በ'ርግጥ ወያኔዎች ልቦና ገዝተው፣ ህሊናቸውን ፈትሸውና ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን እስከአሁን ማጥፋት እንዳልቻሉ አገናዝበው፤ የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ በመጠየቅ፣ሁሉን አቀፍ ለሆነ ዲሞክራሲያዊ ሽግግር ራሳቸውን ቢያዘጋጁ፤ ለሀገሩ ቅን የሚያስብ ሁሉ ደስታውን ባልቻለው ነበር። ደግሞም ማድረግ ካለባቸው ዛሬ ሳይሆን ትላንት ነበር፤ ትላንትም ባይሆን ዛሬ ነበር። አዎ....ትላንትም ዛሬም አላደረጉትም። የማንነት ባህሪያቸውና አላማቸው አይፈቅድላቸውምና።
ስለዚህም ተወደደም ተጠላ ወያኔን ለማስወገድ አስግዳጅ ሀይል መፈጠር ግድ ይሉዋል።
የሀገር ውስጥ ተቃዋሚዎችም ከፍርሀት ቆፈናችሁ ተላቃችሁ ለህዝብና ለሀገራችሁ ማንነታችሁን የምታሳዮበት ግዜ አሁን ነው። የትግሉ መነሻም ሆነ መድረሻ ለኢትዮጵያናዊያን በኢትዮጵያዊያን እስከ ሆነ ድረስ እንዳለፈው ግዜ "የከክልኝ-ልከክልህ" አይነት ቅንጅት/ካውንስል/ግ'ባር ሳይሆን፤ ለህዝብ ግልጽ የሆነና እውነተኛ ዲሞክራሲ፣ እውነትኛ አንድነትና ህብረት መፈጠር አለበት። ሀገርንና ትውልድን የማትረፍ ጥያቄ፤ ከወሬ፣ ከወረቀትና ከኢተርኔት ከፌስቡክ መፈክር አልፎ፣ እውነቱን በማውጣት፣ ራስን
በመፈተሽ፣ ካለፈው በመማርና 'ራስን ለክቡር አላማ ለመሰዋአትነት በማዘጋጀት፤…… 1ኛ/ ተግባር! 2ኛ/ ተግባር! 3ኛ/
ተግባር!.... ከሁላችንም ይጠበቃል።
No comments:
Post a Comment