Friday, February 15, 2013

ለመከላኪያ ለመከላኪያ ሰራዊት ሰራዊት ጥያቄ ጥያቄ አለኝ አለኝ…….? …….?



ከትእዝብት አድማሱ

      ሰሞኑን የኢትዮጵያ ቴለቨዥን ስከታተል ሶስት ድራማዎች ጎን ለጎን ሲካሄዱ ታዝቤአለሁ። አንደኛው 
ድራማ የመከላኪያ ሰራዊት ሳምንት በሚል እየተካሄደ ያለው ሰልፍና ኤግዚቪሽን ነው። ሁለተኛው ድራማ ጅሃዳዊ ሐራካት ፊልም በሚል ተደጋግሞ የቀረበው አስቂኝና አሳዛኝ ድራማ ነው። ሶስተኛው ድራማ ደግሞ የህወሓት 38 በዓል የትግራይ ህዝብ ልደት ነው እየተባለ በውጭና በሀገር ቤት ሲከበር ማየቴ ነው። በኔ አመለካከት ሶስቱም አላማቸውና ግባቸው አንድ ዓይነት ሆኖ ነው ያገኘሁት። አላማቸው በርዕደ መሬት እየተናወጠ ያለው ቡድን በህዝብ ፊት ሀይል (ጡንቻ) ያለው መንግስት መኖሩን ለማሳየት ሲሆን በሌላ መልኩ ደግሞ የአንድ ሞኖፓላዊ ድርጅት ጠባቂና ተከላካይ የሆነው የህወሓት ሰራዊት እየተባለ የሚነገርለትን መከላኪያ መልኩንና ቀለሙን በመቀያየር ኢትዮጵያዊ ሰራዊት መስሎ እንዲታይ እየተደረገ ያለው ጥረት ነው። ወጣም ወረደ የሶስቱም ድራማዎች ግብ የኢትዮጵያ ህዝብ ለመብቱ እንዳይተጋል በሀይል በማስፈራራት ከነሱ ውጭ በኢትዮጵያ ምድር ሌላ ተቀናቃኝና ለነፃነቱ የሚታገል እንዳይበቅል አንገቱን ለማስደፋት የተወጠነ ነው። ይህን ዓይነቱ የወያኔ የመንደር ደናቁርት ምትሃታዊ ተንኰል የወለደው የፈጠራ ተውኔት ደግሞ ባዶና ውሸት መሆኑን ኢትዮጵያዊ ቀርቶ ሌላም ጠንቅቆ ያውቀዋል።ውሸት ሲደጋገም ሓቅ ይመስላል”  ይላልና ስንክሳር መፅሐፋቸው። ወደ ተነሳሁበት ወደ ጥያቄዬ ልግባ፡- 10 ጥያቄዎች ናቸው። ልብ ብላችሁ ተከታተሉ፡………

1. ሰራዊቱየሕገ መንግስት ዘብ ነውእየተባለ በተደጋጋሚ ሲነገርለት እንሰማለን።  ለመሆኑ የተኛው ሕገ
መንግስት ነው? እውነት መከላኪያ ሰራዊት የሕገ መንግስት ዘብ ቢሆን ኖሮ የህዝብ ድምፅ በኃይል ሲነጠቅ፣ ሕገ መንግስቱ ለአንድ ሰው ብሎም ለአንድ ድርጅት መጠቀምያና መገልጊያ ሆኖ ሲቆር፣ የፍትሕና የዳኝነት ተቋማት ነፃነታቸውንና ውሳኔያቸውን በጥቂት መሪዎችና ካድሬዎቻቸው በግልፅ በአቋራጭ ሲነጠቅ ሲደፍርና ሲጣስ ለማን ነው አቤት የሚባለው? የመከላኪያ ሰራዊቱ ዘብነትና ህዝባዊነትስ የቱ ላይ ነው? ለመሆኑ ይህቺን ሚስኪን ሀገራችን ባለቤትዋ ማን ነው? እናንተ የሰራዊት አባላት የታጠቃችሁት መሳሪያም ሆነ የምታገኙት ጥቅምና ደመወዝ ከመሪዎቻችሁ ኪስ የወጣ ሳይሆን የህዝብ ገንዘብና የሀገሪትዋን አንጡራ ሀብት መሆኑን ትዘነጋላችሁ የሚል ጥርጣሬ የለኝም። ነገር ግን የመሳሪያችሁ አፈ ሙዝ ያነጣጠረው በማን ላይ ነው?

2. አሁን ያለው ሰራዊት ካለፉት ስርዓቶች የተሻለና ለሀገሩ ሉዓላዊነትና ለህዝብ ልዕልና የቆመ ነው እየተባለ ነጋ ጠባ ሲነገርለት እንሰማለን። ለመሆኑ ይችን ሀገር ከባዕዳን ወራሪዎች እየተዋጋ ክብርዋን በደሙ ጠብቆ ያቆያት ማን ነው? በአንፃሩ የሀገሩን ብሄራዊ ጥቅም፣ ዳር ድንበሩንና የባህር በሩን መጠበቅ አቅቶት የሻዕቢያ ባለሟል በመሆን መሬቱን ለባዕዳን አሳልፎ በመስጠት ሽባ ሀገር ያወረሰን የሃፄ ሀይለስላሴ ሰራዊት ነውን? ሌላ ቀርቶ የአውሮጳ ቅኝ ገዢዎች እንኳን ያን ያህል ያልደፈሩን በአሁኑ ዘመን ግን ከባዕድ ሀይል  (ከሻዕቢያ) ጋር ተመሳጥሮ ህዝባችንን ያስደፈረና ያስገደለ የሃፄ ኃይለስላሴ ሰራዊትና መንግስት ነውን?
 
3. የመከላኪያ ሰራዊት ከህዝብ አብራክ የወጣ፣ የህዝብና የሀገር ፍቅር ያለው የድል ሰራዊት ነው ሲባል
እሰማለሁ። ባንድ በኩል ያስቀኛል በሌላ በኩል ደግሞ ያሳዝነኛል። የሚያሳዝነኝ ባድመን ነፃ ታወጣለህ ተብሎ የዘመተው ሀይልና የተከፈለው መስዋእትነት ከንቱ ሆኖ መቅረቱ ነው። ጉዳዩ እስከ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ይድረስ እንጂ የመጨረሻ አሸናፊ ሆኖ የተገኘው ሻዕቢያ ነው። ሻዕቢያ ያሻነፈበት ምክንያት ደግሞ ሀቅ ስለያዘ ሳይሆን እናት ሀገራችን በፅናት የሚከራከርላት ቁርጠኛ ኢትዮጵያዊ ልጅ በማጣትዋ መሆኑን ማንም ይገነዘበዋል። ታዲያ የኛ መከላኪያ እውነት የሀገርና የህዝብ ፍቅር ያለህ ሰራዊት ከሆነክ ባድመ የማን ነው የሚል ጥያቄ አንስተህ ታውቃለህን? ከጥዋቱ ባድመ የኤርትራ መሆኑን የሚታወቅ ከሆነ ለምን ያን ያህል ደም እንዲፈስ ተደረገ? ብለህ መሪዎችህን ጠይቀህ ታውቃለህን?
 
4. የኤርትራ መገንጠል ሰላም ያመጣል ሲባል ነበር። ነገር ግን ባሰበት እንጂ አልበረደም። ሰሜኑ አሁንም
የጦርነት ቀጠና ነው። እስካሁንዋ ደቂቃ ድረስ ህይወት እየተቀጠፈ ይገኛል። ይህ ትራጀዲ መቋጫው መቼ
ነው ብለህ ትገምታለህ? በሰሜኑ ክፍላተ ሀገራችን አሁንም በየቀኑ በሻዕቢያ ታጣቂዎች እየታፈኑ የሚወሰዱትን በሽዎች የሚገመቱ ዜጎቻችን የት እንደደረሱ የሚታወቅ ነገር የለም። ዜጎቼ ናቸው ብሎ ጥብቅና የሚቆምላቸው አስታዋሽ ኢትዮጵያዊ መንግስትም ገና አልበቀለም። ታዲያ እናንተ የመከላኪያ ሰራዊት አባላት በዳር ድንበሩ አካባቢ በቀበሮ ጉድጓድ በምሽግ ተቀምጣችሁ በፍርድ ያለቀለትና የሞተ መሬት እየጠበቃችሁ መኖሩ ትርጉሙ ምንድን ነው? የራሱን ህዝብና ሀገር ድህንነትና ሰላም መጠበቅ ያልቻለ ሰራዊት የድል ሰራዊት ነው ሊባል ይችላል ወይ? በራሱ መሬት ላይ ዘላቂ ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ ያቃታው ሰራዊት የሌላ ሀገር ህዝብ ሰላም መጠበቅና ለፍትሕ መቆም ይችላልን?
 
5. የኢትዮጵያ መከላኪያ ሰራዊት የሀገርና የህዝብ ፍቅር አለው የሚለው አባባል ከነአቶ በረከት ስምዖን፣ አቶ ቴድሮስ ሐጎስ እና ሌሎች የአቶ መለስ ራዕይ ወራሾች ነን ከሚሉት መሪዎች አመለካከትና ፓሊሲ ጋር
የሚቃረን አይሆንም ወይ? አቶ በረከትበሰላሳ ዓመት ዕድሜ ክልል ያለው ወጣት ስለ ዳር ድንበርና የባህር
በር ጉዳዩ አይደለም ረስቶታልየሚሉ ናቸው። ሰራዊቱም በነሱ ራዕይና ፓሊሲ የቀረፁትና የሚመሩት እነዚህ ናቸው። ታዲያ የሰራዊቱ የሀገርና የወገን ፍቅሩ የቱ ላይ ነው?

6. የመከላኪያ ሰራዊት የልማት ምንጭና የዕድገት ተምሳሌት ነው እየተባለ ሲነገርለት እንሰማለን። በአፈ ሙዝ የሚገነባ ሀገር ቢኖር ኖሮ ሰሜን ኰሪያን በቀዳሚነት ልትጠቀስ ትችል ነበር። ነገር ግን አልሆነም። መሆንም አይችልም። በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ መከላኪያ የሙሱናና የዝርፊያ ተምሳሌት እንጂ የልማት ምንጭ መሆን አልቻለም ብለው በጭብጥ መረጃ እያስደገፉ የሚናገሩ ብዙ ናቸው። በትግራይ አካባቢ በህዝቡ ዘንድ መከላኪያ ማለትዱባይ ወይም ጅዳተብሎ እንደሚጠራም ጓደኞቼ ነግረውኛል። ምክንያቱም በመከላኪያ አካባቢ ወፍራም ዘመድ ያለው ሰው በአንድ ጊዜ ሚሊዮነር ሊሆን ይችላል የሚል ትእዝብት ስላላቸው ነው። ስለሆነም መከላኪያና ህወሓት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅ በሆኑበት ሁኔታ በየከተማው ፎቅ የሌለው ጀነራልና ኰኔሬል የለም ቢባል ውሸት አይደለም። ታዲያ ወገኖቼ የሀገር ልማትና ሌብነት አብሮ ይሄዳል ወይ?

7. በየዓመቱ በመቶ ሽዎች የሚገመቱ ወጣቶች ከየትምህርት ተቋማቱ እየተመረቁ በየቀኑ ስራ ፍለጋ ሲንከራተቱ ይታያል። ስራ አገኙ ከተባለ ደግሞ ከኰብል ድንጋይ ያለፈ አይደለም። ካላገኙ ደግሞ ወደ ስደት በመጉረፍ የባዕድ ሲሳይ ሆነው የሚቀሩ ወጣት ምሁራንና ባለሙያዎች ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። በአጠቃላይ በሀገሪትዋ ሙሱና ከኤይድስ የባሰ የሰደድ በሽታ በሆነበት ወቅት መከላኪያ ብቻውን የልማት ምንጭ የሚሆንበት መመዘኛ ምንድን ነው? ሌላው ባለሙያ እየበተኑና እያመከኑ መከላኪያ የልማት ማእከል እንዲሆን የሚደረግበት ሚስጢርስ ምን ይሆን?
 
8. ሌላው የታማኝነት ጥያቄ ነው። እርግጥ ነው አምባ ገነኖች ሰራዊቱን ሲቀርፁና ሲያዋቅሩ በአምሳላቸው ስለሆነ ከሀገርና ከህዝብ በላይ የመሪዎቹን ስልጣንና ድህንነት እንዲጠብቅና እንዲንከባከብ ይገደዳል። የኢትዮጵያ መከላኪያ በተመሳሳይ በነፃነትና በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ታንፆ ያደገ ሳይሆን በአቶ መለስ ዜናዊ አመለካከትና ለአንድ ድርጅት ፍላጎትና አላማ መገልገያ ተብሎ የተቀረፀ መሆኑን ራሳቸው የመከላኪያ ሰዎች እየተናገሩ ይገኛሉ። እውነታቸው ነው። ዛሬ ከኢትዮጵያ ካርታ ይልቅ የአንድ ግለ ሰብ መሪ ፎቶ ግራፍ የበለጠ ክብር የተሰጠበት ሁኔታ ይታያል። ዛሬ መለስ እንደ መሪ ሳይሆን እንደ ፈጣሪ የሚታይበት ጊዜ መሆኑን በግልፅ እየታየ ያለ ጉዳይ ነው። ታዲያ ሀቁ ይህ ከሆነ የሰራዊቱ ታማኝነት ቅድሚያ የሚሰጠው ለማን ይሆን? የሰሜን ኰሪያና የኢትዮጵያ መከላኪያ ሰራዊት መሰረታዊ የባህሪይ፣ የአቋም፣ የአደረጃጀትና የደክትሪን ልዮነት አላቸው ብላችሁ ታምናላችሁን?

9. የኢትዮጵያ መከላኪያ ሰራዊት ገለልተኛ ነው ሲባል ይሰማል። ገልተኛ ማለት ደግሞ በሀይማኖት፣ በፓለቲካ አመለካከት፣ በነፃ ዳኝነት፣ በፍትህ አካላትና በዜጎች የግልና የቡድን ነፃነት ላይ ጣልቃ የማይገባ ማለት ይመስለኛል። ሀቁ ይህ ከሆነ የአንድ ፈላጭ ቆራጭ የፓለቲካ መሪ ፎቶግራፍ እንደ ታቦተ ፅዮን ተሸክሞ የሚሄድና የሚያመልክ ሰራዊት ገለልተኛ፣ የህዝብ ወገንተኛ፣ ነፃ የፍትሕና የልማት ሰራዊት መሆን ይችላል ብላችሁ ታምናላችሁን?

10. የመጨረሻ ጥያቄ ለህወሓት ታጋዮች፣ ካድሬዎች፣ ደጋፊዎቻቸው ነው። በራሳቸው አንደበትእኛ ህወሓቶችኤርትራን ከኤርትራውያን በላይ ታግለን ያስገነጠልናትና ነፃ ያወጣናት እኛ ነንብለው በማያሻማ መልኩበሚያምኑት በአቶ ስብሓት ነጋ መሪነት የተፈጠረው የትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት (ህወሓት) ዛሬ በመከላኪያሰራዊት ታጅቦ 38ኛው የልደት በዓሉን እያከበረ ይገኛል። ይህ በዓል ደግሞ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜው ሳይሆንየትግራይ ህዝብ ልደት ነው እየተባለ በአደባባይ መከበር ከጀመረ እኖሆ ግማሽ ምእተ ዓመቱን ሊያስቆጥር ጥቂት ዓመታት ነው የቀረው። እንዲያውም በዓሉ የአንድ ፓለቲካ ድርጅት መታሰቢያ ቀን ከመሆን አልፎ በትግራይ ህዝብ ዘንድ እንደ አንድ ቅዱስ ቀን ተቆጥሮ በፍትሃተ ፀሎትና በድግስ እንዲያከብረው እየተደረገቆይቷል። ዛሬም በተመሳሳይ ደራማ በውጭም በሀገር ውስጥም ሲከበር እያየን ነው። ነገር ግን ጥያቄው 
  • የካቲት 11 የማን ልደት ነው? የበረከት? የስብሓት? የቴድሮስ? የመለስ? የጥቂት ካድሬዎች? ወይስ በስሙና በደሙ እየተነገደበት ሳይወድ በግድ የኤርትራ ነፃነት ማዳበሪያና የጥቂት ከሃዲ መሪዎች የስልጣን አገልጋይና መሳል ሆኖ እንዲኖር እየተደረገ በሁለት አለንጋ እየተገረፈ የሚገኘው ህዝብ ልደት ነውን?  
  • የትግራይ ህዝብ በጀግኖች አባቶቹ የሰማእታቱ መቃብር ላይ ቆሞ የህወሓትን ልደት በጭፈራና በዳንኬራ የሚያከብርበት ዋና ምክንያት ምን ይሆን? እውነት በደሙ ራሱ የገነባትን ሀገር ተመልሶ ራሱ በማፍረስ ዛሬ ባህር አልባ የሆነች ሽባ ሀገር ይዞ በመቅረቱ ደስ ብሎት ይሆናል ብላችሁ ታምናላችሁን
  • የትግራይ ህዝብ የህወሓት ልደትን የሚያከብረው ባድመ የኛ ነው፣ መሬትህ በባዕድ ተደፍረዋል፣ ዛሬም እንደ ትናንቱ ተነስ!! ክተት!! ተብሎ የከፈለውን መስዋእትነት ከንቱ ሆኖ በመቅረቱንና መሬቱን ተሸንሽኖለባዕድ በመሰጠቱ  ምክንያት ደስተኛ ስለሆነ ነው ብላችሁ ታምናላችሁን?

አትረፍ ያለው በሬ ቆዳውን ለከበሮ ይውላል እንዲሉህወሓት የትግራይን ህዝብ ሁለት ጊዜ ገድሎታል። አንድ ኤርትራን ነፃ ለማውጣት በአስር ሽዎች የሚቆጠሩ ለጋ ወጣቶች በሳህል በረሃ የአምራ ሲሳይ ሆነው እንዲቀሩ አድረጓል። ሁለተኛ ደግሞ ህዝቡ አድኑን እያለ ሲጮህ ጆሮ ዳባ በመስጠት አሳልፎ ለጅብ በመስጠት ዳግም በሻዕቢያ ወረራ እንዲቀጠቀጥና እንዲደማ አድርገዋል። ለዚህም ነው ደደቢት የጥቂት ከሃዲዎች በዓል እንጂ የትግራይ ህዝብ ልደት አይደለም የምንለው። ዛሬ ጥቂት ሙሰኞቹን በዊስኪ እየተራጨን የምናጅብበት ጊዜ ሳይሆን ህዝብና ሀገር ማእከል ያደረገ አጀንዳ ይዘን ለመብታችን የምንታገልበት ወቅት ነው።   

No comments:

Post a Comment