Saturday, June 14, 2014

ትውልድ ራሱን ከዘረኝነት ማራቅ ታሪካዊ ግዴታው ነው !

ትውልድ ራሱን ከዘረኝነት ማራቅ ታሪካዊ ግዴታው ነው !

ከጠባቦችና የግንጠላ አራማጆቸ ጎራ እንደሚስተጋባው ከንቱ ታሪክ አገራችን ኢትዮጵያ በድንገት የዛሬ መቶ አመት የተከሰተች ሳይሆን በብዙ ዘመናት የዜጎች መስዋዕትነት የተገነባች አገር ናት። ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ለማድረግ የብዙ ሚሊዮንና የአያሌ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ህይወት ተገብሮባታል። ይነሰም ይብዛም፣ ይጉላ ይደብዝዝ፣ ሁሉም ህዝብ ለዚያች አገር ግንባታ አሰተዋፅኦ አድርጉአል። በሌሎች አገሮች ታሪክም እንደተከሰተው ሁሉ በኢትዮጵያም ታሪክ ጦርነት የሀገር ግንባታው ሂደት አካል ሆኖ ተገኝቷል። በሂደቱ ለጠፋው ህይወትና ለደረሰው በደል የዛሬው ትውልድ ከቶም ተጠያቂ ሊሆን አይገባውም።

የዘመናት በደልና ቁርሾን ዛሬ ህይወት ሰጥቶ በማናፈስና በማመርቀዝ የህዝብ ግኑኝነትን፣ አነድነትና፣ ትስስርን ለማፍረስና ህዝብን እርስ በርስ ለማናቆር መጣሩ የተሳሳተ ብቻ ሳይሆን ወንጀልም ነው። ለነገሩማ ዛሬ ህፃን፣ ሽማጊሌ፣ ሴት ፣ወንድ ሳይለዩ በጭፍን ጥላቻ የሚጨፈጭፉ የሚያርዱና ገደል የሚጥሉ ሁሉ ያለፈ ታሪክን ገድል በመጥቀስ ከወንጀላቸው ነፃ ሊሆኑ አይችሉም።

ለሀገር አንድንትና ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር የሚካሄደው ትግልግቡ እንነዲደርስ ከተፈለገ ወጣቱ ትውልድ ዘረኝነትን (Ethno-Fascist, Ethno-Chauvinist)   ትምክህትን አንጋሽ፤ የቅኝ ገዥ ተስፋፊ ደጋፊ ልሂቃናት የፈጠሩት ህልዮ፤ አገርን በታታኝ. ከፋፋይ መሆኑን ተረድቶ መራቅና አንድነትን ለመጠበቅ መታገል ግዴታው ነው። በአንድ ፅንፍ የሚታየው ጎጂ አቋም ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ክዶ በመብት ሽፋን ግንጠላን አያራገበ በአሶሳ፤በአረካ፤ በአርባጉጉ፤ በሎቄ፤ በአሰቦት በበደኖ ፤በጋምቤላ፤ በቡርጂ፤ በቦረና፤ በጌዲዎ፤ወዘተ የተከሰቱ እልቂቶችን አስከትሏል። በዚህ ዘረኛ ጎጠኛ ቡድንና በመሰሎቹ እየተራገበ ያለው የአንድንት፣ የዘርና የሃይማኖት ጥላቻ እንዲሁም የክፍፍል እሳት ታሪክን እየካደ የዕርስ በርስ ግጭትን እያስፋፋ የአንድነትንና የአብሮነትን ስረ- መሠረት እየነቃቀለ ህዝብን በጎሳ፣ በጎጥ፣ በቛንቛን፣ በሃይማኖትን፣ ... ደረጃ በልቶና ሸንሽኖ አሽመድምዶ ለማጥፋት የሚደረግ የፀረ-አነድነት (Ideology Of Neocolonialism) ሴራ ነው።

ይህ የፀረ- ኢትዮጵያ ጽንፈኛ አቋም መገንጠልና ማስገንጠል በሚለው (Ideology Of Neocolonialism) ወያኔያዊ ተግባሩና መፈክሩ ይገለጣል። የሕዝብን ማንነትና የቆየ የጋራ ታሪክ ይሰብራል። በኢትዮጵያዊነት ላይ ሳይታክት ይዘምታል። ዘረኝነትን እንደፀጋ ተላብሶ፤ ለዴሞክራሲ አፍአዊ ግብርን እየከፈለ፤ ክፍፍልንና ጥላቻን ያነግሳል።

ሌላኛው ፅንፋዊ አቋም ደግሞ ራሱን እንደ የአንድነት አባውራ ሰይሞ በጥቅል መፈክር የውጭ ተልእኮን በድብቅ ለማስፈጸም ተጨባጭ ሁኔታን እየካደ በህሊናውም በጆሮውም ላይ የተኛና የነፃነት ፈላጊውን የህብረተሰብ ክፍል እያወገዘ ህዝቡ ምን እንደሚያስፈልገው እኛ እናውቅለታለን በሚል የወያኔን ዘረኛ የጥላቻ ፖለቲካ በመገልበጥ አንድን ህዝብ በጅምላ እያወገዘ ፈለግሁት የሚለውን አንድንተ ማጅራት ይመታል። በዘረኞች በጎጠኞችና በጨቋኞች ላይ እንደመዝመት ፈንታ ለጭቆና መፍትሔ የሚሹትንና የሀገረሰብ መብት ይከበር ያሉትን ክፍሎች በምሬት ያወግዛል። ስለሆነም ሁለቱም ከፋፋይና ጎጅ ፅንፎች ናቸው።

የሀገር አንድነትን ክግዛታዊ ክልል ባሻገር ከህዝብ ጥቅምና አንድነት ጋር በማዋሀድ ከገለፅነው የጠባቦቦች መጠቀሚያ የሆነውን ዘረኛ የጥላቻ አክራሪነት ልንሰብረው እንችላለን። ለሀገር አንድነት የሚደረገው ታሪካዊ ገድል ከዘረኞች (Ethno-Fascist, Ethno-Chauvinist) ጋር መፋጠጡ የማይቀር ሀቅ ነው። ስለዚህም ኢትዮጵያ እንድትዳከምና እንድትጠፋ ማለትም ህዝቧ በጎሳና በሃይማኖት ተከፋፍሎ ወደ ዕርስ በርስ አስከፊ ጦርነት እንዳይገባ የታሪክ ባለአደራ የሆነው ኢትዮጵያው ወጣት ትውልድ ቀን ቀጠሮ ሳይሰጥ ለነፃነት ሲል መደራጀትና መታገል ይገባዋል።

ሀገርን ከጥፋት ለማዳን እየተደረገ ያለው የትግል ተልዕኮ ስኬታማ ሊሆን የሚችለው የሀገር አንድነትን መድልኦ አልባ ከሆነ የሀገረሰብ መብት ጋር አጣምረን ይዘን ከተገኘን ብቻ ነው። የምንታገልላት ኢትዮጵያዊ የሀገረሰብ መብቱ፤ መላው  ሀገረሰባዊ እሴቶች (ቛንቛ፣ ሃይማኖት፣ ባህል...) ሙሉ በሙሉ ተከብረው፣ የሃገራዊ የጋራ እሴቶች ሆነው በሁሉም ተቀባይነት አግኝተው ተገቢው እውቅና፣ እንክብካቤ አግኝተው፤ የሚገባቸውን ሥፍራና ቦታ ሲያገኙ የሀገረሰቡ መብቶች ሁሉ ተከብረው ለዜጎች ሁሉ እኩል ሀገር ሆና ለምትገኝ ኢትዮጵያ መሆኑ በግልፅ ይታወቃል

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ህያው ሆነው ያሉና የሚቀጥሉ ናችው። ሆኖም በዘር፣ በጎሳ፣ በጎጥ፣ በቛንቛን፣ በሃይማኖትን፣...  አገር ከፋፋይ (Breakup and division of existing Independent State into small dependent neo-colonial states) ስርአትን አንጋሽ የሆነ (Ideology Of Neocolonialism) ርዮትን አንግቦ ለሀገር አንድነትን ጠንቅ በመሆን የሚታወቀውን ዘረኝነትን (Ethno-Fascist, Ethno-Chauvinist) አምርረን መታገል የኢተዮጵያና ኢተዮጵያዊነታችን ማንነት መገለጫ ግዳጃችን ነው። በመሆኑም ትውልድ እራሱን ከዘረኛ ርዮት አንጋሽ  አራማጅ  እራሱን አርቆ አገሩንና ሕዝቡን መታደግ ያለበት አሆነ መሆኑን አውቆ፣ በወያኔና ባባሪ ተባባሪ እኩይ ድረጅቶች ደጋፊ ሕሩያን አማካኝነት፤ እለት ተለት በሰረበተ ዲስኩር (Sychopatic Statement) ቀንብበው፤ ፈብርከው በሚፈጥሩት፤ ስነኳፍ፣ ዘረኝነትን አነጋሽ አጀንዳዎች ሳይጠመድ፤ በጋረ ለጋራ ሀገርና ሕዝብ የነፃነት ትግል ተነሳሽ በመሆን፤ ትውለድ በፅናት በቆራጥነት ተደራጅቶ እራሱን ከዘረኝነት አጽድቶ የድረሻውን፤ የበኩሉን  ታሪካዊ ድርሻ የሚያበረከትበት ግዜ ዛሬ መሆኑን፤  ጠንቅቆ ሲያውቅ ብቻ ነው።



ድል ለኢትዮጵያ!!!

Friday, May 9, 2014

THE HUMAN RIGHTS SITUATION IN ETHIOPIA CONTINUES TO WORSEN

As the United Nations Human Rights commission prepares to evaluate and assess the records of the regime in Ethiopia this same repressive regime has been busy

·        Arresting journalists;
·        Beating up bloggers;
·        Engaging in land grab activities and thereby removing farmers from their lands and forcefully resettling them elsewhere;
·        Killing students who protested peacefully;
·        Murdering people in Gondar who said No to the expropriation of their lands and houses;
·        Trafficking children in an ill-disguised scam and profitable operation called adoption;
·         Trafficking young girls to the Middle East unto domestic slavery;
·         Keeping more than 40,000 dissenters behind bars and in labor camps;
·         Repressing (Gambella,the Ogaden,etc) and engaging in ethnic cleansing of Amharas;
·         Fanning ethnic and regional conflict between the people;
·         Engaging in massive corruption involving billions;
·         Trampling on due process of law and the elementary notions of democracy;
·         Forcing citizens into exile;
·         Collaborating with Sudan, Kenya and Djibouti to harass and hurt refugees;
·         Condoning child prostitution, genital mutilation, and preteen marriages and violating the rights of women and children as a whole.


Torture is systematic and brutal. Ethnic discrimination is regime policy and choice. Dissidents are kept in notorious prisons like Kaliti, Zwai, Dedesa and Bir Sheleko not to mention secret/ghost prisons which are not accessible to foreign observers. The Addis Abeba regime has issued a decree against NGO and charity organizations making their work almost impossible. A sweeping and convenient law called a law against terrorism has been the justifying ground for the arrest and condemnation of critical journalists, writers and poets. Books are banned but not openly though effectively. Several independent journalists are in prison accused as terrorists because of their critical articles. The regime has banned opposition radios (most are jammed), blocked several web sites claiming political and security reasons and even gone as far kidnapping dissidents from neighboring countries. Several opposition organizations are deemed illegal and their leaders and members denied the chance to have legal existence in their own country. And yet the regime enjoys extensive support from the West because it is considered an ally in the so called war against Terror. In Somalia, where the regime has sent troops, it has been accused of atrocities.

The human rights record of the TPLF/EPRDF is dismal and worsening by the month. It has spent millions of dollars on lobbyists and so called human rights organizations that deny its violations and spin lies and false reports. To dupe others, it has set up its own human rights commission (the so called Inba Astebacki Committee or “Tears Wiping Away Committee” without dealing with the issue of why the people are weeping in the first place), which is a dead body by all accounts.

No freedom of the press and association. Complete totalitarian control of the civic society and the banning and dissolution of civic associations. Forcing people to make contributions to the regime’s pet projects ranging from building a dam to helping the so called Meles Zenawi Foundation. Economic injustice against the people with no wage increment for years in the face of 35% inflation, full control of the economy by State controlled companies, spreading famine and poverty. Child labor, the breakup of the health system, the ankruptcy of the education system all define the existing regime. A climate of fear and the reality of cruel repression exists. The country is on the brink of disaster in all aspects. The primary need for democratic governance and the respect of human rights is absent. The violation of human rights knows no bounds and the regime has arrogantly refused to give any explanation on the fate of the thousands of political prisoners, on that of the disappeared since 1991, on the conditions of its jails, prisons and labor camps, its routine trampling on due process and the rule of law.

The UN Commission on Human Rights should rise to the occasion and must condemn the regime for its illegality and violations.



BY SOCEPP

INJUSTICE ANYWHERE IS INJUSTICE EVERYWHERE
SOCEPP, 30 RIGA COVE, WINNIPEG,MB R2P 2Z7,CANADA


E MAIL: SOCEPP @AOL.COM




ሰበር ዜና- የዞን 9 ጦማርያን በማዕከላዊ እስር ቤት መደብደባቸውን እናበውስጥ እግራቸው ላይ ግርፋት መፈፀሙ ታወቀ


''የዞን 9 ጦማርያን ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል
የዞን 9 ጦማርያንን የጊዜ ቀጠሮ ሊያይ ተሰየመው ችሎት ዛሬ ሌላ አሰቃቂ ዜና አብሮ ሰምቷል፡፡ ሁለቱ የዞን9 አባላት በፍቃዱ ሃይሉና አቤል ዋበላ በማእከላዊ መመታታቸውን እና ውስጥ እግራቸው ላይ ግርፋት እንደተፈጸመባቸው የገለጹ ሲሆን ፓሊስ ማስረጃ የላቸውም ሲል ተከራክሯል፡፡ ለክርክሩ ምላሽም ውስጥ እግራቸውን ለፍርድ ቤቱ ማሳየት እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ቶርቸር ህግ መንግስታዊ አይደለም ሲል "አስተያየቱን" ሰጥቷል፡፡ እነደትላትናው ሁሉ በተመሳሳይ ምክንያቶች የተነሳ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው ሲሆን ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ 10 ቀናትን ለምርመራ ፈቅዶአል፡፡
በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ለተከሳሾቹ ጭብጨባ እና ፉጨት ማሰማት የተከለከለ ሲሆን ተከሳሾች ሲወጠ ባሳዩት አጋርነትም ከዛሬ በሁዋላ ካጨበጨባችሁ እነዳትገቡ እናደርጋለን የሚል ማስፈራሪያም ተሰጥቷል፡፡ / ስንታየሁ የተባሉ የሬጅስትራር ሰራተኛ ጭብጨባውን እና ፉጨቱን ለዳኛ በመንገር (በተለመደ ቋንቋ በማቃጠር) አጋርነት እያሳዩ የነበሩትን ወጣቶች ተግባር ለማስቆም ሞክረዋል፡፡
ዞን 9 በድጋሚ የዞን 9 አባላት ያወሰድዋቸው ምንም አይነት የአሸባሪነት ስልጠና እንደሌላ እያረጋገጠ በህገ መነግስቱ አንቀጽ 18 መሰረት ማንኛውም ሰው ጭካኔ የተሞላበት ኢሰብአዊ ከሆነ ክብሩን ከሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት የመጠበቅ መብት አለው ቢልም በታሰሩ አባላቶቻችን ላይ የደረሰውን ግርፋት አጥብቆ ያወግዛል።''  ይላል ዜናው።