Wednesday, May 6, 2015

አገር አትሞት ጠባቂ ትውልድ አላትና


አገር አትሞት ጠባቂ ትውልድ አላትና


ቀና ሲታጣ፤ ይመለመላል ጎባጣ (ንብር ነቢራ፤ ዕውር ተመርዒያ) ሆነና፤ የትግሬ ነጻአውጭ ድርጅት ወያኔ ራሱን ዴሞክራቲክ አድርጐ በማቅረብ ውሎበት በማያውቀው የፖለቲካ ፈለግ ራሱን ዲሞክራት በማስመሰልና ለማቅረብ ብዙ ለፍፏል ብዙ ድራማንም ከይኖ አቅረቧል። አልፎ ተርፎም መልካም አስተዳደርን ይወሸክታል። ሆኖም የወያኔ እውነተኛ ተፈጥሮ እየተጋለጠ መጥቷል።

ወያኔ/ኢህአድግ ዛሬ በአገዛዝ ባለቤትነቱ፣ በነፍጥ አንጋችነቱ በተለይም በቅጥረኝነቱ የተነሳ ያደረገው ሁሉ ማለፊያ፣ የተናገረ እውነት ተደርጐ በባእድኑ ዘንድ ቅቡልነት አለው። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያዊው በታሪኩ የሚኮራ ሁሉ፣ የወያኔን አገር ጠልለቱንና እያደረሰ ያለውን ጥፋት ተረድቶታል። ወያኔ በባእድኑ ድጋፍ ማግኘቱ በብርቱ የተስተዋለ ነው። የውጩ ኢ-ሰብዓዊነትና ፀረ- ኢትዮጵያ የሚጠበቅና የሚፈልጉት ቢሆንም በአገራችን ፋሽዝም ሥር ሰዶ ላለፉት ሁለት አስረት አመታት በወያኔ-ህውሓት/ኢሕአዴግ ተግባራዊ እየኾነ ይገኛል

የተፈለገውን ቀለም መሆን የማይታክተውና የማይቸግረው ወያኔ-ህወሃት/ኢሕአዴግ ያለፈው ስርአት ተገርስሶ በተከፈተው የሥልጣን በር መሰስ ብሎ ከገባ ጀምሮ የአገሪቱ መደፈርና የሕዝብ መዋረድ፣ ስቃይና ሰቆቃ፣መከራና ችግር፣ መሰደድና መገደል፣ በጠላት እጅ መውደቅ፣ የአረብ አገሮች አገልጋይና ተወራጅ መሆን፣ መደብደብ፣ በእሳት ተቃጥሎ፤  በካራ አነገት ተቆረጦ መገደል፤  ሰሞኑን በደቡብ አፍሪካ፣ በሊቪያ ባህረ ዳረቻ፣ በየመን ወ.ዘ.ተ በወገን ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶች፤ የወያኔ-ህውሓት/ኢሕአዴግ አረመኔያዊ የወራሪ አሰተዳደር የሁለት አስረት ዓመት የጥፋት ተግባርና ውጤት ነው። ፋሽዝምን እንቃወማለን፣ እናወግዛለን እያለ በጫካ ያናፋ የነበረው ወያኔ/ህውሓት ዛሬ በዴሞክራሲ ድባብ ሥር እየተገበረው ያለ አገርና ሕዝብን ማዋረድና መዝረፍ፣ መቀጣጫ እያለ በግፍ ማሰርና መግደል ምን ተብሎ ሊጠራ ነው? ወደ ኃላ ተመልሰንና የአሁኑን ሁኔታ ብንመለከት የበዴኖ፣አጋሮ፣ የአርባጉጉ፣ የጎንደር፣ የኝዋኽ፣የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ታፍነው የተሰወሩት፣ 97 የሰላማዊ ሰልፍ ግድያና እስራት፣ የማጂ_ጉራ ፈርዳ፣ የቤንሻንጉል ማፈናቀልና ግድያ ምን ሊባል ነው። ሃውዜን እየተባለ የደረሰና የሚደርሰው የጭፍጨፋና አፈና ተግባር ምን ተብሎ ሊጠራ ነው? ከፋሽስት በምን ይለያል?

ወያኔ-ህውሃት/ኢሕአዴግ ሕዝብን በመናቅ የትም አትደርሱም በማለት በትምክህት በመዛት የተናገሩበት ጊዜ በርካታ ነው። የበላይ አባወራ ቱባ ቱባ ባለስልጣኖቻቸውም “ጦርነትን መስራት እንችላለን” ትዕግሥት ገደብ አለው” በማለት ያሰፈሩትን ለማስረጃ መጥቀስ በቂ ነው፡(ለመሆኑ ሌላው ሕዝብ ጀግንነት የለውም፣ ትዕግሥቱስ ገደብ ገደብ አያውቅም? ያውም እየተበደለ)ግብዝነት ወይስ ምን?

በአገራችንና በሕዝባችን ታሪክ ውስጥ ከቶም እንድ እንደአሁኑ ሳንጃ በአንገቱ ላይ ተወድሮ ጦር ተሰብቆበት ለጥቂት ዘረኞች ኑሮ ገነት፤ ለብዙኃኑ ሕዝብ ደግሞ የሲኦል ኑሮ የኾነበት ጊዜ የለም። ንፉቀ ፋሸስታዊ አንባገነን ስርአት ዛሬ በወያኔ-ህወሃት/ኢሕአዴግ ጊዜ ነግሷል ሥርም ሰዷል።  በሥልጣን ላይ ለመቆየት፣ሃብቷን በዝብዞና ሽጦ ለማፈራረስ በታቀደው የአገዛዝ ሽብር ተግባር፣ አነባገነንት በዴሞክራሲ ታዛ ሥር ወያኔ በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ እየፈጸመው ያለ ለመሆኑ ሁሉም አገር ወዳድና ወዳጅ ሁሉ ይረዳው።


የወያኔ-ህውሓት/ኢሕአዴግ ቡድን በቀጥታም ሖነ በ እጅ አዙር - ሕዝብ ይጨፈጭፋል፣ ያስፈራራል፤ ሕዝብንም  የማደናገሪያ ፕሮፓጋንዳን ያስፋፋል፣ ውሽት ይዋሻል ያስዋሻል፤ ትምክህተኛና ጦርነት ፈላጊነቱም የተፈጠረበት ባህሪው ነው። የወያኔ-ህውሓት፤ እራስ ወዳዶችን፣ ሆዳሞችን፣ ግብዞችን፣ ዱርየዎችን መሳሪያ ያደርጋል፤ ድጋፍ ሰጭ ድረጅቶችን በአምሳሉ ቀርጾ አደራጅቶ ያስፋፋል፣ ተለጣፊ ያበዛል።  ይህም ለመሆኑ በግብር ላላፉት ሁለት አስረት አመታት የታየ ታሪካዊ ሀቅ ነው።

ላለፉትም ሁለት አስረት አመታት ወያኔ-ህውሓት/ኢሕአዴግ፤ መንግሥቱን የመሰረተው፤ በብዙሃኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንገት ላይ ካራ ወይንም ሳንጃ በመደገን ነው።ወያኔ-ህውሓት/ኢሕአዴግ መንግሰት ተብዬው የዘረኛ ቡድን ሽብርተኝነት በመዋጋት እያሉ ሕዝብን የሚጨፈጭፉት፤ ተቃዋሚ ግለሰቦችን ለመግደል ብቻ አይደለም እነሱን በማሰቃየትና በሚያሰቅቅ መልክ በመግደል ሕዝቡ እንዲሸበርና እንዲፈራ በማድረግ ለመግዛት እሳቤን በማድረግ ነው

ዘረኛ አንባገነኑ ወያኔ-ህውሓት/ኢሕአዴግ ጭቁኖችን እየጨፈጨፈ በማስፈራራት የሚገዛ ነው ከተባለ ከሕወሓት/ወያኔ በላቀ ያውም በዘሩ/በቋንቋው ምክንያት በታሪካችን ማግኘት ያስቸግራል።ወያኔ በዚህ ሥራው ከፋሽስት በምን ይለያል? እየተፈጸመብን?እየተደረገና እያየነው እየደረሰብ ነው።ፋሽስታዊ ሥራ በአገርና ሕዝብ በኢትዮጵያ ላይ እየተፈጸመ ነው።

“It is nothing new or surprising, a dictator or a group of dictators in uniform or suit, also in a robe and turban etc., would never abandon the idea that he or they are above all. He would consider himself a God’s handpicked leader. Therefore, lasting compromises with him are impossible and thus he would refuse to allow other ideas to cramp his authority. The guiding principles and policies they use are based on fear. Fear has always been used to silence people and groups in a population. Fear is widespread in all dictatorial systems. Fear is a powerful motivator in enforcing tolerance, obedience, and making people submit to authority, it is a pillar of totalitarian systems. Fear from State has always been tangibly present in all totalitarian, and cult systems, such as Italy under Mussolini, Nazi Germany under Hitler, China under Mao, the Soviet Union under Stalin, and the Arabs and other states under the Islamic regime. The threat of punishment, torture and being killed is widely dispersed enough to cause fear. Fear has systematically been spread by state institutions throughout history.” 


ወያኔ-ህውሐት/ኢሕአዴግ ሕዝብ እንደ መንጋ ይከተላቸው ዘንድ እንዳሴሩ ናቸው፣ ወዳሴላሰማ የመኖር ዋስትናውን አደጋ ላይ ጥለውታል። ፋሽስት የማደናገሪያ ፕሮፓጋንዳን ያስፋፋል፣ ሁሉም አዲሃሪያን ሕዝቡ አሜን ብሎ እንዲገዛ የማያቋርጥ ማደናቆሪያ ውሸትን ይዋሻሉ። ዛሬ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሥራ አጥተው የምጽዋት አሳዳጅ በሆኑበት የተቃዋሚ ድርጅቶች መሪዎች፣አባላቶቹ ሲታሰሩ፣ሲገደሉ፣ጽፈት ቤታቸው ሲዘጋ፣ የነፃ ፕረስ ጽሀፊዎች፣አሳታሚዎች ዘብጥያ የሚወረወሩበት፣ የሃይማኖት ቅራኔና ጣልቃ ገብነት፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ የመከራ፣ የእንግልት፣ የችግር ጩሆት በሚያሰማበትና አገር በምትፈራርስበት በዚህ ፈታኝ ወቅት ወያኔ በፕሮፓጋንዳ መሳሪያዎቹ ምን እያሰማን ነው?

ምን እያወጋን ነው? ሰላም ሰፍኖ፣ የዲሞክራሲ ፀደይ ፈክቶ፣ ፍትህ ሰፍኖ፣ አንድነት ተጠናክሮ፣ ብሔራዊ ብልጽግና ተገኝቶ፣ ልማቱ፣ እድገቱ፣ ህዳሴው፣ ጤንነቱ፣ ትምህረቱ፣ ጥጋቡ፣ የርሻው ምርቱ ሳይቀር በሁለት አሃዝ አድጐ እየተባለ የውሸት ኩየሳ አይደለም የሚከመርልን! ፋሽስቶች ዋሾዎች ናቸውና ከወያኔ/ህወሃት የበለጠ ዋሾ የት ሊገኝ እንዳውም የናዚው ጀርመን አዶልፍ ሂትለር የእኔ ታሪክ በሚለው መጸሐፉ ትንንሽ ውሸቶች ተለምዶያዊ ስለሆኑ ትልልቅ ውሸቶችን መዋሸት እንደሚያሻ የገለጸውን። ዛሬ ወያኔ/ህውሃት በዋናነት በተለይም ሟቹ መለስ ዜናዊና አገዛዙ እንደሚጠቀሙበት በግልጽ የታወቀ ነው።ፋሽስት ማደናገሪያ የተፈጥሮውና ተግባሩ በውሽት የገነነ እሙን ሆኗል። ስለዚህም ነው ወያኔ አንድ ጊዜ የግራው አልባኒያ አቀንቃኝ በሌላ ጊዜ ደግሞ የነፃ ገበያ ተርቲበኛ እያለ የሚገላበጠው።ወያኔ ዋሾ የሆነውን ተግባሩን ስንረዳ፣ መለያው የሆነውን ውሸት ስናስተውል ለጽ/ቤታችው ዘበኛ የሌላቸውን፣ በእጃቸው ዱላ እንኳን ያልያዙ ግለሰቦችን ጦርነት አወጁብን፣ ሽብር አስነሱብን፣ ቦምብ አፈነዱ፣አመጽ አስነሱ ብን በማለት ራሱ በራሱ ወንጅሎ በውሽት ምስክርና ፍርድ ቤት ያዳመጠበትና የተቀበለበት ሁኔታ ይጤናል።

ፋሽስት ትምክህተኛ (እብሪተኛ) ጦርነት ፈላጊ ነው። ፋሽስታዊያን ፀረ-ጭቁኖች ስለሆኑ የብዙሃኑን ስብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት አያምኑበትም። ፋሽስት ትምክህተኛ ጦርነት ፈላጊ ነው ተብሏል። ትምክህተኝነት የሚመነጨው ከማን አህሎኝ እኩይ ስሜት ባህሪ በመሆኑ ማን አህሎኝ ያለ እኔ እብሪት የሚቀፈቀፈውና የሚጫረ ከወታደራዊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ የበላይነት እንደሆነ ይገለጻል። ስለሆነም ዛሬ የቤተ መንግሥቱ ባለቤት ወያኔ-ሕውሓት የወታደራዊ የበላይነት የፈጠረለት እብሪት ከዚህም የመነጨ ትምክህትነት አለው። ጦረኛነቱም ደግሞ አማጢና ሽፍታ (ወያን) በነበረበት በጫካ ዘመኑ ለመሆኑ በውል ይታወቃል።


አሁን በሥልጣን ላይ እያለም ጦርነት መፈለጉ፣ የሚያደርስው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ያመለክታል። በየጊዜው የሚያደርስው ጭፍጨፋ፣ በመትረየስ መረፍረፍ፣ የአዲስ አበባ ተማሪዎች ላይ በየካቲት አደባባይ የደም ጐርፍ ማፍሰስ፣ ቤተክርስትያንን ማቃጠል፤  ገዳማትን ማፍረስና መነኮሳትን ማሳደድና መግደል፣ ሕዝብን ከቦታው ማፈናቀልና መግደል ሃብቱን መቀማት ... ወዘተ ወያኔ/ህውሃት ወዳጅነት ለማፍራት ሳይሆን ለጦርነት ፍላጐት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። ዘወትር ስለ ሃውዜን ማውራትና መስበክ ሰላማዊ አያደርግም፣ ሰላምንም አያመጣም ?

ወያኔ/ኢህአድግ የፖለቲካ ሥራው ተቃዋሚዎችን ወደ ትጥቅ ትግል እየገፋና አመጽን እየጫረ ጦር ይምጣ እያለ የሚያልም አረመኔ ፋሽስት ነው። ስይጣን ቢያረምም ባህታዊ አይሆንም” እደሚሉ የአዛውንቱ ቢሂል የወያኔ ልፈፋው ቢጠና ጦርነት ነው። ወያኔ-ህወሃት ጦርነትን እንደ ታላቅ ጥበቡ፣ እንደ ታላቅ እሴቱ በመቁጠር ሕዝብን በሚፈልገው መንገድና መልክ ለመቅረጽ መውተርተሩ ዴሞክራሲና ስብዓዊ መብት የሚባለውን አለማወቁንና አለማመኑን ያስጤናል። ድሮስ ! ወያኔ ጠባብ ጎጠኛ ፋሽስት ነው ምን መልካም ምግባር ይኖረዋል? ከወያኔ-ህውሃት/ኢህአድግ ሰላምና ዴሞክራሲ የማይታሰብ ነው።

ፋሽስት በራስ ወዳዶች፣ በዱርዬዎች፣በወሮባላዎች የሚመሰረት ስርአት ነው። ሥራአጥ ወንዶችንና ሴቶችን የጎዳና ተዳዳሪ በማለት ሰይሞ እንደ ቀንደኛ መሳሪያ ይጠቀምባቸዋል። ወያኔ/ህወሃት በኢትዮጵያ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመት ያሳየን ይህንኑ ነው። ከየሁለተኛው ደረጃ ፈርጥጠው ጫካ የገቡ የትግራይ ተወላጆች፣ ቤተሰብ ለማስተዳደር እንኳን ሙከራ ያላደረጉ ተመክሯቸው ነፍሰ ገዳይ የሆኑ ናቸው። እንዲሁም የወያኔ ፋሽስት አጃቢዎች በውጭ አገር በስደት የኖሩ ከትምህርቱ ትምህርት፣ የሌላቸው የተወነባበደባቸው፤ ዝንቱ ከንቱ ኑሮን የኖሩ፤ በምንዳ ተታለው በበሉበት መጮህ የለመዱ በጨው እንደተታለለች ፍየል ሆዳቸውን አስቀድመው፤ ከወያኔ ጋር ወግነው የግንቦት የወያኔ አቢዮተኞች በመሆን ከመረብ ወዲህና ከመረብ ባሻገር ካሉ ጎጠኞች ጋር ተቀናጅተው የምንወዳትን ኢትዮጵያን፣ ነፃነት አፍቃሪ ሕዝቧን እያፈራረሱ ያሉት።ፋሽስታዊ ባህሪያቸውም የሚንጸባረቀው የተማረውንና የሥራ ልምድ ያካበተውን አገር ወዳድ በማባረርና በማስወጣት በዱርየነትና በወሮበላነት አብረው ያሉት በመሾምና ያገርመንም ሃብት ተቃርጦ ሀብታም አድረጎ መሳሪያም በማድረግ ነው።

"Controlling information and controlling dissent are part of what goes into maintaining a totalitarian state," Jerrold Post, director of the political psychology program at George Washington University.

አንባገነኖች ማህበራትን ያስፋፋሉ ሁሉም በማህበር እንዲደራጅ ያደርጋሉ።ነገር ግን ማህበራቱን በራሳቸው ታማኝ መቆጣጠርን የበለጠ አድርገው ይጠቀሙበታል።ስለዚህም አነባገነናዊ ማህበራት ይቋቋማሉ።እነዚህን ማህበራት የራሳቸው የፍላጐት ማሟያ አድርገው ሲጠቀሙባቸው ይገኛሉ።ዛሬ ምናልባትም በታሪካች የመጀመሪያ የሆነው የድርጅቶች ፍልፈላ በዚህ በወያኔ ዘመን በከፍተኛ ደረጃ እየተሰራበት ነው።

ወያኔ በአምሳሉ እየፈጠረ፤  የምንጥስ ምናምን ተለጣፊ ለዘረኛ አላማው ጭብል መሟያ አድርጓል፣ የብዙ ዜጐችን ደም አፍሷል። ያልጠፈጠፈው ተለጣፊ ድርጅት የለም። ወያኔ ከራሱ የትግሬ ክፍል በቀር ተደራቢ ፈጥሮ ያላወጣበት ቦታ አይታይም። ወያኔ ጠባብ ዘረኛና በቪኒቶ ሞሶሎኒ የፋሽስት የቅኝ ገዥ መሰረተሃሳብ ተረቆ የተሰራ ፀረ-ኢተዮጵያዊ  ድርጅት ነው። አንባገነንነተም የወያኔ አገዛዝ አይነተኛ ባህሪ ነው።የጣሊያን ፋሽስት ዓለማ ዛሬ በቆዳ እንጂ በመሰሉ እየተፈጸመ ይገኛል።

ይህም በአገራችን የወያኔ አገዛዝ አይነተኛ ባህሪ ሆኖል ይበልጡንም የወያኔ/ህውሃት ፋሽዝም በረቀቀ መልክ በወያኔ ለመካሄዱ ምስክሩ ራሱ የችግሩ ሰለባ ጥዋ ቀማሽ የኾነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው።ወያኔ የራሱን መጥፎ ስምና ባህሪ ለሌሎች በመስጠት ለሚፈጽመው ግፍ ሁሉ ሰበብ በማበጀት፣ ማንነቱን ለመሸሸግ ቢጥርም በዴሞክራሲ ሽፋን ቢለፍፍም አንባ ገነንነቱና ፋሸታዊ መገለጫ ባሕሪው፤ አግጦ፣ አፍጦ እየታየ ይገኛል። ያዳኝ ውሻ ፀጉር ባአፉ ነውና የወያኔ/ህውሃት ባህሪና የጎጠኛነት ተፈጥሮው ፀሐይ የሞቀው ሃቅ ነው።

የወኔ የማንነት ባህሪና ተግባሩ ሁሉ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት ናቸው።ወያኔ ተፈጥሮው ጎጠኝነት፣ ባህሪው ፋሽስታዊ ነው።

ወያኔ፤ በሰነአእምሮ ማንነት ቀወሰ ውስጥ የተዘፍቁ፤ በክፉኛ የአእምሮ በሽታ ስቃይ የሞረሹ፤


  • በሕዝብ ስቃይ ተደሳቾች፤ ( sadistic)
  • ሰብአዊነት የማይሰማቸው (antisocial)
  • በጅምላ ሕዝብን የሚፈረጁ፤ (paranoid) (እብሪተኛ፣ ትምክህተኛ፣ ነውጠኛ፣ ነፍጠኛ፣... )
  • እራስ ወዳዶች፤ (narcissistic) (ሁሉም ለኛ፤ ሃብቱም ስልጣኑም ሁሉም ሁላ ሁሉም የሚሉ)
  • በዘር፣ በጎሳ፣ በጎጥ፣ በዝምድና፣ በአብሮ አደግነት፣ በጉረብትና... የሚወግኑ፤ (schizoid)
  • ችግር ፈጣሪዎች፣ ችኮቢሶች፣ አመለቢሶች፣ ነጭናጮች (schizotypal


ክፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ስብስብ በውስጡ አቅፎ የያዘ ግንባር ለመሆኑ፤ አውደ የሰነልቦና የአነባገነኖች ማንነት ባሕሪ በሚል በኮላራዶ ዩኒበርሰቲ የመሃበረሰብ ሰነልቦና ተመራማሪ ልሂቃን ኮሊጅና ሲጋል (Coolidge and Segal)  በጋራ ያወጡትን ጥናተ ምርምር ከአገራችን  ያለፉት ሁለት አስረት ዓመታት ጭብቶች ጋር በማገናዘብ፤ በማመሰካከር እወነትነቱን ማወቅ ይቻላል።  

Personality psychologists Coolidge and Segal from the University of Colorado, hypothesized a “big six” constellation of personality disorders that may commonly reflect the personalities of dictators more generally: sadistic, antisocial, paranoid, narcissistic, schizoid, and schizotypal.” However, views differ.



psychopaths have a particular way of seeing the world. They know they're different and they easily recognize others like themselves even in a crowd. They're the enlightened, we're the rabble; they're the worthy, we're the useless eaters; they're the wolves, we're the sheep. And they know that, if those contemptible others - that is, all the rest of us - were to see them for what they are, they'd be locked up, or worse. That "injustice" - living in a world that would limit their "freedom" to prey on others - is what goads them on to create a nightmare world for the rest of us, with all the injustice of Orwell's vision and all the dead-end absurdity of Kafka's allegories. And once they have power, they intend to keep it. Objective science is thus a dangerous thing to political psychopaths and must be silenced at all costs.



ይህንም ፀረ-ኢትዮጵያ፣ ፀረ-አንድነት፣ ኢ-ዴሞክራሲዊ፣ ኢ-ሰብዓዊ አረመኔዊ ተግባሩን ለሁለት አስረት ዓመታት የኢትዮጵያ ሕዝብ በኢትዮጵያዊ ትዕግሥትና አርቆ አስተዋይነት ሲደበደብ፣ ሲባረር፣ሲገደል፣ ሃብት-ንብረቱ ሲዘረፍ፣ ዳርድንበሩ ሲወሰድ፣ አገሩ ለሁለት ስትከፈል፣የውሃ በር ሲታጣ፣ በዘር በጎሳ በቋንቋ በሃይማት አገር ስትታመስ፤ አነዱ ከሌላው ወገን በጎጥ ለይቶ በወያኔዎችዎች ጠብአቀጣጣይነት አጫሪነት፣ ተጣልቶ ደም ሲፋሰስ፣ በወያኔ መንግስትና በአረብ መነግስታት ቅንጅት፤ የሥራ እድል ፈጠራ ተብዬው ስም... ወጣቶችን ለዘመናዊ ባርነት ከአገር እዲሰደዱ በማድረግ፣ ሲገደሉ፣ የተማረ ወገን ሲገደል፣ ሲሰደድ፣ አገር ለውጭ ባለሃብት ስትሽጥ፣ ለውጭ ባነኮችም በወላግድነት እደትያዝ ሲደረግ፤  ይህ ሁሉ ሲሆን እስከ አሁን በዝምታ ታግሰሃል። እጅግም ዝምታና ትዕግሥት እንደ አለማወቅና ፍርሃት ስለሚታይ መናቅንና መደፈርን ያስከትላል።

በዚህም ሁኔታ ዛሬ ኢትዮጵያ ተደፍራለች፣ ሕዝቧ ተዋርዷል፣ የታሪክ ክብሯ ተንቋል።ለብዙ ሺህ አመታት የኛ ቀደምት ትውልዶች አጥንት ደማቸውን በማፍስስ ታፍራና ተፈርታ የኖረች አገር ዛሬ በዚህ ወቅት ትውልድ መካን ሆና ጥቃቱና ጥፋቱ እጅግ ተነባብሯል። ኢትዮጵያዊ ወገኔ ሆይ !ፍርሃት ከአደጋ የመከላከያ ባህሪ እንጂ እየሸሹ ለመጥፋትና ለመሞት አይደለም።ይህ ጭቆናና ጥቃት ሊያበሳጭ፣ሊያናድድህና ሊያስቆጣህ ይገባል።ሰውነህና ለመብትና ለነፃነት መታግልና ለመጭውም ትውልድ ለልጆችህ አገር ማቆየት ይኖርብሃል።

ለዚህም ነው አገር አትሞት ጠባቂ ትውልድ አላትና የተባለው።የኛ ቀደምት አባቶች/እናቶች እኛ ሞተን አገር ትኑር ብለው ለኢትዮጵያ ታላቅ መስዋዕትነት  ከፍለዋል። ታሪክ ምስክርነትዋን መዝግባለች።ዛሬም የኢትዮጵያዊያን ወኔና ጀብዱ፣አትንኩኝ ባይነት ይደገም። ወያኔ ኢትዮጵያዊነት የሌለው አረመኔ ፋሽስት ነው።

ስለሆነም ይህ ወያኔዊ ድርጊትና ባህሪ ከኢትዮጵያ ምድር እንዲወገድና እንዲጠፋ ወያኔ-ህውሃትን ወይንም በሽፋን ስሙ ኢሕአዴግ በይስሙላ ምርጫ ሳይሆን፤ በሕዝባዊ አመጽ ተገፍትሮና ተፈንግሎ ከነርዕዮተ ዓለሙና ሥርዓቱ መወገድ አለበት። በተለጣፊ የፖለቲካና ስውር አጀንዳ ባላቸው ድርጅቶች ሕዝብ ግራ ሳይጋባ በሀገር ፍቅር ልቡ የነደደውን፣ ለአገር ነፃነት ቆርጦ የተነሳውን ኢትዮጵያዊ ወገነህን ለይተህ ትግሉን በማጧጧፍ ሕዝብ በአንድኑቱና በኢትዮጵያዊነቱ ብርታት ክንዱን አስተባብሮ ለብሔራዊ አለኝታው በፅናት መታገል ይጠበቅበታል። በኢትዮጵያዊነቱ፣ በአሀዳዊ ኢትዮጵያ ታሪክ ለሚኮራና በአገር አለኝታ ኃላፊነትና ግደታ ለሚሰማው በተግባርም መስዋዕትነት ለአቀደ ሁሉ የቀረበ ጥሪ ጭምር ነው። ለትዕግሥት ገደብ እንስጥ፣ አንዋረድ ፣ትውልድ እንጠብቅ፣አገርና ሕዝብ እናድን።


ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !

ፈረደ ታሪኩ





No comments:

Post a Comment