩን በዘር ፖለቲካው ትይዩየአማራየኦሮሞየትግራይየሱማሊያየደቡብ “ ---- ወዘተ መምህራን ማህበር እያለ ለማዋቀር የቀየሰውን እቅድ አዲሱ የኢመማ አመራር በግልጽና በአደባባይ ስለተቃወመ ወያኔ/ኢህአዴግ በማህበሩና በአባላቱ ላይ እመቃ፣ ወከባ እስራት ማፈናቀል መሰወር በአውራ ጠራራ መግደል ( የአቶ አስፋ ማሩን ግድያ ያስታውሷል) ሥራየ ብሎ ተያያዘው። ሁለንተናዊ ድጋፍ በመስጠት ተለጣፊ ማህበር አቋቁሞ ሕጋዊ ማህበሩንና አመራሩን እየከሰሰ 4 ጊዜ ለኢመማ /ቤት ቢፈርድም በአስፈጻሚው አካል ፍትህ እንዲኮላሽ አድርጓል።የባሰውና የከፋው አደጋ የትምህርቱ ጥራት እንዲዘቕጥ የሠራው በመምህራን በኢመማ በተተኪው ትውልድና በአገሪቱ ላይ ከደረሱት አደጋዎች የሚደመር ነው።ኢመማና መምህራን ካለፉት ሥርዓቶች በከፋ መልኩ አደጋ ላይ የወደቁት በዚህ ከፋፋይና አምባገነናዊ ቡድን ነው።

ዘንድሮ የካቲት ላይ ሆነን የየካቲት 1941 . የኢመማ ልደት 1966 ዓም የካቲት የኢትዮጵያ መምህራን የመብት ጥያቄና ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ከዚያም ቀጥሎ የሕዝብን ሥልጣን በጠመንጃ ነጥቀው እንቅጣህ እንግዛህ የሚሉትን ፋሽስቶች ስናስብ ላፍታ እንኳን ላለመታገል ዳተኛ የማንሆንበት የታሪክ አጋጣሚ ላይ እንዳለን ነው የሚሰማን። አሁንማ የአገራችን ህልውና በጥያቄ ምልክት ውስጥ የገባበት ሁኔታ ላይ ነው የምንገኘው ምን እስከሚሆን ነው ዝም ብለን የምንመለከተው? ቤታችን የውጪ ጠላቶቻችን ምሽግ ሆኖ የለ ! ክብር ነፃነት --- ሁሉም ነገር የሚገኘው በአገር ነው። ይህ ጉዳይ ለእኛ ለመምህራንና ለምሑራን ትልቅ አገራዊ ኃላፊነት ነው። ግዴታችንን እንወጣ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ጋር በመሆን ለአገራቸውና ለሕዝባቸው የሕይወት መስዋዕትነት የከፈሉት እና ዘርዓይ ደረስ ሞገስ አስገዶም አብርሃ ዶቦጭ እኮ መምህራን ነበሩ። ለአገር መሞት አኩሪ ግዳጅ መሆኑን ያስተማሩ ብርቅየ ጀግኖች አርአያነታቸውን ልንከተላቸው ይገባል። የካቲት ለኢትዮጵያ መምህራን ልዩ ትርጉም አለው ወያኔዎች ለባንዳነት ተልእኳቸውን ለማሳካት የተሰበሰቡበትን የካቲትን ሊያዜሙለት ሲዳዳቸው ስናይ ምንኛ በታሪክ በባሕል፣ በሕዝብና በእውነታ ላይ እየተቀለደ እንደሆነ በምሬት ነው የሚታወሰን።

የኢትዮጵያ መምህራን የካቲት ብዙ አባላት መሪዎች አጋሮቻቸው ሳይቀሩ ገድል የሠሩበት ስለሆነ ታሪኩን በተግባር እያደሱ ራሳቸውን ተተኪውን ትውልድ ባጠቃላይ አገሪቱን የሚታደጉበት እንዲሆን ትግሉን ከሕዝቡ ጋር በማቀናጀት እንዲገፉበት በሰደት የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አባላት አስተባባሪ ኮሚቴ ጥሪውን በተደጋጋሚ ያቀርባል። እንኳን ለኢመማ 65 ዓመት ምስረታ አደረሳችሁ


መምህራን 1966ቱን የካቲት ታሪክ ይደግሙታል!!!
By Coordinating Commitee of Exiled Members of Teachers Association
Email: eta1941@yahoo.com

Thursday, March 6, 2014

Criminal gangs are targeting African immigrants for extortion, British police warned [telegraph]

Formularbeginn

Formularende

Formularbeginn

Formularende


British police have been warned that Africans in the UK are being targeted for extortion by foreign gangs, the Telegraph can disclose.
Europol, the European crime intelligence agency, has said that families are being forced to pay tens of thousands of pounds to free relatives who have been kidnapped.

Officials warned that criminal gangs are demanding £20,000 from European “contacts” of African immigrants for the hostage to be released.
Rob Wainwright, the Director of Europol, said that the organisation “has issued a warning to all police forces in Europe that this form of international extortion may also be happening in their areas”.

“In response to any increase in cases reported to national competent authorities in Europe, the centralised analysis of this data at Europol would enable the detection of cross-border links between different cash handlers.
“Europol is ready for coordinated action with Interpol to deal with the problem in Europe and the Sinai region.”

The Telegraph has spoken to one man in Birmingham who paid more than $35,000 (£20,917) for his sister to be released.

The man, who works as a taxi driver in Birmingham, asked for his surname to be withheld because he is concerned that the gangs may target other family members in his home country.

“I paid the money to save her life”, said Dawit. “I sold all that I could and borrowed from family and friends.

“The main thing is that she is safe and alive, but because she was tortured. She begged me to save her life. It was the worst thing in the world”.
He said that he knew another Eritrean man from Birmingham who was also forced to pay thousands of pounds to free a relative who had been kidnapped.
Europol said that data provided by national law enforcement authorities showed that “individuals of Eritrean origin living in Sweden and at least two other European countries” have received demands for money to free relatives who had been kidnapped and tortured in Sinai.

They said that “the extortion operations were run by organised crime groups (OCGs) of Bedouin origin exploiting irregular migrants who had been kidnapped in Eritrea and Sudan by OCGs of Rashaida origin.

Europol said that they are aware of cases where family members and friends have paid between 4400 euros (£3623) to 25,700 euros (£21,161) to free hostages.

Soren Pederson, from Europol said, “In most cases, the extortion processes involved multiple negotiation steps and sequential increases in the ransom amount.

“Payments were made to multiple cash handlers used by organised criminal groups in locations inside and outside of Europe.”
Few cases have been prosecuted, because victims are often too scared to tell the police, but last year, a Stockholm court has charged two Swedish nationals with extortion in connection with the kidnappings of Eritrean asylum seekers.
The men allegedly demanded $33,000 (£19,721) from families living in Sweden for the safe return of their relatives.

Amnesty International said that it has received “numerous reports” of refugees and asylum seekers being held captive in the Sinai Peninsula of Egypt.
A report produced by the organisation last year said that hostages held in Sinai are “subjected to brutal violence and inhuman treatment during attempts to extract ransom payments from their families”.

Amnesty said that the information they had “indicates that there is an extensive network of criminal groups which include smugglers and traffickers operating through Eritrea, Ethiopia, Sudan and Egypt.

“They are reportedly heavily-armed…The networks include agents that collect the ransom money in countries including Israel, Saudi Arabia, the US, and throughout Europe”.

When Dawit’s sister was kidnapped as she walked to work in Eritrea last July, he reported the incident to police in the UK, but was told they were unable to help because she was not a British citizen.

The gang holding his sister called their mother and demanded $10,000 (£5975) was paid to them within two days.

If they did not receive the payment, the gang said she would be taken to Sinai and it would cost $35,000 (£20,917) for her release.
“The men knew we could not find $10,000 in one of two days”, said Dawit. “We were very scared and we wanted my sister to be able to return to her children, but we could not find the money that quickly.

“So then men took my sister to Sinai, where they made her call my family. They beat her and she was crying on the phone. She begged us to save her life.
“I sold two cars I had in Sudan and luckily I have lots of good friends, so we paid the money, but it took a long time for her to be release.

“The main thing is that she is safe and alive, but she has lost her hearing in one hear because of the beatings and also has a bad infection.”

Dawit’s sister is now in Ethiopia and the family are trying to raise enough money to get her back to her children in Eritrea.

By Claire Newell, and Holly Watt