Thursday, July 31, 2014

" ስንቅህን በአህያ ፤ ምሥጢርህን በጉያ "

ኢትዮጵያ ነጻ ሀገር ሆና የራሷን መንግሥት በመመስረት ከታወቀችበት ዘመን አንስቶ፤ መሪዎቿ በቀናዒነት ሀገሪቱን ከውጭ ወራሪ ኃይሎች ሲከላከሏት ቆይተዋል። በየዘመናቱ ወረራው ቢመጣባትም፤ ሁሉንም ከሕዝቡ ጋር በመሆን እየተዋጉ መልሰውታል። የዚህም ዋና አብነት፤ መሪዎችና ዜጎች መተባበራቸው ነበር። በገዥዎቹና በመሪዎቹ መካከል የነበረው ግንኝነት ፍጹም ዕጹብ- ደንቅ ነበር ማለት ባይቻልም፤ በሀገር ነጻነትና ሉዋላዊነት ረገድ ግን፤ ነፋስ የማይገባበት ውኅድትና ትብብር ነበረ ማለት ያስደፍራል። የጋራ ሀገራቸውን ለማዳን ኃይላቸውን አስተባብረው መቆም አማራጭ እንደ ሌለው አበክረው አውቀውና ተረድተውት ነበር ማለትም ያስችላል። የሕዝብና የመሪዎች በአንድ መንፈስ መቆም ደግሞ፤ ሀገሪቱ ከቅኝ ገዥዎች ወረራ እራሷን ተከላክላ እንድትቆይ አስችሏታል።

የውጭ ወራሪዎች ከተባረሩ በኋላ ግን ገዥዎች ሕዝቡን እየጨቆኑ መግዛታቸውን ይቀጥሉበታል። ሕዝቡም የመከራ ቀንበሩን እንደተሸከመ መራራ ኑሮውን ይገፋል። ለሀገር መሥዋዕት ለመቆም፤ በቤተ መንግሥት ውስጥ ጮማ እየቆረጠ ጠጅ እያንቆረቆረ በሚቀማጠለው ልዑልና የእለት ጉርሱ የዓመት ልብሱ ባረረበት ገበሬ መካከል፤ ብዙም ልዩነት ባየካሰትም የመሥዋዕቱ ክብደት የሚመዝነው ግን በአርሶ-አደሩና በተራው ሕዝብ ህይወት ላይ ነበር ማለት ይቻላል።

ኢትዮጵያ በዘመናት ነጻ ሀገር ሆና እንድትኖር ካበቋት ዐበይትና መሠርታዊ ነገሮች አንዱ፤ ዜጎቿ የሀገራቸውን የውስጥ ምሥጢር መጠበቃቸው ዋናው አብነት ነበር። " ምሥጢርክን በጉያ ስንቅህን በአህያ ! " የሚለው ግንዛቤ፤ የዚያን ጊዜ ነዋሪዎች፤ሀገራዊ ባኅልና ጠበይ ነበር። የሀገርን መሥጢርና የውስጥ ገመና እንኳንስ ለውጭ ጠላት አሳልፎ መስጠት ቀርቶ፤ እርስ በእርሱም ቢሆን በአደባባይ አውጥቶ መውያየት ብልኅነት አልነበረም። ጸያፍና እንደ ነውረኝነትም ያስቆጥር ስለነበር፤ ሁሉም ዜጋ የየራሱን ክብርና ስበዕና ለመጠበቅ ሲልም ጭምር፤ በአደባባይ ላለመዝረክረክ ብርቱ ጥንቅቄ ያደርጋል። ይህ ብሄራዊ / ኢትዮጵያዊ ባኅርይና ሥነሥርዓት፤ ለባዕዳን ወራሪዎችና ለሌሎቹም የሀገሪቱ ባላንጣዎች እንዲሁም፤ በጠቅላላው፤ የኢትዮጵያን ውስጠ- ምሥጢር ለማወቅ ሲያፈነፍኑ ለነበሩ ሁሉ አስችጋሪ ሆኖ ቆይቷል። የሀገርን ውስጠ- ምሥጢር መጠበቅ፤ የውጭ ጠላት ሰርስሮ እንዳይገባ ለመከላከል የሚያስችል ፍቱን መድህኒት ሆኖ ቆይቷል። የዛሬውን አያደርገውና !

አርበኛው በዝቶ፤ ሀገር ወዳድ ሞልቶ- ተርፎ በነበረበት በዚያን ታሪካዊና አስደናቂ ዘመን፤ የሀገር ውስጠ- ምሥጢር ተጠብቆ ቆይቷል። ያም ሲባል፤ ቁጥራቸው ግምት ውስጥ የማይገባ ጥቂት ከሃዲያንና ለሆዳቸው ብቻ ያደሩ ሰዎች እንደነበሩ ደግሞ መዘንጋት አይገባም። የዚህ ክስተት መኖሩ ደግሞ አያስደንቅም። ለምን ቢባል ? በማንኛውም ኅብረተ ስብ ውስጥ "በያንዳንዱ 12 ሐዋርያት ውስጥ፤ አንዳንድ ይሁዳ ስለማይጠፋ" ነው። እጅግ የሚያስደንቀው ግን፤ በአሁኑ በወያኔ ዘመን፤ የከሃዲያንና የሀገር ሻጩ ቁጥር እየበረከተ መምጣቱ ነው። ታዲያ " እያንዳንዱ ኅብረተሰብ የሚገባውን መንግሥት ያገኛል" የሚለውን ስላቅ ሙሉ ለሙሉ ለመቀበል ባይቻልም፤ ለአላፊ- ጠፊ ጥቅም ሲባል፤ ከሃዲውን ወያኔን የሚደግፉ ውህዳን ግብረ- ይሁዳ መብቅላቸው፤ ለስላቁ ማጠየቂያና መደላድል መሆናቸው ይበልጡኑ ያስገርመናል።

የአንድነት ኃይሉ፤ ከነኝህ አይነቶቹ ምሥጢር ዘክዛኪዎችና ጥብቋቸውን በየጊዜው ከሚለዋውጡ ክፍሎች ራሱን ካላጸዳ፤ ዉጤት ያስመዘግባል ተብሎ መጠበቅ፤ የኅልም እንጀራ ነው። በተለይም ደግሞ፤ ለመጣው መንግሥት ሁሉ ታማኝ አገልጋይ ለመሆን የሚገለባበጠው ሁሉ፤ ሀገርን ለማዳን በሚደረግው ትግል ውስጥ ዕምነት ሊጣልበት የሚገባ ሆኖ አልተገኘም። " ምሥጢር የባቄላ ወፍጮ አይደለም " እንዲሉ፤ ለወሬ ማጣፈጫ እንዲጠቅም ታስቦና ሁሉን ያውቃል እባላለሁ ከሚል ከንቱ ውዳሴ በመነሳት ብቻ መነኛውንም ነገር እንደ ቀዳዳ ስልቻ ማዝረክረክ የሚጠቅመው፤ የወያኔን ሥርዓት እንጅ ለማንም አይረዳም። በሀገርና በሕዝብ ላይ ከባድ ጥፋት ከፈጸሙ በኋላ፤ የንሰሀ ጸጸት ቢያደርጉ፤ የጠፋችው ሀገር ልትመለስ አትችልም። ይሁዳ፤ በክኅደቱ ተጸጽቶ ራሱን በዛፍ ላይ ቢሰቅልም ቅሉ፤ ጌታውን ክርስቶስን፤ ከሮማውያን ስቅላት ሊያድነው አልተቻለውም። " ልመና ሳሉ በቁመና ! " በመሆኑ፤ ኢትዮጵያን ከዘረኞች ጥፋት ማዳን የሚቻለው፤ ቀኑ ሳይመሽ ዛሬ ሁሉም በቁሙ ተባብሮ በመቆም መሆኑን፤ ልቡ በክኅደት ያልተሰለበ ዜጋ ሁሉ ያምንበታል

የወያኔ አገዛዝ፤ እንኳንስ ከወዶ- ገባዎች በነጻ የሚጎርፍለትን ኢንፎርሜሽን አግኝቶ ይቅርና፤ እንዲያውም በተጠናከረውና በሰላው የመረጃ መዋቅሩና አሰራሩ ጠላቶቹን እያጠቃ፤ ደጋፊዎቹን እያነቃ የሚርበተበት ዘረኛ ደርጅት ነው። የመረጃ ተቋሙን ለማደራጀት የቻለው ደግሞ፤ በራሱ ክኅሎትና ብቃት፤ ችሎታና ጭንቅላት እንዳልሆነ የሚያውቅ ያውቀዋል። የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም፤ ለባዕዳን አለቆቹ አሳልፎ የሰጠ በመሆኑ፤ የራሳቸውን ጥቅም እንዲጠብቅላቸው ሲሉ፤ ባዕዳን ኃይሎች፤ በሥልጣኑ እንዲቆይ የሚያስችለውን ነገር ሁሉ በመፈጸም ላይ ናቸው።

ባዕዳን አለቆቹ ከሚረዱት ሁሉ ዓይነተኛው ጉዳይ ደግሞ፤ የኢንተሊጀንስ ወይም የስለላ ተቋማቱን በሁለንተናዊ ረገድ ማደራጀት ነው፡፡ የስለላ ተቋማቱን ከማደራጀት አልፈው ተርፈው፤ በሥልጣና፤ በስለላ መሳሪያዎች ግንባታ፤ በኤሌክትሮኒክስ ሳይንስና አሰራር ደረጃ ይተባበሩታል። ከራሳቸው የኢንተለጀንስ ወይም ስለላ ድርጅቶች ጋርም ያስተባብሩለታል። ተቃዋሚ ድርጅቶችንና ግለሰቦችንም እየተከታተሉ ይይዙለታል። ፡የተቃዋሚዎቹንም እንቅስቃሴ ሁሉ የጠልፉለታል። የስለላ መርቦችንም በመዘርጋት፤በሁሉም የኢትዮጵያ ኅብረተስብ ውስጥ ሰርስረው እንዲገቡ አድርገውለታል። ሰላዮችንም በሙያው የተራቀቀ ችሎታ እንዲያገኙ ያሰለጥኑለታል። ኢትዮጵያን በማጥፋት ላይ የሚገኘው ወያኔ፤ ኢንተለጀንስን/ ስለላን አስመልከቶ ከባዕዳን የሚያገኘው ርዳታና ትብብር፤ የሚያስርገም ሆኗል።

የተቃዋሚ ድርጅቶች አለመተባበርና ያሰራራቸው ዝርክርክነት ተጨምሮ፤ ለወያኔ የስለላ ሰራተኞች ሰርስሮ ለመግባት አመች ሆኔታን አመቻችቶላቸዋል። የሚያስገርመው ደግሞ፤ ይህንን የስለላ ጥቃት አሁንም ቢሆን፤ ተቃዋሚ ነኝ የሚለው ክፍል ሁሉ፤ የቱን ያህል እንደተገነዘበውና ምንስ ያህል ጥንቃቄ እንደሚያደርግ በእርግጠኝነት ማወቅ አለመቻሉ ነው። ሰኔና ሰኞ የተገጣጠመለት ወያኔ ግን ሁኔታዎቹን ሁሉ ለመጠቀም እንቅፋት አላጋጠመውም።

ሁኔታዎቹ ሁሉ አሁን ባሉበት ደረጃ ይቀጥላሉ ማለት ግን አይደለም በዕርግጥም ይቀየራሉ ሁኔታዎቹን የሚቀይራቸው ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ የተባበረ ትግል እንደሚሆን ደረትን ነፍቶ መናገር ይቻላል። የወያኔ የበላይ ጠባቂዎቹ ሁሉ፤ የማይበገረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል መፋፋሙን ሲገነዘቡ፤ ወያኔን አጋልጠው እንደ ነጋበት ጅብ እንደሚፈረጥጡ፤ በሌሎች ሀገሮች ተደጋግሞ የታየ ሀቅ ነው።


ለዚህም፤ የሶቪየት ኅብረትንና ደርግን፤ የግብጹን ሆስኒ ሙባረክና አሜሬካንን፤ የኢራኑን ሻህ ባሃላቢንና አሜሪካንን እንደ ታሪክ ማስረጃ ጠቅሶ ማለፍ ይቻላል። ባዕዳኑ፤ ዘለዓለማዊ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ ደግሞ፤ ከሚመጣው አዲስ አገዛዝ ጋር ሰልፋችውን እንደሚያስተካክሉ ልንጠራጠር አንችልም። ዋናው ጥያቄ ግን፤ እረ ለመሆኑ፤ የኢትዮጵያን ዘላቂ ጥቅም የሚያስጠብቅላት ማን ሊሆን ይችላል ? የሚለው ነው። ይህንን ጥያቄ መመለስ የሚገባው፤ ማንኛውም የሀገሪቱ ዜጋ መሆን እንዳለበት እናምናለን የራስን ሀገር ጥቅም ለውጭ ባዕዳን አሳልፎ የሚሰጥ ቡድን፤ ኢትዮጵያ በታሪኳ ሲገጥማት ይኽ የአሁኑ የከፋ ሆኗል። እንደ እግር እሳት የሚያንገበግበው ግን፤ ሁሉ መሥዋዕት ተከፍሎ፤ ዛሬ ሀገራችን በአስከፊ ሁኔታ ሆና ማየቱ ነው።

ይህ ሀቅ እንዳለ ሆኖ እነኝህ የውጭ ኃይሎች፤ ከወያኔ ጋር እየተባበሩ፤ ይኽንን ተግባር የሚያከናውኑት፤ ሆን ብለው አስበውበት የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመጎዳት ሲሉ ብቻ ነው ብሎ ለማለት ባያስደፍርም፤ ዛሬ ወያኔን የሚደግፉትና የድርጊቱም አባሪ-ተባባሪ ለመሆን የወሰኑት ግን የራሳቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ መሆኑ ደግሞ የሚካድ አይደለም።

ዘላቂ ጥቅማቸውን የሚያስጠብቅላቸውን ሁሉ በዘላቂ ወዳጅነት ደረጃ ያስተናግዳሉ ባይባልም፤ ወያኔን ግን በጊዚያዊ አገልጋይነቱ ይጠቀሙበታል እንጅ፤ አለቅነታቸውንና ሽርክናቸውን እስከ ዘለቄታው ድረስ እንደማይዘልቁበት እናውቃለን። ይህንን ለማለት የሚያስችለውም፤ " ዘላቂ ጥቅም እንጅ፤ ዘላቂ ወዳጅም ይሁን ዘላቂ ጠላት ብሎ ነገር የለም " የሚለውን የምዕራባውያን የዲፕሎማቲክ ይትብሃል ስለምንገነዘብ ነው። ያም እንዳለ ሆኖ፤ ወያኔ፤ ታማኝነቱን እያረጋገጠ ታዛዥነቱን እስከቀጠለላቸው ድረስ፤ የበላይ ጠባቂዎቹ ሆነው እንደሚሰነብቱ መዘንጋት አይገባም። በወያኔና በባዕዳን ኃይሎች መካከል ያለው ግንኙነት የአለቃና ጭፍራ ቁርኝነት ነው ጌቶቹ ሲጠሩትና ሲያዝዙት፤ አቤት- ወዴት ብሎ ያሉትን መቀበል ነው። ይህ ባኅርይ ደግሞ ለማንኛውም ሀገር-ወዳድ ኢትዮጵያዊ የሚዋጥለት አይሆንም። ለዚህም እኮ ነው፤ ሀገር ወዳድ መሪዎች በባዕዳን ኃይሎች የማይወደዱት።

በኢትዮጵያ፤ ሀገር ወዳዶ መሪዎች እስካልበቀሉ ደርስ ደግሞ፤ ሀገራችን ያልፍላታል ተብሎ የሚታሰብ አይሆንም።

ይህንን ሀቅ የተገነዘበ ዜጋ ሁሉ፤ ሀገር ወዳድ ዜጎችን እያበቀለ ማፍራትን አበክሮ ሊያስብበት ይገባል። በዚህ ረገድ ተስፋ የሚደረገውም በየዘመናቱ፤ ኢትዮጵያ ሀገራችን ዕውነተኞቹ ሀገር ወዳዶች የሚፈልቁባት ሀገር በመሆኗ ነው።

እነርሱ ደግሞ፤ ወደ መድረኩና ወደ ፖለቲካው ምኅዳር ሊመጡ የሚችሉት፤ እንደ "ዲዮጋን፤ በጠራራ ፀሀይ በፋኑስ ተፈልገው" ሳይሆን፤ እያንዳንዳቸው፤ ምግባራቸውንና ተግባራቸውን የሞራል ልዕልናቸውንና ታማኝነታቸውን በድርጊት ያስመሰከሩ እንዲሆኑ ይጠበቅባቸዋል እነኝህ ደግሞ ወላዲቷ ኢትዮጵያ በድባብ ትሂድ እንጅ ሞልተው ተርፈዋል ብለን ማመን እንፈልጋለን። ባንጻሩ ግን፤ ሰው ያላወጣ ትውልድ፤ " የሰው ያለህ!" እያለ በመጮሁ ብቻ ሰው ሊወጣለት የማይችል መሆኑን መገንዘብ ይገባል። አርበኛንና ሀገር ወዳድ ዜጎችን እያጠፉ አዲስ አርበኛን ማግኘት ያስቸግራል ምክንያቱም፤ እስካሁን እንደታየው ከሆነ፤ " የፊት ወዳጅህን ከፍነው በሻሽ፤ የኋለኛው እንዳይሸሽ !" ብለው እያዘኑ ያለፉትን ታላላቅ አርበኞች ታሪክ እየሰማን በማደጋችን ነው።

አርበኞች እየበቀሉ በመሰዋት፤ የነርሱን ፈለግ የሚከተል ትውልድ እያፈሩ ካለፉ፤ የነርሱ መሥዋዕትነት ከንቱ ሆኖ አይቀርም። የመሥዋዕቶቹና የሰማዕታቱ ገድል ዉጤት አስመዝግቧል ለማለት የሚቻለውም፤ ተተኪው ትውልድ  የነርሱን ዓርማ በማንሳት ሀገሩን ከጥፋት ለማዳን ሲችል ነው። ለዚህ ውጤት ዓብነት ከሚሆኑት መካከል ዋነኛው የራስን ምሥጢር እየጠበቁ የጠላት ሰላዮችን እየተከላከሉ ማምከን ወይም ከጥቅም ውጪ ማድረግ ይሆናል። ምሥጢርህን በጉያህ ይባላል እንጅ አዝረክርክው አልተባለም! በማንም ቀለምና ካባ የሚመጣ አምባገነን ለሥልጣኑ መሠረት አድርጎ የሚጠቀምባቸውና ሕዝብንም ለመጨቆን የሚገለገልባቸው ልዩ ልዩ የመጨቆኛ ማሳሪያዎች ይኖሩታል። በሕዝብ የተጠላ በመሆኑም፤ የሕዝብን ተቃዉሞ ይፈራል። ሥልጣኑን እየጠበቀ ዕድሜዉን ለማራዘም የመጨቆኛ መሳሪያዎቹን አዘጋጅቶ ማጠናከር የቅድሚያ አጀንዳው ወይም ተልኮው ይሆናል። የሕዝብ አመፅ በማንኛውም ወቅትና ሁኔታ ይነሳብኛል ብሎ ስለሚሰጋ፤አመፁን ለማዳፈን ማንኛውንም የኃይል ርምጃ ከመውሰድ አይቆጠብም። ይህን ለማሳካት ሲልም፤ እራሱ ያወጣውንም ህግ ቢሆን እንኳ ከመጣስ ወደ ኋላ አይልም።

ዛሬ በኢትዮጵያ የተዘረጋው ዘረኛ ሥርዓት አራማጆች የሚፈፅሙትም ይህንኑ ነው። ለኅልውናቸው አስጊ የመሰላቸውን ሁሉ ለማጥፋት የዓለም አቅፍ ህጎችን ሁሉ በመጣስ ድንበር -ዘለል ውንብድናን ሳይቀር ያካሂዳሉ።

የስለላ ተቋሞቻቸውን የሚቆጣጠሩት ከራሳቸው ብሄር የተውጣጡ አባሎች ናቸው። ዛሬ፤ በኢትዮጵያ የመንግሥት ታሪክ ተወዳዳሪ የማይገኝለትን ጸረ ሕዝብ የኢንተለጀንስ ተቋምና የስለላ ድርጅቶችን የገነባው ወያኔ ሆኗል። ለዐብነት የሚከተሉትን የኢንተለጀንስ አገልግሎት ልዩ ልዩ ተቋማትን እንመልከት

1.   በሕዝብ ደኅንነት ስም የተዋቀረው የወያኔ መረጃና ስለላ ድርጅት፤

2.   በናዚ ጀርመን ጌስታፖ አምሳያ የተደራጀው የፖሊስ /አጋዚ፤ፊዲራል...// ድርጅት
3.   ወያኔ የጻፋቸውን የመጨቆኛና የመቅጫ ህጎችን እየተረጎሙ የሚበይኑ "ዳኛች" የወያኔ ጠበቆችና "አቃቢ- ህጎች"
4.   ለምርመራና ማሰቃያ የተሰናዱ ዘመናዊ መሳሪያዎችና የስቃይ እስር ቢቶች......
  1. የሕዝብን አመፅ ለመቋቋምና ለማፈን ሲባል የሠለጠነ፤ የተደራጀና የታጠቀ ሠራዊትና ልዩ ምሥጢራዊ አፋኝ ቡድኖች፤
  2. ፕሮፓጋንዳቸውን የሚያዘንቡበት መገናኛ ብዙሃንና የኅትመት አገልግሎቶችን የሚጠቀሙባቸው ተቋማት ሁሉ፤
  3. ኤሌክትሮኒክስ ሰርቬላንስ ወይም ክትትል-ጠለፋ (የስልክ፤ የኮምፒውተር፤ የሴል ፎን መገናኛንና ራዲዮ ጠለፋ፤ ወዘተ.)
  4. በኅብረትስቡ ውስጥ ተሰግስጎ በመግባትና በብዛት ሰርስረው በስውር የተቀመጡ ሰላዮችና ወሬ አቀባዮች፤ ለነኝህ ሁሉ ማንቀሳቀሻ የሚሆነው ገንዘብ፤ ምን ያህል እንደሚሆን ትክክለኛውን አሃዝ በዕርግጠኝነት ቀርቶ በግምት እንኳን ቢሆን ለመናገር የሚችል አይኖርም። ምክንያቱም፤ ባጃቱ ወይም ወጪው በብርቱ ምሥጢር ስለሚያዝ ነው።

ያም ሆኖ፤ በበርካታ መቶዎች ሚሊዮን ብር እንደሚሆን፤ የምሁር ግምቶች አሉ። ይህ ሁሉ የሀገር ሀብት የሚፈሰው ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ታጥቆ ለተነሳ ዘረኛ ሥርዓት መጠበቂያ መሆኑ ታሪክ በሀገራችን ላይ በሚያሳየው ምፀት ላይ እንገረማለን።

ይህንን ሁኔታ ባጭሩ ለመገንዘብ ከቻልን፤ ምን መደረግ አለበት ? በሚለው ላይ ትኩረት ሊደረግበት ይገባል እንላለን። በበኩላችን የሚከተሉት ነጥቦች ቅድሚያና ትኩረት እንዲያገኙ ለሕዝብ እናሳስባለን። ለተቃዋሚ ኃይላትም ጥሪ እናስተላልፋለን

1.    የወያኔን የስለላ መረቦችን ለመከታተልና ለመበጣጠስ፦

. በመሀከላችን ሰርስረውና አድፍጠው የሚገኙትን ሰላዮቹ ማጋለጥና መንጥሮ ማውጣት፤
. በሁሉም የኅበረተስብ ውስጥ በተለያዩ ሽፋኖች ተመድበው የመረጃ ሥራ የሚሰሩትን ጠንቅቆ ማውቅና መለየት፤ እነኝህ ግለሰቦች ከየትኛውም ጎሳና ሙያ የተውጣጡ እንደሚሆኑ መረዳትና፤ ወያኔንን ከልብ ሊደግፉ ባይችሉም፤ ለጥቅም ብቻ ሲሉ ሀገርን ለመጉዳት እንደሚችሉ አለመዝንጋት፤

2.   የተቃዋሚ ክፍሎች ከወያኔ ሰላዮች ነጻ ያልሆኑ መሆናቸውን አውቀው አስፈላጊዉን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል። የጓዳ ምሥጢር የሚያቀብሉ ውስጥ- አዋቂዎች የሚያስከትሉት ከባድ ጉዳት መሆኑን መረዳት እንዝኅላል ከመሆንያድናል።

3.   ከወያኔ ጉዳትና ጥቃት፤ የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ወይም የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪ ወይም የሃይማኖት ተቋማት ወዘተርፈ ይጮሁልናል ብሎ ማሰብ ከንቱ ምኞት መሆኑን ተረድቶ ራስን ጠብቆና በራስ ኃይል ብቻ ተማምኖ መታገልና ሀገሪቱን ከጥፋት ማዳን። ሰሞኑን ወያኔ፤ በአንድ ስደተኛ ታጋይ ላይ የወሰደውን ድንበር -ዘለል ውንብድና ያጢኗል።

4.   የሕዝብን የተባበረ የአመፅ ትግል የትኛውም የስለላና ድርጅትና የመረጃ ስምሪት እንደማያቆም መረዳት ይገባል።

ይህንን ሀቅ አውቆ ተባብሮ መታገልና ሀገርንም ከጥፋት ማዳን አማራጭ የለውም! አሁን በሚታየው ዝርክርክነት፤ ሀገሪቱን ማዳን ይቅርና፤ ራስንም መከላከል አልተቻለም። ይህ ጥቃትና ጉዳት በየአንዳንዱ ቤት እያንኳኳ መምጣቱን የስሞኑ ድርጊት ተጨማሪ የማስጠንቀቂያ ደወል ሆኗል

" ያልጠረጠረ ተመነጠረ " ነውና፤ ሰላዮችን እየጠረጠሩ፤
ጠላትን እየመነጠሩ መታገል ለድል ያበቃል !


 ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኖራለች !

Saturday, July 12, 2014

Ethiopia: Young bloggers jailed for over two months without charge

Six members of blogging group Zone 9 and three other journalists could face terrorism charges in one of the world's deadliest countries for journalists

 “We blog because we care!” This is the slogan and rallying cry of Zone 9, a group of young Ethiopians writing about social and political issues in their country. For over two months however, blogging has been out of the question for most of them. In late April, six members of the group – which takes its name from an area of Addis Ababa’s notorious Kaliti prison, where several journalists are jailed – were arrested and have been detained since.

Befeqadu Hailu, Abel Wabela, Atnaf Berahane, Natnael Feleke, Mahlet Fantahun, Zelalem Kibret – all between the age of 25 and 32 – have been accused of “working with foreign organisations” and “receiving finance to incite public violence through social media”, but have yet to be formally charged. Journalists Edom Kassaye, Tesfalem Weldeyes and Asemamaw Hailegiorgis were also arrested for their alleged links to Zone 9. 

The story of the case so far, as covered by the blog Justice Matters, makes for worrying reading. The group were initially taken to Maekelawi detention centre, where according to Human Rights Watch, political prisoners have been tortured. They have been prevented from communicating with lawyers and family members. Hearings have predominantly served to extend the police’s investigation period. Police have also appeared to move away from accusing them of conspiring with foreign organisations and towards a terrorism charge, under which other journalists have been sentenced.

Zone 9 have been active since May 2012 and this is not the first time the group has attracted the attention of the authorities. According to their Facebook page, their mission is to provide an “alternative independent narration of the socio-political conditions in Ethiopia and thereby foster public discourse that will result in emergence of ideas for the betterment of the Nation”. They have organised online campaigns, including #EthiopianDream, encouraging their fellow citizens to share messages “question[ing] themselves and discuss[ing] their dream for the country”.

Their work has proved unpopular with the government of Prime Minister Hailemariam Desalegn, who came to power following the death of long-time leader Meles Zenawi in 2012. The country’s leadership has continuously come under international criticism for its abysmal record on free expression and other human rights.

The majority of media is state-controlled or sympathetic to the government, with critical news outlets and journalists routinely targeted. Ethiopia is the world’s third worst jailer of the press, according to the Committee to Protect Journalists. The sweeping anti-terrorism legislation put in place in 2009 is often utilised to crack down on oppositional voices. Journalist Eskinder Nega publicly questioned the law and its implementation, only to be convicted to 18 years in prison under it in 2012.

Beyond crackdowns on press freedom, the country’s Muslim community has been hounded by the government, opposition protests are regularly banned, and foreign NGOs are not allowed to work on political and human rights issues.

Zone 9 was set up against this backdrop, and the group soon discovered the, too, were seen as a threat. The blog has been blocked and members have faced harassed at the hands of security services. Last September they took what would end up being a seven-month hiatus from publishing, due to the pressures connected to running the site. The six were arrested only days after announcing that they were to resume blogging.

Despite the fact that internet penetration in Ethiopia currently stands at around 1 per cent, authorities seems very aware of the web’s potential as a platform for free expression and, in turn, dissent. Paul Brown of BBC Monitoring believes the Zone 9 arrests “suggest that the government is taking online activism seriously – probably because elections are due next year.” There have even been reports of the government “training” internet users to post attacks on those who criticise authorities online and to post messages of support for the regime.

Zone 9 co-founder Endalkachew H/Michael recently spoke to CPJ from New York; he left Ethiopia to study in the US shortly before his colleagues were arrested. He says the government are trying to control the flow of information. “There is no plurality of voices in government and media. And they want to control that because there is a sort of plurality on the internet. If you go into the Ethiopian social media sphere, you see all kinds of comments about the government and opposition groups,” he explains.

The government, meanwhile, has denied any wrongdoing, saying the arrests are not connected to journalism but “serious criminal activity”.

“We don’t crack down on journalism or freedom of speech. But if someone tries to use his or her profession to engage in criminal activities, then there is a distinction there,” Getachew Reda, an adviser to the prime minister told Reuters

But the story has drawn widespread condemnation, from international human rights organisations to news outlets to diplomats, with even US Secretary of State John Kerry calling it a “serious issue”. The hash tag #FreeZone9Bloggers has in the past few weeks accumulated outrage and solidarity from across the world. Endalkachew H/Michael says this attention in important. “I want the public to remain focused on this issue. The government is trying to make the public forget the human rights violations and journalists’ poor situation in Ethiopia.”


Source: indexoncensorship


Monday, July 7, 2014

Ethiopia: Fears for Safety of Returned Opposition Leader

Yemen Unlawfully Deported Andargachew Tsige, Concerns over Possible Mistreatment

JULY 7, 2014

 We are deeply concerned for Andargachew Tsige’s safety. Ethiopia needs to demonstrate that it is holding Andargachew in accordance with its international obligations, and he should be allowed immediate access to a lawyer, his family, and to British consular officials.

Leslie Lefkow, deputy Africa director
(London) – An exiled Ethiopian opposition leader unlawfully deported by Yemen back to Ethiopia is at risk of mistreatment including torture. Andargachew Tsige is secretary-general of Ginbot 7, a banned Ethiopian opposition organization, and was convicted and sentenced to death in absentia in separate trials in Ethiopia in 2009 and 2012.

The current whereabouts of Andargachew, a British national, is unknown, raising concerns for his safety. The Ethiopian government should take all necessary steps to ensure Andargachew’s safety and his right to a fair trial. Many individuals arrested in politically related cases in Ethiopia are detained in Addis Ababa’s Maekelawi prison. In an October 2013 report, Human Rights Watch documented the use of torture by authorities against detainees in Maekelawi, including members of opposition political parties and organizations, as well as journalists.

“We are deeply concerned for Andargachew Tsige’s safety,” said Leslie Lefkow, deputy Africa director. “Ethiopia needs to demonstrate that it is holding Andargachew in accordance with its international obligations, and he should be allowed immediate access to a lawyer, his family, and to British consular officials.”

Yemeni officials arrested Andargachew at El Rahaba Airport in Sanaa, Yemen, on June 23 or 24, 2014, while he was in transit on a flight from Dubai to Eritrea. They did not permit him consular access to UK embassy officials and summarily deported him to Ethiopia, credible sources told Human Rights Watch, despite his being at risk of mistreatment.

Yemeni authorities initially denied any knowledge of Andargachew’s detention and transfer to Ethiopia. Ethiopian government officials publicly called for his extradition from Yemen on July 3.

Under the Convention against Torture, which Yemen ratified in 1991, a government may not “expel, return (‘refouler’) or extradite a person to another State where there are substantial grounds for believing that he would be in danger of being subjected to torture.” These protections override any extradition treaty or other security arrangement that may exist between Yemen and Ethiopia.

Trials in absentia generally violate the defendant’s right to present an adequate defense, concerns heightened in cases involving the death penalty.

“Yemen blatantly violated its international legal obligations by deporting someone to Ethiopia who not only is at serious risk of torture, but also faces the death sentence after being tried in absentia,” Lefkow said.

Ginbot 7, of which Andargachew is a founding member, was established in the aftermath of Ethiopia’s controversial May 2005 national elections. The Ethiopian government banned Ginbot 7, which has advocated the armed overthrow of the Ethiopian government, and officially considers it to be a terrorist organization.

The government has prosecuted Ginbot 7 members and leaders in trials that did not meet international fair trial standards. In November 2009, a court convicted Andargachew and 39 others under the criminal code on terrorism-related charges. Andargachew, who was tried in absentia, was sentenced to death. In June 2012, he was convicted again in absentia, this time under the abusive 2009 anti-terrorism law, along with 23 journalists, activists, and opposition members. Again, he was sentenced to death.

Human Rights Watch has repeatedly criticized provisions in Ethiopia’s anti-terrorism law that violate due process rights guaranteed under Ethiopian and international law. At least 34 people, including 11 journalists and four Ginbot 7 leaders, are known to have been sentenced under the law since late 2011 in what appeared to be politically motivated trials; the real number is likely much higher. Suspects held under the law may be detained for up to four months without charge, among the longest periods under anti-terrorism legislation worldwide.

Ethiopian courts have shown little independence from the government in politically sensitive cases. Defendants have regularly been denied access to legal counsel during pretrial detention, and complaints from defendants of mistreatment and torture have not been appropriately investigated or addressed – even when defendants have complained in court.

The Ethiopian government routinely denies that torture and mistreatment occurs in detention. It restricts access to prisons for international observers, monitors, and consular officials, making it difficult to monitor the number and treatment of prisoners. In several cases documented by Human Rights Watch, Ethiopian security officials have arrested foreign nationals, denied knowledge of their whereabouts, and delayed access for consular officials for long periods.

In 2007 Human Rights Watch documented the forced transfer of scores of men, women, and children from Somalia and Kenya to Ethiopia. One of the men, Bashir Makhtal, a Canadian citizen of Ethiopian origin who was accused of membership of the Ogaden National Liberation Front (ONLF), a banned armed movement in Ethiopia, was denied consular access for 18 months. Meanwhile in 2010 and again in 2012, refugees registered with the United Nations High Commissioner for Refugees in Kenya were unlawfully returned to Ethiopia and told Human Rights Watch that they were subsequently tortured in detention. In all of these cases, the individuals were accused of belonging to groups that the Ethiopian government has designated as terrorist groups.

“Given its appalling track record of mistreating members and perceived supporters of banned groups, Ethiopia should know that the world will be watching how it treats Andargachew Tsige,” Lefkow said.