ኢትዮጵያ
ነጻ ሀገር ሆና የራሷን መንግሥት በመመስረት ከታወቀችበት ዘመን
አንስቶ፤ መሪዎቿ ፤ በቀናዒነት ሀገሪቱን ከውጭ ወራሪ
ኃይሎች ሲከላከሏት ቆይተዋል። በየዘመናቱ
ወረራው ቢመጣባትም፤ ሁሉንም ከሕዝቡ ጋር በመሆን እየተዋጉ መልሰውታል። የዚህም
ዋና አብነት፤ መሪዎችና ዜጎች መተባበራቸው ነበር።
በገዥዎቹና በመሪዎቹ
መካከል የነበረው ግንኝነት
ፍጹም ዕጹብ- ደንቅ ነበር ማለት ባይቻልም፤ በሀገር ነጻነትና ሉዋላዊነት ረገድ
ግን፤ ነፋስ የማይገባበት ውኅድትና ትብብር ነበረ ማለት ያስደፍራል። የጋራ ሀገራቸውን ለማዳን ኃይላቸውን አስተባብረው መቆም
አማራጭ እንደ ሌለው አበክረው አውቀውና ተረድተውት ነበር
ማለትም ያስችላል። የሕዝብና የመሪዎች በአንድ መንፈስ መቆም ደግሞ፤ ሀገሪቱ
ከቅኝ ገዥዎች ወረራ እራሷን ተከላክላ እንድትቆይ አስችሏታል።
የውጭ
ወራሪዎች ከተባረሩ በኋላ ግን ገዥዎች ሕዝቡን እየጨቆኑ መግዛታቸውን ይቀጥሉበታል። ሕዝቡም
የመከራ ቀንበሩን እንደተሸከመ
መራራ ኑሮውን ይገፋል። ለሀገር መሥዋዕት ለመቆም፤ በቤተ መንግሥት ውስጥ ጮማ እየቆረጠ ጠጅ እያንቆረቆረ በሚቀማጠለው
ልዑልና የእለት ጉርሱ የዓመት ልብሱ ባረረበት ገበሬ መካከል፤ ብዙም ልዩነት ባየካሰትም ፤ የመሥዋዕቱ ክብደት የሚመዝነው ግን በአርሶ-አደሩና በተራው ሕዝብ ህይወት ላይ ነበር ማለት ይቻላል።
ኢትዮጵያ
በዘመናት ነጻ ሀገር ሆና እንድትኖር ካበቋት
ዐበይትና መሠርታዊ ነገሮች አንዱ፤ ዜጎቿ የሀገራቸውን የውስጥ ምሥጢር መጠበቃቸው
ዋናው አብነት ነበር። " ምሥጢርክን
በጉያ ስንቅህን በአህያ ! " የሚለው
ግንዛቤ፤ የዚያን ጊዜ ነዋሪዎች፤ሀገራዊ ባኅልና ጠበይ ነበር። የሀገርን መሥጢርና የውስጥ ገመና እንኳንስ ለውጭ ጠላት አሳልፎ መስጠት ቀርቶ፤ እርስ በእርሱም ቢሆን በአደባባይ አውጥቶ መውያየት ብልኅነት አልነበረም። ጸያፍና እንደ ነውረኝነትም ያስቆጥር
ስለነበር፤ ሁሉም
ዜጋ የየራሱን ክብርና ስበዕና ለመጠበቅ ሲልም ጭምር፤ በአደባባይ ላለመዝረክረክ ብርቱ ጥንቅቄ ያደርጋል። ይህ ብሄራዊ / ኢትዮጵያዊ ባኅርይና
ሥነሥርዓት፤ ለባዕዳን
ወራሪዎችና ለሌሎቹም
የሀገሪቱ ባላንጣዎች እንዲሁም፤ በጠቅላላው፤
የኢትዮጵያን ውስጠ-
ምሥጢር ለማወቅ ሲያፈነፍኑ ለነበሩ
ሁሉ አስችጋሪ ሆኖ ቆይቷል። የሀገርን ውስጠ- ምሥጢር መጠበቅ፤ የውጭ ጠላት ሰርስሮ እንዳይገባ ለመከላከል የሚያስችል
ፍቱን መድህኒት ሆኖ ቆይቷል። የዛሬውን አያደርገውና !
አርበኛው
በዝቶ፤ ሀገር ወዳድ ሞልቶ- ተርፎ በነበረበት በዚያን ታሪካዊና አስደናቂ ዘመን፤ የሀገር ውስጠ- ምሥጢር ተጠብቆ ቆይቷል።
ያም ሲባል፤ ቁጥራቸው ግምት ውስጥ የማይገባ ጥቂት ከሃዲያንና ለሆዳቸው ብቻ ያደሩ ሰዎች እንደነበሩ ደግሞ
መዘንጋት አይገባም። የዚህ ክስተት መኖሩ ደግሞ አያስደንቅም። ለምን
ቢባል ? በማንኛውም ኅብረተ ስብ ውስጥ
፤ "በያንዳንዱ 12 ሐዋርያት ውስጥ፤ አንዳንድ ይሁዳ ስለማይጠፋ"
ነው። እጅግ የሚያስደንቀው ግን፤ በአሁኑ በወያኔ ዘመን፤ የከሃዲያንና የሀገር ሻጩ ቁጥር እየበረከተ መምጣቱ ነው። ታዲያ ፤ " እያንዳንዱ ኅብረተሰብ የሚገባውን መንግሥት ያገኛል" የሚለውን ስላቅ ፤ ሙሉ ለሙሉ ለመቀበል ባይቻልም፤ ለአላፊ- ጠፊ ጥቅም ሲባል፤ ከሃዲውን ወያኔን የሚደግፉ ውህዳን ግብረ- ይሁዳ መብቅላቸው፤ ለስላቁ ማጠየቂያና መደላድል መሆናቸው ይበልጡኑ ያስገርመናል።
የአንድነት
ኃይሉ፤ ከነኝህ አይነቶቹ ምሥጢር ዘክዛኪዎችና ጥብቋቸውን
በየጊዜው ከሚለዋውጡ ክፍሎች ራሱን ካላጸዳ፤ ዉጤት ያስመዘግባል ተብሎ መጠበቅ፤ የኅልም እንጀራ ነው። በተለይም ደግሞ፤ ለመጣው መንግሥት ሁሉ ታማኝ አገልጋይ ለመሆን የሚገለባበጠው ሁሉ፤ ሀገርን ለማዳን በሚደረግው ትግል ውስጥ ዕምነት ሊጣልበት የሚገባ ሆኖ አልተገኘም። " ምሥጢር የባቄላ ወፍጮ አይደለም " እንዲሉ፤ ለወሬ ማጣፈጫ እንዲጠቅም ታስቦና
ሁሉን ያውቃል እባላለሁ ከሚል ከንቱ ውዳሴ በመነሳት ብቻ መነኛውንም ነገር
እንደ ቀዳዳ ስልቻ ማዝረክረክ የሚጠቅመው፤ የወያኔን ሥርዓት እንጅ ለማንም አይረዳም። በሀገርና
በሕዝብ ላይ ከባድ ጥፋት ከፈጸሙ በኋላ፤ የንሰሀ ጸጸት ቢያደርጉ፤ የጠፋችው ሀገር ልትመለስ አትችልም። ይሁዳ፤ በክኅደቱ ተጸጽቶ ራሱን በዛፍ ላይ ቢሰቅልም ቅሉ፤ ጌታውን ክርስቶስን፤ ከሮማውያን ስቅላት
ሊያድነው አልተቻለውም። " ልመና ሳሉ በቁመና ! " በመሆኑ፤ ኢትዮጵያን ከዘረኞች ጥፋት ማዳን የሚቻለው፤ ቀኑ
ሳይመሽ ዛሬ ሁሉም በቁሙ ተባብሮ በመቆም መሆኑን፤ ልቡ በክኅደት ያልተሰለበ ዜጋ
ሁሉ ያምንበታል ።
የወያኔ
አገዛዝ፤ እንኳንስ ከወዶ- ገባዎች በነጻ የሚጎርፍለትን ኢንፎርሜሽን አግኝቶ
ይቅርና፤ እንዲያውም በተጠናከረውና በሰላው የመረጃ መዋቅሩና አሰራሩ ጠላቶቹን እያጠቃ፤ ደጋፊዎቹን እያነቃ
የሚርበተበት ዘረኛ
ደርጅት ነው። የመረጃ
ተቋሙን ለማደራጀት የቻለው ደግሞ፤ በራሱ ክኅሎትና ብቃት፤ ችሎታና ጭንቅላት እንዳልሆነ የሚያውቅ ያውቀዋል። የኢትዮጵያን ብሄራዊ
ጥቅም፤ ለባዕዳን አለቆቹ አሳልፎ የሰጠ በመሆኑ፤ የራሳቸውን ጥቅም
እንዲጠብቅላቸው ሲሉ፤ ባዕዳን ኃይሎች፤ በሥልጣኑ እንዲቆይ የሚያስችለውን ነገር
ሁሉ በመፈጸም ላይ ናቸው።
ባዕዳን አለቆቹ ከሚረዱት ሁሉ ዓይነተኛው ጉዳይ ደግሞ፤ የኢንተሊጀንስ ወይም የስለላ ተቋማቱን በሁለንተናዊ ረገድ
ማደራጀት ነው፡፡ የስለላ ተቋማቱን ከማደራጀት አልፈው ተርፈው፤ በሥልጣና፤ በስለላ
መሳሪያዎች ግንባታ፤ በኤሌክትሮኒክስ ሳይንስና አሰራር ደረጃ ይተባበሩታል። ከራሳቸው
የኢንተለጀንስ ወይም
ስለላ ድርጅቶች ጋርም ያስተባብሩለታል። ተቃዋሚ ድርጅቶችንና ግለሰቦችንም እየተከታተሉ
ይይዙለታል። ፡የተቃዋሚዎቹንም እንቅስቃሴ ሁሉ የጠልፉለታል። የስለላ መርቦችንም በመዘርጋት፤በሁሉም የኢትዮጵያ ኅብረተስብ
ውስጥ ሰርስረው እንዲገቡ አድርገውለታል። ሰላዮችንም በሙያው
የተራቀቀ ችሎታ እንዲያገኙ ያሰለጥኑለታል። ኢትዮጵያን በማጥፋት ላይ የሚገኘው ወያኔ፤ ኢንተለጀንስን/ ስለላን
አስመልከቶ ፤
ከባዕዳን የሚያገኘው ርዳታና ትብብር፤ የሚያስርገም ሆኗል።
የተቃዋሚ
ድርጅቶች አለመተባበርና ያሰራራቸው ዝርክርክነት
ተጨምሮ፤ ለወያኔ የስለላ ሰራተኞች ሰርስሮ ለመግባት አመች ሆኔታን አመቻችቶላቸዋል። የሚያስገርመው ደግሞ፤ ይህንን የስለላ ጥቃት አሁንም ቢሆን፤ ተቃዋሚ ነኝ የሚለው ክፍል ሁሉ፤ የቱን ያህል እንደተገነዘበውና ምንስ
ያህል ጥንቃቄ እንደሚያደርግ በእርግጠኝነት ማወቅ አለመቻሉ ነው። ሰኔና ሰኞ የተገጣጠመለት ወያኔ ግን ሁኔታዎቹን ሁሉ
ለመጠቀም እንቅፋት አላጋጠመውም።
ሁኔታዎቹ
ሁሉ አሁን ባሉበት ደረጃ ይቀጥላሉ ማለት ግን አይደለም ። በዕርግጥም ይቀየራሉ ። ሁኔታዎቹን የሚቀይራቸው
ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ የተባበረ ትግል እንደሚሆን ደረትን ነፍቶ መናገር ይቻላል። የወያኔ የበላይ ጠባቂዎቹ ሁሉ፤ የማይበገረው የኢትዮጵያ ሕዝብ
ትግል መፋፋሙን ሲገነዘቡ፤ ወያኔን
አጋልጠው እንደ ነጋበት ጅብ እንደሚፈረጥጡ፤ በሌሎች ሀገሮች ተደጋግሞ የታየ ሀቅ ነው።
ለዚህም፤
የሶቪየት ኅብረትንና ደርግን፤ የግብጹን ሆስኒ ሙባረክና አሜሬካንን፤ የኢራኑን
ሻህ ባሃላቢንና አሜሪካንን እንደ
ታሪክ ማስረጃ ጠቅሶ ማለፍ ይቻላል። ባዕዳኑ፤ ዘለዓለማዊ ጥቅማቸውን
ለማስጠበቅ ሲሉ
ደግሞ፤ ከሚመጣው አዲስ አገዛዝ ጋር ሰልፋችውን እንደሚያስተካክሉ ልንጠራጠር አንችልም። ዋናው
ጥያቄ ግን፤ እረ ለመሆኑ፤ የኢትዮጵያን ዘላቂ ጥቅም የሚያስጠብቅላት ማን
ሊሆን ይችላል ? የሚለው ነው። ይህንን ጥያቄ መመለስ የሚገባው፤ ማንኛውም የሀገሪቱ ዜጋ መሆን እንዳለበት እናምናለን ።
የራስን ሀገር ጥቅም ለውጭ ባዕዳን አሳልፎ የሚሰጥ ቡድን፤ ኢትዮጵያ በታሪኳ ሲገጥማት ይኽ የአሁኑ የከፋ ሆኗል። እንደ እግር እሳት የሚያንገበግበው ግን፤ ያ ሁሉ መሥዋዕት ተከፍሎ፤ ዛሬ ሀገራችን በአስከፊ ሁኔታ ሆና ማየቱ ነው።
ይህ
ሀቅ እንዳለ ሆኖ ፤ እነኝህ የውጭ ኃይሎች፤ ከወያኔ ጋር እየተባበሩ፤ ይኽንን ተግባር የሚያከናውኑት፤ ሆን
ብለው አስበውበት ፤
የኢትዮጵያን ሕዝብ
ለመጎዳት ሲሉ ብቻ ነው ብሎ ለማለት ባያስደፍርም፤ ዛሬ
ወያኔን የሚደግፉትና የድርጊቱም አባሪ-ተባባሪ ለመሆን የወሰኑት ግን የራሳቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ መሆኑ ደግሞ የሚካድ አይደለም።
ዘላቂ
ጥቅማቸውን የሚያስጠብቅላቸውን ሁሉ በዘላቂ ወዳጅነት ደረጃ ያስተናግዳሉ ባይባልም፤ ወያኔን
ግን በጊዚያዊ አገልጋይነቱ ይጠቀሙበታል
እንጅ፤ አለቅነታቸውንና ሽርክናቸውን እስከ
ዘለቄታው ድረስ እንደማይዘልቁበት እናውቃለን። ይህንን ለማለት የሚያስችለውም፤ " ዘላቂ
ጥቅም እንጅ፤ ዘላቂ ወዳጅም ይሁን ዘላቂ ጠላት ብሎ ነገር የለም " የሚለውን
የምዕራባውያን የዲፕሎማቲክ
ይትብሃል ስለምንገነዘብ ነው። ያም እንዳለ ሆኖ፤ ወያኔ፤ ታማኝነቱን እያረጋገጠ ታዛዥነቱን
እስከቀጠለላቸው ድረስ፤
የበላይ ጠባቂዎቹ ሆነው እንደሚሰነብቱ መዘንጋት አይገባም። በወያኔና በባዕዳን ኃይሎች መካከል ያለው ግንኙነት የአለቃና ጭፍራ ቁርኝነት ነው ። ጌቶቹ ሲጠሩትና ሲያዝዙት፤ አቤት- ወዴት ብሎ ያሉትን መቀበል ነው። ይህ ባኅርይ ደግሞ ለማንኛውም ሀገር-ወዳድ ኢትዮጵያዊ የሚዋጥለት አይሆንም። ለዚህም
እኮ ነው፤ ሀገር ወዳድ መሪዎች በባዕዳን ኃይሎች የማይወደዱት።
በኢትዮጵያ፤ ሀገር
ወዳዶ መሪዎች እስካልበቀሉ ደርስ
ደግሞ፤ ሀገራችን ያልፍላታል ተብሎ
የሚታሰብ አይሆንም።
ይህንን ሀቅ የተገነዘበ ዜጋ
ሁሉ፤ ሀገር ወዳድ ዜጎችን እያበቀለ ማፍራትን አበክሮ ሊያስብበት ይገባል። በዚህ ረገድ ተስፋ የሚደረገውም
፤ በየዘመናቱ፤ ኢትዮጵያ ሀገራችን ዕውነተኞቹ ሀገር
ወዳዶች የሚፈልቁባት ሀገር በመሆኗ ነው።
እነርሱ
ደግሞ፤ ወደ መድረኩና ወደ ፖለቲካው ምኅዳር ሊመጡ የሚችሉት፤ እንደ "ዲዮጋን፤
በጠራራ ፀሀይ በፋኑስ ተፈልገው" ሳይሆን፤ እያንዳንዳቸው፤ ምግባራቸውንና ተግባራቸውን
፤ የሞራል ልዕልናቸውንና ታማኝነታቸውን በድርጊት ያስመሰከሩ እንዲሆኑ ይጠበቅባቸዋል ። እነኝህ ደግሞ ወላዲቷ ኢትዮጵያ በድባብ ትሂድ እንጅ ሞልተው ተርፈዋል ብለን
ማመን እንፈልጋለን። ባንጻሩ ግን፤ ሰው ያላወጣ ትውልድ፤ " የሰው
ያለህ!" እያለ
በመጮሁ ብቻ ሰው ሊወጣለት የማይችል መሆኑን መገንዘብ ይገባል። አርበኛንና ሀገር
ወዳድ ዜጎችን እያጠፉ አዲስ አርበኛን ማግኘት ያስቸግራል ። ምክንያቱም፤ እስካሁን እንደታየው ከሆነ፤ " የፊት ወዳጅህን ከፍነው በሻሽ፤ የኋለኛው እንዳይሸሽ
!"
ብለው እያዘኑ ያለፉትን ታላላቅ አርበኞች ታሪክ እየሰማን በማደጋችን ነው።
አርበኞች
እየበቀሉ በመሰዋት፤ የነርሱን ፈለግ የሚከተል ትውልድ እያፈሩ ካለፉ፤ የነርሱ መሥዋዕትነት ከንቱ ሆኖ አይቀርም። የመሥዋዕቶቹና የሰማዕታቱ ገድል ዉጤት አስመዝግቧል ለማለት
የሚቻለውም፤ ተተኪው
ትውልድ የነርሱን ዓርማ በማንሳት ሀገሩን ከጥፋት ለማዳን ሲችል ነው። ለዚህ ውጤት ዓብነት ከሚሆኑት መካከል ዋነኛው የራስን ምሥጢር እየጠበቁ የጠላት ሰላዮችን እየተከላከሉ ማምከን
ወይም ከጥቅም ውጪ ማድረግ ይሆናል። ምሥጢርህን በጉያህ ይባላል እንጅ ፤ አዝረክርክው አልተባለም!
በማንም ቀለምና ካባ የሚመጣ አምባገነን ለሥልጣኑ
መሠረት አድርጎ የሚጠቀምባቸውና ሕዝብንም
ለመጨቆን የሚገለገልባቸው ልዩ ልዩ የመጨቆኛ ማሳሪያዎች ይኖሩታል። በሕዝብ
የተጠላ በመሆኑም፤ የሕዝብን ተቃዉሞ ይፈራል። ሥልጣኑን እየጠበቀ ዕድሜዉን ለማራዘም ፤ የመጨቆኛ መሳሪያዎቹን አዘጋጅቶ
ማጠናከር የቅድሚያ አጀንዳው ወይም ተልኮው ይሆናል። የሕዝብ አመፅ በማንኛውም ወቅትና ሁኔታ ይነሳብኛል ብሎ
ስለሚሰጋ፤አመፁን ለማዳፈን ማንኛውንም የኃይል
ርምጃ ከመውሰድ አይቆጠብም። ይህን
ለማሳካት ሲልም፤ እራሱ ያወጣውንም ህግ ቢሆን እንኳ ከመጣስ ወደ ኋላ አይልም።
ዛሬ
በኢትዮጵያ የተዘረጋው
ዘረኛ ሥርዓት አራማጆች የሚፈፅሙትም ይህንኑ ነው። ለኅልውናቸው አስጊ የመሰላቸውን ሁሉ ለማጥፋት የዓለም አቅፍ ህጎችን ሁሉ በመጣስ ድንበር -ዘለል ውንብድናን ሳይቀር
ያካሂዳሉ።
የስለላ
ተቋሞቻቸውን የሚቆጣጠሩት
ከራሳቸው ብሄር የተውጣጡ አባሎች ናቸው። ዛሬ፤ በኢትዮጵያ የመንግሥት ታሪክ ተወዳዳሪ የማይገኝለትን ጸረ
ሕዝብ የኢንተለጀንስ ተቋምና የስለላ ድርጅቶችን የገነባው
ወያኔ ሆኗል። ለዐብነት የሚከተሉትን የኢንተለጀንስ አገልግሎት
ልዩ ልዩ ተቋማትን እንመልከት ፦
1.
በሕዝብ ደኅንነት ስም የተዋቀረው የወያኔ መረጃና ስለላ ድርጅት፤
2.
በናዚ ጀርመን ጌስታፖ አምሳያ የተደራጀው የፖሊስ /አጋዚ፤ፊዲራል...// ድርጅት ፤
3.
ወያኔ የጻፋቸውን የመጨቆኛና የመቅጫ ህጎችን እየተረጎሙ የሚበይኑ "ዳኛች"፤ የወያኔ ጠበቆችና "አቃቢ- ህጎች"
4.
ለምርመራና ማሰቃያ የተሰናዱ ዘመናዊ መሳሪያዎችና የስቃይ እስር ቢቶች......
- የሕዝብን አመፅ
ለመቋቋምና ለማፈን ሲባል
የሠለጠነ፤ የተደራጀና የታጠቀ ሠራዊትና ልዩ
ምሥጢራዊ አፋኝ ቡድኖች፤
- ፕሮፓጋንዳቸውን የሚያዘንቡበት
፤ መገናኛ ብዙሃንና
የኅትመት አገልግሎቶችን የሚጠቀሙባቸው
ተቋማት ሁሉ፤
- ኤሌክትሮኒክስ ሰርቬላንስ
ወይም ክትትል-ጠለፋ
(የስልክ፤ የኮምፒውተር፤ የሴል
ፎን መገናኛንና ራዲዮ
ጠለፋ፤ ወዘተ.)
- በኅብረትስቡ ውስጥ
ተሰግስጎ በመግባትና በብዛት
ሰርስረው በስውር የተቀመጡ
ሰላዮችና ወሬ አቀባዮች፤ ለነኝህ
ሁሉ ማንቀሳቀሻ የሚሆነው
ገንዘብ፤ ምን ያህል
እንደሚሆን ትክክለኛውን አሃዝ
በዕርግጠኝነት ቀርቶ በግምት እንኳን
ቢሆን ለመናገር የሚችል
አይኖርም። ምክንያቱም፤ ባጃቱ
ወይም ወጪው በብርቱ
ምሥጢር ስለሚያዝ ነው።
ያም
ሆኖ፤ በበርካታ መቶዎች ሚሊዮን ብር እንደሚሆን፤ የምሁር ግምቶች አሉ። ይህ ሁሉ የሀገር ሀብት የሚፈሰው ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ታጥቆ
ለተነሳ ዘረኛ ሥርዓት መጠበቂያ መሆኑ ፤ ታሪክ በሀገራችን ላይ በሚያሳየው ምፀት ላይ እንገረማለን።
ይህንን
ሁኔታ ባጭሩ ለመገንዘብ ከቻልን፤
ምን መደረግ አለበት ? በሚለው ላይ ትኩረት ሊደረግበት ይገባል
እንላለን። በበኩላችን
የሚከተሉት ነጥቦች
ቅድሚያና ትኩረት እንዲያገኙ ለሕዝብ
እናሳስባለን። ለተቃዋሚ
ኃይላትም ጥሪ እናስተላልፋለን ።
1.
የወያኔን የስለላ መረቦችን ለመከታተልና ለመበጣጠስ፦
ሀ. በመሀከላችን ሰርስረውና አድፍጠው የሚገኙትን ሰላዮቹ ማጋለጥና መንጥሮ
ማውጣት፤
ለ. በሁሉም የኅበረተስብ ውስጥ በተለያዩ ሽፋኖች ተመድበው የመረጃ ሥራ የሚሰሩትን ጠንቅቆ ማውቅና መለየት፤
እነኝህ ግለሰቦች ከየትኛውም ጎሳና ሙያ የተውጣጡ እንደሚሆኑ መረዳትና፤ ወያኔንን ከልብ ሊደግፉ ባይችሉም፤ ለጥቅም ብቻ ሲሉ ሀገርን ለመጉዳት እንደሚችሉ አለመዝንጋት፤
2.
የተቃዋሚ ክፍሎች ከወያኔ ሰላዮች ነጻ ያልሆኑ መሆናቸውን አውቀው አስፈላጊዉን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል።
የጓዳ ምሥጢር የሚያቀብሉ ውስጥ- አዋቂዎች የሚያስከትሉት ከባድ ጉዳት መሆኑን መረዳት እንዝኅላል ከመሆንያድናል።
3.
ከወያኔ ጉዳትና ጥቃት፤ የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ወይም የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪ ወይም የሃይማኖት ተቋማት ወዘተርፈ ይጮሁልናል ብሎ ማሰብ ከንቱ ምኞት መሆኑን ተረድቶ ራስን ጠብቆና በራስ ኃይል ብቻ ተማምኖ
መታገልና ሀገሪቱን ከጥፋት ማዳን። ሰሞኑን ፤ ወያኔ፤ በአንድ ስደተኛ ታጋይ ላይ የወሰደውን ድንበር -ዘለል ውንብድና
ያጢኗል።
4.
የሕዝብን የተባበረ የአመፅ ትግል የትኛውም የስለላና ድርጅትና የመረጃ ስምሪት እንደማያቆም መረዳት ይገባል።
ይህንን
ሀቅ አውቆ ተባብሮ መታገልና ሀገርንም ከጥፋት ማዳን አማራጭ የለውም! አሁን በሚታየው ዝርክርክነት፤ ሀገሪቱን ማዳን ይቅርና፤ ራስንም መከላከል አልተቻለም። ይህ
ጥቃትና ጉዳት በየአንዳንዱ ቤት
እያንኳኳ መምጣቱን የስሞኑ ድርጊት ተጨማሪ የማስጠንቀቂያ ደወል ሆኗል ።
"
ያልጠረጠረ ተመነጠረ " ነውና፤ ሰላዮችን እየጠረጠሩ፤
ጠላትን እየመነጠሩ መታገል ለድል ያበቃል !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኖራለች !