Monday, July 7, 2014
Sunday, July 6, 2014
Friday, July 4, 2014
British government statement on extradition of Ethiopian leader, Andargachew Tsege
British government statement on extradition of Ethiopian leader, Andargachew Tsege
This statement was issued today by the Foreign and Commonwealth Office.
This statement was issued today by the Foreign and Commonwealth Office.
On the case
“A British national, Andargachew Tsege, was reported missing in Yemen on 24 June. Since then UK officials have pressed the Yemeni authorities at senior levels to establish his whereabouts, including meeting with the Yemeni Ambassador in London this week. We are aware of reports that he may now be in Ethiopia and we are urgently seeking confirmation from the relevant authorities given our deep concerns about the case. We are continuing to provide consular assistance to his family.
“We are aware of reports that he may now be in Ethiopia and are urgently seeking confirmation. If confirmed this would be deeply concerning given our consistent requests for information from the Yemeni authorities, the lack of any notification of his detention in contravention of the Vienna Convention and our concerns about the death penalty that Mr Tsege could face in Ethiopia.”
On the British Government’s stance on the death penalty
“The UK opposes the death penalty in all circumstances as a matter of principle. Its use undermines human dignity, there is no conclusive evidence of its deterrent value, and any miscarriage of justice leading to its imposition is irreversible and irreparable. We continue to call on all countries around the world that retain the death penalty to cease its use.”
source: Martin plaut
Saturday, June 14, 2014
ትውልድ ራሱን ከዘረኝነት ማራቅ ታሪካዊ ግዴታው ነው !
ትውልድ ራሱን ከዘረኝነት ማራቅ ታሪካዊ ግዴታው ነው !
ከጠባቦችና የግንጠላ
አራማጆቸ ጎራ እንደሚስተጋባው ከንቱ
ታሪክ አገራችን ኢትዮጵያ በድንገት የዛሬ መቶ አመት የተከሰተች ሳይሆን በብዙ ዘመናት የዜጎች መስዋዕትነት የተገነባች
አገር ናት። ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ
ለማድረግ የብዙ ሚሊዮንና የአያሌ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ህይወት ተገብሮባታል። ይነሰም ይብዛም፣ ይጉላ ይደብዝዝ፣ ሁሉም ህዝብ ለዚያች አገር ግንባታ አሰተዋፅኦ አድርጉአል። በሌሎች
አገሮች ታሪክም እንደተከሰተው ሁሉ
በኢትዮጵያም ታሪክ
ጦርነት የሀገር ግንባታው ሂደት አካል ሆኖ ተገኝቷል። በሂደቱ
ለጠፋው ህይወትና ለደረሰው በደል የዛሬው ትውልድ ከቶም ተጠያቂ ሊሆን አይገባውም።
የዘመናት በደልና ቁርሾን ዛሬ ህይወት ሰጥቶ በማናፈስና በማመርቀዝ
የህዝብ ግኑኝነትን፣ አነድነትና፣ ትስስርን
ለማፍረስና ህዝብን
እርስ በርስ ለማናቆር መጣሩ የተሳሳተ ብቻ ሳይሆን ወንጀልም ነው። ለነገሩማ ዛሬ ህፃን፣ ሽማጊሌ፣ ሴት ፣ወንድ ሳይለዩ በጭፍን
ጥላቻ የሚጨፈጭፉ የሚያርዱና ገደል
የሚጥሉ ሁሉ ያለፈ ታሪክን ገድል በመጥቀስ ከወንጀላቸው ነፃ
ሊሆኑ አይችሉም።
ለሀገር አንድንትና ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር
የሚካሄደው ትግል
ከግቡ እንነዲደርስ ከተፈለገ ወጣቱ ትውልድ ዘረኝነትን (Ethno-Fascist,
Ethno-Chauvinist) ትምክህትን አንጋሽ፤ የቅኝ ገዥ ተስፋፊ ደጋፊ ልሂቃናት የፈጠሩት ህልዮ፤ አገርን በታታኝ.
ከፋፋይ መሆኑን ተረድቶ
መራቅና አንድነትን ለመጠበቅ መታገል ግዴታው
ነው። በአንድ ፅንፍ የሚታየው ጎጂ አቋም ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ክዶ በመብት ሽፋን ግንጠላን አያራገበ በአሶሳ፤በአረካ፤ በአርባጉጉ፤
በሎቄ፤ በአሰቦት በበደኖ ፤በጋምቤላ፤ በቡርጂ፤ በቦረና፤ በጌዲዎ፤ወዘተ የተከሰቱ
እልቂቶችን አስከትሏል።
በዚህ ዘረኛ ጎጠኛ ቡድንና በመሰሎቹ እየተራገበ ያለው
የአንድንት፣ የዘርና
የሃይማኖት ጥላቻ
እንዲሁም የክፍፍል እሳት ታሪክን እየካደ የዕርስ በርስ ግጭትን እያስፋፋ የአንድነትንና የአብሮነትን ስረ-
መሠረት እየነቃቀለ ህዝብን በጎሳ፣ በጎጥ፣ በቛንቛን፣ በሃይማኖትን፣ ... ደረጃ
በልቶና ሸንሽኖ አሽመድምዶ ለማጥፋት
የሚደረግ የፀረ-አነድነት (Ideology Of Neocolonialism) ሴራ
ነው።
ይህ የፀረ- ኢትዮጵያ ጽንፈኛ አቋም መገንጠልና ማስገንጠል በሚለው
(Ideology Of Neocolonialism) ወያኔያዊ ተግባሩና መፈክሩ ይገለጣል። የሕዝብን ማንነትና የቆየ የጋራ ታሪክ ይሰብራል። በኢትዮጵያዊነት ላይ
ሳይታክት ይዘምታል። ዘረኝነትን እንደፀጋ
ተላብሶ፤ ለዴሞክራሲ አፍአዊ ግብርን እየከፈለ፤ ክፍፍልንና
ጥላቻን ያነግሳል።
ሌላኛው ፅንፋዊ አቋም ደግሞ ራሱን እንደ የአንድነት አባውራ
ሰይሞ በጥቅል መፈክር የውጭ ተልእኮን በድብቅ
ለማስፈጸም ተጨባጭ
ሁኔታን እየካደ በህሊናውም በጆሮውም ላይ የተኛና የነፃነት ፈላጊውን የህብረተሰብ ክፍል
እያወገዘ ህዝቡ ምን እንደሚያስፈልገው እኛ እናውቅለታለን በሚል የወያኔን ዘረኛ የጥላቻ ፖለቲካ በመገልበጥ አንድን
ህዝብ በጅምላ እያወገዘ ፈለግሁት የሚለውን አንድንተ ማጅራት ይመታል። በዘረኞች በጎጠኞችና በጨቋኞች ላይ እንደመዝመት ፈንታ
ለጭቆና መፍትሔ የሚሹትንና የሀገረሰብ መብት ይከበር ያሉትን ክፍሎች በምሬት ያወግዛል። ስለሆነም ሁለቱም ከፋፋይና ጎጅ ፅንፎች ናቸው።
የሀገር አንድነትን ክግዛታዊ ክልል ባሻገር ከህዝብ ጥቅምና አንድነት ጋር በማዋሀድ ከገለፅነው የጠባቦቦች
መጠቀሚያ የሆነውን ዘረኛ የጥላቻ አክራሪነት
ልንሰብረው እንችላለን።
ለሀገር አንድነት የሚደረገው ታሪካዊ
ገድል ከዘረኞች (Ethno-Fascist,
Ethno-Chauvinist) ጋር መፋጠጡ የማይቀር ሀቅ ነው። ስለዚህም ኢትዮጵያ እንድትዳከምና እንድትጠፋ ማለትም
ህዝቧ በጎሳና በሃይማኖት ተከፋፍሎ
ወደ ዕርስ በርስ አስከፊ ጦርነት እንዳይገባ የታሪክ ባለአደራ የሆነው ኢትዮጵያው ወጣት ትውልድ ቀን ቀጠሮ ሳይሰጥ ለነፃነት ሲል መደራጀትና
መታገል ይገባዋል።
ሀገርን ከጥፋት ለማዳን እየተደረገ ያለው የትግል ተልዕኮ ስኬታማ ሊሆን የሚችለው የሀገር አንድነትን መድልኦ አልባ ከሆነ የሀገረሰብ መብት ጋር አጣምረን ይዘን ከተገኘን ብቻ ነው። የምንታገልላት ኢትዮጵያዊ የሀገረሰብ መብቱ፤ መላው ሀገረሰባዊ
እሴቶች (ቛንቛ፣ ሃይማኖት፣ ባህል...) ሙሉ በሙሉ ተከብረው፣ የሃገራዊ የጋራ
እሴቶች ሆነው በሁሉም ተቀባይነት አግኝተው ተገቢው እውቅና፣ እንክብካቤ አግኝተው፤ የሚገባቸውን ሥፍራና ቦታ ሲያገኙ፤ የሀገረሰቡ መብቶች ሁሉ ተከብረው ለዜጎች ሁሉ እኩል ሀገር ሆና ለምትገኝ ኢትዮጵያ መሆኑ በግልፅ ይታወቃል።
ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ህያው ሆነው ያሉና የሚቀጥሉ ናችው። ሆኖም በዘር፣ በጎሳ፣ በጎጥ፣ በቛንቛን፣ በሃይማኖትን፣... አገር ከፋፋይ (Breakup and division of
existing Independent State into small dependent neo-colonial states) ስርአትን አንጋሽ
የሆነ (Ideology Of Neocolonialism) ርዮትን አንግቦ ለሀገር አንድነትን ጠንቅ በመሆን የሚታወቀውን ዘረኝነትን (Ethno-Fascist, Ethno-Chauvinist)
አምርረን መታገል የኢተዮጵያና ኢተዮጵያዊነታችን ማንነት መገለጫ ግዳጃችን ነው። በመሆኑም
ትውልድ እራሱን ከዘረኛ ርዮት አንጋሽ አራማጅ እራሱን አርቆ አገሩንና ሕዝቡን መታደግ ያለበት አሆነ መሆኑን አውቆ፣ በወያኔና
ባባሪ ተባባሪ እኩይ ድረጅቶች ደጋፊ ሕሩያን አማካኝነት፤ እለት ተለት በሰረበተ ዲስኩር (Sychopatic
Statement) ቀንብበው፤ ፈብርከው በሚፈጥሩት፤ ስነኳፍ፣ ዘረኝነትን
አነጋሽ አጀንዳዎች ሳይጠመድ፤ በጋረ ለጋራ ሀገርና ሕዝብ የነፃነት ትግል ተነሳሽ በመሆን፤ ትውለድ በፅናት በቆራጥነት ተደራጅቶ
እራሱን ከዘረኝነት አጽድቶ የድረሻውን፤ የበኩሉን ታሪካዊ ድርሻ የሚያበረከትበት ግዜ ዛሬ መሆኑን፤ ጠንቅቆ ሲያውቅ ብቻ ነው።
ድል ለኢትዮጵያ!!!
Subscribe to:
Posts (Atom)
-
ብዙ አንገብጋቢ የሆኑ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች አሉ፡፡ የቱን ጥለን የቱን እንደምናነሳ ራሱ ይቸገራል፡፡ ወዲህ ስንል በፖለቲካው መድረክ የዴሞክራሲው አፈናና እመቃ ገዝፎ ይታያል ብቻ ...
-
ዘርፎ አዘራፊ ስርአት ክፍል ፩ ልማት (Development)፣ እድገት (Growth) እደሚታወቀው፤ ልማታዊና (Development) እድገታዊ (Growth) የሚባሉ ሰነ - ቃላት፤...
-
የኢትዮጵያ ጀግኖች ታሪክ ሲነሳ፤ በግንባር ቀደም ከሚጠቀሱት መካከል ደጃዝማች ባልቻ አባ ነፍሶ በዋናነት ይጠቀሳሉ። በአባታቸው ኦሮሞ፣ በናታቸው የጉራጌ ተወላጅ የሆኑት ባልቻ ሳፎ ( ባልቻ...