በስመ አብ፤ ወወልድ፤ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን።
“የገበያ ግርግር ለሌባ ያመቻል”
የርዕሰ አድባራት ለንደ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አባላት
ገንዘብና ጉልበታቸውን አፍስሰው፤ ጥረውና
ግርው ህንፃ ቤተ ክርስቲያን ከትልቅ ግቢ፤ መኖሪያና መገልገያ ህንጻ ጋር በመግዛት በስደት ሃገር የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆነችን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተ ክርስቲያንን አቆሙ።
ይህንን በሕዝብ ሃብትና ጉልበት፤ በእግዚአብሔር ቸርነት
የተመሠረተን ቤተ
ክርስቲያን አባ
ግርማ ከበደ ሕዝብን በመካድ የቤተ ክርስቲያኗ ባለቤት ሕዝብ ሳይሆን እኔ ነኝ ብለው በመነሳት አባላቷን አግልለው አዛዥና ፍላጭ ቆራጭ ለመሆን ሲሉ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁከትና መከፋፈል እንዲቀሰቀስ አስደረጉ።
ሕዝበ ክርስቲያን በዚህ ቤተ ክርስትያንን የሚያረክስና
ምንኩስናን የሚያዋርድ
የአባ ግርማ ከበደ ሥራ ተገርሞና አዝኖ ሳይጨርስ በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ
ችግር ከመቀስቀሱ በፊት የቤተ ክርስቲያኗ አባላት
በዓይን እንኳ አይተዋቸው የማያውቁት
አቡነ እንጦንስ ደግሞ ከየት መጡ ሳይባል ከአባ ግርማ ከበደ ጋር ግንባር በመፍጠር በቤተ ክርስቲያኗ ላይ ነግሻለሁ በማለት አባላቷ ፍትሕን በመጠበቅ በብርድና በዝናብ ውስጥ ሲጸልዩ እያዩ እግዚአብሔርን ሳይፈሩና ሕዝብን ሳያፍሩ የእግዚአብሔር ቤት የሆነችውን የሕዝብ ቤተ ክርስቲያን የሴራ
አዋጃቸው ማሰሚያ መድረክ፤ ሕዝብን የናቁና ሥነ ምግባር የጎደላቸው አንደበታቸው ያልታረመ
ባለጌዎች መደንፊያ ቦታ አደረጓት።
ይባስ ብለውም በሕዝብ ገንዘብ ተገዝቶ በከፍተኛ የሕዝብ ገንዘብ ወጪ የታደሰውንና ለታዳጊ ህፃናት መማሪያና ለጽሕፈት ቤትነት መጠቀሚያ ሆኖ ሲያገለግል የነበረው የቪካሬጅ ህንፃ ውስጥ ዘለው በመግባት አይናቸውን አፍጥጠው
መኖሪያዬ እዚህ ነው በማለት የሕዝብ መገልገያን ንብረት ንብረታቸውና መኖሪያቸው እያደረጉት
ይገኛሉ።
በዚህም አላቆሙም አቡነ እንጦስ ከአባ ግርማ ከበደ ጋር እጅና ጓንት ሆነው በመስራት የሕዝብ ንብረት የሆነውን ህንፃ ቤተ ክርስቲያንና የመኖሪያ ህንጻ ከሕዝብ ዘርፎ ሙሉ በሙሉ የሳቸውና የደጋፊዎቻቸው ሃብትና ንብረት አድርጎ ለማኖር እንዲቻላቸው ከሕዝብና
ከእውነት ጋር በመቆም እውነተኛውን የክህነት ተግባር በማከናወን ላይ
ያሉት ካህናትን እኔን ደግፋችሁ በለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ላይ
ካላነገሳችሁኝ አጠፋችኋለሁ
በማለት የማስፈራሪያና ማስጠንቀቂያ ደብደቤ
ሲሰጡ ከቆዩ በኋላ እነሆ አሁን ደግሞ ወደ ማውገዝ ደረጃ ደርሰዋል።
በዚህም በአሁኑ ወቅት ካሉት ካህናት መካከል ቀደምት የሆኑትንና ከ20 ዓመታት በላይ ቤተ ክርስቲያኗን በቅስና
በማገልገል “ወርቅ
በእሳት ይፈተናል” እንዲሉ በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ
ችግር ሲፈጠር ለእውነትና ለፍትሕ
በጽናት የቆሙት ዋነኛው መልአከ ብርሃን ቀሲስ ብርሃኑ ብሥራት ናቸው።
ሌሎች ለሥልጣንና ለንዋይ ሲሉ ስጋዊ ዓላማን በማስቀደም በሕዝብ
ላይ በሚፈጽሙት ክህደትና በደል ምክንያት ካህናቱና ምእመናኑ ተማሮ ከእምነቱ በመራቅ እንዳይበተን የሕዝብ
ካህን ሆነው ያለምንም ክፍያና ገቢ መንጋውን ሰብስበው የክህነት አገልግሎትን በመሥጠት
የእውነተኛ ካህን
ተምሳሌት የሆኑት፤ መልአከ ብርሃን ቀሲስ ብርሃኑ ብሥራት መሆናቸውን አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ሃቅ ሆኖ እያለ፤ አባ እንጦንስ የቤተ ክርስቲያኗን አባላት
የጎዱና ያጠቁ መስሏቸው እኚህን እውነተኛ አገልጋይ ካህን፤ ሥልጣነ ክህነታቸውን ሽሬአለሁ
በማለት በዕለተ እሑድ (23/03/2014) በራሷ
በርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አዋጅ አስነብበዋል ባለ
አራት ገጽ ደብዻቤም አሰራጭተዋል።
በዚህ አባ እንጦንስ ከኔ ጋር የሴራዬ ተባባሪ ሆነህ ሕዝብን ካላጠቃህና ከእውነት ይልቅ ለሃሰት ካልቆም አስወግድሃለሁ ወይም
አጠፋሃለሁ በሚለው
ተግባራቸው በዓለማችን
ከታወቁ የአንባገነን ገዢዎች ካልሆነ በስተቀር ብጹዕ ከተባለ መንፈሳዊ አባት ጋር ጨርሶ ሊያመሳስላቸው አይችልም። ሊወስዱት
በሞከሩት የውግዘት እርምጃም ሕዝብን ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርንም በመናቅ
ክቡሩንና ጥንታዊውን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ሃይማኖታችንን የአሳፋሪና
አስነዋሪ ተግባራቸው መጠቀሚያ ማድረጋቸው በመሆኑ ሊያፍሩበትና ሊሸማቀቁበት ይገባል።
በዚህ እንኳንስ ብጹዕ ከተባለ መንፈሳዊ አባት ቀርቶ ከማንኛቸውም ለሂሊናው ተገዢ የሆነ ሰው የማይጠበቅ በተንኮልና
ሴራ የተቀነባበረ ወፈ ግዝት ተግባራቸው አባ
እንጦንስ ሲያፍሩበትና ሲዋረዱበት ይኖራሉ
እንጂ በንጽሕና በመቆም እውነትና ሕዝብን በማገልገል ላይ የሚገኙትን መልአከ ብርሃን ቀሲስ ብርሃኑ ብሥራት ክርስቶስን፤ እውነትንና ሕዝብን
ከማገልገል ተግባራቸው
ለአንዲት ሴኮንድ እንኳን ሊያሰናክላቸው አይችልም።
እንደሚታወቀው አባ
እንጦንስ አሁን በህይወት የሌሉት የአቡነ ጳውሎስ ጉዳይ አስፈጻሚ በመሆን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2007
ወደ ለንደን በመጡበት ወቅት ይዘውት በመጡት ፖለቲካዊ ተልዕኮ ምክንያት ርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን እንደማትቀበላቸው ሲረዱ
ከዛን ጊዜ ጀምሮ ከቤተ ክርስቲያኗ ጋር
ምንም ዓይነት ግንኙነትና ቁርኝት
ሳይኖራቸው የሥላሴና
የገብረኤል አብያተ
ከርስቲያናትን በመያዝ
ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንን በአይነ ቁራኛ በመከታተል ሲቻላቸውም
ለማዳካምና ለመከፋፈል
ሲጥሩ መቆየታቸው የሚታወቅ ነው።
በርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ
የአስተዳደር ችግር
በተፈጠረበት ወቅት
አባ እንጦንስ የምመኘውን ለማሳካት
ይጠቅመኛል በሚል
ሕዝብን ከበደሉና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ካዋረዱ
ከአባ ግርማ ከበደ ጋር በማበር ከ2013 ጀምሮ የቤተ ክርስቲያኗ ባለቤት
የሆነውን ሕዝብ በጠላትነት ፈረጁ።
በእግዚአብሔር ቸርነት
ቤተ ክርስቲያኗን ዋልታና ማገር ሆኖ ያቆማትን ሕዝብ ከአባ ግርማ ጋር ሆነው በማባረር የሃብትና ንብረት ባለቤት መሆን እችላለሁ በማለት ጳጳሳትን ከኢትዮጵያ በማስመጣት ጥረት
አድርገው አልሳካ ሲላቸው አባ ግርማን ይዘው ኢትዮጵያ በመሔድ የቤተ ክርስቲያኗን አባላትና በስደት ላይ የሚገኘውን ኢትዮጵያ በጥቅሉ ሃይማኖት የሌለው በደለኛና ኃጢአተኛ አድረገው በመዝለፍ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ።
ከኢትዮጵያው አገዛዝና
ለንደን ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ
ሙሉ ድጋፍና ትብብር እየተደረገላቸው መሆኑንም በጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ
በማረጋገጥ በዛ
መሠረት ከአባ ግርማና ተባባሪዎቻቸው ጋር ሆነው ለ10 ወራት ያህል ተዘግታ የነበረችውን ቤተ
ክርስቲያን የቤተ
ክርስቲያኗን አባላት
ባገለለ ሁኔታ ከ29/12/2014 ጀምሮ
በሕገ ወጥ መንገድ በማስከፈት የቤተ ክርቲያኗ አባላት እደጅ ተወርውረው ቤተ
ክርስቲያኗ የሌላ
ቤተ ክርስቲያን አባላት መገልገያ እንድትሆን በማድረግ
በቤተ ክርስቲያኗ ላይ ነግሻለሁ አሉ።
ለእውነትና ለፍትሕ
ቆመው በመታገል ላይ የሚገኙት የቤተ ክርስቲያኗ አባላትም ምንም እንኳ መብታቸውን ለማስከበር የትኛውንም
አማራጭ መጠቀም እንደሚችሉ ቢያውቁም
ሕግና ሥርዓትን በመጠበቅ፤ ከሁሉም
በላይ ደግሞ በተቀደሰችው ቤተ
ክርስቲያን ውስጥ
የሚነሳ ሁከትን ለማስቀረት ሲሉ
ጉዳዩ ሕጋዊ መፍትሔ እስከሚሰጠው ራሳቸውን ጎድተው ዝናብና ብርድ እየተፈራረቀባቸው ጸሎታቸውን
በውጪ ማካሄዱን ቀጠሉ።
እንደ ዘመኑ አንባ ገነን ገዢዎች ከንዋይና ከስልጣን በስተቀር ፈሪሃ እግዚአብሔርም ሆነ ለሕዝብ ከበሬታ የሌላቸው አባ እንጦንስ የባህሪ አጋራቸው የሆኑትን አባ ግርማን እና ተከታዮቻቸውን በመሣሪያነት
በመጠቀም ቤተ ክርስቲያኗን የመሠረቷትንና ያቋቋሟትን አባላቷን ከኤምባሲ በሚገኝ ገንዘብ በሚቀጠር የግል ሴኩሪቲ አማካኝነት ከቤተ ክርስቲያን አይደለም ከቅጥር ግቢዋ ጭምር ለማባረር የሚቻላቸውን ሁሉ አደረጉ።
ይህንን ሁሉ ካደረጉ በኋላ ነው አባ እንጦንስ ዛሬ ደግሞ ከእውነትና ከፍትሕ ጎን በመቆም ሕዝብን በማገልገል ላይ
በሚገኙ ካህናት ላይ አዲስ የጥቃት ዘመቻ የከፈቱት። ለመሆኑ
አባ እንጦንስ እንኳንስ ለእውነትና ለፍትሕ ሲል ሕዝብን በንጽሕና በማገልገል ላይ
ያለ ካህንን ቀርቶ የረከሰና የኦርቶዶክስ ሃይማኖትንም
ሆነ ምንኩስናን በማዋረድ ላይ ያለ ካህንን ማውገዝና መሻር የሚያስችል መንፈሳዊና
ሕጋዊ ብቃት ያላቸው ሰው ናቸው ወይ? እውነተኛ ታሪካቸውስ ምንድን ነው? የሚለውን ወደፊት በማስረጃ ተደግፎ ሲወጣ ለማየት በተስፋ እንጠብቃለን።
አባ ግርማ ከበደም ሆኑ የእሳቸው ባህሪ ተወራራሽ የሆኑት አባ እንጦንስ ሕዝብን በመናቅ በእብሪት ተሞልተው በሕዝብ ሃብትና ንብረት ላይ ፈላጭ ቆራጭ በመሆን የሰውን መብት ጥሰው ስብዕናን በማዋረድ የሚያደርጓቸውና የሚፈጽሟቸውን ተግባራት ሁሉ የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን አባላትና የማርያም ወዳጆች እንዳለፈው ጊዜ አሁንም የእውነት አምላክ የሆነውን ክርስቶስን ተማምነው የትኛውንም ሃሰት፤ ተንኮልና ደባ ሁሉ በእውነት ኃይል ያሸንፉታል። ይህንንም
በመገንዘብ መላው
የቤተ ክርስቲያኗ አባላትና የድንግል ማርያም ወዳጆች ሁሉ የተነሱብንን ከሃዲዎች፤ ሃሰተኞችና
እብሪተኞች ለመታገል
ከምንጊዜውም በበለጠ
ቁርጠኝነት በመነሳት
ሕጋዊ መብታችሁን ታስከብሩና ቤተ
ክርስቲያናችሁን ታድኑ
ዘንድ ክርስቲያናዊ ጥሪአችንን እናስተላልፋለን!!
በተጨማሪም ይህን
የአባ ግርማ ከበደና የአባ እንጦንስን የሸፍጥ
ሥራ፤ መላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ካህናትና ምእመናን እንዲያወግዙት፣ ላባታችን
ለመልአከ ብርሃን ቀሲስ ብርሃኑ ብሥራትና የርዕሰ አድባራት ለንደ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንን ለማዳን ለሚደረገው ጥረት የሚቻላችሁን ድጋፍ እንድትሰጡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
የርዕሰ
አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን አባላት ካህናትና ምእመናን።
ወስብሐት
ለእግዚአብሔር!!
አባሪ ግላዊ አስተያየት
“ለቁጣ ለውግዘት መፍጠን ያምባገነንነት መለኪያ እነጅ የብልህ መሪነት ምልክት አይደለም።...
ሲፈልግ የሚገድለውን ሲፈልግ የሚያስረውን የዜጋ ስቃይ የምንመለከተው የአምባገነን ውጤት ነው።”
ምቱር የወያኔ ጳጳሳትም ሆኑ ምቱር የወያኔ ካሕናት የኢተዮጵያ ኦረቶዶክሰ ተዋሕዶ ሃይማኖት
ለማዳከም የእምንት ተከታዮቿን ለመበተን በአገርም ሆነ ከአገር ውጭ
ቤተክርስቲያንን ለማድከም የሚያደርጉት መሰሪ የተንኮል ሴራ በጋራ ማክሽፍ የማንኛውም ኢትዮጵያዊ የጋራ ጉዳይ በመሆኑ፤ የወያኔን
አንባገን ሰነስርአትን ገርስሶ በጋራ ለመጣል የምንታገል፣ ጥነታዊ ቤተክርሰቲያናችንን ለማዳን ቀና ደፋ የምንል በዓለም ዙሪያ በስደት
የምንገኝ ዜጎች ሁሉ ትብብር መፍጠር ግድ ነው። ድር ቢያብር አነበሳ ያስር ነውና በጋራ ለጋራ እምነታችን በሁሉም ዙሪያ ትብብር
ፈጥረን፤ የበግ ለምድ ከለበሱ ምቱር የወያኔ አደር ጳጳሳት፣ ካሕናት ተኩላዎች ቤተክረሰተያንን ማዳን፣ ከመቼው ጊዜ ዛሬ አስፈላጊነቱ
የታመነ ነው። በመሆኑም ምእመን ግንኙነታችሁን አጠንክሩ የጋራም መድረክ ፈጥራችሁ አድማሳችሁን አስፍታችሁ ጉልበታችሁን አሳድጉ፤
ሥራችሁንም በስልት ቀይሳችሁ በአነክሮ መንፈሳዊ አስብኦተ የታነጸ በእራስ ገዝ ስነምግባር እየተመራችሁ ከህሊናችሁ ጋር ሳትጣሉ ምድራዊውንም
ሆነ መሎኮተዊ ሕይወታችሁን አስደሳች ሥራን ለመስራት መነሳሳት ቀኑ ዛሬ ነው፤ ተነሱ በጋራም ተባበሩ፣ እረስበ በእራሳችሁም ተረዳዱ
በጋራም ተደራጁ፣ አገራቸሁ ሕዝባችሁ ለነጻነት በሚደያደርጉተ ሰላማዊ ትግል ሁሉ ተባባሪ ሁኑ፤ ተባረኩ።
መልካም የሰንበት ቀን ለሁላችሁ!!!
No comments:
Post a Comment