Friday, September 6, 2013

የመልስስ ዜናዊ ኑዛዜ በቴላፓቲ (telepathy)

በቅድሚያ የዚህ የቴላፓቲ ቃለመጠይቅ (interview) ፈቃደኛ ሁነው፤ሰዓቱንም አክብሮ በመገኘቶ በራሴና በቴላፓቲ ዜና አዘጋጆዎች ስም ላመሰግኖት እወዳለሁ።

አቶ መለስ ፥ እኔም ይህን እድል የሰጣችሁኝ የቴላፓቲ ጋዜጠኞች ላመሰግን እወዳለሁ።
ጥያቄ ፥ አቶ መለስ ልጂ እያሉ ቤተሰብዎት ስለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት አንስተው ሲወያዩ ወይም ሲጫወቱ ይሰሙ ነበርን?

መልስ፥ አዎ እሰማ ነበር።

ጥያቄ ፥ በቤተሰብዎት በተለይም በወላጆችዎ አመለካከት ስለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ምን ትርጉም ነበር የሚሰጡት?

መልስ፥በቤተሰቤና በወላጆቼ አመለካከት ኢትዮጵያ ማለት የአማራ አገር፤ ኢትዮጵያዊነት ማለት አማራነት ነው እያሉ ነበር የሚያወሩት።

ጥያቄ፥ አዱስ አበባ ዩኒቨርስቲ በህክምና ሳይንስ የሁለተኛ ዓመት ተማሪ እንደነበሩ ከመስማት ሌላ ከዚያ በፊት የት የትእንደተማሩና የተማሪነትዎ ሕይወት ምን ይመስል እንደነበረ የምናውቀው ነገር ስለሌላ፤ ሊገልጹልን ፈቃደኛ ነዎትን?

መልስ፥ የአንደኛ ደረጃ ትምህርቴ ያጠናቀኩት በንግሥት ሳባ መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አድዋ ሲሆን የሁለተኛ ድረጃ ትምህርቴ ያጠናቀኩት በጀነራል ዊንጌት ት/ቤት አዲስ አበባ ነው።

ጥያቄ፥ የተማሪነት ግዜዎ እንዴት ያስታውሱታል

መልስ፥ የተማሪነቴ ዘመን ጥሩ አልነበረም ጓደኛ አልነበረኝም። ትልቁ ችግሬ ጓደኛ ማጣት ነበር።

ጥያቄ፥ ለምን ጓደኛ ወይም ጓደኞች (peer groups) የማግኘት ችግር ገጠሞዎት?

መልስ፥የከሃዲ ቤተስብ፣የባንዳ ቤተሰብ፣ እየተባልኩ እገለል፣እሰደብ፣ኧናቅ ሰለነበረ፤ የተማሪነት ሕይወቴ፥ ምሬት፣ሃዘን፣ ብስጭት፣ትካዜ ወዘተ የተሞላበት ነበር።

ጥያቄ፥ ወደ ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) እንዲሄዱ የግፋፋዎት ከላይ የተጠቀሱትን ሁኔታዎች ናቸው ማለትይቻላልን?

መልስ፥ አዎ! በሚገባ!

ጥያቄ፥ የሕወሃት ዓላም ምን ነበር?

መልስ፥ ከአማራ የነጻ የትግራይ ትግሪኝ ሪፕብሉክ ለመመሥረት ነበር።

ጥያቄ፥ ነጻ የትግራይ ሪፕብሉክ (sovereign Tigrie) ለመመስረት የሚያስችል አስተማማኝ አቅም ያገኛችሁት መቼ ነበር?

መልስ፥ የአውዜን ገበያተኞችን በደርግ አውሮፕላን ካስደበደብን በኋላ ነበር።

ጥያቄ፥ እንዴት ንጹህ ገበያተኞችን በቦምብ መደብደብ ለሕወሓት ሃይል ሊሆን ቻለ? እስቲ ያብራሩት? 

መልስ፥ (1) የትግራይ ወጣቶችን ስሜት ስለቀሰቀ ቁጥሩ ማስተናገድ ከምንችለው በላይ ወጣት ወደ ሕወሃት ጎረፈ (2) ያንን እልቂት በቪዲዮ ቀርጸን የዓለም ሕዝብ እንዲያየው በማድረጋችን ከምእራባዊያን መንግሥታት በተለይ ከእንግሊዝና ከአሜሪካ ከፍተኛ የመሣርያ፣የገንዘብ፣የቁሳቁስ፣የሞራል፣የስለላ ድጋፍ ወዘተ ስላስገኝልንና የውጊያ ሃይላችን እጅግ በጣም ከፍ በማለቱና በደርግ ሠራዊት ምርኮኞች ስንጥለቀለቅ ነው ከአማራ የነጻ የትግራይ ሪፕብሉክ የመመሥረት አቅማችን
ያወቅነው።

ጥያቄ፥ፖለቲካዊ ርዕዮታችሁ (ideology) ሶሻሉዝም (socialism) እንደነበረ፤ ጫካ እያላችሁ ያውም ሥልጣን ላይ ልትወጡ ሁለት ዓመት ሲቀራችሁ ለ(BBC)ጋዜጠኞች የምትከተሉት የአልባኒያን ሶሻሉዝም እንደሆነና የወቅቱ የአልባኒያ መሪ ‘ኤንቨርዎዣንንም’ አድንቃችሁ ስታስረዱ አዳምጫለሁ። ታዲያ እንዴት እንግሊዝና አሜሪካ ከጎናችሁ ሊሰለፉ ቻሉ?

መልስ፥ እንደዚህ የምትረዱን ከሆነ እናንተ የምትሉን ሁለ እንፈጽማለን ብለን ቃል ገባንላቸው።

ጥያቄ፥ የወያኔ አባላ የደርግ ካደሬ በመሆን በርካታ የኢሕአፓ አባላት ገለዋል፣አስገድለዋል፣ አስጠቁሞዋል ወዘተ እየተባለ ይወራል፤ ለዚህ ምን መልስ አለዎት?

መልስ፥ ትክክል ነው፤ ደርግ ባካሄዲቸው የገፍና የተናጥል ግድያዎች ሁለ የእኛ ስውር ሚና አለበት። ከጀነራሌ ተፈሪ ባንቲ እስከ ስልሣዎቹ ጀነራሎች ግድያ የእኛ ስውር ምክርና ቅስቀሳ አለበት። መንግሥቱ ሊቀድም ነው፤ እነ-እገሌ ሊያጠፉት ተዘጋጅቷል የሚል ወሬ ለመንግሥቱ ጆሮ እንዲደርስ በማድረግ።

ጥያቄ፥ከእነዚያ ሁለ መሥራች የ(ሕወሓት) አባልች እንዴት እርስዎ የወያኔዎች መሪ ሊሆኑ ቻሉ?

መልስ፥ የሕወሓት አመራሮች በእኔ ሥር ማድረግ ለእኔ ከባድ አልነበረም።ምክኒያቱም እነ-ሊነን፣ እስታሊን፣ ማኦ፣ ሂትለር፣ ሞሶሎኒ፣ ጀነራል ፍራንኮ ወዘተ ሥልጣን ለመጨበጥ የተጠቀሙባቸው ስሌቶች አዘውትሬ በጥንቃቄ አነብ ነበርና።

ጥያቄ፥ የሕወሓት መሪ ለመሆን ከተጠቀሙባቸው ሥልቶች አንዱን ወይም ጥቂቶቹን ሊጠቅሱልን ይችላሉን?

መልስ፥ (1) እያንዳንዳቸውን የፖለቲካ ብስለት፣ ጥንካሬ፣ ድክመትና ባለስሥልጣን ያላቸው ምኞት ወይም ጉጉት ተከታትዬ አጠናሁ
(2) ማርክሲስት-ሊኔኒስት የጥናት ቡድን ወይም ክንፍ መሥርቼ ደጋፊዮቼን አጠናከርኩ
(3) ለሥልጣን የሚያሰሠጉኝን የሕወሓት መሪዮች ደካማ ጎን እያጋነንኩ ለሕወሓት አመራር ብቁ እንዳልሆኑ ሥውር ቅስቀሳ በማድረግና በማስደረግ በአስቾካይ በሞት እንዲቀጡ ወይም ከሕወሓት እንዲወገደ እያደረኩ ደካሞችን ሁሉ በቁጥጥሬ ሥር አዋልኳቸው።

ጥያቄ፥ የ(ሕወሓት) አባል ከመሆኖ በፊትም ሆነ ከሆኑም በኋሊ ኢትየጵያን እገዛታለሁ የሚል ምኞት ኖርዎት ያውቃለን?

መልስ፥ አዎ፤ በኅልሜም በውኔም ያቺ አገር የመግዛት ምኞት ነበረኝ።

ጥያቄ፥ ለምን ? የኢትዮጵያ ሕዝብ አስተሳሰብ ለመቀየር? ኢትዮጵያን ለማሳደግ? ከስልጣን የሚገኝ ምቾትና ዝና ከመፈለግ አኳያ?

መልስ፥ የዚህ መልስ ሁለትም ሦሥትም አይደለም። መልሱ አንድ ነው፤ ዋናው ምኞቴ ያቺን አገር እየገዛኋት ብትንትኗን ለማውጣት ነበር።

ጥያቄ፥ ያቺን አገር ለማፍረስ ያወጥዋቸው ዕቅድች ምን ምን ነበሩ?

መልስ
§        (ያጭር ጊዜ ዕቅድ ቁጥር 1)፥ በአማራ ሥርወ መንግሥታት የሰለጠኑትን የቀድሞቹ ፡ የምድር ጦር፣ የፖሊስ ሠራዊት ፣ የባህር ኃይል፣ የደኅንነት/የፀጥታ ኃይል፣ የመሣርያ ግምጃ ቤቶች ወዘተ በቁጥጥር ሥር ማዋልና መደምሰስ፤  
§        (ያጭር ጊዜ ዕቅድ ቁጥር 2)-: ከላይ የተጠቀሱትን ተቋማት፣ የከፍተኛ ትምህርት (የዩኒቨርስቲዮችና የኮላጆች) ተቋማት (institutions)ማፍረስ ፤
§        (ያጭር ጊዜ ዕቅድ ቁጥር 3)፥ ከሊይ የተቀሱትን የምድር ጦር፤ የአየር ኃይል፣ የፖሉስ ሠራዊት፣ የደኅንነት፣ የከፍተኛ ትምህርት ኃይሎችና ተቋማት ለትግራይ ነጻነት በተዋጉና በትግርኛ ተናጋሪ ኃይልች መተካት፤  
§        (ያጭር ጊዜ ዕቅድ ቁጥር 4)፥ በሥልጣን ላይ ለመረጋጋት እንቅፋት ይሆኑብናል የምነላቸውን መመንጠር፤  
§        (ያጭር ጊዜ ዕቅድ ቁጥር 5)፥ በእኛ እምነት ያቺ አገር የመቶ ዓመታት ታሪክ ብቻ ያላት ስለሆነች ያንን ማስተማርና መጻፍ።በእኛ እምነት የዚያች አገር ባንዲራ (እናተ ሰንደቃዓላማ) የምትሉዋት ጨርቅ መሆኑን ማስተማርና በ (ሕወሓት) ወርቃማ ባንዲራ መተካት።
§        (የረዥም ጊዜ ዕቅዳችን ቁጥር 1)፥ ትግራይን ከሚያጎራብቱ ክፍለ ሃገራት ለም የሆኑትን መሬት ወስደን ወደ ትግራይ በማጠጋጋት ትግራይን አንደ ትልቅ ረፕብሉክ ማድረግና ማበልጸግ፤
§        (የረዥም ጊዜ ዕቅዳችን ቁጥር 2)፥ አሰብ፣ምጽዋና በአድሜን ጨምሮ ኤርትራን ነጻ ማውጣት፤
§        (የረዥም ጊዜ ዕቅዳችን ቁጥር 3)፥ የጦር መሣርያዎችን፣ የጤፍ፣የገብስ፣ የኑግ፣ የሠሊጥ ምርታ ምርቶችን በመስጠት፤የገንዘብ ካሳ በመክፈልና የቡና ምርት ወደ ውጭ ገበያ እንዲላኩ (export) እንዲያደርጉ በማድረግ ኤርትራን ማጠናከር፤
§        (የረዥም ጊዜ ዕቅዳችን ቁጥር 4)፥ በጎሳ ቋንቋ የተዋቀረ ክልላዊ አስተዳደር በመፍጠርና እርስ በርሱን በማናከስ (by creating Bantustanization) የዚያችን አገር ዳርድንበር፣አንድነትና ማኅበራዊ ባህለን (social culture) ማፈራረስና ማናጋት፤
§        የረዥም ጊዜ ዕቅዳችን ቁጥር 5)፥ የዚያች አገር የምጣኔ ሃብት (economy) እና የንግድ ዘርፍ በኤፈርት፣ በትግራይና በኤርትራ ተወላጆጅች እጅ እንዲገባ ማድረግ፤
§        (የረዥም ጊዜ ዕቅዳችን ቁጥር 6)፥ ከዚያች አገር መሬት ቆርሶ በመስጠት ሱዳን የመልካ ምድርዋን ግዛት እንድታስፋፋ ማድረግ፤
§        (የረዥም ጊዜ ዕቅዳችን ቁጥር 7)፥ ትግሬዎችን በገፍ ወደ፥ አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ካናዳ፣ አውሮፓ፣ እስካንዲናቪያ አገሮች ልኮ በማስተማር የነገውን የዚያችን አገር ሕዝብ የዕውቀት ሞተርና መሪ ማድረግ። ማለት የትግራይ ሪፐብሉክ (ብሄር ግዛት) ምስረታ ካልተሳካ፤
§        (የረዥም ጊዜ ዕቅዳችን ቁጥር 8)፥ ከዩኒቨርስቲ እስከ አንደኛ ደረጃ ያሉትን የዚያች አገር የትምህርትና የመምህራን ጥራት ዝቅ ማድረግ፤ ከአንደኛ ደረጃ እስከ ዩኒቭርስቲ ያሉትን የሃገረ ትግራይ ትምህርት ቤቶች የትምህርትና የመምህራን ጥራት ካደጉ አገሮች የትምህርትና የመምህራን ጥራትጋር ተመጣጣኝ ማድረግ ወዘተ ።

ጥያቄ ከላይ የተጠቀሱትን ያቺን አገር የማጥፋት ዕቅዳችን ያረቀቁና አሁንም በሕወሓት አመራር ቁልፍ ቁልፍ ቦታ የያዙት፤ እርስዎንም ጨምሮ- በወንድ አያታቸው ወይም በአባታቸው ወይም በእናታቸው አባት በኩል ጣሊያንን ወግነው ኢትዮጵያን የወጉ (የባንዳ ኤርትራውያን ቤተስብ) ስለመሆናው ነዋሪነታቸው አውስትራሊያ የሆነው አቶ ገብረመድህን አርአያ መስክሮዋል። ይህ መሰረተቢስ ክስ (allegation) ነውን ውይስ እውነትነት ያለው ክስ ነው?

መልስ፥ ገ/መድህን አርአያ እውነቱ ነው፤ ከአሁን በኋላ እኔ ብደብቀው ታሪክ ፀሐፊዎች ስለሚያጋልጡኝ የምድር ላይ ውሸቶቼንም ባለሁበት በሰማይ ቤት ክፉኛ እያሰቃዩኝ ስለሆነ ከአሁን በኋላ ላለመዋሽት ወስኜአለሁ።

ጥያቄ የኤርትራዊነት ዝርያ ያላባቸውን በበትረ መንግሥትዎ ወሳኝ ወሳኝ በሆኑ የሥልጣን ተዋረዶች ያስቀመጡበት ምክንያት ምንድነው?

መልስ (1) አማራ ኤርትራውያንን በቅኝ እንደገዛቸው ሁለ ኤርትራውያን በተራቸው አማራን የእጅ አዙር ቅኝ (indirect colonizers) ለማድረግ
(2) ባባትም በእናትም የኤርትራዊነት ዝርያ ከሌለባቸው ከሕወሓት መሪዮዎችና ከወያኔ አባላት ከሚቃጣብኝን ጥቃት እንዲጠበቁኝ ቃል ስለገቡልኝና የበለጠም ስለማምናቸው ።

ጥያቄ ለምን ነበር ያባትዎን አገር (ያህቺን አገር) እያደከሙ የእናትዎን አገር ኤርትራና የጎረቤት አገር ሱዳንን ማጥናከር የመረጡት?

መልስ በአጭሩ ሁለቱም- ለደረስኩበት የሥልጣን ምንጭ ወይም መሠረት ስለሆኑ ውለታቸውን መክፈል ነበረብኝ።

ጥያቄ፥ ዓለም በጎሣ፣ በብሄር፣በብሄረሰብ፣በእምነት፣በርዕዮት ወዘተ ከተከፋለበት ታሪካዊ ወቅት አሁን እስከ ደረስንበት ታሪካዊ ወቅት አንድ መሪ የሚገዛውን አገር ለማስፋፋት ሲጥር እንጂ-የዚያን አገር የባህር በርና ዳር ድንብር ለባዕዳን ያቀራመት ወይም አሳልፎ የሰጠ መሪ ‘እርስዎ ብቻ ኖዎት’ ይባላል። ይህንን እንዴት ያዩታል?

መልስ (1) አዎን ጥሩ ታሪክ ያላቸው መሪዎች እንዳሉ ሁለ መጥፎ ታሪክ ያላቸው መሪዎች አሉ። ይህንን ጠንቅቄ አውቃለሁ
(2) እኔ ቁጭቴን ተወጥቼ እንደዚህ ለየት ያለ (unique) ታሪክ እንዲኖረኝ ነው የፈለኩት
(3)ማስደሰት የፈለኩት ያቺን አገር የሚጠሏትን ከበርቴ ምዕራባውያን መንግሥታት እና አረቦችን ነው ። ታርኬም አሳምረው፣ አድንቀውና አጀግንነው የሚጽፉት እነዚሁ ሃይሎች ናቸው
(4) የእኔ ታሪክ የዝያች አገር ሕዝብ ምኑም ስላልሆነ በፈለጉት መልክ አጨማልቀው ቢጽፉት ግድየለኝም።

ጥያቄ፥ ከትግራይ ትግሪኝ ሪፕብሉክ አልፋችሁ ኢትዮጵያን መግዛት የሚያስችላችሁን ሁኔታዎች መፈጠራቸውን ያወቃችሁት መቼ ነበር?

መልስ (1) በዋናነት የኢሕአፓ ከአሲምባ መውጣትና የመዋጋት አቅሙን መዳከም
(2) የስልሣ ጀነራልች መገደል
(3) የደርግ ሠራዊት የመዋጋት ችሎታ ከግዜ ወደ ጊዜ እየተዳከመ መሄድ
(4) የምእራቡን የከበርቴ መንግሥታት በተለይም እነ-አሜሪካና እንግሊዝ ከጎናችን መሰለፍ
(5) የመንግሥቱ ኃይለማርያም አጋር የነበረው ረሺያ ከእነ-ጭፍሮቹ ከነበሩበት የኃይል ሚዛን መውደቅ፤ ወደ አዲስ አበባ የመገስገስ መንገዳችን ጨርቅ አደረገልን።

ጥያቄ፥ ጠቅላላውን ኢትዮጵያን ለማስተዳደር ወደ አዲስ አበባ በመገስገሱ ላይ አብዛኛውን የሕወሓት ሠራዊት ስላልተስማማ በመካከላችሁ ጭቅጭቅ ተከስቶ ነበር ይባላል፤ ይህንን ሊያብራሩልን ይችላሉን?

መልስ አዎን በእኔ ሥር የሚመራው የሕወሓት አመራር አጀንዳና የሕወሓት ሠራዊት አጀንዳ ለየብቻ ነበር። የሕወሓት ሠራዊት የተዋጋው ትግራይን ከአማራ አገዛዝ ነጻ ማውጣት በሚል ነበር። ስለሆነም ሠራዊቱ ትግራይን ነጻ አውጥተናልና ከዚህ ማለፍ የለብንም ብሎ ተሟገተን። አማራ ለረዥም ዓመታት ስለገዛን ተራችን እንግዛቸው በሚል ስላሳመናቸው ወደ አ.አ በመገስገሱ ላይ ተስማማን።

ጥያቄ፥ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ዱሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዱግ) እንደታዋቅሩ የመከርዋችሁ አሜሪካኖችና እንግሉዞች ናቸው ይባላል፤ ይህ አባባል ምንያህል እውነትነት አለው?

መልስ፥ እውነት ነው፤ የእነሱ ምክር የሌለበት አንዳችም ነገር አልሠራንም። በዚያች አገር ሕዝብ የተሻለ ተቀባይነት እንዲኖራችሁ ኢሓአድግ (EPRDF) አዋቅሩ ብለው መከሩን።

ጥያቄ፥ የአጼ ኃይለሥላሤና የዳግማዊ ምኒሉክ ቤተመንግሥቶች ምቾት እንዴት ነበር?

መልስ ምንም አይለም፤ በተለይም ለጫት መቃሜያና በተቃዋሚዮቻችን ሊይ ለማሴር። አዜበ ግን እጅግ በጣም ወዳው እስከ እለተሞታችን መልቀቅ የለብንም ብላ ትሟገት ነበር።

ጥያቄ፥ያቺን የሚጠሎት አገር ለሃያ አንድ ዓመታት ያህል እገዛታለሁ የሚል ምኞትና ዕቅድ ነበረዎትን?

መለስ እውነቱን መናገር ካስፈለገ ከአምስት ዓመት በላይ ያቺን አገር እገዛታለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር።

ጥያቄ፥ ታዲያ ያቺን አገር ለሃያ አንድ ዓመታት ለመግዛት ያስቻልዎት ጥበብ ምንድነው?

መልስ (1) የጠመንጃ አፈሙዝ
(2) ካደሬዮችን በብዛት አሰልጥነን አንድ ካደሬ አምሥት ሰዎች እንዲመለምልና እንዲሰልል
በማሰለፍ
(3)ኦሮሞችን በአማራው ሊይ በማስነሳትና የዚያች አገር ሕዝብ በቋንቋና በጎሳ በማካለል
(4) ወህኔ ቤቶችን በማስፋፋት
(5) አሜሪካን፣እንግሊዝን፣ የአውሮፓንና የእስካንዲናቪያን ከበርቴ አገሮች መንግሥታት ከጎናችን መሰለፍ
(6)ቻይናን እንደ አማራጭ ኃይል ከጎናችን በማሰለፍ
(7) በጥትቅም ሆነ በሰላማዊ የፖላቲካ ትግል ጠንካራ ተቃዋሚ ስላላገጠመን የስልጣን ዘመኔ አልጋ ባልጋ ሆነሌኝ።

ጥያቄ፥ መተከለዎ (principle) የጠመንጃ አፈሙዝ ሥልጣን ከነበረ፤ ለምን ለዲሞክራሲ ጥብቅና የቆሙ መስለዎ ይለፍፉ ነበር?

መልስ (1) ዶላር በግፍ ለሚሰጡኝ የከበርቴ አገሮች መንግሥታት ለማታለል
(2) ዲሞክራሲ!! ስል ሥልጣኔን የማይነካ/ኩ ዲሞክራሲ ማለቴ ነው ፤ ለምሳሌ የእኔ በትረ-መንግሥት የማይቃወሙና በሥውር እኔን የሚደግፉ ተቃዋሚዮችን ማቋቋም፣ መጠጣት፣መጨፈር፣ ጫት መቃም፣ የራቁት ዳንስ ቤቶች መክፈት፣ የወንድና የሴት ግብረሰድሞች ከተለያዩ አገርች ወደ እዚያች አገር እንዲጎርፉ መፍቀድ ወዘተ።

ጥያቄ፥ እስከ ብሔራዊ ምርጫ 1997 ባለው ጊዜ፤ ሥሌጣን የሙጥኝ ብለው ይዘዋል፤ ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዮዎች በምርጫ እንዲይሳተፉ መንገድ ዘግተዋል ወዘተ እየተባለ ሲወቀሱና ሲከሰሱ፤ የእርሰዎ መልስ ጠንካራ ተቃዋሚ ስላጣሁ ነው፤ ለማን ላስረክብ የሚል ነበር። ታዲያ በ 97ቱ ብሔራዊ ምርጫ ሲሸነፉ ለምን የመንግሥትዎ ሥሌጣን ለአሸናፊው ፓርቲ አለቀቁም?

መልስ (1) ከሊይ እንደጠቀስኩት በሥልጣን ላይ እንድቆይ ለረዱኝ በከበርቴ አገሮች መንግሥታት ዘንድ ዲሞክራት መሪ ለመምሰል ነበር ስለዲሞክራሲ እለፍፍ የነበረው
(2) እሸነፋለሁ ብዬ ጭራስ አልጠበኩም ነበር
(3) አዜብ ሥልጣን አስረክበህ ከዚህ ግቢ ከወጣን እፈታሃለሁ አለችኝ
(4) የከበርቴ አገሮች መንግሥታት በተለይም ቶኒ ብለርና ጆርጅ ቡሽ ሥልጣን ላይ እንድቆይ ፈለጉ

ጥያቄ፥ ያንን የሕዝብ ሥልጣን ለማስከበር ሰላማዊ ሰልፍ የወጡትን፥ ሽማግሌዎችን፣ አሮጊቶችን፣ አዛውንቶችን፣ ለጋ ወጣቶችና ሕጻናትን በእርስዎ ትዛዝ በልዩ ገዳይ ሃይል (squad) በአጋዚያን ከሁለት መቶ ሰዎች በላይ ሲጨፈጭፉ፤ እርስዎ በሸራተን ሆቴል ሴት ልጆዎን አቅፈው የ12ኛ ክፍል ግራጁየሽን ሲያከብሩ እንደነበረ ተዘግቦዋል። ይህ ዜና ያፀድቁታል ወይስ ይክዱታል?

መልስ (1) ካሜራ የያዘው ነገር ለመካድ ስለሚያስቸግር ዜናውን አፀደኩት ማለት እውነተኛ ዜና ነው (2) የዚያች አገር ሕዝብ እንኳን ሁለት መቶ- በሚሉዮንም ቢሞት ግድየለኝም።

ጥያቄ፥ እ.አ.አ ግንቦት 18/2012 በተርመንት ሜሪላንድ (Thurmont,Maryland,USA) በኢንደስትሪ ባድጉት ስምንት (G8)  አገሮች ስብሰባ ንግግር በማድረግ ላይ እያሉ ጋዜጠኛ አቶ አበበ ገሊው መለስ አምባገነን!!!፣ ከልማት በፊት፣ ከምግብ በፊት ዲሞክራሲ፣ መለስ አምባገነን!!! በማለት እንደመብረቅ ሲጮሁብዎት፤ ለምን ነበር ያን ያህል የደነገጡት?

መልስ (1) ያንን ያህል በሚያደንቁኝና በሚያከብሩኝ ታላላቅ የዓለም መሪዮች ፊት እንደዚያ በመደፈሬና ክብሬ በመገፈፉ ነበር እጅግ በጣም የደነገጥኩት።

ጥያቄ፥ ከዚያ ክስተት በኋላ ለተወሰኑ ሣምንታት አደባባይ ላይ ካለመታየትዎም ሌላ ጭልፊት እንዳስደነገጣት ጫጩት ወይም ተቅማጥ እንደያዘው ኮስስዎ ወደ አደባባይ ብቅ አሉ። ድንጋጤው ነው እንድዚያ ያደረጎት ወይስ ሌላ ችግር ነበረቦዎት?

መልስ (1) አዎ በድንጋጤው ምክንያት ለሁለት ሣምንታት ያህል በተቅማጥ ተሰቃየሁ (2) ድንጋጤው ጽኑ አእምሮ መረበሽ (acute depressive or major depressive disorder-MDD) ስላደረሰብኝ ቀድሞ ከነበረብኝ አእምሮ በሽታዬ ጋር ተደማምሮ ለሞት አበቃኝ።

ጥያቄ፥ በ 57 ዓመት ዕዴሜዎ አሁን ወደ አሉበት ዓለም ባይሄዱ ኖሮ ያቺን አገር ምንያህል ተጨማሪ ዓመታት ሊገዝዋት ያስቡ ነበር?

መልስ (1) ዕድሜዬ እንደ ሙጋቤ ቢረዝም ኖሮ ያንን ያህል (80-90) አመታት እየገዘኋትና እየቸረቸርኩ ላጠፋትና ከጎን የትግራይ ሪፕብሉክ ለመመሥረት ዕቅድ ነበረኝ።

ጥያቄ፥ በእርስዎ ሰም የተቀመጠ $3.5 ቢሉየን ዶላር፣ በልጅዎ ስማሃሌ መለስ ስም የተቀመጠ $5.00 ቢሉየን ድሊር ተገኝቶ የዓለም ሕዝብ መወያያ ሆኖዋል። ባለቤትዎ አዜብ ግን የባለቤቴ የወር ደሞዝ $4000 ብር ብቻ ነበር በማለት ይሟገታሉ። ይህንን እንዳት ያዩታል?

መልስ ጉድ ሆንኳ! በዘመኑ ታላላቅ መሪዮዎች ያንን ያህል የተከበረውን ስሜ ጠፍቷሊ! በሕይወት እያለሁ በጠመንጃ ሃይል ለረዥም ጊዜ የተገዛ ሕዝብና በቅኝ ግዛት ሥር የዋለ ሕዝብ አእምሮ (mind) ከሰውኛ ባሕሪ ወደ እንሰሳኛ ባሕሪ ስለሚቀየር የሚነገረውን ሁለ ይቀበላል እያልኩ እነግራት ስለነበረ፤ አዜብ ያንን ነው ያንጸባረቀችው።

ጥያቄ፥ በርግጥም አስክሬንዎ በአዲስ አበባ ቅድስተ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ቅጽር ግቢ ተቀብሯልን?

መልስ ሞኛችሁን ፈልጉ፤ ነገ ወያኔ ሲወድቅ አስክሬኔ ከመቃብሬ አውጥታችሁ ለጅብ ልትሰጡ? የሬሳዬ ሣጥን ብቻ ነው አዱስ አበባ ከላይ በተጠቀሰው ቦታ የተቀበርው። ተናዝዤ ስለነበረ እውነተኛ አስክሬኔ የተቀበርው በአደዋ ነው ።

ጥያቄ፥ አሁን ያሉበት ዓለም ሕይወት ምን ይመስላል?

መልስ ምቾት በዚያች አገር ቤተመንግሥት ቀረ። እዚህ ከማንም ተራ ሰው ነፍስ (soul) ጋር መተራመስ ነው። ልክ ከርቸሌ ውስጥ እንደ መኖር ማለት ነው። ሌሊት ሌሊት አጋንንቶች እየወሰዱ በምድር ላይ የሠራኸውን ተናገር እያለ ይገርፉኛል። ያሰቃዩኛሌ። ከሞት በኋላ (life after death) ገሃነምና መንግሥተሰማይት የሚባል ነገር የለም የሚለውን የአሕዛብ አስተምሕሮ (Social fascism Doctrine) ተከትዬ የፈጸምኳቸውን ግፎች አድነው እያሰቃዩኝ ነው ። ነፍሴ የመጨረሻውን ፍርደን እየጠበቀ ነው። እስካሁን እየተነገረኝ ያለው ነፍስ እነ-ሂትለርና እስታሊን ያሉበት የዳቦ መጋገሬያ ዓይነት ምድጃ (furnace) ውስጥ እንደሚቀመጥ ነው።

ጥያቄ፥ ከርሰዎ ሞት በኋሊ ስለሆኑት ሁኔታዎች ጥያቄ አሎትን? አዎ አለኝ።

የአቶ መለስ ጥያቄ ፥ የቀብሬ ስነሥራዓት እንዴት ነበር?

መልስ ግሩም ድንቅ የቀበር ሥነሥራዓት ተደርጎሎዎታል። የቀረ የዓለም መሪ አልነበረም።በግድም በውድም እንዃንስ ጤነኛውን ፣ አንካሣውም፣ ዓይነ-ሥውሩም፣ በሁለም የአገራችን ሆስፒታልች የሚገኙትን ታማሚዮች፣ የጎዳና ተተዳዳሪዮች ወዘተ ተሰልፈውሎታል፤ የልማታዊ አስለቃሽ ቡድንም አበለ ከተቆረጠላቸው ለቅሶኞች ጋር በመሆን ለቅሶ አድርጎሎዎታል።

የአቶ መለስ ጥያቄ፥ ማን ነው እኔን የተካው ጠቅላይ ሚኒስተር?
መልስ፥ እርስዎን የተካው አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ነው።

ጥያቄ፥ በዚህ ሊይ የሚያክሉት ነገር አለዎትን?

የአቶ መለስ ጥያቄ፥ የአቶ ኃይለማርያም ጠቅሊይ ሚንስተር መሆን እጅግ በጣም አስደስቶኛል። ምክንያቱም ለወያኔዎች ፍጹም ታዛዥ ነውና። አዜብ ከእኔ ሞት በኋላ በምን ሁኔታነው ያለችው?

መልስ፥አዜብ በብስጭት ራሷን ገላ ወድ እርሰዎ ሣትመጣ አትቀርም። ምክንያቱም
(1) ያለውዴታዋ በግድ ከቤተመንግሥት አስወጧት
(2) ከኤፈርት ዳይሬክተርነት ተወግዳ በምትካው ከእርሰዎ በፊት ውሽማዋ የነበረው
አቶ ብርሃነ ኪ/ማርያም (ብርሃነ ማርት) ተሾመ
(3) በሙስና ክስ ሊመሰርትባት እየታሰበ ነው።

ጥያቄ፥ ሰዎች ሲሳሳቱ፣ የተመኙትን፣ ያለሙትን፣ያቀዱትን ወዘተ ሣያሳኩ፤ እርጅና ሲድርርስባቸው፣ አደጋ ሲያገጥማቸው፣ታመው ሞት አፋፍ ሊይ ሲሆኑ አንጻራዊ ፀፀት አላቸው። እርስዎ ታመው እንደ ማይድኑ ሲያውቁ ዋንኛና ትልቁ ጸጸትዎ ምን ነበር?

መልስ፥ ያቺን አገር ሱማላያን ወይም አፍጋኒስታን ሳላስመስላት በሞት መቀደሜ ነው ትልቁ ፀፀቴ።

ጥያቄ፥ ለሕወሓት መሪዎች የሚያስተላልፉት መልዕክት አልዎትን?

መልስ፥ አዎ አለኝ፥
(1) ጓድቼ! በርግጥ የምትውዱኝና ነፍሴን ማስደሰት ከፈለጋችሁ ያቺን አገር ሱማሌ ወይም አፍጋኒስታን ሳታስመስሎት ሥልጣን እንዳትለቁ
(2) የአዜብ ነገር አደራችሁ (3) ሓወልቴን በዚያች አገር መዲና በ (አ.አ) እንዳትተክሉ፤በፍላጎትም ሆነ በግድ እናንተ ሥልጣን ለቃችሁ በአማራ ሲተካ በመድሻና በዶማ ያፈራርሱታል። የእኔን ሓውልት ለዚያች አገር ሕዝብ ምኑም አይደለም፤ ስለሆነም ሓውልቴ በመቀሌና በአደዋ ትከለሉኝ።

የጋዜጠኛው ስንብት፥ ለትብብሮ እያመስገንን በሚቀጥለው የቴላፓቴ (telepathy) ቃለመጠይቅ (interview) እስክንገናኝ ነፍሶ (soul) በድህና አ/ይሰንብት።


§         [telepathy ፡ የሩቅ ቀልባዊ የመንፈስ ግንኙነት]

ታጠቅ መንጂ

Wednesday, September 4, 2013

የሙስናው ጉዳይ

በተንጣለለ ቪላ ውስጥ ከበድ ያሉ እንግዶች "ጸዳ" ባሉ ምግብና መጠጦች እየተስተናገዱ ነው። ታዋቂ ግለሰቦች፤ ባለስልጣናት እና አርቲስቶች የቀረበላቸውን ብፌ በልማታዊ ወጋቸው እያወራረዱ ሳሉ አንድ እንግዳ ነገር በመሃላቸው ተከሰተ። ሞቅ ባለው የአይቴ ነጋ ገብረእግዚአብሄር ድግስ ላይ ያልተጋበዙ ሁለት ሰዎች ዘው ብለው ከግብዣው ክፍል ገቡ። የፌዴራል ፖሊስ አባላት ነበሩ።

በዚህ ያልተለመደ ክስተት የአቶ ነጋ እንግዶች አልተደናገጡም ነበር። ይልቁንም የፌዴራል ፖሊሶቹ ለተጨማሪ ጥበቃ የመጡ ነበር የመሰላቸው። አንድ ብርጌድ ያህል ጦር አስከትለው የመጡት ፖሊሶች ግን አቶ ነጋ ገብረእግዚአብሄርን አስጠሯቸው። አቶ ነጋም ለጥሪው እንደወትሮው በመወጣጠርና ፍጹም ትእቢት በተሞላበት አነጋገር ምላሽ ሰጡ። በፖሊስ አባላቱ እና በአቶ ነጋ መካከል የሃይለ-ቃል ልውውጥ ተጀመረ። እሰጥ እገባው አንድ፣ ሁለት እያለ ሄደና በመጨረሻ ተካረረ። በዚህ ሰዓት አቶ ነጋ ስልክ መደዋወል ያዙ። ከፍተኛ የሚባሉ ባለስልጣናትና ምኒስትሮች ደወሉ። ከዚያም በመቀጠል፣ ጀነራሎች ደወሉ... የጦር መኮንኖች፣ የፓርቲ ባለስልጣናት...ሁሉም ተደወለ። የባለስልጣናቱ ምላሽ ግን ጥሩ እንዳልነበር ከአቶ ነጋ ፊት ላይ ይነበብ ነበር። ወዳጆቻቸው ሁሉ እንደ ቱኒዚያው ቤን አሊ በአንድ ጊዜ ከዷቸው።

"በል - - ውጣ!" አለ አንደኛው የፖሊስ አባል፣ የስልኩን ሽርጉድ በጥሞና ከተከታተለ በኋላ።

"ምን ማለትህ ነው? እኔኮ ነጋ ነኝ። ነጋ ታሪኩ!" አሉ። አነጋገራቸው የጀምስ ቦንድን ይመስል ነበር። በዚህ ጊዜ ታዲያ እጃቸውም አላረፈም። ከጎን ያሸጎጡትን መሳርያ ለማውጣትም ዳዳቸው።

በቅጽበት ግን ፌዴራል ፖሊሱ ቀደማቸው። በድንገት "!" የሚል ድምጽ አዳራሹን አናጋው። የፖሊሱ አይበሉባ የግራ መንጋጭላቸው ላይ ሲያርፍባቸው ጊዜ፤ አይቴ ነጋ ነገር አለሙ ተደበላለቀባቸውና እጅ መስጠትን መረጡ። ግብር ሊያበሉ በጠሯቸው የክብር እንግዶቻቸው ፊት፣ ከዚህ በላይ መዋረድ አልፈቀዱም። ሁለት እጃቸውንም ወደ ፖሊሱ በመዘርጋት ለብረት ማሰርያው
ራሳቸውን አመቻቹ። እጃቸው የኋሊት ከተጠፈረ በኋላም አቶ ነጋ እንዲህ አሉ። "በቃ! ህወሃት አበቃለት!"

"ባለሃብቱ" በዚህ ሁኔታ በፖሊስ መኪና ተጭነው ወደ እስር ቤት ሲሄዱ፣ ተጋባዥ እንግዶቹም እግሬ-አውጭኝ እያሉ ከስፍራው አፈተለኩ። ይህ ታሪክ ድራማ ሊመስል ይችላል። ግን በእውን የተፈጸመ ሃቅ ነው። ታሪኩን ያጫወተኝ ሰውም እዚያ ግብዣ ላይ ግብር ሊበላ ተገኝቶ ነበር። እንደ አግራሞቱም "ይህ መቼም የፈጣሪ ስራ ነው።" ከማለት ውጪ ስለ ጉዳዩ እንድምታ የሰጠው ማብራሪያ የለም።

ነጋ ገብረእግዚአብሄር የነፃ ትሬዲግ ኃላፊነቱ የተወሰነ (ሰዎች ያልተወሰነ ይሉታል) የግል ማህበር ባለቤት ነበሩ። ድርጅታቸውም እንደስሙ ከሁሉም ነገር ነጻ ነበር። ከግብር ነጻ፤ ከቁጥጥጥር ነጻ፤ ከፍተሻም ነጻ። በመቶዎች የሚቆጠሩ የጭነት መኪናዎች እቃ ጭነው በየኬላው ሳይፈተሹ እንዲያልፉ የተሰጠ ልዩ መብት ሁሉ እንደነበራቸው ይነገራል። ዛሬ ፈጣሪ ሲፈርድባቸው በኢፍትሃዊ መንገድ ቢልየነር ያደረጋቸው ስርዓት፤ ያው ስርዓት ሰለባ አደረጋቸው... ነጋ ገብረእግዚአብሄር ለአቶ መለስ ዜናዊ እና ለባለቤታቸው ለወ/ አዜብ መስፍን ቅርብ - በጣም ቅርብ ነበሩ። ለጉምቱ ባለስልጣናት ይሰጡት የነበረው እጅ መንሻ ከዚህ አይነት ውርደት እና እስራት ሊያድናቸው አልቻለም። በትግራይ ውስጥ 40 ሚሊየን ብር በላይ አውጥተው በስማቸው ያሰሩት የቴክኒክ ኮሌጅም እንደ ውለታ አልተቆጠረላቸውም።...

ይህችን አጭር መጣጥፍ ለመጫር እንደተቀመጥኩ አንድ ዜና በኢሜይል ደረሰኝ። የዜናው ርእስ "ጀነራል ባጫ ደበሌ የአዋሽ ባንክ ሰራተኞችን ከሥራ እንዲባረሩ አደረጉ!" ይላል። ባጫ ደበሌ የባንክ ሰራተኞቹን ያባረሩዋቸው ‘’እኔ ጀነራል ባጫ ደበሌን እንዴት አታውቁኝም?’’ በሚል በሰራተኞቹ አለመታወቃቸው አበሳጭቷቸው ነበር። ወደ ፌስ ቡክ ጎራ ስልም አንዳንዶች በዜናው ላይ ሲወያዩ አስተዋልኩ። ይህ እኮ አዲስ ክስተት አይደለም። ለብዙ ጊዜ የሚደጋገም እና የተለመድ ነገር ዜና ሊሆን አይችልም። ውሻ ሰውን ሲነክስ ዜና አይሆንም። በተቃራኒው ግን ሰው ውሻን ከነከሰ ዜና ይሆናል። እንዲህ አይነቱ ክስተት ስር የሰደደ የስርዓቱ ባህርይ ነው። ባጫ ደበሌ እነዚያን ሰዎች ማስገደል የሚያስችልም ስልጣን እና መብት ያላቸው የአዜብ ሰው መሆናቸውን አንዘንጋ። ጀነራል ባጫ በተልእኮ ትምህርት ከአንድም ሁለተኛ ዲግሪ እንዲገዛላቸው ካደረጉ በኋላ፣ ለምርቃታቸው ስነ-ስርዓት፣ ሰንጋዎች ጥለው፣ የሙዚቃ ባንድም አስመጥተው፣ መንገድ ሁሉ እንዲዘጋ አድርገው ሲያበቁ፤ በተለመደው ብሬክ ዳንሳቸው መንደሩን የቀወጡ ሰው ናቸው። በብርሃን ፍጥነት ከኪነት ጓድነት ወደ ጀነራል የተሸጋገሩት ባጫ ደበሌ በመደበኛ የስራ ጊዜያቸው ጫት ይነግዳሉ። በትርፍ ጊዜያቸው ደግሞ በዜጋው ላይ እንዲሁ እንደዋዛ እየቀለዱ እስካሁን አሉ። የነገውን አንድዬ ብቻ ነው የሚያውቀው። የፍትህ ሳይሆን የግለሰቦች የበላይነት የሰፈነበት ሃገር ስልጣንን ያላግባብ መጠቀም ሙስና ሊደንቀን አይገባም። የፍትሃዊ ስርዓት መጥፋት ነው ሙስና።

ፕሮፌሰር አል ማርያም ባለፈው መጣጥፉ ስለሙስና ሲጽፍ ከሙስና ሁሉ በላይ ሙስና የሚሆነው የፍትህ መጓደል እንደሆነ አስነብቦናል። የፍትህ መጥፋት ስብእናን፣ ነጻነትንና ንብረት ማጣትን ያስከትላልና። In my view, denial of due process (fair trial) is the highest form of corruption imaginable in the “justice sector” because it results in the arbitrary deprivation of a person’s life, liberty and property. (Al Mariam)

ከሰሞኑ ደግሞ ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም ምንጩ ያልታወቀ ሃብት አፍርተሃል በመባል ተወንጅሎ ወህኒ የወረደው የወልደስላሴ ወልደሚካኤልም ዜና በስፋት እየተሰራጨ ነው። ወልደስላሴ ሌላኛው የአዜብ መስፍን የቅርብ ሰው ነበር። በዚህ ጉዳይ ላይ ዳዊት ከበደ በስፋት ትንታኔ ስለሰጠበት እዚህ ላይ አልደግመውም። ወልደስላሴ ግን ከህወሃት የጫካ ትግል ጀምሮ ቀልፍ ቦታዎች ላይ ተመድቦ የሰራና - የመለስ ቀኝ እጅ የነበረ ሰው ነው። ታማኝ አገልጋይም ስለነበረ በህወሃት ውስጥ ወሳኝ ቦታ ነበረው።

ከወልደስላሴ እስር በኋላ ብዙዎች በህወሃት ውስጥ ውጥረት እንዳለ መናገር ጀምረዋል። ውስጥ ለውስ እየተንከባለለ ያለው ውጥረትማ ከከረረ ትንሽ ዘግየት ያለ ይመስላል። በውጥረቱ የተነሳም በባለስልጣናቱ መካከል እርስ በርስ መተማመን ከጠፋ ቆየ። አንድ ውስጥ አዋቂ ስለዚህ ሁኔታ ሲያጫውተኝ አባላቱ በምሽት ሲወጡ እንደ ጅብ ጎን ለጎን ነው የሚሄዱት። ጅብ ስለሚፈራ ብቻውን አይሄድም። ሁሌም ተጠራርቶ በቡድን ይሄዳል። ከባልንጀራው ጋር አብሮ ሲሄድ ደግሞ ጎን ለጎን መሆን አለበት። ፊትና ኋላ ከሆኑ እርስበርስ ይበላላሉ።

በአሁኑ የህወሃት አሰላለፍ ግን አንደኛው ወገን ከኋሊት መጥቶ የቀደመ ይመስላል። ከፊት ያለው የኋላውን መብላት ጀምሯል። ተገላቢጦሽ የሆነው ይህ አስገራሚ ክስተት ነው ውጥረቱን ይበልጥ ያከረረው። የአዜብን ቡድን የማጥፋቱ ሂደት ላይ ግን ከፍተኛ ጥናት ሳይደረግ አልቀረም። የፖለቲካ ሃይል አሰላለፉ ላይ ሚዛን የደፋው አንደኛው ቡድን ከደሙ ንጹ ባይሆንም የሙስናውን ወንጀል ለብቀላ መጠቀምያ ማድረጉ የአደባባይ ምስጢር ነው።

አንዳንድ የዋሆች ታዲያ ይህ የጸረ-ሙስና ዘመቻ አቶ መለስን ለማሳጣት እየተደረገ ያለ ድራማ እንደሆነ ይናገራሉ። አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝንም የሚያመሰግኑም አልጠፉም። አቶ ሃይለማርያም ብዙውን ክስተት እንደ ተራው ሰው በዜና እንደሚሰሙ የሚያውቁት በቅርብ ያሉት ሰዎች ብቻ ናቸው። ለነገሩ እሳቸውም አስቀድመው "የእኔ ስራ ከፊትም ሆነ ከኋላ የሚሰጠኝን ትእዛዝ እየተቀበሉ ማስፈጸም ብቻ ነው።" ብለዋል። ከፊትና ከኋላ ብቻ ሳይሆን ከላይና ከታችም መመርያ እየተቀበሉ ያስፈጽማሉ። በሙስናው ስም የሚካሄደው ጨዋታ ከሳቸው ራዳር ውጭ ያለ መሆኑን ለመረዳት የፖለቲካ ጥበብን አይጠይቅም።

አቦይ ስብሃት በአንድ ቃለ-መጠይቅ ላይ ስለዚህ ጨዋታ ሲናገሩ 10 ሚሊዮኑ ዘራፊ ቁጭ ብሎ 10 ሺው መታሰር የለበትም ብለው ነበር። አቦይ ስብሃት በሙስና ወንጀል ዋናው ተጠያቂ እንደሆኑ ቢታወቅም እውነት ብለዋል። ከሌላው ጋር ሲነጻጸር ከአቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ ቤት ተገኘች ተብላ በኢቲቪ ጭምር ስትታይ የነበረችው 26 ኢሮ ኢምንት ናት። Global Financial Integrity (GFI) በመባል የሚታወቀው አለማቀፍ የገንዘብ ግልጸኝነት ተቋም 2001 እስከ 2010 ብቻ ከኢትዮጵያ ተዘርፎ ወደውጭ የወጣው ገንዘብ 16.5 (አስራ ስድስት ነጥብ አምስት) ቢሊየን ዶላር ነው ሲል መረጃውን ከነማስረጃው ይፋ አድርጓል። ይህ ድርጊት ደግሞ በሙስና ከዘቀጡ ሃገራት ኢትዮጵያን በመጀመሪያው ደረጃ ላይ አስቀምጧታል። ልብ በሉ! 16.5 ቢሊየን ዶላር ከአራት በላይ "ህዳሴ" ግድቦችን ያሰራል። ከሁለተኛው አለም ጦርነት በኋላ መላው አውሮፓን ከውድቀት ያስነሳው የማርሻል ፕላን በጀት 20 ቢሊየን ዶላር ነበር። ከኢትዮጵያ በስምንት አመታት ጊዜ ውስጥ ብቻ የወጣው 16 ቢሊየን ዶላር ደግሞ አፍሪካ ካለችበት ውድቀት ሊያስነሳት የሚችል ገንዘብ እንደሆነ የኢኮኖሚ ጠበብት ይናገራሉ።

.. ኢንተርናሽናል የተባለው የማድሪድ ጋዜጣ / አዜብ መስፍን በአንድ ቀን ግብይት ብቻ ለልብሷ 1.5 ሚሊዮን ዶላር እንዳወጣች ዘግቧል። አዜብ መስፍን ባለፈው የህወሃት ስብሰባ ላይ ተገኝታ ስትናገር ግን የአቶ መለስ የወር ደሞዝ 250 ዶላር እንደሆነ ነበር የተናገረችው። አዜብ 1.5 ሚሊዮን ዶላር ልብስ በአንዲት ምሽት ስትሸምት መንግስት ድጎማ አድርጎላት ከሆነ ይኸው በይፋ ይነገር። 250 ዶላር የወር ገቢ በሚሊዮን ዶላር ወጪ ማድረግ የሚቻልበት ሚስጥር የአባባ ታምራት ገለቴ ምትሃት ካልሆነ ታዲያ ምን ሊሆን ይችላል? ይህንን መራራ ሃቅ የጸረ-ሙስናው ኮሚሽንን የሚነዳው ቡድን እንዴት ችላ ሊለው ቻለ? በዚህ ጉዳይ ላይ በርካታ ታዛቢዎች የሚሰጡት አስተያየት የሚያስኬድ ይመስላል። ቡድኑ በቅድሚያ ወደ እነ አዜብ ሰፈር የሚወስደው መንገድ ላይ ያሉ ከእንቅፋቶችን ሁሉ ማጥራት አለበት።

በዛሬይቱ ኢትዮጵያ እንደ ቀልድ የሚነገሩ አንዳንድ እውነታዎች ለማመን የሚከብዱ ናቸው። አንዱ 'ልማታዊ ባለሃብት' በሪል ስቴት ስም የተመራው ቦታ ሲሰላ ከጅቡቲ የቆዳ ስፋት በልጦ ተገኘ። ይህ ሰው ትንሽ ቆይቶ ህገ-መንግስታዊ መብቱን በመጠቀም የመገንጠል ጥያቄም ሊያነሳ ይችላል እያሉ ያወሩ ነበር - በዚያ የቀኑት ባልንጀራዎቹ። በመጨረሻ ግን "ባለሃብቱ" በሙስና ታሰረና ይዞት የነበረው መሬት ለነ ቱሬ ዘመዶች በሄክታር ሁለት ብር ሂሳብ ተቸበቸበ። ለነገሩ 3.5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ከዜጋው እየተቀማ ለውጭ ዜጎች በተቸበቸባት ሃገር ይህ ምንም ላይደንቀን ይችላል።

የሙስና ሰለባ የሆነው የሌላኛው ባለስልጣን ቤት ሲበረበር ደግሞ ብሄራዊ ባንክ ይመስል ነበር። እዚያ ቤት ውስጥም የአለም መገበያያ ገንዘብ ተገኘ። ዶላር፣ ኢሮ፣ ድራም፣ የን፣ ፓውንድ፤ ክሮን፤ ፍራንክ፣ ዲናር፣ ረንቢኒ ... እንዲያውም የኤርትራ ናቅፋ በገፍ ነበር። ከአቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ 26 ዶላር ተጋንና በቲቪ ስትቀርብ የዚህኛው ንግድ ፈቃድ የሌለው ባንክ በግል እጅ ሲገኝ ሜዲያም ዝም ማለትን መረጠ። በዚህ ጊዜ ነበር የአሳሪው ቡደን ሃላፊ የኮሎኔል መንግስቱን ንግግር የተጠቀመው። "ደፍረውናል፣ ንቀውናል።.. ብታምኑም ባታምኑም በቁም ሞተናል።"

አነጋገሩ ለምን ሃገር ተዘረፈ ሳይሆን እኛ ታግለን ለዚህ የደረስን የቁርጥ ቀን ታጋዮች ቁጭ ብለን እንዴት ከኋላ የመጣው ሊበልጠን ቻለ ለማለት ነበር። የሙስናው ዘመቻ ድራማ ቁልፍ እዚህ ላይ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ወደፊት በሰፊው እሄድበታለሁ። ለአሁን ግን በአቶ ኤርምያስ አመልጋ የሚደነቅ ታሪክ ጽሁፌን ልቋጭ።

በዚያ ሰሞን የአክሰስ ሪል ስቴት ሥራ አስኪያጅና የቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት አቶ ኤርምያስ ጠቅል አመልጋ፣ በተለይ በውጪ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለመኖሪያ ቤት ግንባታ 1.4 ቢሊዮን ብር በላይ ከሰበሰቡ በኋላ፣ ከሃገር መጥፋታቸው ተዘግቦ ነበር። ታዲያ አቶ ኤርምያስን የሚረግሙ ጌጃ ዲያስፖራዎች እንዳሉ ሁሉ እሳቸውን የሚያደንቁም አልጠፉም። ስለአቶ ኤርምያስ በቀልድ እየተመሰለ ብዙ ነገር ይወራል። የተከበሩ ሎሬት አፈወርቅ ተክሌን እና አቶ ኤርምያስን የሚያመሳስላቸው ነገር ቢኖር ሁለቱም የተዋጣላቸው ሰአሊያን መሆናቸው ነው ተብሏል። ለላሜ ቦራው ዲያስፖራ እንዲሰሩ ገንዘብ የተከፈለባቸው ቤቶች ሁሉ ባማሩ ስዕሎች በወረቀት ላይ ዱቅ ብለዋል። በንዴት ገንዘቡን ሊያስመልስ የሚሄደው ሁሉ በስእሎቹ እና በአቶ ኤርምያስ ምትሃታዊ ንግግር እየተማረከ እንዲያውም ለሁለተኛና ሶስተኛ ቤት የከፈለው ዲያስፖራ ቁጥር ትንሽ አይደለም። አቶ ኤርምያስ በአንድ በኩል በሙስና ክስ እየተፈለጉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ከሃገር በቦሌ አድርገው እንዲወጡ የተደረጉ "ጀግና" ባለሃብት ናቸው።

ለፖለቲካው እንግዳ ለሆኑ ሰዎች፤ እነዚህ ሁሉ ፈጠራ ሊመስሉ ይችላሉ። ግን የኢትዮጵያ ህዝብ የእለት ተለት ገጠመኞች ውስጥ አንድ እጅ እንኳን የማይሞሉ እውነታዎች ናቸው።

ክንፉ አሰፋ