Saturday, November 15, 2014

ዘርፎ አዘራፊ ስርአት


ዘርፎ አዘራፊ ስርአት 


ክፍል

ልማት (Development)፣ እድገት (Growth)


እደሚታወቀው፤ ልማታዊና (Development) እድገታዊ (Growth) የሚባሉ ሰነ-ቃላት፤ ከረጅም ዘመናት ጀምሮ በምዕራቡ ስነ-ትምህረት (Social Sciences)   አላግባብ ተጠልፈው፤ ሌላ ርዮታዊ ትርጉም እዲኖራቸው ከመደረጉ በፊት፤ ቀድም ሲል በሰነ-ህይወት (Biological Sciences) የነበራቸውን ቅድመ ስነ-ቃላዊ ትርጉም፤ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት መጀመሪያ በምእራቡ የስነ-ትምህርት ልሂቃኖች ተጠልፎ፤ ለርዮተዓለም ማስፋፊያ መሣሪያነት እዲያገለግል አዲስ መሰረተ አሳብን እዲያንጸባርግ ተደረጎ አዲስ የስነ-ትምህረት ትርጉም እዲኖራቸው ታስቦ በአዲስ ተቀንቅነው እዲፈጠሩ ተደረጓል። ከዚህም ጋር ተያያዥ በማድረግ ሰነ-ቃላቱ በሰነ-ህይወት ሳይንስ (Biological Sciences) ያላቸውን መደበኛና ትክክለኛ ትርጉም በዝርዝር መዳሰሱ አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን፤ በስነ-ቃላቱ ዙሪያ ያሉትን ርዮተዓለም አዘል የሆኑ፤ መሰረተ ሃሳባት ከዬት እደፈለቁ፤ በምን እሳቤ ሊፈልቁ እደቻሉ፤ በአጽንዎ መርምሮ ማየቱ  ምን ያህል ሳይነስ እደ ሀይማኖታዊ ዶግማና፣ ቀኖ አምሎካዊ እየሆነ እየተቀነቀነ አየተደረሰ እዳለ በአንክሮ መርምረን እደንረዳ ይረዳናል። በምዕራቡ የስነ-ትምህረት (Social Sciences) ልሂቃን ሰነ-ህይወታዊ የሆነ ስነ-ቃል አይገባበት ገብቶ፤ ተጠልፎ፤ በምዕራቡ ርዮት ተለውሶ ሌላ ትርጉም አዘል ሆኖ፤ በስነ-ትምህርት  ተቃባይነትን አግኝቶ፤ ለሰሜን አሜሪካ፣ ለአውሮፓና ኤዝያ፣ የአጋብሶ አደር (CAPITALIST) ኢኮኖሚ ኅልዮ መገለጫ በመሆን እያገለገሉ እደሚገኙ፤ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህም፤ በተለይም የምዕራቡና የምሥራቁ ርዮተዓለም ግብ ግብ ትንቅንቅ በተጀመረበት ዘመን፤ ልማተዊ የሚለው ስነ-ቃል ኢኮኖሚያዊ አዘል ብቻ በመሆን ሳይገታ፤ ፖለቲካዊ፣ መሐበራዊና ስነ-ልቦናዊ በመሆን፤ የሕብረተሰብ ለውጥ አቅጣጫ አመላካች ሂደት ሆኖ በኅልዮ ለመጀመሪያ ተደርሷል።

ልማታዊ የሚለው ስነ-ቃለ ኅልዮ መሰረቱ የቀዝቃዛው ጦርነት በመሆኑ፤ የተፈጠረበትመ አላማ፤ በስልጣኔ ወደኋላ የቀሩ የሶስተኛው ዓለም ተብየውን አገራት ስለጡን ለመሆን አውሮፓና አሜሪካ የደረሱበት ሕብረተሰብ ደረጃ መድረስ አለባቸው፤ ይህም የሚሆነው አነድና አነድ በሆነ መንገድ ብቻ እደሆነ ያደረገ፤ የለውጡንም መንገድ የአጋብሶ አደር ስርአተ መንገድን በመከተል ብቻ እደሆነ አስገዳጅና አይቀሬ በምንም መንገድ ሌላ አማራጭ መንገድ እደሌለ አስመስሎ፤ የለውጥ መንገድን አጥሮ አሳጥሮ፤ ከፍተኛው የለውጥ ደረጃም አሜሪካና አውሮፓ  የደረሱበት የለውጥ ደረጃ ያደረገ የመጨረሻውም የሰው ልጆች የሕብረተስብም ደረጃ የአጋብሶ አደር ስርአት ብቻ አድራጊ፤  የተሰኙ፤ መሰረተ አሳባትን በርዮተዓለማዊ መርሆች  ተቀንብቦ ተሰርቶ፤  የእጅ አዙር ቅኝ ገዥ ተስፋፊ ስርአትን ለመጥቀም  ሲባል  አደሆነ ይታወቃል።
ልማታዊም ሆነ እድገታዊ የተሰኙት ርዮት አዘል ኅልዮ ሆነው ተቀንቅነው ሊፈጠሩ የቻሉበት ምክንያቶች ሲመረመር 

1)   .. 1950 ጀምሮ አያሌ የሆኑ የአፍሪካም፣ የላቲን አሜሪካና፣ የኤዝያ አገሮች ከቀድሞ የአውሮፓ የአሜሪካና የጃፓን የቅኝ ገዥዎች ነፃ መሆኑ፣

2)   ነፃ የሆነትም የአፍሪካ፣ የላቲን አሜሪካና የኤዝያን አገራትም በቅኝ ገዥ ስርአት በነበሩበት ዘመን የደረሰባቸውን ግፍ፣ ጭቆና፣ ሰቆቃ፣ ብዝበዛና የተፈጥሮ ሃብት ዝርፊያን በነማን እደተፈጸሙ ጠንቅቀው በማወቅ፤

3)   እነዲሁም እነዚህ የአፍሪካ፣ የላቲን አሜሪካና፣ የኤዝያ አገራት ከቅኝ ገዥ ስርአት መዳፍ ውሰጥም ለመላቀቅ ባደረጉት የነፃነት ትግል አጋር የሆኗቸውና ለነፃነት ትግላቸው ፍጹም ድጋፍን የሰጧቸው  የሶሻሊስት ስፍር ተብየው አገሮች በመሆኑ፤

4)   ለነዚህም አገራት የሕብረተሰብ ለውጥ ሽግግር  የአጋብሶ አደር የሕብረተሰብ ደረጃን ሳያልፉ (NON-CAPITALIST PATH) (J. Slovo, in Discussion Contributions on: A Critical Appraisal of the Non-Capitalist Path and the National Democratic State in Africa, Marxism Today, June 1974. R. Ulanovsky, "Sorne Aspects of the Non Capitaiist Way for Asian and African Countries," World Marxist Review, Sept. 1969. . V.I. Lenin, "The Second Congress of the Communist International" Collected Works, Vol 31, p. 244.) በቀጥታ ከፍተኛ ወደሆነው የሶሻሊዝም (Socialism) የሕብረተሰብ ሽግግር መተላለፍ ይቻላል የሚል መሰረተ ሀሳብ በብዙ የሶስተኛው አገራት ተቀባይነት ማግኝት፤

5)   ከቅኝ ገዥዎች እራሳቸውን ነፃ ያደረጉ የአፍሪካ፣ የኤዝያና የላቲን አሜሪካ አገራት ይህን ፀረ-አጋብሶአደር (ANTI- CAPITALIST) መሰረተ ሃሳብ መከተል፤

እደሆኑ መረጃዎች ያሳዩናል።

በመሆኑም፤ ጉዳዩም ያሳሰባት አሜሪካ፤ ከሌሎች አበር የአውሮፓ አገራት ጋር በመተባበር፤ በዓለም ዙረያ ያላትን የበላይነት ተቀባይነት ላለማጣት ስትል፤  የሶስተኛው ዓለም ተብየው አገራት ወደሷ ስፍር የምትመልስበትን፤ መንገድ በመቀዬስ፤  ከላይ እደተጠቀሰው፤ በአጋብሶአደር የእጅ አዙር ቅኝ ገዥ ርዮት ላይ መሰረት ያደረጉ፤ ታሪኩን የረሳ፣ ካባቱ ገዳይ ይተኛል የሚል መርሆ በመከተል፤ ነፃነታቸውን ለተቀዳጁ፤ ለአፍሪካ፣ ለላቲን አሜሪካና፣ ለኤዝያ አገራት በኅልዮት ደረጃ የሚያገልግሉ፤ ኅልዮተ ስንክሳራት ፈብርካ፤ የቀዝቃዛውንም ጦርነት በርዮት ደረጃ በበላይነት ለማሸነፍ በሚል፤ ልማታዊ የተሰኘ ስንክሳር  ከአበር የአውሮፓ አነደኛ አገራት ተብየዎቹ ጋር ደርሳ፤ መጀመሪያ የኢኮኖሚ፤ ከዚያም ቀስ በቀስ በልዩ ልዩ ሰነ-ትምህረት ዘርፎች ሰርስረው እዲገቡ አስደርገው፤ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ በፈጠሯቸው አጋዥ ዓለም አቀፍ  ተቛማትና ድረጅቶች በመረዳት፤ በእጅ አዙር፤ በየጊዜው እየታረሙ፤ በአዳዲስ መሰረተ አሳባት በመደገፍ፤ ተቀንቅነው አዲስ ኅልዮት ሆነው በመፈጠር፤ ሙሉ ለሙሉ ዓለምን በአሜሪካንና በአውሮፓ ቁጥጥር ውሰጥ አስገቢ አጋዥ ዋና መሳሪያ በመሆን እያገለገሉ እደሚገኙ እውን ነው።

ስለሆነም፤ እድገታዊ፣ ልማታዊ የተሰኙ ድረሳነ ስንክሳሮች .. 1950 ጀምሮ በምዕራቡ የስነ-ትምሕረት ተቀባይነት አግኝተው የስነ-ትምሕረትም አካል ሆነው በአዲሱ የእጅ አዙር ቅኝ ገዥ ርዮት (Ideology Of Neocolonialism) ተቀንቅነው  በኅልዮ መልክ ተደርሰው ለመላው ዓለም  ከድህነት መውጫና፤ ወደ ከፍተኛ አውሮፓና አሜሪካ የደረሱበት የለውጥ ደረጃ የሚያደርስ፤ መንገድ በሚል፤ በአዋጅ ታውጀው፡ በመርኅ ደረጃ፤ የኋላ ቀር ድሃ አገራትም ሆኑ ሁለተኛው ዓለም የተሰኙት አገራት አዲገለገሉበት፤ በሚል፤ እነዚህኑ ከላይ የተጠቀሱትን፤ አገራትና፣ ሕዝብ፤ ከቁጥጥራቸው ውስጥ አስገብተው፤ ቀደም ሲል በቅኝ ገዥነት ይበዘብዙ የነበረውን፤ የተፈጥሮና የሰው ሃብት፣ እዲሁም፤ ዘረኝነትን ያማከለ፤ የበላይነትን፤ በቀጣይነት ተንሰራርቶ፤ በነፃ ተብየው፤ ግን እነሱ በበላይነት በሚቆጣጠሩትና፤ በነሱ ሁለንታዊ ቁጥጥር  በተቛቛሙ ዓለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የመሐበራዊ ድረጅቶች ጥላ ስር ቀሪውን ዓለም በእጃቸው አስገብተው፤ በቀጣይም፤ በአሜሪካን የበላይነት የሚመራውን፤ የሰሜን አሜሪካ፣ የአውሮፓና፣ የኤዝያን ፓሲፊክ አገራት ሁለ ገብ ጥቅም በዓለም ዙርያ ለማንገስ እደሆነ እውቅ ነው።

ይህን እኩይ የሆነ ተግባራቸውንም ለመከውን፤ ይረዳቸው ዘነድ፤ የፀረ- አጋብሶ አደር የለውጥ ጎዳና (NON- CAPITALIST PATH) የተሰኘውን፤ ለነፃ የአፍሪካ የኤዝያንና የአፍሪካ አገራት አገልጋይ፤ ይሆናል ተብሎ የታመነበትን፤ የሕብረት የለውጥ መንገድ፤ በዓለም ዙሪያ ተቀባይነት የነበረውን፤ የኅልዮ መሰረተ ንድፈ አሳባትን ጠልፈው፤ የራሳቸው በማደረግ፤ የአጋብሶ አደር የለውጥ መንገዶች (CAPITALIST PATH) የተሰኙ፤ ልማታዊ እድገታዊ በሚል ስም በስነ-ህየውት የሚታወቁ ስነ-ቃላትን ተውሰው፤ በመርሆ ደረጃ፤ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ በስነ-ትምሕረታዊ የተምሮ ማሰተማር፣ የጥናትና ምርምር፤ የመንግስታት ታላላቅ የፖለሲ አረቃቂ ተቛማት፤ አልፎም፤  ዓለም አቀፍ የአውሮፓ የአዝያ_ፓሲፊክና የስሜን አሜሪካን ባላሃበትና (Global finance and Corporate Capital) ዓለም አቀፍ የበላይ ኢኮኖሚ ተቛመ ጥምረት (Multilaterial Institutions of Global Economic Surveillance, G7, IMF, WB, WTO, ...)  አባሪነት፣ ተባባሪነት በመደገፍ፤ እዳዲስ መሰረተ አሳባተ ኅሊናት፤ ከጊዜ ግዜ እየታከለባቸው እደ አዲስ ኅልዮት በመሆን፤ በመላው የሰነ-ትምህረት ዘርፎች በአዲስ ተቀንቅነው፤ ተፈብረከው፤ ተስፋፍተው፤ እዲደረሱ በማድረግ፤ ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም በሚል ተምሳሌት፤ ልማታዊ፣ እደገታዊ በተሰኙ ኅልዮተ ኅሊናተ ርዮት በመረዳት፤ በዓለም ዙረያ በመስፋፋት፤ ዓለምን በአንድ ማእከል ውስጥ አስገብተው፤ በሳይንሳዊ አነባገነንት ለመግዛት እየተንቀሳቀሱ እደሚገኙ  በአጽነፆ ጎሌ ሆኖ ይታያል።


ልማት እድገት የተሰኙት ስነ-ህይወታዊ  ስነ ቃላትም፤  የስነ-ኢኮኖሚ ዘርፍ አገልጋይ በመሆን፤ በተለይም በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት፤ እነዲሁ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ፤ ላድጉ ተብየዎቹ፤ ለሰሜን አሜሪካ፣ ለአውሮፓና፣ ለኤዝያን ፓሲፊክ አገራት ግልጋሎት ሰጭ እደነበሩም፤ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላም፤ በአያሌ የኢኮኖሜትሪክ ሞዴሎች በመታገዝ፣ የአዲሱን የእጅ አዙር ቅኝ ገዥ ተስፋፊ ርዮትን (Ideology Of Neocolonialism) አገልጋይ፤ ቁልፍ የሆነ ሚና እየተጫወቱና፤ ግልጋሎት እያበረከቱ እዳሉ እውቅ ነው።

በሰነ-ህይወታዊ (Biological Sciences) ልማት፣ እደገት ሲቀኝ

ልማት እድገት የሚባሉት ሁለት ስነ-ቃላት መሰረታቸው ከስነ- ሕይወት ሳይንስ የተገኙ መሆናቸው ይታወቃል። በአገራችንም የሚገኘው ሰፊው ሕዝባችን አርሶ አደሩ፣ አርብቶ አደሩ፣ ሆነ ቀሪው የሕብረተሰብ ክፍል እነዚህ ሰነ ቃላት የሰው ልጅ ከተፈጠረበት ዘመን አንሰቶ፤ በእራሱ በቤተሰቦቹና በአካባቢው ተከሰተው የሚታዩ ባህሪ ተፈጥሮ እደሆነ ጠንቅቆ ያውቃል። ስለዚሕ እነዚህ ሰነ-ቃላት የሰውን ልጅ ዘአካልም ወይንም ስነ-ግብርአካለዊ መዋቅረ ቅርጽ፣ ልኩት ተጓዥ ለውጥንም ሆነ ክስተተ ባህሪ ለውጥን አመላኮች እደሆነ፤ በየትኛው የዓልም ዙሪያ የሚኖር ሰው በአንክሮ የሰነ-ህይወት ትምህረት ያልተማረም ቢሆን፤ አካባቢውን በአንክሮ መርምሮ የሚያውቀው፤ የሚረዳው መሰረተ የእውቀት ግኝት ውጤት ነው። በተፍጥሮዋዊ ሂደትም በሰው ልጅ ምድራዊ የሕይወት ዘመን፤ ከሕፃንነት እሰከ ጉምረታዊነት፤ ዘአካለዊና ስነ-ባህሪያዊ (ሕፃንነት፤ጉምረታዊነት) ተጓዥ ለውጥ ስነ-ትርጓሚ፤ በለት ተለት ሕይወታቸን ተከሰተው የምናያቸው ተፈትሮዋዊ ሂደቶች ናቸው። አነዚሁ ሰነ-ቃላት በምዕራቡ በስነ-ህይወት ሳይንስ ደግሞ ሲዳሰሱ ያላቸው ስነ-ቃላዊ የትርጉም ልዩነትም ሆነ ግነኙነት/ድርግራጎት እደሚከተለው ይገለጻል። ሆኖም የቃላቱንም ትርጉም ባባቶች ተምሳሌታዊ ገለጻ፤ አሣን መብላት በብልሃት፤ የፈረንጅን እውቀት፤   በጥንቃቄ፤ በብስለት አነደሚሉ በአንክሮ መርምሮ ስንዴውን ከገለባው እየለየን ማየት ግድ ይሏል።

እድገት (Growth)  በስነ-ህይወታዊ ያለው ትርጉም


እድገት የሚለው ስነ ቃል በስነ-ህይወት ሲተረጎም አካላዊ ወይንም ስነ-ግብራካላዊ መዋቅረ ቅርጽ፣ ልኩት ተጓዥ ለውጥን አመልካች የሚል ፍች ሲኖረው። እድገት የሚለውም ቃል አካለዊ ሆነ ሰነ ገብራካላዊ ከሕፃንነት እሰከ ጉምረታዊነት የሚታዬ ተጓዥ ለውጠ ክስተትን አመላካች በመሆን ይጠቀሳል።

እደምሳሌነትም ማንኛውም የዘአካል ክብደት ወይንም ቁመት መጨመር እድገት ይባላል። በመሆኑም እድገት ከውልደት አሰከ ጉልምስና እድሜ የሚቆይ ህይዋታዊ ተጓዥ ክስተት ነው።  

እደሚታወቀው ሕፃናት ከተወለዱ በሗላ ምግብ ያስፈልጋቸዋል። የሚመገቡትም ምግብ ሰውነት ይሆናቸዋል። በዚህ ወቅት አዲስ ህዋስ ይፈጠራሉ፤ የህፃናቱንም አካለዊ እዲጎለብት ምክንያት ይሆናሉ። ይሄ አከላዊ ጎልበታ እደገት ይባላል።     

የልማት ስነ-ህይወታዊ ተኮር ትረጉም (Development)

ልማተዊ የሚለው ቃል ሲተረጎም የዘአካል ቅረጻዊ፤ ልኩታዊ ተጓዥ ለውጥን ከሕፃንነት አሰከ ጉምርታዊነት ወቅት ተከስተው የነበሩ በሕፃንነት የነበሩ  የዘተ ባህሪ ወደ ጉምርታዊ ክስተ ባህሪ አደተሸጋገሩ፤ ጉምረታዊም በመሆን አደሚያገለግሉ የሚል ትረጉም ይይዛል። በመሆኑም ልማታዊ የሚለውም ቃል ልኩታዊ ብቻ ሳይሆን ጉልበታዊ የዘአካላት (Organs) ለውጥንም ያካትታል።  
 
በመሆኑም በአነድ ግለሰብ የተለያዩ ዘአካላት አማካኝነት የሚከናወኑ ስነ-ልቦናዊ ለውጦች እድገት በመባል ይጠራሉ። ለምሳሌም ያሕል አነድ ህፃን በመጀመሪያ እጆቹን ተይዞ፤ አቱ ሥግራ፣ ተቱ ሥግራ አልያም ዳዴ ዳዴ እየተባለ ይሄዳል ቀስ በቀስም የሰውነቱ አጥነቶችና ጡንቻዎች አድገው ሲጠነክሩ በዳዴ መሄዱን አቁሞ፤ መጀመሪያ በሁለት እግሩ መቆም ከዚያም በሁለት እግሩ መራመድን ይጀምራል። እነገዲህ በአጭሩ እድገት ማለት በዳዴ መሄድ፤ መቆምና፤ ከዚያም በሁለት እግር መራመድ ማለት ነው።

በስነ-ህይወት ሳይነስ  የልማትና፤ የእድገት ልዩነት


እደሚታወቀው ብዙ ሰዎች ልማትና እድገት ሕብረ ቃል አድርገው አነድ አይነት ትረጓሜ ይሰጧቸዋል። ግን ሁለቱም ለየቅል የሆኑ ትረጓሜ ያላቸው ስነ-ቃል በመሆን ይታወቃሉ። የመጀመሪያው ስነ-ቃለ እደገት የሚለው ሲሆን አካላዊ ወይንም ስነ-ግብረአካላዊ የመዋቅር ለውጥ የሚል ትርጓሜ ሲኖረው፤ ሁለተኛው ሰነቃል እድገታዊ የሚል ሲሆን፤ የዘአካላት ገቢራዊ ስርአተ ለውጥ በሚል ይተረጎማል። በመሆኑም ልማታዊ ሆነ እድገታዊ (አካለዊ ለውጥ) ስነልቦናዊ ለውጥን አስተናጋጅ በመሆን ይለያያሉ።

በተመሳሳይነትም ሲታዩ ልማት ታይታዊ ባህሪን የተላበሰ፤  በግለሰብ አካላዊ ላይ ተኮር ያደረገ ለውጥ ያማከለ በመሆኑ፤ በቀጥታ መለካት ይችላል። ልማት በተወሰነ ደረጃ የሚያመክንና የሚቆም ሂደት ነው። ልማት ዘላለማዊ የሆነ ክስተት አይደለም። እድገት ግን ውስጣዊ ተፈጥሮ ያለው በመሆን ይገለጻል። በመሆኑም በምንም መለኪያ በቀጥታ ሊለካ አይችልም። ግን ሊመክንና ሊቆም ይችላል። ዋናው የእድገት ትኩረትም የአእምሮን መጠን ማስፋት ብቻ ሳይሆን የአስተሳሰብን ሂደትን ጉልበታን ያካትታል። 

ከሁሉም በላይ ልማት ብዛታዊ ተፈጥሮ የተሰኘ ባሕሪያ ሲኖረው፣ እድገት ግን አእምሮትና ውስጣዊ ባሕሪ የተሰኙትን ባሕሪያትን ይዞ ይገኛል። ልማት ጃጅተው ሲያረጁ፤ እደገት ደግሞ በጉምርታዊነት ወቅት ያሚያከተሙ ክስተቶች ናቸው። ልማት ባህሪያዊ ወይንም ጠባያዊ ለውጦችን አመላካች ሲሆን፤ ከዚህም በላይ እደገትና ልማት ተወራራሽና፤ ጥገኛ በመሆናቸው፤ አነዱ ሌላው ላይ ተጽእኖዊ ለውጥን ያስከትላል። በመሆኑም አነዱ ሌላው ላይ ተጽእኖ በመፍጠር አዲለወጥ ያደርጋል። የእድገት በበሽታ ምክንያት መቆም፤ ወይንም ያለግዜው መተጓጎል፤ እድገትን እደሚጎዳ ሁሉ በእኩል ደረጃ ልማትንም ይጎዳል።
             

በሰነ-ህይወት አራቱ የልማት ዝንበላ ተብለው የሚታወቁት

1)      አእምሮዊ ልማት (Cognitive Development)
2)      መሐበራዊ ልማት (አካባቢ ተኮር ልማት ) (Social Development)
3)      ውሰጠ ሰሜታዊ ልማት (Emotional Development)
4)      አካላዊ ልማት (Physical Development)  
     
v     አእምሮዊ ልማት የሚለው ስነ-ቃል፤ ተጣቅሶ የሚቀርበው፤ ችግሮችን በአንክሮ መርምሩ አውቆ መፍተሄ የማገኘትን ችሎታ በስርአት ተግባር ላይ የመዋል ክህሎታዊ ዝንበላ ሲሆን፤ ይሄው ስነ-ቃል ሰሜት ተኮር መላምታዊ ምሁራዊ የእድገት ዝንበላ የሚል ትረጓሜን በማግኘት ይዞ ይገኛል።

v     መሐበራዊ ልማት በእርስ በእርስ ተሳትፎ ግነኙነት፣ ድረግራጎት ላይ መሰረት ያደረገ ባህሪ ዝንበላ፣ መሐበራዊ እድገት በሚል ይገለጻል።

v     ሰሜታዊ ልማት ዳሰሳዊና ክህሎታዊ ዝንበላ ሰሜታዊ ልማት በሚል ይገለጻል።



v     አካላዊ ልማት የተደራጀ የምድገት ጭመራ ዝንበላ በሚል ይገለጻል። በታክሎም፣ አከላዊ ልማት በተደራጀ መልኩ አካለዊ እደገት የሚል ትረጉም ይዞ ይገኛል።  

እደገት፣ ልማት በሰነ- ትምህርት (Social Sciences) ያላቸው ትርጓሜ

እድገት፣ ልማት የተሰኙ ሰነ-ህይወት ወለድ ስነ ቃል እንዴት ስነ-ትምህረታዊ እደሆኑና የምዕራቡን የበላይነት መገልገያ ዘረኝነትን አንጋሽ የሆኑትን የፍልስፍና የሳይንስና የስነ-ልቦናዊ መሰረተ አስተምህሮን በመገልገል ሌላ የስነ-ቃለ ትርጓሜ ተሰጥቷቸው በሕልዮ ተቀንቅነው ተደርሰው በስነ-ትምሕረት እውቅናን አዳገኙና፤ በምዕራቡም ልሂቃን እንዴት ዓለም አቀፋዊ እደሆኑ በመረጃ መዳሰሱ፤ አስፈላጊና ግንዛቤን አስጨባጭ ነው። ምንም እነኳ እድገትና ልማት ተወራራሽ ስነ ቃል እደሆኑ ቢታወቅም፤ ዳሰሳውን ልማት በሚለው ስነ-ቃል ላይ ተኮር በማድረግ ይሆናል።                                          
በምዕረቡ የስነ-ትምህረት ተቛማት አውሮፓን አንጋሽ የሆኑ የፍልስፍና (Hegelian Dialectic) የሳይንስና (Social Darwinism) የስነ-ልቦናዊ ( Freudian Social Psychology Theory) መሰረተ አስተምህሮን በመገልገል ልማት የተሰኘውን ከስነ-ሕይወት ሳይንስ ወስደው፤ በሕልዮ ደረጃ በአራተ  ክፍሎች መድበው ያቀርቡታል።


1)   ዘመናዊነት (Modernization)
2)   ጥገኝነት (Dependency)
3)   ዓለምአቀፋዊነት (World-Systems)


4)   ሉላዊነት (Globalization)

ዘመናዊነት (Modernization)


ዘመናዊነት የተሰኘው ኅልዮ በተለይም በምዕራቡ አገራት በስነ-ትምሕረት ዘርፎች ከፍተኛ ቦታ ተሰጥቶት እ.ኤ.አ ከ1950 ጀምሮ ጎሌ ኅልዮ በመሆን ከፍተኛ ቦታን አዲኖሮው ተደርጓል። በአስራ ሰምንተኛውን ምእተ ዓለም በምዕራብ አውሮፓ እሩቡ ዘመናት የፈጀውን ልዩልዩ የብቸኛ ዝረያ እድገትና ልማት ጥናት ከተሰኘው የስነ-ህይወት ሳይነስ፤ መሰረተ ሃሳባት ጋር በውህድ እደተፈጠርም ይታወቃል።  የስነ-ህልዮ ስእላዊ ግለጫነት (Metaphor) በሰነ-ትምህረት ተለውጦ፤ ሕብረተሰብ፤ ፖለቲካ፤ ኢኮኖሚና የኢኮኖሚ ተቛማት እደ ዘአካል ተፈጥሮአዊ ልኩታዊ ተጓዥ ለውጥ እዳላቸው ተደረገው በመቅረብ፤ የሕብረተሰብ የኑሮ እድገት ልማት (Growth, Development) ኢተለዋዋጫዊ  ባለአቅጣጫ፤ ፍጹም ቅርብ መንገድ የሚከተል ሆኖ ተገልጿል። ይህም ወህደት በተጨባጭ መላወን ዓለም ምዕራባዊ ማድረግ እደሆነም፤ ተፈጥሮዋዊ ሂደት ተብዬውም የምዕራብ አውሮፓና የሰሜን አሜሪካ የሽግግርና የልማት ፈለግን የተከተለ፤ እነዚህም አገራት እንዴት አድረገው ሕብረተሰባዊ ሽግግር እዳደረጉና ልማተዊ እደሆኑ በግልባጭ የተቀረው ዓለም የነሱን መንገድ ብቻ በመከተል መጓዝ እዳለበት ሌላም አማራጭ እደሌለው እሳቤን ያደረገ ነው።

ምንም እነኳን፤ ዘመናዊነት የተሰኘው ስነ-ቃል፤ በለት ተለት መገልገያ ቛንቛ ሲገመገም፤ ዘመን ያመጣው፤ ጊዜ ያመጣው የሚል ቀጥተኛ ትረጓሜን እዳለው እውቅ ነው። ዋናው ነገር ግን፤ ዘመን ተለዋዋጭ እደሆነና፤ ዝቅም ሲል፤ በሴኮነድም፣ በደቂቃም፣ በስዓታትም በቀናት፣ በሳምታትም፣ በወራት፣ በዓመታት፣ በክፍለ ዓመታት እደሚለካ ሁሉ፤ ዘመናዊ (ዘመን አመጣሽ/ባእድ አመጣሽ) የተሰኘው ክስተትን አመላካች ስነ-ቃል እደሆነ፤ ከቃሉ የለት ተለት ትረጉም መረዳት ይቻላል። እዲህም ከሆነ የሰውልጅ ተፈጥሮ፤ መደብ አልባ የመጀመሪያ የጋርዮሽ ስነስርአት ፈጥሮ ከነሮበት እሰከ ዘሬው መደባዊ የሕብረተሰብ ስነስርአት ደረጃ ድረስ ተሽጋግሮ፤ ዛሬ ያለበት የአጋብሶ አደር ስነስርአት (Capitalism ) ደርሳል። ከላይ እደተገለጸውም  ዘመናዊነት የተሰኘው የልማት ዘርፈ ኅልዮ የአጋብሶ አደር (Capitalism ) ስርአት የበላይ ያደረገ፤በሞዴልነትም አነድ አቅጣጭን የያዘና፣ የአሜሪካን የልማት ሞድ (Development Pattern in the United States) ቅጅ ግልባጭ በመሆን ቀደም ሲል ይታወቃል።

በሚገርም ሁኔታ፤ የዚሁ ኅልዮ ደራሲ የሆኑት አሜሪካና፣ አውሮፓ የነሱ የዘመናዊነት መንገድ (The Captialist Modernization Path) ብቸኛ ወደር የለሽ አማራጭ የለሽ አድርገው በማቅረብ፤ እነሱ የበላይ ሌላው የበታች እነሱ አቅጣጫ መሪዎች፤ ሌላው ተመሪ ሆኖ፤ በኢ-ሳይንሳዊ፣ ዘረኛና (Raciological Theory/Ethnological Theory)፤ ስነ-ልቦናዊ መርሆችን ያቀፉ ድርሳነ ስንክሳራትን፤   በተሃድሶ ፈብረከው ደረሰው አዲሱ የዘመናዊነት ኅልዮ በሚል እያቀረቡ እደሚገኙም መረጃ ይጠቁማል። (Modernization: Theories and Facts. Author(s): Adam Przeworski and Fernando Limongi. Reviewed work(s):Source: World Politics, Vol. 49, No. 2 (Jan., 1997), pp. 155-183. Published by: Cambridge University Press) ልማታዊ የተሰኘ ኅልዮ የሰው ልጅ የሕብረተሰብ ሽግግር ለውጥ ሂደት ተደረጎ በመታየት፤ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታትም፤ ልማታዊ ኅልዮት በሚል፤ በተምሮ ማሰተማር፣ በጥናትና፣ በምርምር፤ በሳይንስ ስም፤ ኢ-ሳይንሳዊ ድርሰቶች፤ በስን-ትምህረት ተስፋፍው፤ ተቀባይነት እዲኖራቸው በመደረግ፤ እደ ሀይማኖተዊ ቀኖናና ትውፊት ሆነው፤ ከዚህ በታች የሚከተሉትን አራት መሰረተ ሀሳባት ይዘው እዲደረሱ ተደርጓል።

      I.      "ዘመናዊነት ስርአት ያለው (systematic process) ሂደት ነው። ዘመናዊ የሚለወመ ስነቃል አጠቃለይ፤ በምድብ ክፍል የሚታይ እጅ በነጠላ ተልይቶ አይታይም" የሚለው ቀዳሚ መሰረተ አሳብ ሲሆን። የልማት ሰርአትም ከላይ በሰነ-ህይወት ልማተዊ ሂደት እዳየነው ተመሳሳይ ሂደት (systematic process) እደሆነ ግልጽ ነው። ዘመናዊነትን የተሰኘ የስነ-ህይወት ዘርፍ እደሌለ እውቅ ነው። ግን ከላይ እደተገለጸው አነዱ የልማት ዘርፍ እዲሆን ተወስኖ፤ የእጅ አዙር፣ የአዲሱን የእጅ አዙር ቅኝ ገዥ መስፋፋት እዲያግዝ ዘመናዊነት በሚል ስም፤  በኅልዮ ተደረሶ እየተስፋፋ ይገኛል። ዘመናዊ የሚለውም ስነ-ቃል፤ በለት ተለት ቛንቛ ሲተይ፤ ያለው ትርጉም፤ ዘመን አመጣሽ፤ ተስፋፊ፣ አጋብሶ አደር አመጣሽ መሆኑ ቀርቶ፤ ሰነ-ህይወት ነክ የሆነ የልማት ስነ ባህሪያትን ተላብሶ፤  እደ ልማት ሂደት ተቆጥሮ፤  ተመሳሳይ ሂደት (systematic process) አዘል፤ በምድብ ክፍል እጅ በነጠላ ለብቻው ተልይቶ መታየት የሌለበት ክሰተት ባህሪ ያለው በሚል  ቀርቧል (Hermassi, E. "Changing Patterns in Research on the Third World", Annual Review of Sociology 4, 1978, 239-257. )  ዘመናዊነት ተመሳሳይ ሂደት ያለው ክስተት እደሆነም አድረጎ ማቅረቡ ትክክል ባይሆንም፤ ዘመናዊነት የሚለውን፤ እንደው ዝም ብለን፤ በድፍን፤ በስነ-ትምህረት የተሰጠውን ስነ-ቃለዊ መሰረተ አሳብ ሳናምን አምነንበት ብንቀበለውም እነኳ፤ ስተቱን፤ ከቶም መሸፋፈን አይቻለንም። ለዚህም መስረጃ በአሜሪካንም ሆነ በአውሮፓ የተደረጉትንና በቻይናና፣ በጃፓን የተደረጉት የዘመናዊነት ሽግግር ሂደቶች በምን መልካቸው፣ በምንም እሳቤ ተመሳሳይ እዳልሆኑ ምንም አያነጋግርም። ሌላው የሚያስገርመው ሕዝባዊ ሪፓብሊክ ቻይና አሜሪካንና አውሮፓን በጥቂት ዓመታት ግዜ ውስጥ እነሱ ለረጅም መቶ አመታት የፈጀባቸውን የልማታዊ ተብየው ሽግግር ሂደትን አልፋ እነሱንም በልጣ በዓለም በአንደኛ ደረጃ መቀመጧ፤ ከላይ የተጠቀሰው መሰረተ አሳብ ትክክል አለመሆኑን አስረጅ ነው።      

   II.      “ዘመናዊነት ማለትም የሽግግር ሂደት ነው። አነድም ሕብረተሰብ ወደ ዘመናዊነት መሸጋገር ከፈለገ ባህላዊ መዋቅሮችንና ባህላዊ እሴቶችን ፈጽሞ በዘመናዊ እሴቶች መተካት ግድ ነው” የሚለው ሁለተኛውም ስነ-ትምህረት መሰረት ያደረገ የዘመናዊ ኅልዮ መሰረተ አሳብ፤  ዘመናዊነት የሽግግር ሂደት እደሆኑና፤ ወደ ዘመናዊነት በሂደት ሽግግር ውሰጥ ለመግባት፤ የግድ ባህላዊ መዋቅሮችንና፣ ባህላዊ እሴቶችን ፈጽሞ በዘመናዊ እሴቶች ማለትም “በአሜሪካና በአውሮፓ” ባህላዊ መዋቅራት መተካት አለባቸው የሚል ሲሆን። (See Huntington, Op. Cit. Pp. 58-60.) ይህም መሰረተ አሳብ ከላይ እደተጠቀሰወ ጃፓንም ሆነች፤ የሕዝባዊ ሪፓብሊክ ቻይና፤ ሲንጋፖርም ሆነች ደቡብ ኮርያ ባህላዊ መዋቅራትንም ሆነ፤ ባህላዊ እሴታቸውን እደያዙ፤ ወደ ዘመናዊነት መሸጋገራቸው በቂ አስረጅ ነው።


III.      ዘመናዊነት የማይቀር የሽግግር ሂደት በመሆኑ፤ ሰርአትን የተከተለና፤ አሸጋጋሪ አፈጣጠር ያለው በመሆኑ፤ የሕበረተሰብ ሰርአተ ለውጥን ይገነባል የሚለውመ ርዮት ተኮር መሰረተ አሳብ ያው ከላይ እደተገለጸው ከብት ሳይገባ፣ ሌባ በረት ሞላ የሚለውን ተምሳሌትን ያመላክታል።        

 IV.      ዘመናዊነት አብዮታዊ ሳይሆን ዝግምተኛ ረጅም ግዜ የሚፈጅ ሂደት ነው የሚለውም መላምትም ሆነ፤ ከላይ በቁጥረ ከአንድ እሰከ ሶሰት የተዘረዘሩት መሰረተ አሳባት መሰረታቸው የአውሮፓና የአሜሪካን ዝግምተኛ ኅልዮት ተከታይ ልሂቃንን አሻራን የያዙ እደሆነ መረጃ ይጠቁማል። (See Huntington, S. The Change to Change:  Modernization, development and politics.  (New York:  Free Press, 1976), pp. 30-31; 45-52..)   
1)    “ኋላቀር ሕብረተሰብ ያላቸው አገራት ሁሉ፤ ባህላዊ ሕብረተሰብ ናቸው። ይህም በመሆኑ በጎሳ በጎጥ በቤተሰሰበ መሰረተ ግንኙነት ላይ የተመሰረቱ  ተቛማትን አሏቸው። ይሄን ሁኔታ በምዕራቡ ባህል መተካት አለባቸው” የሚል ሲሆን፤ ይህንንም መሰረተ አሳባት በማስፋፋት፤ ሌላው ፔርሶነ የተሰኘው የዘመናዊነት ልሂቅም በማከል “ኋላ በቀሩ ሀገራት (LDCs) ያሉ ባህላዊ ቤተ አምልኮች እደ ቤተ-ሂነዱ፣ እደ ቤተ- እስላምና፤ የመሰሉ አህዳዊ ቤተ-አምልኮችን በሞላ

v    ኢ-ሳይነሳዊና ኢ-ሴኩላር
v    ለመሐበረሰብም ሆነ፤ ከቦታ ቦታ፤ ከሀገር አገር ለመዘዋወር እነቅፋትና
v    ለሕዝብ ብዛት መጨመር ምክነያት አድረጎ በመግለጽ፤  

የምዕራቡ ዓለም ባህላዊ ለውጥ እዲያካሂዱ ድጋፍ በማድረግ፤ የሶስተኛው ዓለም ተብየው አገራት የበላይ ባለስልጣናትን ልጆቻች፤ በምዕራቡ ትምህረት ቤቶችና፣ ዩኒበርሲቲዎች አሰማረቶ ማሰልጠን” እደሚገባ፤

2)    ቅድመ መሰረት፤ ለለውጣዊ መነሳሳት፤
ዘመናዊነት እደ መንኮራኩር አነኮብኩቦ ለመምጠቅ የሚያስችሉ፤ ቁሰ ግብአቶች፤ እደ ካፒታል፣ እደ ቴክኖሎጅ የመሳሰሉትን፤ በመዋለ ፈሰስ ስም፤ ከምዕራቡ አገራትና የንግድ ተቛማት ማግኘት፣ እርዳታንና ስጦታን ከምዕራቡ አገራት መንግስታት ጠይቆ በማግኘት፤ (McClelland, D. Bussiness Drive and National Achievement.  (New York:  Basic Books, 1964), pp. 167-170.) 

3)   ለውጣዊ የመነሳሳት ሂደት፤
ሶስተኛው የዘመናዊነት ደረጃ ባህላዊ የሆኑ ዝንበላወችንና፤ መሐበረሰባዊ ተቛማትን፤ የምዕራቡን ተቛማት ተሰተካካይ በሆነ መተካት ይላል። በእነደዚህ አለ ሁኔታም፤ በጎሳም፤ በጎጥ፤ በቤተሰብም ተሳሰሮ ያለ መሐበረሰብ በምዕራቡ አገራት በተቛቛሙ መሥራቤቶች ሁሉ እየተዘዋወሩ ሥራ ፈለጋ አነድ ቦታ ሳይወሰን፤ እራቅ ወዳለ ሥፍረማ በምሄድ ይንቀሳቀሳል የሚል መሰረተ አሳብን ያሰተጋባል።

4)    ወደ ጉልምታዊነት ማምራትና፤
የተሰኘው የዘመናዊንት ሂደት ደረጃ የተሰመረው፤ ሀገር ውስጥ የተመረቱ ምረቶችን፤ ለምዕራቡ ሀገር ኤክስፖርት በማድረግ በዓለም አቀፍ የንግድ ስርአት መካፈልና፤
 
5)   ከፍተኛ ፈጆታን ተጠቃሚ ሕብረተሰብ፤
ይህም የልማት ለውጥ ደረጃ፤ የሶስተኛው ዓለም ተብየውን ሕብረተሰቡ ሙሉ ከገጠሬነት ወደ ከተሜነት የሚሸጋገርበት፤ የሕዝብም ኑሮ በሁሉም ዘርፍ እደ አሜሪካና፣  እደ አውሮፓ ከፍተኛ የኑሮ ደረጃ እደሚደርሰ የሚል መሰረተ አሳባትን ያንሽራሽራል። 
በቁጥረ አራት የተጠቀሰውን የዘመናዊነት መሰረተ አሳብ በዋናነት አቀንቅኖ  ያወጣው ቢል ሮስቶው (Bill Rostow) የተሰኘው አሜሪካዊው ልሂቅ መሆኑ ይታወቃል። ይህም በቢል ሮስቶ የተቀነቀኑ መሰረተ አሳባትም፤ ተሻሽሎ፤ ታልኮት ፔረሶን ከተባለ የትሀድሶ ማክስ ቬበር ተከታይ በፈጠረው “ስነ-መኅበረሰብ” ኅልዮት፤ (Parsons’ sociological theories) ከተሰኘው የተገኙ፤ የዝግምተኛ ሂደት አመላካች በሚል፤ የአዲሱ የዘመናዊነት ኅልዮ መሰረተ አሳባት በመሆን ከዚህ በታች እደሚከተለው ቀርበዋል።      

በስነ-ታሪክ እድገት፤ልማት የተሰኙ ስነ-ቃላት ሲዳሰሱ


ከታሪክም አንፃር ስንገመግመው ዘመናዊ የተሰኘው ኅልዮት እዲፈጠር ዋና ምክነያቶች ናቸው ተብለው የሚታመንባቸው፤

1)   በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በስተመጨረሻ፤ ጦርነቱን የተቀላቀለችው  አሜሪካ፤ እደ ታላቛ ብርቲናያ፣ ፈረንሳይና ጀርመን በጦርነቱ ምክነያት የነበራት ሶሲዮ-ኢኮኖሚዊ መዋቅርና ሀብት ተንኮታኩቶ፣ ደቆ፤ባለመጥፋቱ፤ በዓለም ደረጃ የመሪነትን ቦታ መቀናጀቷ፤ እነዚህን በጦርነት የደቀቁ አገራት በማረሻል ፕላን የተደገፈ የመልሶ ግነባት ሥራን ድገፋ ማድረጓ፤ (So, A.  Social Change and Development.  (Newbury Park, California:  SAGE, 1991), pp. 17-23. Liz, R. Crecimiento Economico, Empleo y Capacitacion.  (Buenos Aires, Argentina:  PNUD, 1993),pp. 27-32. )

2)   በዘመኑም የነበረው የሶሻሊስት ንቅናቄ መስፋፋት፤ የቀደሞዋም የሶቪዬት ሕብረት አገር በምስራቅ አውሮፓ ብቻ ሳይወሰን፤ በቻይናና በኮርያ ተቀባይነትን አግኝቶ በኤዝያ በመላው የዓለም ዙሪያ መስፋፋት ስጋትና፤

3)   ቀደም ሲሉ በአውሮፓውያን ቅኝ ገዥ ስር ወድቀው የነበሩ የአፍሪካ፤ የአዝያና፤ የላቲን አሜሪካ አገራት ነፃ መሆንና፤ እነዚህም አገራት  የምስራቁን ካንፕ ይቀላቀላሉ አለያም ተራማጅ የሆነ ፖለቲካን በመከተል በዓለም ተከስቶ የነበረውን የቀዝቃዛው ጦርነትን ኃይል ያዛባሉ በሚል ስጋት የገባው በአሜሪካን የበላይነት የሚመራው የምዕራቡ ካምፕ፤ የምስራቁን ርዮት ለማዳከም፤ በሶስተኛ አገራትም ተቀባይነት ይኖራዋል በሚል ኢኮኖሚን አራማጅና፣ ነፃነትን አስጠባቂ ልማታዊ ሞዴል የሚል ሕልዮ ቀንቅነው መድረሳቸው መረጃ ይጠቁማሉ።( Chirot, D.  Social Change in a Peripheral Society:  The creation of a Balkan colony.  (New York:  Academic Press, 1993), pp. 32-34; 56-59. Ramirez, N.  Pobreza y Procesos Sociodemograficos en Republica Dominicana.  (Buenos Aires, Argentina:  PNUD, 1993), pp. 34-42.)


    
ዘመናዊነት የተሰኘው ኅልዮ በተለይም በምዕራቡ አገራት በስነ-ትምሕረት ዘርፎች ከፍተኛ ቦታ ተሰጥቶት እ.ኤ.አ ከ1950 ጀምሮ ጎሌ ኅልዮ በመሆን ከፍተኛ ቦታን እዲኖሮው ተደርጓል። በአስራ ሰምንተኛውን ምእተ ዓለም በምዕራብ አውሮፓ እሩቡ ዘመናት የፈጀውን ልዩልዩ የብቸኛ ዝረያ እድገትና ልማት ጥናት ከተሰኘው የስነ-ህይወት ሳይነስ፤ መሰረተ ሃሳባት ጋር በውህድ አደተፈጠርም ይታወቃል።  የስነ-ህልዮ ስእላዊ ግለጫነት (Metaphor) በሰነ-ትምህረት (Social Sciences) ተለውጦ፤ ሕብረተሰብ፤ ፖለቲካ፤ ኢኮኖሚና የኢኮኖሚ ተቛማት እደ ዘአካል ተፈጥሮአዊ ልኩታዊ ተጓዥ ለውጥ እዳላቸው ተደረገው በመቅረብ፤ የሕብረተሰብ የኑሮ ደረጃ መክሊት፤ እድገት ልማት (Development, Groth) ኢተለዋዋጫዊ ባለአቅጣጫ፤ ለፍጹምነት እጅግ ቅርብ መንገድ የሚከተል ሆኖ ተገልጿል። ይህም ወህደት በተጨባጭ መላወን ዓለም ምዕራባዊ ማድረግ እደሆነም፤ ተፈጥሮዋዊ ሂደት ተብዬውም የምዕራብ አውሮፓና የሰሜን አሜሪካ የሽግግርና የልማት ፈለግን የተከተለ፤ እነዚህም አገራት እንዴት አድረገው ሕብረተሰባዊ ሽግግር አዳደረጉና ልማተዊ እደሆኑ በግልባጭ የተቀረው ዓለም ተቀብሎ፤ የነሱን መንገድ ብቻ በመከተል መጓዝ እዳለበት ሌላም አማራጭ እደሌለው እሳቤን ያደረገ ነው።    
ዘመናዊነትም  በምዕራቡ አንጋሽ የስነ-ትምሕረት ኅልዮ ሲተነተን፤ ሁለንታዊ የአውሮፓና የሰሜን አሜሪካ የፖለቲካ የኢኮኖሚና የመሐበራዊ (ባሕል፤ ታሪክ፣ ሥልጣኔ፣ ወግ፣ ስነስርአት) ፍጹም የበላይነትን ያነገበ፤ የቱም ሕብረተሰብ  በነሱ መክሊት እና እነሱ በሠሩት፤ በፈጠሩት የሳይነሳዊ አንባገነንት ሁለንታዊ ቁጥጥር ውስጥ አሰገቢ፤ ሕልዮ አድሆነ ግልጽ ነው። በፖለቲካም አገላለጽ ይህን እውን ማድረግ ማለትም፤ የነሱን የበላይነት (Eurocentric, Weastern-Centric) ማንገስና፤ እራስን ለጥገኝነት አሳለፎ መሰጠት እደሆነ ይቆጠራል። በተጨማሪም፤ ዘመናዊነት የተሰኘውን ኅልዮ፤ እውን እዲሆን ማድረግ ማለት፤ የሀገረሰብን ማንነት አውድሞ አጥፍቶ፤ አምላክ ባምሳሉ እኛን ሰዎችን እደፈጠረን ሁሉ፤ የተቀረውን ዓለም በአሜሪካና በአውሮፓ አምሳል አርቅቆ ዘመናዊ አድረጎ እደመፍጠር እደሆነ ማለት ነው።ይህም መሰረተ አሳብ ቅዠት እንጅ እወን እዳልሆነ፤ ትላነት በኋላቀርነት በአሜሪካንና በአውሮፓ ተፈረጀው የነበሩ አገራት፤ ዛሬ የአሜሪካንና የአውሮፓ ተፎካካሪ ሆነው መነሳት፤ እደውም በኢኮኖሚም አልፈው በዓለም ደረጃ ቀድዳሚ የመጀመሪያ ስፍራን እደተቀዳጁ፤ የሕዝባዊ ሪፑብሊክ ቻይና    እዲሁም የሌሎች ታዳጊ ተብየው አገራት ታሪክ ምስክር ነው።
ምንም እነኳ አውነታው ከላይ የተጠቀሰው መሆኑ ቢታወቅም፣ እነሱ መሪ እኛ ተመሪ እነሱ ሁሉን አዋቂ አስተማሪ፤ እኛ ደቀመዛሙረት ሆንን፤ ሁሉን መቀበል እዳለብን ተደረጎ፤ ዘመናዊውነት ተግባራዊ የሚሆነው፤

v    በሀገረሰቡ ደረጃ፤ ፀረ-አጋብሶ አደር ፖለቲካዊ ተጽእኖ አላቸው፤ ተብለው የታመነባቸውን፤ ቤተአምልኮዎችን፤ የሀይማኖት ተቛማትንና፤ ሌሎች አገራዊና፣ ሀገረሰባዊ እሴቶችን አጎልባች ተብለው የታመነባቸውን፤ በሕዝብ ተቀባይነት አለቸው ተብለው የሚገመቱትን፤ መሐበራዊ፣ ታሪካዊ፣ ባህላዊ እሴቶችን፣ ገንቢ መሐበራሰባዊ መልካም የሕዝብንና የሀገርን ወጎችን ልምዶችን ስነስርአቶችን ጠባቂ፤ አጠንካሪ ናቸው የተባሉ መሐበራዊ መዋቅሮችን ሲመክኑ፤
v    መንግስትና ቤተ አምልኮን በመለየት ወይንም ሴኩላሪዝም በሚል፤ መንግስት በተዘዋዋሪ በቤተ-አምልኮ መካከል ቅራኔዎችን ለመፍታትና፤ እኩልነትን ለመፍጠር በሚል ሀይማኖታዊ ተቛማትን እርስ በእርሳቸውም ሆኑ በውሰጣቸው በሆነ ባልሆነ ምክንያት እየታመሱ እዲዳከሙ አድረጎ ሲጠፉ፤
v    ሀገረሰብን በአዲሱ የእጅ አዙር ርዮተ ሕልዮት ልዩ ልዩ ተጽእኖዎች ውስጥ አስገብቶ እዲቀበል ማድረግ፤ ማለትም ሀገረሰብን ፍጹም ተገዥ የሚአደረግ የፖለቲካ ስርአት አጠናክሮ አስፋፍቶ ሲጎለበት፤ (See Smelser, N.  Toward a Theory of Modernization.  (New York:  Basic Books, 1964), pp. 276-278.)
ብቻ እደሆነ ያመለክቱናል።

(ይህም ማለት፤ ከአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ፤ አነፃር ሲታይ፤ በአገራችን ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የሚደረጉ፤ ዛሬም እየተደረጉ ያሉ፤ በወያኔ-ህውሐት/ኢሕአድግ እየተፈጸሙ የሚገኙትን በቤተ ክረሰትያን፤ በቤተ አስልምና፤ ወንጀሎች በምን ሽፋን አደተፈጸሙ ዛሬም እየተፈጸሙ እዳሉ፤ በነማን አማካሪነትና እረዳትነት ታጅበው አደተፈጸሙ ዛሬም በመፈጸም እዳሉ አጉልቶ አሳይ ምስክር ነው። ... )

በምዕራቡ ቤተ-ትምሕረ፤ ዘመናዊነት፤ ለነሱ እዲያመችና፤ በእነሱ አምሳል አስመስለው፤ ትንሽ ልጅ እደሚጫወትበት፤ አሻንጉሊት አሳምረው፤ በስነ-ቛንቛ በስነ-ልቦና አርቀው ሰርተው፤ የሶስተኛው ዓለም ተብዬው አገራት፤ ያላቸው አገራዊ እሴቶች ሁሉ፤ በጅምላ በሗላ ቀርነት በመፈረጅ፤ አፍሪካዊ ታሪክ ሁሉ፤ አፈታሪክ አድረገው፤ ገንቢ ባህሉም ሆነ ወግ ስነስርአቱም ሀገረሰብን አሰተቃቃፊ አነድ አደራጊ በመሆኑ፤ አላስፈላጊና እደውም ለለውጥ እንቅፋት ተደርጎ በመታየቱ፤ በእነሱ አስተምሮ ለውጥ የሚፈልግ ሁሉ ሀገራዊ ማንነቱን መካድ እዳለበትና፤ በእነሱ በሰሜን አሜሪካ በአውሮፓና በኤዝያን ፓሲፊክ አምሳል ተቀርጾ መፈጠር እዳለበት፤ ፍረድ ተፈረዷል። በሌላም አነጋገር፤ ዘመናዊነት የተሰኘውን አዝጋሚ የሕብረተሰብ ሽግግር፤ ጠዋት ማታ እደምንደግመው ጸሎት ተቀብለን፤ ተግባር ካላደረግን፤ ዘመናዊት የተሰኘ በማር የተለወሰ መርዝ ከቶም እደማንቀምስ በአንክሮ የልማታዊ ዘርፍ የሆነው ዘመናዊነት የተሰኘው ኅልዮ ያሳስበናል። በእነሱ ግምት፤  እኛ ብቻ ሳንሆን ሶስተኛው ዓለም ተብዬው አገራትም ቢሆኑ ወደ ዘመናዊነት ደረጃ መሸጋገር የሚችሉት፤ እደኛው የሰሜን አሜሪካንና፣ አውሮፓ ቀንቅነው ደርሰው የፈጠሩላቸውን፤ ዘመናዊነት የተሰኘውን፤ የልማት ጎዳና ብቻ በመከተል፤ ብቻ እደሆነ፤ በነሱ ግምት ይህም ሊሆን የሚችለው፤ አውሮፓና የሰሜን አሜሪካን አገሮች የደረሱበት የዘመናዊነት የሕብረተሰብ ደረጃ ለመድረስ አላማችን አድረገን እነሱ በቀየሱልን የልዮ መንገድ መጓዝና መንቀሳቀስ ሰንችል ብቻ እደሆነ በአንድ እጃቸው አሜሌ ጨው በሌላ እጃቸው ደግሞ ጅራፍ ይዘው እደ ሁኔታው እያሰተናገዱ እዳሉ እሙን ነው።

የሰሜን አሜሪካንና፣ የአውሮፓ የዘመናዊነት ደረጃ በልዮ ፍጹም ተደረጎ ተጓዣዊ ሳይሆን፤ ለሰው ልጅ የሕብረተሰብ  ለውጥ ግስጋሴ መክሊታዊ    “as time goes on, they and  we will increasingly resemble one another because the patterns of modernization are such that the more highly modernized societies become, the more they resemble one another”. [6] ህልዮ ሆኖ፤ በመሰረተ ሃሳብነት ደረጃ  በመወሰዱ፤ የሁሉም የሕብረተሰብ የመጨረሻ የለውጥ ግስጋሴ መንገድ አቅጣጫ እሱ ብቻ እደሆነ፤ ዘመናዊ የአጋብሶ አደሩ ሕብረተሰብ (የአነደኛው ዓለም) የለውጥ ግስጋሴ፤ የሰውልጆች የመጨረሻው፤ የሕብረተሰብ ሽግግር መድረሻ አድረገው በማቅረብ፤ ብዙም በሳይንስም ስም በመወሻከት ልያሞኙን ይሞክራሉ። የሌባ ልብ አድረግ መልሶ መላልሶ ልብ ያወለቅ ሆኖም፤ ያጋብሶ አደር ስነስርአት መድሎ አልባ ሆኖ እናንተም ሆናችሁ ሌሎቹ በሂደት እኛ የደረስነበት ልማታዊ ደረጃ ትደርሳላችሁ፤ በዓለም ዙረያ የዘመናዊነት ልዮ የሚከተሉ ሁሉ የለውጥ ግስጋሴያቸው እየጨመሩ ሲሄድ ተመሳሳይነት ወደመሆን ደረጃ ይጠጋሉ፤ እናንተም እዲሁ እደሉ አላችሆ፤ ይሉናል። በአሜሪካና በአውሮፓ ሞድ (Pattern) መሰረት፤ ከፍተኛ የዘመናዊነት ደረጃ የደረሱ የአነደኛው ዓለም አገራት ሕብረተሰብ ከሞላ ጎደል ተመሳሳይነት አደሚኖረወ ልዮው አክሎ ይገልጻል።

ከዚህ በላይ እዳየነው፤ ዘመናዊነት ማለት፤ አውሮፓዊ ወይንም አሜሪካዊ አድረጊ ሂደት አደሆነ፤ በምእራቡ ዓለም የዘመናዊነት ልዮ ድረሳነ ስነጽሁፍም ታጅቦ፤ ለአውሮፓና ለአሜሪካን ርዮት ዓለም የበላይ ገዥነት አንጋሽነት ታስቦ መፈጠሩ ቁልጭ ብሎ ይስተዋላል። ስለዚህም አገራቱ፤ ማለትም፤ አውሮፓና አሜሪካ ተወዳዳሪ የማይገኝላቸው እንከን የሌላቸው የኢኮኖሚ ልማትና፤ ዲሞከሪያሳዊ መረጋጋት ያለባቸው ተደርጎ ለማሳዬት የተሰላ ሙከራ እደሆነም አያነጋግርም። (Tipps: 1976, 14) ከዚህም በተጨማሪ በዘመናዊነት ሕልዮ ስነጸሁፍ ዘመናዊነት የማይቀለበስ የማያቛርጥ ሂደት እደሆነ የገለጻል። በሌላ በኩል ደግሞ፤ አነድ ጊዜ የሶስተኛው ዓለም ተብዬው አገራት ከምዕራቡ ጋር ግንኙነት ከፈጠሩ በምንም መንገድ ዘመናዊ የተሰኘውን የልማት መንገድ አደማይላቀቁና፤ ከዘመናዊነት ጋር ተቆራኝተው አደቆረቡ ባልና ሚስቶች ሳይፋቱ እሰከመጨረሻ ተጋብተው አደሚቀጥሉ፤ በምንም መንገድ ከዘመናዊነት ተጽእኖ ነጻ ሊሆኑ አደማይችሉ የሚል ስነ-ልቦናዊ ስንክሳርም ደብሎ አነዴ ከገቡ መውጫ የለም የተሰኘ የስነ-ልቦና ካራ አነገት ላይ ወድሮ በማስፈራራት ይገልጻል። [7] 

በምዕራቡ የተደረሱ የዘመናዊ ልማት ሕልዮ ድረሳነ ስንክሳር ማለትም ስነጸሁፍ ከላይ በተጠቀሱት መሰረተ ሀሳባት ብቻ ባለመውሰን፤ ዘመናዊነት ተራማጅ በረጅምም ፈጹሞ የማይቀርና አስፈላገ ሂደት እደሆነም ለማሳመን ይሞክራሉ። እዚህም ላይ መገንዘብ ያለብን ዘመናዊነት የሚለው ቃል ከአውሮፓና ከሰሜን አሜሪካ ማንነት ጋር ተያይዞ የሚታይ ነው። ይህም ማለት ዓለምን በሞላ ምዕራባውያን ማድረግ ማለት ነው።    

በአጠቃላይ ዘመናዊነት ቀርፋፋ ብዙ ጊዜን የሚፈጅ ሂደት መሆኑን። ስለሆነም ዝግምተኛ (Evolutionary) እነጅ (Revolutionary) አብዮታዊ ለውጥን አደማያሰገኝ። ለውጥንም ለማግኘት የብዙ ትውልድ እድሜን አለያም አያሌ ምዕተ ዓመታት አደሚፈጅና፤ መሰረታዊ ለውጦችንም ማየት የሚቻለው ከረጅም የጊዜ ሂደት በሗላ እደሆነ ይገለጻል። አበዮታዊ ለውጥ፤ ስር ነቀል ለውጥ መሆኑን ሰለሚታወቅ የሰሜን አሜሪካና የአውሮፓ የዓለም ገዥነት በሰው ልጅ የሕብረተሰብ እድገት ሰር ነቀል ለውጥ አዳያጋጥመውና ተገርስሶም እዳይወድቅ በሌላም መድልኦ አልባ ስርአት እዳይተካ አስብኦት በማድረግ  ዝግምተኛ የተሰኘ ለውጥ ነው ማለቱም ስርአቱ ተቀውሞ እዳይደረሰበትና ተቃዋሚም እዳይኖረው አደሆነ ይታወቃል። ይህም ማለት ስርአቱ እረጅም እደሜ ሰለሚያስፈልገው የሶስተኛው ተብየው ሕዘብና አገራት በባርነትና በጥገኝነት ላይ ወድቀው፤ ጥቂት  የመንግስት አካልት ተብየው ኰሳኩንስ ሃላፊነትት የጎዳላቸው አገር ከሃዲ ሃላፊነት የጎደላቸው ቅጥረኛ ወሮበሎች፤ ከዓለም አቀፍ የፋይናስ ቱጃሮች ቡድኖች ጋር በመመሳጠር፤ በነፃ ንግድ በመዋለፈሰስ ፍሰት፣ ቴክኒዎሎጅን በማሳደግ፤ ለሕዝቡ የጤና አገልግሎት በመስጠት፣ ድህነትን አነዴና ለመጨረሻ ታሪካዊ ለማድረግ፤ የወሊድ እናቶችን ሞት ለማስወገድ፤ የሕጻናትን ሞት ለመቀነስ፣ ብድረ ለማግኘት፣ እርዳታ ለማግኘት ወ.ዘ.ተ በሚል ስም የአገራቱን የተፍጥሮ ሃብት፤ ለም የእረሻ መሬት፣ ወና ዋና የሚባሉ ግልጋሎት መስጨ የኢኮኖሚ ድረጅቶች፣ የቴሌኮሚኒኬሽን፣ የፖስታ፣ የኤሌትሪክ የመንገድና ትራንስፖርት፣ የትምህርተና አገልግሎት መሰጫ፤ ባጠቃላይ አገራቱ ያላቸው ሀብት ተላላፈው ለአሜሪካ፤ ለአወሮፓና ለኤዝያን ፓሲፊክ አገራት ዓለም አቀፍ የቱጃሮች ቡድን ቀስ በቀስ አዝጋሚ በሆነ መንገድ አሳልፎ ሰጥቶ፤ ሕዝብንና አገራቱን በሕዝብ ቅነሳ ስም አጥቶ፤ በአዲስ ዘመን አመጣሽ መደሐኒት የለሽ በሽታ ተበክሎ እዲያልቅ፤ በአገራቱም ለዘመናት በአንድነት አብረው የሚኖሩትን  ሀገረሰብ በቋንቛ ፣ በጎሳ፣ በጎጥ፣ በሃይማኖት ችግር ተፈጥሮ አዲተላለቁ ማድረግ፤ ታሪጋቸውን ባህላቸውን መላውን የአገራቱን ገንቢ ነባር መሐበራዊ እሴቶችን ማጥፋት፣ የአገራቱም ሕዝብ ለነሱ አገልጋይ ባሪያ ሆኖ በሀገሩ ባለቤት ሳይሆን ባእድ ሆኖ አነገቱን ድፈቶ ተቀጥሮ የሚኖርበት፤ ቤተ-አምልኮዎች የማምለኪያ ቤቶቻቸው፤ ምዕመናን የሚያገለገሉበት ሳይሆን፤ሰከሮ ማበጃና ዳነኪራ መምቻ የሚደረጉበት፤ የአምልኮ አባቶች መለኮታዊ መንገድን በመከተል ፈንታ ምድራዊውን ሕይወት ናፋቂ የሆኑበት፤ ... ማለት ነው።     

ከዚህም በዘለለ በአጠቃለይ ዘመናዊነት የተሰኘው የልማት ቲወሪ መሰረተ አሳባት በሙሉ ከአውሮፓና ከአሜሪካን አዝጋሚ ሕልዮ (Evolutionary theory) የተወሰደ መሆኑ ቢገለጽም። [8] እውነቱ ግን ከአዝጋሚ ሕልዮ (Evolutionary theory) ብቻ ሳይሆን ከላይ አደተገለጸው ከሄግል ዲያሌክቲክ ([Hegelian Dialectic: The first step (thesis) is to create a problem. The second step (antithesis) is to generate opposition to the problem (fear, panic and hysteria). The third step (synthesis) is to offer the solution to the problem created by step one: A change which would have been impossible to impose upon the people without the proper psychological conditioning achieved in stages one and two.]) [9] ከፍሮይዳዊንነት ስነልቦናዊ አስተምሕሮና ( Freudian Social Psychology Theory) [10]-[11]፣ ከዳርዊንነታዊነት  (Social Darwinism) [12]-[15] ተዳቅሎ ከተፈጠሩ ሕሊናተ ኅልዮት እደሆነ እሙን ነው። በመሆኑም አነደኛ ልማት አድገት የተሰኙት ስነ-ቃላት አመጣጣቸው ከስነ-ህይወት ሳይንስ አደሆነ ከላይ በዝርዝር ተቀምጠዋል።ልማትም ሆኑ እድገት በመጀመሪያ ደረጃ ያለቦታቸው ገብተው ብዥታን አዲፈጥሩ ሆነ ተብለው ስነ-ልቦናን አጨላሚ፤ የአውሮፓና የሰሜን አሜሪካ የበላይነት ዘረኝነትን መሰረት በማድረግ፤ ተቀንቅነው በሕልዮት ለመደረሳቸው፤ በመጀመሪያ የሕልዮቱ ደራሲዎችን እነማን ናቸው ብሎ መዳሰሱ ግድ ነው። በመረጃ እደሚታወቀው ሕልዮቱን የደረሱት  ሳይኮሎጅስት (Psychologist)፣ ሶሻል ሳይኮሎጂስት (Social Psychologist)፣ የሃይማኖት ሶሲኦሎጂስት (Sociologist of Religion) ፖለቲካል ሶሰሎጅሰት (Political Sociologist) መሆናቸው፤ እነዚህም ልሂቃናት የአጋብሶ አደር ርዮት ደጋፊ መሆናቸውና፤ እነዚህ ልሂቃናት በውነት የሞራል ግዴታ ኖሯቸው አልያም ለሶስተኛው አገራት ለተሰኙት አዝነው እዳልሆነ እውቅ ነው። ምክንያቱም የአጋብሶ አደር ስርአት በትረፍና ኪሳራ ሰሌት፤ ትርፍን ብቻ በመፈለግ  መሰረተ አሳብ ላይ የተመሰረተ ርዮት በመሆኑ። ሁለተኛም ዘመናዊነት ማለት አውሮፓዊነትና ነጭ አሜሪካዊነት እደሆነ ሕልዮቱ እራሱ ገላጭ ነው። እዚህ ላይ አውሮፓዊነት ስንል ዘረኝነት ማለታችን ነው።     ዘመናዊነት ማለት ሰፊው የዓለም ሕዝብ ያለውን የመሀበራዊ እሴቶች  እደ ሗላ ቀርነትና በማየት የሚፈርጅና፤ እሴቶቹም መጥፋት ያለባቸው አደናቃፊዎች እደሆኑ ይኮንናል። በሕልዮም መሰረት የአውሮፓና የአሜሪካ (አውሮፓዊያን አሜሪካን) ዘመናዊ እደገት የመጨረሻውና እነከን የማይወጣለት እደሆነ፤ አደጉ የሚባሉትም አገራት ወደፍጹምነት እየተቃረቡ እደሚሄዱ፤ በሌላ በኩል ደግሞ የሶስተኛው ዓለም ተብዬ አገራትም እዲሁ ያደጉትን አገራት ተብዬውን እየቀረቡ አደሚመጡ፤ ይህም ሊሆን የሚችለው እነሱ ቀይሰው የሰጡዋቸው መንገድ ተከተለው ሲሄዱ ብቻ እደሆነ የሚል መሰረተ አሳብን ያነሽራሽራል። ይህም መሰረተ አሳብ ቀደም ሲል የነበረውን የሕብረተ ሰብ እድገት ሕልዮት የመጨረሻ ደረጃ ኮሚኒዝም ነው የሚለውን መሰረተ አሳብን ለማጣጣል ታስቦ የተፈጠረ መሆኑ ይታወቃል። ስለሆንም ኮሚኒዝም የተሰኝው የሕብረትሰብ ስርአት የመጨረሻው በመሆን ፈንታ አጋብሶ አደር የሕብረተሰብ ስርአት ስሙን እዲለውጥ ተደርጎ ልማታዊነት (ዘመናዊነት) የሚል የተውሶ ስም ወስዶ አዲስ አስመስሎ መቅረጽ በአሜሪካን የሚመራው የእጅ አዙር ቅኝ ገዥ ተስፋፊዎች ግድ ሆኖበታል። ምክንያቱም አንድም አበዮታዊ ለውጥን በመፍራት ሲሆን፤ ሌላውም በፀረ-አጋብሶ አደር ትግል የተሰማሩትን የሶስተኛውን ዓለም እንቅስቃሴ ለማዳከም ሲባል ሆን ተብሎ የተፈጠረና መላውን የዓለም አገራት ጥገኝነት አስገብቶ በአንድ አገዛዝ ስር አውሎ በአነድ መአከል በአምባገነንት ለመግዛት እሳቤን ያደረገ ነው። ስለሆነም ነው አባታዊ አገዛዝ የሚለውም ቃል ባሕላዊ የሚል ቃል ተለጥፎለት፤ በነሱ እሳቤ የሶስተኛው ዓለም ተብዬው አገራት በሙላ ባሕላዊ የሚል ቃላት የተለጠፉላቸው። ባሕላዊ የሚለውም ቃል ሗለ ቀር ማለት ተደርጎ በመወሰዱ፤ ዛሬ ዛሬ ልማተዊነት ዘመናዊነት እየተባለ የሚጠራው ግን የአጋብሶ አደር ስርአት በመሆን ቢታወቅም፤ የሕብረተሰብ ለውጥ አበዮታዊ እዳልሆነ ላለመቀበል በማሰብ ሕብረተሰባዊ ለውጥ ዝግመኛ አድረጎ ማቅረብም፤ ታሪክን ክለሳና ከእውነት የራቀ ነው። ለዚህም በአውሮፓም ሆነ በተቀረው የዓለም ክፍል ማለትም በአፍሪካ በኤዝያና በላቲን አሜሪካ የተደረጉ የሕብረተሰብ አብዮታዊ ለውጦች ታሪካዊ ምስክሮች በመሆን የሚጠቀሱ ናቸው። ሰለዚህ የሕብረተሰብ ለውጥ አዝጋሚያው አድረጎ ማየቱም በሕብረተሰብ ውሰጥ የሚቃረኑ መደቦች እደሌሉ አድረጎ ማቅረብና አጋብሶ አደር አልያም ልማታዊ ተብዬው ስርአት መድሎ አልባ አድረጎ ማቅረብ የተሳሳተና መሰረተቢስ ውሸት ነው። የአጋብሶ አደር ወይንም ልማታዊ ዘመናዊ ተብዬ እሴቶችም በመሰረቱ አሜሪካና አውሮፓን መሰረት ያደረጉ ባህላዊ እሴቶች ማለት ሲሆኑ፤ የሌላውን ዓለም አስገድዶ የራሱን ባህላዊ እሴቶችን  ሗላ ቀር ነው ብሎ በማንቛሸሽ ሀገረሰቡ እዲተው የማድረግ ሥራ ከሕብረተሰብ እድገት ለውጥ ጋር ሳይሆን ባሕላዊ ቅኝ ገዥነትን ለማስፈፋት ታቅዶ የሚሠራ ሥራ ነው። ከዚህም በተረፈ ዘመን አመጣሽ እደሸቀጥ ዕቃ በየጊዚያቱ የሚለዋወጥ ሞራልና ኤቲከስ የሌለው የቀድሞውን ዋጋቢስ ያደረገ ባህላዊ እሴት ከጥቅሙ ጉዳቱ የበዛ መሆኑ፤ እየታወቀ፤ የሶስተኛ ዓለም ተብዬው አገራት ባህላዊ እሴታቸውን ወርውረው ይጣሉ፤ ለልማት፣ ለዘመናዊነት አደናቃፊ ነው የሚሉ መሰረተ ሃሳብትን  አነግቦ በመነሳት እነዚህንም መሰረተ አሳባት በርዮት ቀንቅኖ ኅልዮ አድረጎ ደርሶ ማሰራጨቱና ተቀባይነት እዲኖረው ማድረጉ አነድም ሆናናነት፣ አለያም ወንጀል እደሆነ በውን የሚታወቅ ነው። 

Edited by:   ነፃነት ለገሠ

ይቀጥላል

Friday, October 17, 2014

Edward Snowden’s Privacy Tips: “Get Rid Of Dropbox,” Avoid Facebook And Google

Edward Snowden’s Privacy Tips: “Get Rid Of Dropbox,” Avoid Facebook And Google

According to Edward Snowden, people who care about their privacy should stay away from popular consumer Internet services like Dropbox, Facebook, and Google.

Snowden conducted a remote interview today as part of the New Yorker Festival, where he was asked a couple of variants on the question of what we can do to protect our privacy.

His first answer called for a reform of government policies. Some people take the position that they “don’t have anything to hide,” but he argued that when you say that, “You’re inverting the model of responsibility for how rights work”:

When you say, ‘I have nothing to hide,’ you’re saying, ‘I don’t care about this right.’ You’re saying, ‘I don’t have this right, because I’ve got to the point where I have to justify it.’ The way rights work is, the government has to justify its intrusion into your rights.

He added that on an individual level, people should seek out encrypted tools and stop using services that are “hostile to privacy.” For one thing, he said you should “get rid of Dropbox,” because it doesn’t support encryption, and you should consider alternatives like SpiderOak. (Snowden made similar comments over the summer, with Dropbox responding that protecting users’ information is “a top priority.”)

[Update: In a June blog post related to Snowden, Dropbox actually says, "All files sent and retrieved from Dropbox are encrypted while traveling between you and our servers," as well as when they're "at rest on our servers," and it points to other security measures that the company is taking. The difference between Dropbox and SpiderOak,as explained elsewhere, is that SpiderOak encrypts the data while it's on your computer, as opposed to only encrypting it "in transit" and on the company's servers.]

[And here's a more complete Snowden quote, from around 1:04:55 in the video: "We're talking about encryption. We're talking about dropping programs that are hostile to privacy. For example, Dropbox? Get rid of Dropbox, it doesn't support encryption, it doesn't protect your private files. And use competitors like SpiderOak, that do the same exact service but they protect the content of what you're sharing."]

He also suggested that while Facebook and Google have improved their security, they remain “dangerous services” that people should avoid. (Somewhat amusingly, anyone watching the interview via Google Hangout or YouTube saw a Google logo above Snowden’s face as he said this.) His final piece of advice on this front: Don’t send unencrypted text messages, but instead use services like RedPhone and Silent Circle.

Earlier in the interview, Snowden dismissed claims that increased encryption on iOS will hurt crime-fighting efforts. Even with that encryption, he said law enforcement officials can still ask for warrants that will give them complete access to a suspect’s phone, which will include the key to the encrypted data. Plus, companies like Apple, AT&T, and Verizon can be subpoenaed for their data.
Beyond the privacy discussion, Snowden talked about how and why he decided to leak documents bringing the government’s electronic surveillance programs to light. He repeatedly claimed that he wasn’t pursuing a specific policy outcome, but just trying to have an open conversation about these issues:

We can have secret programs. You know, the American people don’t have to know the name of every individual that’s under investigation. We don’t need to know the technical details of absolutely every program in the intelligence community. But we do have to know the bare and broad outlines of the powers our government is claiming … and how they affect us and how they affect our relationships overseas. Because if we don’t, we are no longer citizens, we no longer have leaders. We’re subjects, and we have rulers.

As for why Snowden hasn’t come back to the United States to stand trial, he said that when he looked at how the U.S. government treated whistleblowers like Thomas Drakeand Chelsea Manning, he became convinced that he wouldn’t be able to present his case to a jury in an open trial.

“I’ve told the government again and again in negotiations, you know, that if they’re prepared to offer an open trial, a fair trial in the same way that Dan Ellsberg got, and I’m allowed to make my case to the jury, I would love to do so,” he said. “But to this point they’ve declined.”

Snowden acknowledged that there’s some irony in his taking shelter in China and Russia, countries that don’t exactly have spotless human rights or privacy records themselves. He said Russia was supposed to be a transit point on his way to Latin America — but his passport was canceled while he was at the Moscow airport.

The New Yorker’s Jane Mayer ended the interview on a light note, suggesting that Snowden was now free to enjoy some vodka. He replied, “I actually don’t drink alcohol. Little-known fact: I’ve never been drunk.”