ልማታዊ ዘርፎ አዘራፊ የጎሳ አንባ
ገነነ መንግሰት
“እውነትን የማያውቅ
ሆናና ብቻ ነው። ግን እውነትን
እያወቀ ውሸት ነው
የሚል ወነጀለኛ ነው።” ቤረተቶለት ብሬሽት
በዘር፣ በጎሳ ፣በሃይማኖት፣ በቛንቛ፣ በፆታ፣ በግብረሰዶም እየተመራ አገራችንን ኢተዮጵያን ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የሚገዙት ወንጀለኛ ለዛሙጥጤ የጎሳ አንባገነን ስብሰብ እየሠሩት ያለውን ሕዝብን አንገት አስደፊ፣ የሀገርን ነፃነት ሰባሪ፣ አብሮነትን ሸርሻሪ ድርጊት... ሁሉ፤ ጥርሱን
ያገጠጠ፣ ድፍን ዓለም በሰፊው በግልጽ የሚያውቀው ሃቅ መሆኑ እየታወቀ፤ መሲሕ፣ ሃሳዊ ድረሳናትን እየደረሱ፤ ለሕዝብና ለሃገር የማይጠቅም፤ ሃገር ገዳይ ፍሬከርስኪ ሥራዎችን በማቅረብ፤ ሰረበተ (Sychopatic
Statement) ዲሰኩር በመፈብርክ፤
የሕዝብን ስነልቦና በዘር፣ በጎሳ፣ በሃይማኖት፣ በቛንቛ፣ በፆታ፣ በግብረሰዶም አየከፋፈሉ፣ አነዱን ካነዱ
እያባሉ ጥላቻን እየፈጠሩ፤ ጥላቻን እያነገሱ፤ የሕዝብን ጭንቅላት ለመቆጣጠር፤ ከጌቶቻቸው በምጽዋት በተሰጠ፤ የፕሮፓጋነዳ ዜና ማሰራጫ መሣሪያዎች ተጠቅመው፤ በሆድ አደር ምንደኞች ወነጀል ሰሪ፣ የናት ጡት ነካሽ ጋዜጠኛ ተብየዎች ጠዋት፣ ማታ የሃሰት
ዜናዎችን አየር ላይ አውለው በማሰለቸት የተጠመዱ፤ ሕዝብንም ከሰሜን አሜሪካ፣ ከአውሮፓ፣ ከኤዝያን ፓሲፊክ ሀገራት በአገር ስም በተገኘ የምጽዋት
የብድር ገንዘብ የግላቸው አድርገው፤ በንቅዘት/በሙስና፣ በጎሳ ኪራይ ሰብሳቢነት በወነጀል ተጨማልቀው፤ ሰለሕግ የበላይነት ሰለፍተሕ፣
ስለ ሰርአተ መድሎዋዊ አልቦነት፤ ቆበራቸውነ ሞልተው እየፎለሉ፤ በልማት
ስም፤ ሕዘቡን ከሚኖርበት ቤት መኖሪያው አላነዳች በቂ ካሳ በማበረር የሚታወቁ፤ በርካሽ የቻይና ሰራሽ መስትዋት የአጊጡ ጥራት የሌላቸው
ሰማይ ጠቀስ ፎቆችን ሕዝብንም ከቦታው እያፈናቀሉ በመገንባት፤ ለውጭ ባላሃብት የሃብት ትርፍ አካባች፤ በባርነት አገልጋይ ሠራተኛን
ማጓጓዣ በሚል፤ የእውነተኛ ብርቅዬ ኢትዮጵያዊ ቅዱስ ሰማእታትን ሀውልት እያነሱ የባቡር ሃዲድ በመስራት፤ ክረምት በመጣ ቁጥር በውሃ
እየተሸረሸረ የሚበላሽ ቁጥራቸው ይሄ ነው የማይባሉ፤ ሕዝብን ለመደለል፤ ባለሶስት፣ ባለ አራት፣ ባለ አምስት መስመር አስፋልት መንገድ
ለናሙና ሠራን ብለው በኳኳቴ ዲስኩር የሕዝብን ጆሮ ያሰለቹ፣ በቅጡ ያልተጠኑ በየጊዜው የሚደረሰሱ፤ ከጥቅማቸው ጉዳታቸው የበዛ፤ የከባቢ የተፈጥሮ ሁኔታን አዛቢ፤ ለሙስና ለንቅዘት ለጎሳ ኪራይ ሰብሳቢነት
የተጋለጡ ግድቦችን ከሕዝብ አፍ አስገድደው በመዋጮ በግዳጅ የቦነድ ግዥ ሕዝብን ደልሎ፤ በማወናበድ፣ በጠራራ ፀሐይ ኪስ የሚያወልቁ፤
እነዲሁም ትላልቅ ለጎሳ ክራይ ሰብሳቢነት የተጋለጡ ፐሮጀክቶችንም መገንቢያ በአገርና፣ በሕዝብ ስም በብድረ ስም የተገኘን፤ ገንዘብ
ሲሶውን በመገልገ፤ ሶስት ሲሶውን በንቀዘት፤ ካባሪ ተባባሪዎቻቸው ጋር ሆነው፤ ዘርፈው የሚያዘርፉ፤ ይባስም ብለው፤ በእንግሊዝና በአሜሪካ
መዋለ ፈሰስ ብድር አቅራቢነት፤ (Hedgefonds and Pension
funds) የሚደረገውን፤ የእርሻ መሬት ቅረምት፤ በአገራችን በማስፋፋ፤ ቤልጅምን የሚያሕል ድነግል የእረሻ መሬት ከሕዝብ ቀምተው፤ ለጌቶቻቸው
ለሰሜን አሜሪካ፣ ለአውሮፓ ለኤዝያና ለነዚሃ አገራት ተባባሪ አባታዊ አንባገነን የአረብ አገራት፣ በመዋለ ሀብት ፈሰስ ግኝት ስም፤
በነፃ፣ በወላግድ የሕዝብን ሀብት አስረክበው፤ [] ሰለቴክኖሎጅ ተጠቃሚነት፣ ስለ ሥራ ፈጠራ፤... በሚል ቱሪናፋ ዲስኩር ሕዝብን በማጭበርበር ወደር የማይገኘላቸው በአፍሪካም ሆነ በመላው ዓለም ብቸኛ የሆኑ ተወዳዳሪ የማይገኝላቸው ቆረጦ ቀጥል፤ ሸርክት፤ ዘረኛ የጎሳ ስርአትን አንጋሽ፤ ለባእዳን ጥቅም ያደሩ፤ በአሽከርነት
ሕዝብንና አገርን አዋራጅ የወንጀል ሥራን፤ በአገርና በሕዝብ ላይ በመስራት የሚታወቁ፤ እደ ወያኔ-ሕውሃት/ኢሃድግ ተብዬ አይነት፤ ሰው-በላ ጉግ ማነጉግ ስብሰብ፤ የትም ዓለም ቢሆን፣ በዘመናችን ወደር የማይገኝለት፤ አገር ከሃዲ፣ ሕዝብን ጨቛኝ፣ ለውጭ ያደረ፣ አጎብዳጅ፣ እደማይገኝ፤ ያለፉት ሁለት አስረት
ዓመታትን፤ የአገራችን የኢትዮጵያ እውነተኛ ድረሳነ ታሪክ የተከታተለ ሁሉ፤ በወያኔ የዘርኛ ልክፍት ተለከፎ ካላበደ ፀረ-ኢተዮጵያዊ ስብስብ፣ አልያም ለሆዱ ተገዝቶ፤ ለሆዱ ያደረ ካልሆነ በስተቀር፤ በአንክሮ መላው የአገራችን ሰፊው ሕዝብም ሆነ፤ ድፍን ዓለም በጠራራ ፀሀይ በሕዝብና በሃገር ላይ ትላነትም ሆነ ዛሬ በዲሞክራቲ በልማት ሽፋን ስም እየተፈጸሙ የነበሩ፤ አሁንም በመፈጸም ላይ ያሉ፤ ከላይ የተጠቀሱት፤ ወንጀሎችን እደሚያውቀው፤ እውን ነው። በማስረጃም ድጋፍ፤ በዝርዝር አነድ ባነድ ማቅረብ የሚቻል፤ መዝገብ የያዘው ሀቅ ነው።
ወያኔ-ሕውሃት/ኢሃድግ ካፈጣጠሩም
የቅኝ ገዥ ተስፋፊ ቩልቃሽ አውሮፓ አንጋሽ ዘረኛ ርዮትን አነግብኦ አነዴ የግራ አለያም የቀኝ ርዮት ጭንብልን አጥልቆ፤ እደ አስፈላጊነቱ
በግራ ሲመቱት ቀኙን በቀኝ ሲመቱት የግረውን አይዲዎሎጅ እየተከተለ እደ አስተማሪዎቹ እደ ናዚው አዶልፍ ሂትለር፤ እደ ፋሽስቱ ዱቼ
ሞሶሎኒ አልያም እደ ሶቬዬቱ ሰታርሊን፤ሲያስፈልገውም እደ ቻይናው ማኦ ሴቱነግ እደ ካምፖዲያው ክሜር ሮዥም የጎሳ አንባ ገነን ጥብቆውን አሰፍቶ፤ ባሰፋው ጥብቆ ልክ የሚያስብ የአጼ
በጉልበቱ የመንደር ልጆች ስብሰብ እደነበረና፤ ንቃተ ሕሊናውም በቁመናው ተለክቶ ተስፍቶ በተሰጠው፤ ጥብቆ ልክ የሚያስብ ትላንትም
ዛሬም እደነበረና እደሆነ፤ አያሌ የሱ አካል ያልሆኑ ወገኖች በመጽሃፍ ስለዚሁ ሊል ዘሊል ስብሰብ በመጽሃፍ በመጣጥፈ ጥናት የደረሱት
መጣጥፍ አስረጅ ናቸው። ስልጣንም በአዲሱ የቅኝ ገዥ ፈቃድ፤ ረዳትነት
ባሜሪካው የደሕንነት ተቛም አባሪነት ስልጣን ላይ እደወጣ፤ አገርንም አዳስገነጠለ፣ በአምሳሉ በታዛዥነት የሚያገለግሉትን ቩልቃሽ
የጎሳ ድረጅቶች በመናጆነት ፈጥሮ ከላይ የተጠቀሱትን የወንጀል ሥራዎች
እደሠራ እየሠራም እደሚገኝ የማይታበል ሃቅ ነው። በማን እየታገዘ እደሚሰራ እራሱ ወያኔ-ሕውሃት/ኢሃድግ የማይክደው ሀቅ ነው። እነዚህም ሀይሎች የአዲሱ የእጅ
አዙር ቅኝ ገዥ የሰሜን አሜሪካ የአውሮፓና የኤዝያን ፓሲፊክ አገራት እደሆኑ አይካድም። እነዚህም ሀገራት የራሳቸው የሆነ ርዮትን አንግበው
ጥቅማቸውንም ለማስጠበቅ መላውን ዓለም በተለይ የቀዝቃዛው ጦርነት ካበቃበት ዋዜማ ጀመሮ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥራቸው ውሰጥ እዳስገቡት
አይታበልም። ቀደም ሲልም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በሗላም፤ እነዚሁ የሰሜን አሜሪካ አገራት፤ ማለትም አሜሪካ በአቛቛመችው፤ (Global finance and Corporate Capital) ዓለም አቀፋዊ የበላይ ኢኮኖሚ ጥምረ ተቛም፤ እንዲሁም ዓለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ ተቆጣጣሪ
(Multilaterial Institutions of Global Economic Surveillance, G7,
IMF, WB, WTO, ...) ተቛማት አመካኝነት፤ ከመቸውም
ጊዜ በበለጠ የአፍሪካ፣ የኤዝያ፣ የላታይን አሜሪካ አገሮችን በኢኮኖሚ ጥገኝነት ውሰጥ አስገብተው፤ ተቀናጅተው እየሠሩ እደሚገኙ፤ የአገራችን ሆነ፤ በአፍሪካ፣ በኤዝይ፣ በላቲን አሜሪካን እየተሠሩ ያሉ ልማታዊ ተብየው ስራዎች የነዚህን ሕዝብና ሀገር ወደተሻለ የእድገት አቅጣጫ የሚያመራ ሳይሆን፤ በመሰረቱ የአዲሱን የእጅ አዙር የቅኝ ገዥዎች ርዮትን የበላይነትን አንጋሽ፤ እነዚሁ ሀይሎች ዓለም በትናንሽ እነሱ የሚቆጣጠሩዋቸው አገራትን ፈጥረው፤ ዓለምን ሙሉ በሙሉ አነድ በማድረግ፤ በቁጥጥር ውሰጥ አስገብተው በአንባገነንት ለመግዛት አልመው የሚሰሩት እነጅ፤ ዲሞክራቲን ለማስፋፋት፤ መድሎ አልባ የሕዝብ እድገትን፤ ብልጽግናን ለማምጣት፤ ድሕነትን ለማጥፋት፣ ቴክኖሎጅን ለማስፋፋት፤ እዳልሆነ፤ በዓለማችን
ትላነትም ሆነ፣ ዛሬ በነዚሁ ሀይሎች፤ በቀጥታም ሆነ፤ በእጅ አዙር ተቀስቅሰው፤ በዓለማችን የምናያቸው ግጭቶች፣ ጦርነቶች፤ የሃብት የይገባኛል ቅርምት ትንንቆች ሁሉ አጉሊ ምስክሮች
ናቸው። እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት የኢኮኖሚ ተቛማትም፤ ዓለም አቀፍ ስም ይስጣቸው እነጅ፤ ግልጋሎት ሰጭነታቸውም ሆነ፤ አፈጣጠራቸው፤ ለሰሜን አሜሪካ ለአውሮፓና ለኤዝያን ዓለም አቀፋዊ ባላሀብት እደሆነ፤ በዓለማችን ዛሬ በኢኮኖሚ መአቀብ፤ በፈቃደ ሕብረት ለፀረ-ሸብርተኝነት ቡድን ስም፤ በሰሜን
አሜሪካ በአውሮፓና በኤዝያን ፓሲፊክ አገራት አጋርነት እየተደረጉ ያሉ በሀገራት ላይ የሚጣሉ ኢኮኖሚያዊ ማእቀቦችም ሆኑ ለሀገራት
የሚሰጡ እርዳታዎች ሁሉ በማን ለምን እደሚደረጉ አጉሊ ምስክሮች ናቸው። በጣም የሚያሳዝነው ግን ትላንት የሶሻሊስት ሰርአት መስፋፋት አስግቶዋቸው፤ በየሃገሩ ደጋፊ
ታዛዥ ድረጅቶች ፈጥረው የጥንት የስልጣኔ መሰረት የሆነትን አገራትን በዲሞክራሲ ማስፋፋት ስም በየአገሮቹ የውሰጥ ጉዳይ ጣልቃ እየገቡ፤ የአገራቸውንም ሕዝብ ጥቅምሕ ተነክቶዋል በሚል እያሰተባበሩ፤ በኢትዮጵያ፤
በኢራን፣ በኢራቅ፣ በሊቪያ፣ በግብጽ፣ በሱሪያ፤ በሱዳን፣... የሚሰሩት፤ አገርን የመበተን እኩይ ሥራም፤ መሰረቱ፤ በውነት ለነዚህ
አገሮች ሕዝብ ዲሞክራሲ ለማምጣት በማሰብ ሳይሆን፤ አውሮፓ አንጋሽ የእጅ አዙር ቅኝ ገዥዎችን የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የመሐበራዊ
የበላይነት ለማስፈን እደሆነ፤ አገሮቹንም በዘር፣ በጎሳ፣
በሃይማኖት፣ በቛንቛ ልዩነት
አሽመድምዶ፣ በትናናሽ
አገራት ከፋፍለው ቆራርጦ፤ ታዛዥ አባወራ እነሱ እደልባቸው የሚዘውሩዋቸው ምንደኞችን ስልጣን ላይ አውጥተው ዓለምን በበላይ አነድ
አድረጎ ለመግዛት እደሆነ አያጠራጥርም። እነዚህም ከላይ የተጠቀሱት አገሮች አማራጭ፤ ከድጡ ወደማጡ ሆኖም ትላንት በአምባገነን ሥርአት ሲታመሱ ዛሬ ደግሞ በዘር፣ በጎሳ፣ በሃይማኖት፣ በቛንቛ ልዩነት ተሽመድምደው፤ እዲጠፉ የሚደረገው ሥራም ማን እያረመደው ያለ ሥራ እደሆነ ድፍን ዓለም የሚያውቀው ነው።
ለእጅ አዙር ቅኝ ገዥ ተባባሪነት
እንግዲህ ያለው ሀቅ ይሄ ከሆነ፤ ባገራችን ላለፉት ሁለት
አስረት ዓመታት አገርን የሚገዛው፤ ሊል ዘሊል የእጅ አዙር ቅኝ ገዥዎች መናጆ፣ የጎሳ አንባገነን መንግስት ተብዬው፤ ሰለ ልማታዊ መንግሰት ቢደሰኩር እደ
ናዚ ሂትለር ወጣቶችንም አስገድዶ የረፍት ጊዜያቸው ከቤተሰቦቻቸው ጋር እዳያሳልፉና ቤተሰቦቻቸውን እዳይረዱ፤ ለመጭውም የትምሕርት ጊዜም
መሰናዶ እዳያደረጉ አስገድዶ ከልክሎ፤ የወጣቱን ጭንቅላት አጠባ፤ ሙከራ
ሥራ ሁሉ፤ ስልጣን ካወጡት ሀይሎች የተሰጠው፤ አገርን ለጥገኝነት ጣይ፤ የቤት ሥራው ነውና፤ ሊገርምን አይገባም። ወጣቱም እራሱንና አገሩን
ለባርነት እደመይጥል፤ እየታዬ ያለ፤ የቀን ተቀን የነፃነት ታሪካዊ ሥራው ምስክር ነው። ዋናው ጉዳይ ግን ፤የወያኔ-ሕውሃት/ኢአሀድግ
እራሱን ልማታዊ መንግሰት ብሎ ሕዝብን ለማታለል የተነሳበትን ምክንያቱን ዳስሶ እውነቱን ለሕዝብ በመረጃ ማቅረቡ ላይ ነው ያለው ዋና ሚስጠሩ። ልማታዊ ምንግስት የሚለውም ሕሊናት በእጅ አዙር ቅኝ ገዥ ተስፋፊ ርዮት
ተኮር ተቀንቅኖ መሰራቱንም ዝርዝር ጉደይ ውሰጥ ከመግባታችን በፊት
ማወቁ ሰርአቱ የማን አገልጋይ እደሆነ ቀደምት ግነዛቤን ያስጨብጣል።
ልማታዊ መንግሰት ለማን?
ልማታዊ የሚለውም ቃል በአገራችን፤ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አነጻር ተያያዥ ሆኖ የሚቀርበው፤ ለጥቂት ዘረኛ የጎሳ ጽንፈኛ
አሸባሪ፤ የባእድ ቅጥረኛ፤ የሕዝብን ደም በሰሪነጋ እየማጉ፤ የአገሪቷን መዋለ ሀብት አዘርፎ በመዝረፍ የሚታወቁ፤ አገረን ለባእዳን፣ የአዲሱ ቅኝ ገዥ ጥገኝነት ተግተው ጠዋት ማታ የሚያገለግሉ፤ አነዴ አብዮታዊ ዲሞክራቲ፣ ሌላግዜ ደግሞ ትራንፎረሜሽን፣ ሲአሰኛቸውም፣ ልማታዊ መንግሰት
እያሉ፤ ራሳቸው ሆንነው፤ ሌላውን ሆናና አዲሆን የሚጥሩ፤ ጭንቅላታቸው የሰባ፤ በጎሳ፣ በጎጥ፣ በቤተሰብ፣ በጓደኝነት፣ በአብሮ አደግነት
ተቧድነው፤ አገሪቱን በፋሸስቱ የዱቼ ሞሶሎኒ ሕሊናት የጎሳ ክልሎች
በቛንቛ ስም ደልድለው፤ አነዱን ካነዱ እያባሉ፤ በሚዘውሯቸው፤ አባሪ ተባባሪ አሸበሪ፤ የጎሳ አባወራዎችን በአስተዳዳሪነት፤ መድበው፣
በጎሳ ኪራይ ሰብሳቢነት፤ ተጨማልቀው፤ የአገርን ሀብት እዳስፈለጋቸው፤ በሚያዙበትና፣ ሲያስፈልጋቸውም፤ ወደውጭ በማሽሽ የሚታወቁትን፤ የወያኔ/ሕውሃት-ኢሃድግና አባሪ ተባባሪ ቡድን እነጅ፤ ከሃገርና ከሕዝብ ጥቅም
ጋር ተያያዥነት ኖሮዋቸው ከቶም የሚቀርቡ አይደሉም። ይሕን አውቆ
እውነት አይደለም በሎ የሚክድ ካለ አነድም ሆናና ነው አልያም ወንጀለኛ ነው።
ልማታዊ መንግሰት ለምን?
እንግዲህ እነዚህ ቡድኖች ናቸው ከንቱ
ሕዝብን መደለያ ቱሪናፋ ዲሰኩሮች እየፈጠሩ ላለፉት ሁለት አስረት አመታትም ሆነ፤ ዛሬም መንግስታዊ የሆኑ ዋና ዋና ተቛማትን ተቆጣጥረው ከላይ አስከታች ባለው እርከን ውሰጥ ተሰግሰገው፤ ስልጣናቸውን
ተገን አድርገው በዘር ማጥፋት፣ በዘር ማጽዳት፣ በስነልቦና የዘርማጥፋት፣ በአገር ክሕደት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በልዩ ልዩ ዘርፍ
ብዙ ወነጀሎች ተሰማርተው፤ በሕዝብና በአገር ላይ የበቀል ወንጀል እረምጃ በመውሰድ ሕዝብና አገርን የሚበቀሉት። ይሕም የሠሩት ዛሬም
የሚሰሩት ወነጅል፤ ተደብቆ አዳይታይ፣ ሕዝብም ተነሳስቶ ትግል አነስቶ ከስልጣናቸው እዳያወርዳቸው፤ በቀጣይነትም ስልጣናቸው ይዞ
ለመቀጠል እዲያሰችላቸው ላም ባለዋለችበት ኩበት ለቀማ ተምሳሌትንት ያለውን መላ መፍጠር ግድ ስለሆነ ኤተኖ ፋሽታዊ ርዮታቸው በልማታዊ
መንግስት ጭንብል ሸፋን ተከናንበው ለመታየት በመወሰን፤ ያው ትላንት እደለመዱት የመንደር ብልጣብልጥ አገርና ሕዝብ አያውቅብንም
አባዜ የተከየነ የዘርፎ አዘራፊ ድራማቸውን በአዲስ ማቅረብ ግድ ሆነ። እደቅዱስ፤ ፈሪሃ እግዚአብሔር እዳደረበት፤ ሰውም በእጁ በቀጥታም
ሆነ በተዘዋዋሪ በንጹሃን ደም የጨቀዬ የባእድ ቅጥር፤ ጨካኝ፤ የወሮበላ አለቃ የነበረውን፤ የወንጀለኞች አባወራን፤ ቅዱስ መንፈስ
በርአይ ተገልጾ የአገር ልማትን እዳሳያው ተደረጎ፤ በአዲሱ የእጅ አዙር ቅኝ ገዥ ርዮት ላይ የተደነገገ ልማታዊ ዘርፎ አዘረፊ፤
እኩይ አቻ የማይገኝለትን ስነስርአት ተብሎ በአዋጅ በዚሁ ፈላጭ ቆራጭ
ወነጀለኛ ትእዛዝ፤ በሀገሪቱ አዋጅ ሆኖ በባለ ርአዩ ተብዬውና በአበሮቹ
እዲሰራበት ተብሎ ሥራ ላይ ዋለ ተብሎ የተለፈፈው። ዛሬ ዛሬ ደግሞ በቆሌቢስ በቅጽል ስሞ ሾተላይ ተብሎ በሚጠራው የበለይ ካደሬ፤ ተልእኮው እዳልተሟላ ተገልጾዋል። ጅራፍ እራሱ ገረፎ እራሱ ይጮሀል ነውና፤ ሰብ አሰባብ ፈጥሮ፤ ሌላው ላይ ማላከክ፤ አላያም ሕዝብን አወናብዶ መደለል ስርአቱ የተካነበት እኩይ ሥራ ስለሆነ ሊደንቀን አይገባም። የሚደንቀው የማወናበድ ሥራውን ነው።
ይህ ሁሉ የማወናበድ ሥራም ልማታዊ መንግሰት ከሚለው መስፈረት
ጋር አያይዞ ያው ሕዝብን ለመደለል እሳቤን ያደረገ ፀረ-ኢተዮጵያዊ፤ ፀረ-ነፃነት አንጋሽ፤ ከዚህ ቀደም ይህው እኩይ ስብስብ በሁሉም
ዘርፍ የአገር አነድነት የሕዝቡ አብሮነት አቆራኝ እሴቶችን ተንደው እዲጠፉ ማድረግ ሥራን በቀጣይነት እዲገፋበት የሚያደርግ መሆኑን
በመገንዘብ፤ ዘርፎ ማዘርፍ ተልእኮ ሥራውንም አነግሶ ለማከናውን እሳቤን በማድረግ እሰቤ እደሆነ አይጠረጠርም። እደሚታወቀው ሕዝብ አብሮ ካበረ እንቢኝን
አነግቦ ይታገላል። ከተከፋፈል ግን ለቁጥጥረ አመች ከመሆኑም፣ እሰከዛሬ ወያኔ-ሕውሃት/ኢሀድግ፤ ሰበበ አሰባባትን እየፈጠረ፤ እደተለመደው፤
ሕዝብ ለሕዝብ እዲናቆር፤ እዲጣላ፤ እዳይተማመን ያደረገዋል። ለዚህም ነው ላለፉት ዓመታት የልብ ወለድ ተረት ተረት ፈጥሮ በታሪክ መልክ
በጎሰኝነት ሰክርው ባበዱ ኤትኖ ፋሽስት ልሂቆቹ አመካኝነት፤ ፀረ-ኢትዮጵያ ታሪክ በመጽሃፍ ተደረሰው እዲወጡ የተደረገው። ለዚህም ነው፤ የአዲሱ የእጅ አዙር ቅኝ ገዥ ባሕልን
አንጋሽ፤ ሥራን ለማስፈጸም፤ አይምሮዋቸው በጎሳ ጽነፈኝነት የተጎዱ ስብስቦች፣ የአገር ጡት ነካሽ፤ ደፋር ከሃዲ የበረት ልጆችን አሰልፈው፤
እ.ኤ.አ በ1889 በቤልጅሙ ንጉስ በንጉስ ሊዎፖልድ ሁለተኛው በኮንጎ የተደረገውን የሴቶች ጡት መቁረጥ ወንጀልን የአገር ታሪክ
አድረጎ በሀሰት በማቅረብ፤ ሃውልት ስርቶ፤ በሃሰት የሃገርንም ሆነ የአፍሪካን ሕዝብን ታሪክ አኮሳሽ፤ አዋራጅ ወነጀልን መፈጸምም፤... እዲሁ ከልማታዊ ዘርፎ ማዘረፍ የእጅ አዙር ርዮት ጋር ተያያዥነት ያለው በመሆኖ የሚታየው። (ለዚህም ነው ከጥነት ከጠዋቱ የወያኔ/ሕውሃት-ኢሃድግ የጋራ ታሪክን ማጥፋት ዋና አላማው አድረጎ የተነሳው። የጋራ ታሪክ ሕዝብን አነድ ሰለሚያድረግ፣ የሕዝብ አነድነት ለወያኔ ተልእኮ እንቅፋት ስለሆነ የሚጠፋበት ምሱ በመሆኑ አጥብቆ ይጠለዋል። )
በመሆኑም ልማታዊ ዘርፎ አዘረፊ ወይንም ልማታዊ መንግሰት ማን
እደፈጠረው፤ ምን እደሆነ እነዴት እደተፈጠረ በሃሪውም ምነ እደሆነ መዳሰሱ ከላይ የተሰነዘሩትን ገለጻዎች አጠናካሪ ጭብጥን ያሰገኛል።
የእጅ አዙር ቅኝ ገዥ ቡድን ትላንት፤ በአፍሪካ በአዝያ በላቲን አሜሪካ፤ እደ ድንገንተኛ ውሃ የሶሻሊስት ርዮት
መላውን አህጉሪቱን ያጥለቀልቃል ብሎ በመስጋት የፈጠሩት ርዮት ላይ የተመሰረተ፤ ያጋብሶ አደር የኢኮኖሚ ሕልዮ እደሆነ፤ ከላይ እደተጠቀሰው
ልማታዊ ዲሞክራቲ የእጅ አዙር ቅኝ ገዥ ተስፋፊ ርዮት እደሆነ፤ ሕልዮቱም የዚሁ ተስፋፊ ኃይልን የፖለቲካ፣ የመሃበራዊና (አውሮፓን አንጋሽ ባህል
ማስፋፊያ) ጥቅም ለማሰጠበቅ እደሆነ በግልጽ ይታወቃል። በመሆኑም፤ የልማተዊ ዲሞክራቲ ሕልዮ መሰረቱ ትናንት ከቀዝቃዛው ጦርነት
ማለቂያ በሗላ ሳይሆን ቀደም ሲል ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በፊት ሶሻሊዝም በዓለም ዙሪያ የነበረው ተቀባይነት ያሰጋው አሜሪካ
በልሂቃናቱ አማካኝነት በዓለም ዙሪያ የአጣውን የርዮት ተቀባይነት እደገና ተንሰራርቶ እዲነግስ ታስቦ ተቀንቅኖ የተፈጠረ ለመሆኑን
በመረጃ ይታወቃል። እሰከ ቀዝቃዛው ጦርነት ማለቂያ ድረስ የምዕራብ
ሀገራት ርዮት በአፍሪካ ይህ ነው የሚባል ተቀባይነት እዳልነበረውም፤ በዘመኑ የነበረው የኃይል አሰላለፍ ምስክር በመሆን ይጠቀሳል።
የልማታዊ ዲሞክራሲ እናት ተብላ የምትጠራውም ጃፓንም ሆነች፤ የምስራቀ ኤዝያን በመባል የሚታወቁትን አገራት እድገተ ታሪክ መዳሰሱ
ጉዳዩን በቅጡ ለማወቅ ግድ ይሏል።
ጃፓን ከናዚ ሂትለር ጀርመን እና ከፋሽሰቷ የቬኒቶ ሞሶሎኒ ጣልያን ጋር በመወግን በፈጠረቸው የሁለተኛ የዓለም
ጦርነት ምክንያት አሉ የሚባሉ ኢነዱሰትሪዎቿ ሆሉ፤ ተንኮታኩተው፤ በአሜሪክን የሃይል ቁጥጥረ ውስጥ እድትወድቅ ተደረገ። በመሆኑም
ጃፓን ከኮሚኒስት አገራት ጋር ባላት የምድረ ፀፋዊ ድነበረተኝነት አማክኝነት፤ እደ ምእራብ ጀረመን ሁሉ የቀዝቃዛው ጦርነት መአከል ሆነች። በመሆኗም፤ የአገሪቱ
የኢኮኖሚ መዋቅሮች መልሶ መስራት፤ ከምእራቡና ከምስራቁ የርዮት ትንቅንቅ አንጻር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ ባጭር ጊዚያት በአሜሪካን
ረዳትነት አገሪቱን መልሶ ለመገንባት እቅድ ተይዞ፤ መላው የአገሪቱ ኢኮኖሚ ተሽመድምዶ ወድቆ የነበረው፤ ባጭር ጊዜ ውሰጥ አገግሞ
ለእድገት እዲበቃ ላካባቢውም ሞዴልነት ሆኖ ኢዲያገለግል ተደረገ። ጃፓንን በተመለከተ ሀቁ ይ ሆኖ ሳለ ያው እደተለመደው በምስራቅ
ኤዝያ የምዕራቡን ርዮትን የበላይነት ለማሳየት ልበ ወለድ ስንክሳሮችን በኢኮኖሚ ሕልዮ ስም ጃፓንን በሞዴልነት ያስቀመጠ ሕልዮ መፍጠር
ግድ ሆነ።
("The post-1945 industrial and
export-led expansions were associated with Cold War structures and were
state-directed and -controlled. The Korean and Vietnam Wars each gave an
economic boost to many of the nations in the region. Also, the anticommunist
East Asian Newly Industrialized Countries (NICs) were supported by the United
States, and dictatorships and authoritarian regimes, with strong militaries and
secret police forces, were installed to sustain anticommunism. These regimes
maintained local political conditions that allowed for the security of U.S.
military bases. Thailand also provided bases for “rest and relaxation” for U.S.
troops—that is, the origins of today’s regional sex trade".) (Stephen Gill teaches in the Department of Political Science at York
University in Toronto. He is the author of a number of books, including
Gramsci, Historical Materialism and International. Relations (Cambridge: Cambridge
University Press, 1993) and, with David Law, The Global Political Economy:
Perspectives, Problems and Policies (Baltimore: Johns Hopkins University Press,
1988. Mystification and the East Asian Model ).
የጃፓን ፈጣን እድገት መብቃት (ልማታዊ ዲሞክራቲ) ዋናው ምክንያት፤ እደሚባለው ከምእራቡ
በተለይም ከቢስማርክ ጀርምን (Prussian development
state) የፐሮዚያን ሰፍነ
ልማታዊ መንግሰት ተብየው የቅኝ ገዥ ተስፋፊ ልማታዊ መርሆ ተቀድቶ በተወሰዱ ትውፊቶች አማካኝነት እደሆነ የሚነገረውም (The
East Asian capitalist development state was borrowed from the West, most
immediately from Bismarck’s Germany. ((For a
thorough discussion of the Prussian development state and the parallels with
Japan, cf. David Landes “Japan and Europe” in W. Lockwood, The State and
Economic Enterprise in Japan, Princeton UP, 1965.) But such borrowing of
course intersects institutions and practices in the borrowing countries, and it
led to different results in Japan, South Korea and most recently in China.) ግማሽ እውነትነቱ እደተጠበቀ ሆኖ፤ በርግጥም ጃፓን አነድ በአነድ የፐሮዚያን ሰፍነ ልማታዊ መንግሰት ተብየው
የቅኝ ገዥ ተስፋፊ የገንዘብ ተቛማትን አሰራር አነድ ላነድ ገልብጣ መወሰዷን የሚያሰይ እውነታ አያጣጥለውም። በርግጥም ጉዳዩም ማን ምን
ከማን ወሰደ ሳይሆን፤ ለልማቱ ሞቶር በመሆን በዋናናት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ የሆኑ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ መዳሰሱ ላይ ነው። እርግጥነው
ከላይ በተቀመጠው ታሪካዊ ማስረጃ መሰረት፤ እ.ኤ.አ ከ1945 በሗላ
የውጭ ኢክሰፖረት ንግድ መስፋፋት ከቀዝቃዛው ጦርነት ጋር በቀጥታ በቁጥጥር ውሰጥ ገብቶ ይሰራበት እደነበር ይታወቃል። በኮሪያና
በቤትናም የነበሩት የጦርነት ግጭቶች ለከባቢው አገራት የኢኮኖሚ እድገትን ማትረፉ የማይካድ ሃቅ ነው። በፀረ/ኮሚኒሰትነት የሚታወቁት
በምስራቅ ኤዝያ ያሉ ዛሬ በኢንዱስትሪ ያደጉ የምስራቅ ኤዝያን (Taiwan
and South Korea...) (ታይዋን፤ ሰሜን ኮረያ...) አገራት በአሜሪካን የሚደገፉ አንባገነንና ፈላጭ ቆራጭ የሆኑ፤
ጠንካራ የሆነ የወታደራዊ፣ የመከላካያ ሰራዊት፣ ጨካኝ የደሕንነትና የፖሊስ ሐይል ያላቸው እደሆኑ፤ እነዚህም ሀይሎች፤ ከምዕራቡ
ርዮት በስተቀር ሌላ ርዮት ቦታ እዳይኖረው ሙሉ በሙሉ በታማኝነት በቁጥጥር ግዳጃቸውን
ሥራ ተሰማርተው አደሚሰሩ መረጃው ይጠቁማል። በማከልም ለአሜሪካ የወታደራዊ የጦር ቤዝ አመች የሆነ በአገሬው ተቀባይነት የሚገኝበትን የፖለቲካ ሁኔታዎችን በማመቻቸት
ሥራም ተሰልፈው የሰሩ እደነበር። አለፈው ተረፈውም ለአሜሪካ ወታደሮች መዝናኛ ታይላነድን መርጠው ወታደሩ እዲዝናና መዝናኛ የፍቶተ ሥጋ
መናሕሪያ መአከል ፈጥረው ትብብር በማድረግ ለ አሜሪካ በሁሉም ዘርፍ አመች ሁኔታን አደፈጠሩ ይታወቃል።
ለዚህመ ውለታ አፀፋ ይሆን ዘንድ፤ አሜሪካና የአሜሪካን ሸሪክ የሆኑት የምዕራቡ ሀገሮች ምድረ ፀፋዊ ፖለቲካዊ (Geopolitical) እሳቤን መሰረት በማድረግ፤ ለነዚሁ ለምሰራቅ ኤዝያን አገራት ገበያቸውን
እደከፈቱላቸው፤ ይህም ሁኔታ ለምስራቅ ኤዝያን አገራት የፈጣን የኢነዲሰትሪ እድገት በሌላም አጠራር “dependent
capitalist development.” “ልማታዊ ጥገኛ አጋብሶ አደር” ስርአት ፈር
ቀዳች በመሆን አደተፈጠረ፤ በመረጃው ተጠቅሶ ይገኛል። እንግዲህ እነዚህ ጭብጥ ሁኔታዎች አልፈው ተረፈው፤ በአሜሪካንን የበላይነት በጃፓንን ሁለተኛ ቀደምትነት፤ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጥምረ ሀይል ሊፈጠር እደቻለ፤ ጃፓንም ካሜሪካን በተለገሳት የበላይነት፤ የምስራቅ ኤዝያ የፖለቲካ ሀይል አነዷ ሆና አደነገሰች መረጃው በአጽንኦት ይጠቁማሉ።
ሆኖም
ባጠቃላይ ዋናው የምስራቅ አዝያ ሞዴል ቁልፍ ዝንባሌ፤ በፋይናንስ ቁጥጥር የተደገፈ መንግሰታዊ የንግድ ተቛማትን "ቁልፍ የሆኑ ኢኮኖሚ ዘርፎችን" ወይንም የግል
"አገራዊ ትላልቅ" በኤክሰፖርት የውጭ ገበያ እድገትና
ከፍተኛ ሀብትን ያሰገኛሉ ተብሎ በታመኑ፤ መንግሰት እደፍለግው፣ እደአሻው በሚያሽከረክረውና በሚዘውረው (Dirigisme) ኢኮኖመያዊ፣ ፖለቲካዊና
መሐበራዊ (አነባገነናዊ) ስርአት መሆኑ መረጃዎች ያሰዩናል። (State-sponsored
capitalism or the East Asian model is an economic
system where the government invests in certain sectors of the
economy in order to stimulate the growth of new (or specific) industries in the private
sector. It generally refers to the model of development pursued in
East Asian economies like Singapore, Japan, Taiwan and
South Korea. (An East Asian Model of
Economic Development: Japan, Taiwan and South Korea, by Paul W. Kuznets. April
1988. Economic Development and Cultural Change, Vol. 36, No. 3, April 1988.) In
recent decades it has also been used to classify the contemporary economic
system in the People's Republic of China. ( Does China follow the 'East
Asian Development Model'?, by Seung-Wook Baek. 2005. Journal of Contemporary
Asia, Vol. 35, No. 4, 2005.)
የልማታዊ ዲሞክራቲ ርዮት በግራውም ሆነ በቀኙ የፖሊቲካ አቀንቃኞች ሂስ እደቀረበበት በጥናቶች ቢታወቁም ጽንሰሀሳቡ ግን የአዲሱን የእጅ አዙር ቅኝ ገዥ ተስፋፋ (ideology of neocolonialism) እርአይ ለማስፈጸም እደሆነ፤ ርዮቱም አውሮፓን አንጋሽ በሆነ እይታ ላይ መሰረትን ያደረገ (Western dominance over such underdeveloped nations, in a
neocolonialist fashion) የምዕራቡን አገራት በአገራዊ የልማት ስም ሸፋፍነው የፈጠሩት በልማት ወደሗላ በቀሩት የአፍሪካ የአዚያና የላቲን አሜሪካ አገራት አገራዊ ልማት ላይ ተጽእኖ ፈጣሪ መሆኑን አነዳነድ ለሂቃናት "disaster
capitalism.” Disaster capitalism አደጋ ፈጣሪ ያጋብሶ አደር ስነስርአት በሚል ቃልም እደሚገልጹት፤ በቀኝም አመለካከታቸው የሚታወቁት የሙያው ልሂቃናት፤ ያዲሱ የእጅ አዙር ቅኝ ገዥ ተስፋፊ ስነስርአት ቀጥሮ ያሰቀመጧቸው፤ እደፍላጎታቸው የሚያዞራቸው አንባ ገነኖች የነጻ ገብያን ስነስርአትን ያዳክማሉ፤ የሚልም ሲሆን በቀኙ ፖለቲካም ጠርዝ አመለካከት የተመረዙ ለሂቃናትም የአውሮፓን አንጋሽ ስነስርአትን ሸርሻሪ ነው በሚል... እደሚተቹ ጥናቶች የመለክታሉ።[11]-[15] ይቀጥላል
ነፃነት ፈረደ
No comments:
Post a Comment