Friday, February 15, 2013

ለመከላኪያ ለመከላኪያ ሰራዊት ሰራዊት ጥያቄ ጥያቄ አለኝ አለኝ…….? …….?



ከትእዝብት አድማሱ

      ሰሞኑን የኢትዮጵያ ቴለቨዥን ስከታተል ሶስት ድራማዎች ጎን ለጎን ሲካሄዱ ታዝቤአለሁ። አንደኛው 
ድራማ የመከላኪያ ሰራዊት ሳምንት በሚል እየተካሄደ ያለው ሰልፍና ኤግዚቪሽን ነው። ሁለተኛው ድራማ ጅሃዳዊ ሐራካት ፊልም በሚል ተደጋግሞ የቀረበው አስቂኝና አሳዛኝ ድራማ ነው። ሶስተኛው ድራማ ደግሞ የህወሓት 38 በዓል የትግራይ ህዝብ ልደት ነው እየተባለ በውጭና በሀገር ቤት ሲከበር ማየቴ ነው። በኔ አመለካከት ሶስቱም አላማቸውና ግባቸው አንድ ዓይነት ሆኖ ነው ያገኘሁት። አላማቸው በርዕደ መሬት እየተናወጠ ያለው ቡድን በህዝብ ፊት ሀይል (ጡንቻ) ያለው መንግስት መኖሩን ለማሳየት ሲሆን በሌላ መልኩ ደግሞ የአንድ ሞኖፓላዊ ድርጅት ጠባቂና ተከላካይ የሆነው የህወሓት ሰራዊት እየተባለ የሚነገርለትን መከላኪያ መልኩንና ቀለሙን በመቀያየር ኢትዮጵያዊ ሰራዊት መስሎ እንዲታይ እየተደረገ ያለው ጥረት ነው። ወጣም ወረደ የሶስቱም ድራማዎች ግብ የኢትዮጵያ ህዝብ ለመብቱ እንዳይተጋል በሀይል በማስፈራራት ከነሱ ውጭ በኢትዮጵያ ምድር ሌላ ተቀናቃኝና ለነፃነቱ የሚታገል እንዳይበቅል አንገቱን ለማስደፋት የተወጠነ ነው። ይህን ዓይነቱ የወያኔ የመንደር ደናቁርት ምትሃታዊ ተንኰል የወለደው የፈጠራ ተውኔት ደግሞ ባዶና ውሸት መሆኑን ኢትዮጵያዊ ቀርቶ ሌላም ጠንቅቆ ያውቀዋል።ውሸት ሲደጋገም ሓቅ ይመስላል”  ይላልና ስንክሳር መፅሐፋቸው። ወደ ተነሳሁበት ወደ ጥያቄዬ ልግባ፡- 10 ጥያቄዎች ናቸው። ልብ ብላችሁ ተከታተሉ፡………

1. ሰራዊቱየሕገ መንግስት ዘብ ነውእየተባለ በተደጋጋሚ ሲነገርለት እንሰማለን።  ለመሆኑ የተኛው ሕገ
መንግስት ነው? እውነት መከላኪያ ሰራዊት የሕገ መንግስት ዘብ ቢሆን ኖሮ የህዝብ ድምፅ በኃይል ሲነጠቅ፣ ሕገ መንግስቱ ለአንድ ሰው ብሎም ለአንድ ድርጅት መጠቀምያና መገልጊያ ሆኖ ሲቆር፣ የፍትሕና የዳኝነት ተቋማት ነፃነታቸውንና ውሳኔያቸውን በጥቂት መሪዎችና ካድሬዎቻቸው በግልፅ በአቋራጭ ሲነጠቅ ሲደፍርና ሲጣስ ለማን ነው አቤት የሚባለው? የመከላኪያ ሰራዊቱ ዘብነትና ህዝባዊነትስ የቱ ላይ ነው? ለመሆኑ ይህቺን ሚስኪን ሀገራችን ባለቤትዋ ማን ነው? እናንተ የሰራዊት አባላት የታጠቃችሁት መሳሪያም ሆነ የምታገኙት ጥቅምና ደመወዝ ከመሪዎቻችሁ ኪስ የወጣ ሳይሆን የህዝብ ገንዘብና የሀገሪትዋን አንጡራ ሀብት መሆኑን ትዘነጋላችሁ የሚል ጥርጣሬ የለኝም። ነገር ግን የመሳሪያችሁ አፈ ሙዝ ያነጣጠረው በማን ላይ ነው?

2. አሁን ያለው ሰራዊት ካለፉት ስርዓቶች የተሻለና ለሀገሩ ሉዓላዊነትና ለህዝብ ልዕልና የቆመ ነው እየተባለ ነጋ ጠባ ሲነገርለት እንሰማለን። ለመሆኑ ይችን ሀገር ከባዕዳን ወራሪዎች እየተዋጋ ክብርዋን በደሙ ጠብቆ ያቆያት ማን ነው? በአንፃሩ የሀገሩን ብሄራዊ ጥቅም፣ ዳር ድንበሩንና የባህር በሩን መጠበቅ አቅቶት የሻዕቢያ ባለሟል በመሆን መሬቱን ለባዕዳን አሳልፎ በመስጠት ሽባ ሀገር ያወረሰን የሃፄ ሀይለስላሴ ሰራዊት ነውን? ሌላ ቀርቶ የአውሮጳ ቅኝ ገዢዎች እንኳን ያን ያህል ያልደፈሩን በአሁኑ ዘመን ግን ከባዕድ ሀይል  (ከሻዕቢያ) ጋር ተመሳጥሮ ህዝባችንን ያስደፈረና ያስገደለ የሃፄ ኃይለስላሴ ሰራዊትና መንግስት ነውን?
 
3. የመከላኪያ ሰራዊት ከህዝብ አብራክ የወጣ፣ የህዝብና የሀገር ፍቅር ያለው የድል ሰራዊት ነው ሲባል
እሰማለሁ። ባንድ በኩል ያስቀኛል በሌላ በኩል ደግሞ ያሳዝነኛል። የሚያሳዝነኝ ባድመን ነፃ ታወጣለህ ተብሎ የዘመተው ሀይልና የተከፈለው መስዋእትነት ከንቱ ሆኖ መቅረቱ ነው። ጉዳዩ እስከ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ይድረስ እንጂ የመጨረሻ አሸናፊ ሆኖ የተገኘው ሻዕቢያ ነው። ሻዕቢያ ያሻነፈበት ምክንያት ደግሞ ሀቅ ስለያዘ ሳይሆን እናት ሀገራችን በፅናት የሚከራከርላት ቁርጠኛ ኢትዮጵያዊ ልጅ በማጣትዋ መሆኑን ማንም ይገነዘበዋል። ታዲያ የኛ መከላኪያ እውነት የሀገርና የህዝብ ፍቅር ያለህ ሰራዊት ከሆነክ ባድመ የማን ነው የሚል ጥያቄ አንስተህ ታውቃለህን? ከጥዋቱ ባድመ የኤርትራ መሆኑን የሚታወቅ ከሆነ ለምን ያን ያህል ደም እንዲፈስ ተደረገ? ብለህ መሪዎችህን ጠይቀህ ታውቃለህን?
 
4. የኤርትራ መገንጠል ሰላም ያመጣል ሲባል ነበር። ነገር ግን ባሰበት እንጂ አልበረደም። ሰሜኑ አሁንም
የጦርነት ቀጠና ነው። እስካሁንዋ ደቂቃ ድረስ ህይወት እየተቀጠፈ ይገኛል። ይህ ትራጀዲ መቋጫው መቼ
ነው ብለህ ትገምታለህ? በሰሜኑ ክፍላተ ሀገራችን አሁንም በየቀኑ በሻዕቢያ ታጣቂዎች እየታፈኑ የሚወሰዱትን በሽዎች የሚገመቱ ዜጎቻችን የት እንደደረሱ የሚታወቅ ነገር የለም። ዜጎቼ ናቸው ብሎ ጥብቅና የሚቆምላቸው አስታዋሽ ኢትዮጵያዊ መንግስትም ገና አልበቀለም። ታዲያ እናንተ የመከላኪያ ሰራዊት አባላት በዳር ድንበሩ አካባቢ በቀበሮ ጉድጓድ በምሽግ ተቀምጣችሁ በፍርድ ያለቀለትና የሞተ መሬት እየጠበቃችሁ መኖሩ ትርጉሙ ምንድን ነው? የራሱን ህዝብና ሀገር ድህንነትና ሰላም መጠበቅ ያልቻለ ሰራዊት የድል ሰራዊት ነው ሊባል ይችላል ወይ? በራሱ መሬት ላይ ዘላቂ ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ ያቃታው ሰራዊት የሌላ ሀገር ህዝብ ሰላም መጠበቅና ለፍትሕ መቆም ይችላልን?
 
5. የኢትዮጵያ መከላኪያ ሰራዊት የሀገርና የህዝብ ፍቅር አለው የሚለው አባባል ከነአቶ በረከት ስምዖን፣ አቶ ቴድሮስ ሐጎስ እና ሌሎች የአቶ መለስ ራዕይ ወራሾች ነን ከሚሉት መሪዎች አመለካከትና ፓሊሲ ጋር
የሚቃረን አይሆንም ወይ? አቶ በረከትበሰላሳ ዓመት ዕድሜ ክልል ያለው ወጣት ስለ ዳር ድንበርና የባህር
በር ጉዳዩ አይደለም ረስቶታልየሚሉ ናቸው። ሰራዊቱም በነሱ ራዕይና ፓሊሲ የቀረፁትና የሚመሩት እነዚህ ናቸው። ታዲያ የሰራዊቱ የሀገርና የወገን ፍቅሩ የቱ ላይ ነው?

6. የመከላኪያ ሰራዊት የልማት ምንጭና የዕድገት ተምሳሌት ነው እየተባለ ሲነገርለት እንሰማለን። በአፈ ሙዝ የሚገነባ ሀገር ቢኖር ኖሮ ሰሜን ኰሪያን በቀዳሚነት ልትጠቀስ ትችል ነበር። ነገር ግን አልሆነም። መሆንም አይችልም። በሌላ በኩል ደግሞ የኢትዮጵያ መከላኪያ የሙሱናና የዝርፊያ ተምሳሌት እንጂ የልማት ምንጭ መሆን አልቻለም ብለው በጭብጥ መረጃ እያስደገፉ የሚናገሩ ብዙ ናቸው። በትግራይ አካባቢ በህዝቡ ዘንድ መከላኪያ ማለትዱባይ ወይም ጅዳተብሎ እንደሚጠራም ጓደኞቼ ነግረውኛል። ምክንያቱም በመከላኪያ አካባቢ ወፍራም ዘመድ ያለው ሰው በአንድ ጊዜ ሚሊዮነር ሊሆን ይችላል የሚል ትእዝብት ስላላቸው ነው። ስለሆነም መከላኪያና ህወሓት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅ በሆኑበት ሁኔታ በየከተማው ፎቅ የሌለው ጀነራልና ኰኔሬል የለም ቢባል ውሸት አይደለም። ታዲያ ወገኖቼ የሀገር ልማትና ሌብነት አብሮ ይሄዳል ወይ?

7. በየዓመቱ በመቶ ሽዎች የሚገመቱ ወጣቶች ከየትምህርት ተቋማቱ እየተመረቁ በየቀኑ ስራ ፍለጋ ሲንከራተቱ ይታያል። ስራ አገኙ ከተባለ ደግሞ ከኰብል ድንጋይ ያለፈ አይደለም። ካላገኙ ደግሞ ወደ ስደት በመጉረፍ የባዕድ ሲሳይ ሆነው የሚቀሩ ወጣት ምሁራንና ባለሙያዎች ቁጥራቸው ቀላል አይደለም። በአጠቃላይ በሀገሪትዋ ሙሱና ከኤይድስ የባሰ የሰደድ በሽታ በሆነበት ወቅት መከላኪያ ብቻውን የልማት ምንጭ የሚሆንበት መመዘኛ ምንድን ነው? ሌላው ባለሙያ እየበተኑና እያመከኑ መከላኪያ የልማት ማእከል እንዲሆን የሚደረግበት ሚስጢርስ ምን ይሆን?
 
8. ሌላው የታማኝነት ጥያቄ ነው። እርግጥ ነው አምባ ገነኖች ሰራዊቱን ሲቀርፁና ሲያዋቅሩ በአምሳላቸው ስለሆነ ከሀገርና ከህዝብ በላይ የመሪዎቹን ስልጣንና ድህንነት እንዲጠብቅና እንዲንከባከብ ይገደዳል። የኢትዮጵያ መከላኪያ በተመሳሳይ በነፃነትና በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ታንፆ ያደገ ሳይሆን በአቶ መለስ ዜናዊ አመለካከትና ለአንድ ድርጅት ፍላጎትና አላማ መገልገያ ተብሎ የተቀረፀ መሆኑን ራሳቸው የመከላኪያ ሰዎች እየተናገሩ ይገኛሉ። እውነታቸው ነው። ዛሬ ከኢትዮጵያ ካርታ ይልቅ የአንድ ግለ ሰብ መሪ ፎቶ ግራፍ የበለጠ ክብር የተሰጠበት ሁኔታ ይታያል። ዛሬ መለስ እንደ መሪ ሳይሆን እንደ ፈጣሪ የሚታይበት ጊዜ መሆኑን በግልፅ እየታየ ያለ ጉዳይ ነው። ታዲያ ሀቁ ይህ ከሆነ የሰራዊቱ ታማኝነት ቅድሚያ የሚሰጠው ለማን ይሆን? የሰሜን ኰሪያና የኢትዮጵያ መከላኪያ ሰራዊት መሰረታዊ የባህሪይ፣ የአቋም፣ የአደረጃጀትና የደክትሪን ልዮነት አላቸው ብላችሁ ታምናላችሁን?

9. የኢትዮጵያ መከላኪያ ሰራዊት ገለልተኛ ነው ሲባል ይሰማል። ገልተኛ ማለት ደግሞ በሀይማኖት፣ በፓለቲካ አመለካከት፣ በነፃ ዳኝነት፣ በፍትህ አካላትና በዜጎች የግልና የቡድን ነፃነት ላይ ጣልቃ የማይገባ ማለት ይመስለኛል። ሀቁ ይህ ከሆነ የአንድ ፈላጭ ቆራጭ የፓለቲካ መሪ ፎቶግራፍ እንደ ታቦተ ፅዮን ተሸክሞ የሚሄድና የሚያመልክ ሰራዊት ገለልተኛ፣ የህዝብ ወገንተኛ፣ ነፃ የፍትሕና የልማት ሰራዊት መሆን ይችላል ብላችሁ ታምናላችሁን?

10. የመጨረሻ ጥያቄ ለህወሓት ታጋዮች፣ ካድሬዎች፣ ደጋፊዎቻቸው ነው። በራሳቸው አንደበትእኛ ህወሓቶችኤርትራን ከኤርትራውያን በላይ ታግለን ያስገነጠልናትና ነፃ ያወጣናት እኛ ነንብለው በማያሻማ መልኩበሚያምኑት በአቶ ስብሓት ነጋ መሪነት የተፈጠረው የትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት (ህወሓት) ዛሬ በመከላኪያሰራዊት ታጅቦ 38ኛው የልደት በዓሉን እያከበረ ይገኛል። ይህ በዓል ደግሞ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜው ሳይሆንየትግራይ ህዝብ ልደት ነው እየተባለ በአደባባይ መከበር ከጀመረ እኖሆ ግማሽ ምእተ ዓመቱን ሊያስቆጥር ጥቂት ዓመታት ነው የቀረው። እንዲያውም በዓሉ የአንድ ፓለቲካ ድርጅት መታሰቢያ ቀን ከመሆን አልፎ በትግራይ ህዝብ ዘንድ እንደ አንድ ቅዱስ ቀን ተቆጥሮ በፍትሃተ ፀሎትና በድግስ እንዲያከብረው እየተደረገቆይቷል። ዛሬም በተመሳሳይ ደራማ በውጭም በሀገር ውስጥም ሲከበር እያየን ነው። ነገር ግን ጥያቄው 
  • የካቲት 11 የማን ልደት ነው? የበረከት? የስብሓት? የቴድሮስ? የመለስ? የጥቂት ካድሬዎች? ወይስ በስሙና በደሙ እየተነገደበት ሳይወድ በግድ የኤርትራ ነፃነት ማዳበሪያና የጥቂት ከሃዲ መሪዎች የስልጣን አገልጋይና መሳል ሆኖ እንዲኖር እየተደረገ በሁለት አለንጋ እየተገረፈ የሚገኘው ህዝብ ልደት ነውን?  
  • የትግራይ ህዝብ በጀግኖች አባቶቹ የሰማእታቱ መቃብር ላይ ቆሞ የህወሓትን ልደት በጭፈራና በዳንኬራ የሚያከብርበት ዋና ምክንያት ምን ይሆን? እውነት በደሙ ራሱ የገነባትን ሀገር ተመልሶ ራሱ በማፍረስ ዛሬ ባህር አልባ የሆነች ሽባ ሀገር ይዞ በመቅረቱ ደስ ብሎት ይሆናል ብላችሁ ታምናላችሁን
  • የትግራይ ህዝብ የህወሓት ልደትን የሚያከብረው ባድመ የኛ ነው፣ መሬትህ በባዕድ ተደፍረዋል፣ ዛሬም እንደ ትናንቱ ተነስ!! ክተት!! ተብሎ የከፈለውን መስዋእትነት ከንቱ ሆኖ በመቅረቱንና መሬቱን ተሸንሽኖለባዕድ በመሰጠቱ  ምክንያት ደስተኛ ስለሆነ ነው ብላችሁ ታምናላችሁን?

አትረፍ ያለው በሬ ቆዳውን ለከበሮ ይውላል እንዲሉህወሓት የትግራይን ህዝብ ሁለት ጊዜ ገድሎታል። አንድ ኤርትራን ነፃ ለማውጣት በአስር ሽዎች የሚቆጠሩ ለጋ ወጣቶች በሳህል በረሃ የአምራ ሲሳይ ሆነው እንዲቀሩ አድረጓል። ሁለተኛ ደግሞ ህዝቡ አድኑን እያለ ሲጮህ ጆሮ ዳባ በመስጠት አሳልፎ ለጅብ በመስጠት ዳግም በሻዕቢያ ወረራ እንዲቀጠቀጥና እንዲደማ አድርገዋል። ለዚህም ነው ደደቢት የጥቂት ከሃዲዎች በዓል እንጂ የትግራይ ህዝብ ልደት አይደለም የምንለው። ዛሬ ጥቂት ሙሰኞቹን በዊስኪ እየተራጨን የምናጅብበት ጊዜ ሳይሆን ህዝብና ሀገር ማእከል ያደረገ አጀንዳ ይዘን ለመብታችን የምንታገልበት ወቅት ነው።   

Monday, February 11, 2013

ፍቅርና አንድነት ያለው ህዝብ ጠላቱን ያሸንፋል



ሉሉ ከበደ

ባለፈው ሂትለርና የወያኔን መሪዎች ባነጻጸርኩበት ጽሁፍ ላይ መለስ ስብሀት በአማራው ህዝብ ላይ በሰፊው ሊያንቀሳቅሱ የሞከሩት እልቂት አንዴት በሚፈልጉት ልክ እንዳልገፋላቸው ሗላ ላይ እናወጋለን ብየ ነበር።

በአለማችን ያሉ ጤናማ መንግስታት በዜጎቻቸው መካከል የመብት ልዩነትና የዘር የቀለም መለያየት፤ ግጭት እንዳይኖር ያለመታከት ይሰራሉ። ይተጋሉ። በኢትዮጵያ ያለው የዲያቢሎሶች መንግስት፤ ሰው በዘሩ ተለይቶ እንዲታወቅ፤ እንዳይስማማም እንዲበላላም ለማድረግ በትጋት ሲሰራ ሀያ ሁለት አመታትን አስቆጠረ።

ስርአትን መቃወም አንድ ነገር ነው።ስርአቱን ወደ ጎን አድርጎ አንድን ክፍለ ህዝብ እንደስርአት ስሎ፤ የመደብ ጠላት አድርጎ፤ አእላፍ ቋንቋ የሚናገርን ሕዝብ ለድህነትህ፤ ለሗላቀርነትህ፤ ተጠያቂ፤ ጠላትህ፤ ያንን ቋንቋ የሚናገረው ዘር ነው ብሎ፤ ባንድ ወገን ላይ የጥላቻ ዘመቻ ማንቀሳቀስ ዘርን ለማጽዳት ከሚደረግ ትልምና እቅድ የተለየ አላማ አለው ማለት ያስቸግራል።

ገዢ መደቦች ለፈጠሩት ስህተት ወይም ወንጀል፤ እነዚያ ገዢዎች የወጡበት ክፍለ ህዝብ እንደ ጠላት ተቆጥሮ ትውልድ በማያቀው ጉዳይና በማይደግፈው ድርጊት እዳ የሚከፍልበት አንዳችም ምክንያት አይኖርም። ባለፉት ሀያ ሁለት አመታት የህውሀት መሪዎች ስልጣኑን በጠመንጃ ተቆጣጥረው በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እያደረሱት ላለው በደልና ወንጀል፤ ለራሱም የችግሩ ሰለባ የሆነው የትግራይ ህዝብ ተጠያቂ ነው የሚል አስተሳሰብ ያለው፤ የሀያ አንደኛው ክፍለዘመን ኢትዮጵያዊ ይኖራል ብየ አላምንም። ምንጊዜም በሀገርና በህዝብ ላይ ለሚፈጸሙ አስተዳደራዊ ወንጀሎች፤ ተጠያቂው በአፈሙዝም ይሁን በምርጫ ስልጣን የተረከበውን ቡድን በበላይነት የሚመሩት፤ የህጉም የፖሊሲውም፤ አውጪዎችና አስፈጻሚዎች በጣት የሚቆጠሩት መሪዎች ናቸው እንጂ፤ ያመሪ የወጣበት የህብረተሰብ ክፍል አይደለም። በተዋረድ እንደየስልጣን ደረጃቸውና ሀላፊነታቸው እስከታች አርከን የወንጀሉ ተሳታፊዎች በህግ ይጠየቃሉ። ሕዝብ ከደሙ ንጹህ ነው።

1983 ወደ ሗላ መለስ ብየ ልጀምረውና በአርሲ አርባ ጉጉ፤ በአሰቦት ደብረወገግ ገዳም፤ በበደኖ፤ እና በሌሎቹም አካባቢዎች ህውሀት ወደ ስልጣን አንደመጣ በአማሮች ላይ ሊያንቀሳቅስ የሞከረው ፍጅት የተፈለገውን ያህል ውጤት ሊያመጣ ያልቻለው፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ለምእተ አመት ያካበተው ውህደት የፈጠረው፤ የወንድማማችነትና የአንድነት መንፈስ፤ አሸናፊ ሆኖ በመገኘቱ፤ ህብረተሰቡ ለዚያ መተላለቅ በቀላሉ ተነሳስቶ እነ መለስ ስብሀት ሚፈልጉትን ባለማድረጉ ነበር። ሌላው ምክንያት ታላቁ ያገር ልጅ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የመሩት እንባ ጠባቂ የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት፤ በዚህ ክፍለ ህዝብ ላይ የሚፈጸመውን ሰቆቃና በደል፤ ወያኔ ይዞት የመጣውን የዘር ማጥፋት እቅድ፤ በያለሙ እንዲስተጋባ በማድረጉ፤ አሁን ያለው የአለም ተጨባጭ ሁኔታ ያንን ሊያስቀጥል የሚችል አለመሆኑን ጌቶቻቸው ስለ ነገሯቸው ሊቀጥሉበት አልቻሉም።
ወደ መጀመሪያው ሙከራቸው ልሂድና የመጀመሪያውን እልቂት ሊያንቀሳቅሱ የሞከሩት የህውሀትንና የኦነግ ወታደራዊ ካድሬዎችን በማሰማራት ነበር። ህውሀትና ኦነግ ያሰማሯቸው የሁለቱ ቡድን መልከተኞች ናቸው አንጂ በአርሲም በሀረርጌም ያን መተላለቅ የፈጠሩት አብሮ የሚኖረው ህብረተሰብ አልነበረም።

ለዚህም ማስረጃ በወቅቱ እዚያው አካባቢ ስለነበርን ሀረርጌ በአካል ህብረተሰቡ ውስጥ ተገኝተን በተለይም ህውሀት ግጭቱን ለማንቀሳቀስ ኢላማ ያደረጋቸው አማሮችና ኦሮሞዎች እንዴት በመተሳሰብ ያንን ሁኔታ እንዳሳለፉት እንድ ተጨባጭ ታሪክ አቀርባለሁ።

ሐረርጌ አንድ ገጠር አውራጃ ውስጥ አማሮች እየታደኑ በሚገደሉበት ሰሞን የህውሀትና የኦነግ ካድሬዎች ባንዲት ገበሬዎች መንደር አንዱን ኦሮሞ ኢትዮጵያዊ ጎልማሳ በገዳይነት ሊመለምሉት እቤቱ ይመላለሳሉ። አስፈላጊ ነው ብለው ያመኑበትን የፖለቲካና የዘር ጥላቻ ትምህርት ለሳምንታት በቤቱ እየተመላለሱ ከሰጡት በሗላ መሳሪያ ያስታጥቁታል። ልብ ይሏል በዚያን ጊዜ እነሱን መቃወም የኦሮሞን ነጻነት መቃወም ተደርጎ እርምጃ ያስወስዳል። ያ ድሀ አርሶ አደር አስፈላጊው የፖለቲካ ትምህርትና መሳሪያ ከተሰጠው በሗላ የተነገረው ተልእኮ ባካባቢው የሚኖሩ አማሮችን ስለሚያውቅ እያደነ እራሱ እንዲገድል ነበር።እዚያው አጠገቡ አብሮ አደግ ጉረቤቱ የሆነ ሰው ይኖር ስለነበረ ሄዶ እንዲገለው ትዛዝ ይሰጠዋል። ይህን ብለውት ከቤት እንደወጡ እሱም አብሮ ይወጣና ቆይቶ ወደቤቱ ተመልሶ ይመጣል።

ከሰአታት በሗላ ተመልሰው ግዳጁን ተወቶ እንደሆነ ይጠይቁታል። እቤቱ የለም ይላቸዋል። አብሮ አደግ ጎረቤቱ ግን ከሚስቱና ከልጆቹ ጋር እሳት ዳር ቁጭ ብለው ይጫወቱ ነበር። እነዛ የኦነግ እና የህውሀት አረመኔዎች ሲመጣ ጠብቆ እንዲገለውና ሪፖርት እንዲያደርግ ማስጠንቀቂያም ጭምር ሰተውት ይሄዳሉ። አሁንም ይህ አርሶ አደር ከቤት ወቶ እነሱ ሲሄዱ ተመልሶ ከቤቱ ይቀመጣል። በድጋሜ ተመልሰው መጡና ትዛዛቸው መፈጸሙን ሊያረጋግጡ “ገደልከው?” አሉት።

ያ ቅዱስ የኦሮሞ አርሶ አደር እንባውን እያፈሰሰ “…እባካችሁ ተውኝ .. ይህን ድሀ አብሮ አደግ ወንድሜን ግደል አትበሉኝ ። ይህንን የኔቢጤ ሚስኪን ብገድለው ድህነቱና ቅማሉ አንጂ ምን ይተርፈኝ መሰላቸሁ። ግደሉኝ ብትፈልጉ… አልገለውም..፡ “ በማለት ያሸከሙትን መሳሪያ ወዲያ ወረወረው። እነዚያ ካድሬዎች ያንን ድሀ አማራ ያን እለት ከነልጆቹ ይዘውት ሄዱ። ወዴት እንዳደረሷቸው ግን አይታወቅም።

በዚያን ጊዜም ሆነ አሁን ከሀያ ሁለት አመታት በሗላ ወያኔዎችም ሆኑ የተወሰኑ ኦነጎች ችግራቸው ለራሳቸው ተጭነውት የሚሰቃዩበትን በሽታ በቀጥታ በህብረተሰቡ ላይ ለማራገፍ ከመጣደፍ በቀር እዚያ የደረሱበት አካባቢም ሆነ በማናቸውም ጥግ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ “በእንዴት ያለ ሁኔታ ነው አብሮ መኖር የያዘው? ትስስሩና ፍቅሩ እምን ድረስ ነው? ውህደቱና ስምምነቱ እምንድረስ ነው ?” ብለው የህብረተሰቡን ሁኔታ ለማጥናት ጊዜ አይወስዱም።የኢትዮጵያ ህዝብ እነሱ በታወሩበት የዘረኝነት በሽታ ታውሮ የሚኖር ነበርም ነውም የሚመስላቸው።

በወቅቱ የታዘብኩትን ሌላ ገጠመኝ ላውጋ። እዚያው ሀረርጌ ውስጥ ነው። ጊዜዋም ያችው ቀውጢዋ ነበረች። አንዲት የወረዳ ከተማ ውስጥ ልዩ ልዩ ብሄረሰቦች ይኖራሉ። አብዛኛው ኦሮሞ ይሁን እንጂ አማራ፤ ጉራጌ፤ አፋር፤ከሶማሌ ብሄረሰብ ኢሳ የሚኖሩበት ከተማ ነች። እነዚህ ክፉ ሰዎች ገና ሁሉንም ተቆጣጥረው እንደጨረሱ ቢሆንም በደንብ አልተረጋጋም። ኦነጎችም እስር እስራቸው ይሉ ነበር። በዚች በማወሳት ትንሽ ከተማ ውስጥ አስተዳዳሪዎች ነን ብለው ኦነጎች ቢሮ ገባ ገባ ብለው የነበረበትና አለቆቻቸውም ከወያኔ ጋር ሽግግር ምክር ቤት ሽር ጉድ ይሉ የነበረ ጊዜ ነው። ክልሉ የኦሮሞ ስለሆነ እናስተዳድራለን ይሉን የነበሩት የኦነግ ታጣቂዎች አምስት ስድስት ትላልቅ የኝነት መኪና ሞልተው፤ ጠመንጃ ተሸክመው፤ ላይ ታች በከተማው ዥው ዥው ይሉ የነበሩቱ እያስተዳደርን ነው ብለው ቢሮ በገቡ በሶስተኛው ቀን፤ ኦሮምኛና ትግርኛ እንጂ አንዲት የአማርኛ ዘፈን እንዳንሰማ በማለት “ይህንን ግም አፍ” ከእንግዲህ ሲያዘፍን የተገኘ እርምጃ ይወሰድበታል ብለው ሖቴሎችና ሻይቤቶች ሳይቀሩ አማርኛ እንዳያዘፍኑ ትዛዝ አስተላለፉ። ጠቅላላው የከተማዩቱ ነዋሪ ፈራ። ወዲያው ደግሞ ቀጠሉና በአራተኛው ይሁን በአምስተኛው ቀን የአማርኛ ቋንቋ እንዳይነገር መመሪያ ሰጡ።

በዚህን ጊዜ ነው የከተማዩቱ ኦሮሞ ነዋሪዎች ከሌሎቹ ነዋሪዎች ጎን በመቆም “አይዞአችሁ። እነዚህ ኦሮሞዎች አይደሉም። ምን እንደሆኑም አናውቅም። ተረጋጉ ።” ብለው በቀጥታ ከነዚያ ሰዎች ጋር መላተም የጀመሩት። በከተማዩቱ የኢሳ ብሄረሰብም ይኖራል ብያለሁ። ለገበያ ይመላለስባታል። እነሱም ክልሉ የኛነው ይሉ ነበረና ይህ ሁሉ ሲሆን ለካንስ ኢሳዎች በጥሞና እየተከታተሉ “ምንድናቸው?” ብለው ይጠይቃሉ። “ኦነግ” ይሏቸዋል። “ኦነግ ምንድነው? ምን ያደርጋሉ እዚህ?” “የኦሮሞ ነጻ አውጭ ናቸው ያስተዳድራሉ” ተባሉ።

በመሰረቱ ከጥንት ጀምሮ የኢሳ ብሄረሰብና ኦሮሞ ይጣላሉ። ልማዳዊ አለመግባባት አለ። የኢሳ ብሄረሰብ ዘላን ከብት አርቢ ስለሆነ ሳር ፍለጋ ከብቶቹን ከቦታ ቦታ በሚያንቀሳቅስበት ጊዜ ኦሮሞዎች የሚኖሩበትንም አካባቢ መድረሱ ስለማይቀር፤ የተሰማሩ ከብቶችን ካገኘ እየቀማም እየዘረፈም ከመንጋው ቀላቅሎ ይዞ መሄድ የተለመደ ነገር ነው። ለማስመለስ መሳሪያ ሳይቀር ይመዘዛል። ሰውም ይሞታል።

እና ታዲያ አሁን በማወሳት ከተማ ውስጥ ሕዝቡን መከራ እያበሉ ያሉትን የኦነግ ተዋጊዎች “ይህ ክልሉ የኛ ስለሆነ ለቃችሁ ውጡ” ብለው ሽማግሌ ይልኩባቸዋል። ጌታዋን የተማመነች በግ ላቷን ደጅ ታሳድራለች እንደተባለው ወይም ወያኔ አለልን ብለው ወይም ደግሞ ኢሳ ተዋጊ መሆኑን አለማወቅ፤ ማስጠንቀቂያውን ከእቁብ ሳይቆጥሩ ሰዉን ማሸበራቸውን ቀጠሉ። በዚህን ጊዜ ኢሳ ጦርነት ሊከፍት ከየገጠሩ እየተጠራራ በከተማዩቱ ሰፍሯል። እነ ኦነግም በበርካታ የጭነት መኪኖች ሞልተው ላይ ታች ይላሉ። ጥቂት የወያኔ ወታደሮች ከተማው ጥግ ሰፍረው የሚሆነውን ይከታተላሉ። ጣልቃም አይገቡም።

አንድ ቀን ጠዋት ማለዳው ላይ ያቺ ትንሽ ከተማ በቀላል ነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያ ተኩስ ልትፈነዳ ደረሰች። ለሁለት ሰአት አካባቢ ሞቅ ያለ ተኩስ ከተሰማ በሗላ፤ መልሶ ጸጥ ለጥ ረጭ አለ። እስከቀትር ድረስ ሰውም ከቤት አልወጣ ከተማዋ ጭር እንዳለች ዋለና ሗላ ላይ የኢሳ ብሄረሰብ ወዲያ ወዲህ ሲል ሁላችንም ከተሸሸግንበት ወተን የሆነውን እናጠያይቅ ጀመር። አዎ እነዚያ ሰዉን ያምሱት የነበሩ የኦነግ ጂሎች መሬት ይግቡ ሰማይ የደረሱበት አይታወቅም። የሞተው ሞቶ የቀሩት ድራሻቸው ጠፍቷል። ወዲያውኑ በየሆቴሉ በየሻይቤቱ የአማርኛ ዘፈን ይሰማ ጀመር። ሰውም ጮክ ብሎ አማርኛ ያወራ ጀመር።

የከተማዪቱ ኦሮሞኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች በዚያን ሰሞን ለቀረው ህዝብ ያሳዩት አጋርነትና ተቆርቋሪነት፤ ያሳዩት ወገንተኝነትና አብሮነት የዘር ድርጅት መሪዎች እጅግ ብዙ ሊማሩበት የሚያስችል ክስተት ነበር።

ታዲያ ግጭቱ ከተከሰተ በሗላ ምን ይሆን ትተው የሄዱት፤ በየቢሮው ጥለውት የሄዱ ሰነድ ካለ ምን ይሆን እቅዳቸው አልንና የተወሰንን ሰዎች በየቢሮው ገብተን መበርበር ጀመርን። ያገኘነው አስደንጋጭ ነገር ቢኖር በከተማዋ ነዋሪ የሆኑ፤ ነዋሪው በጠቅላላ የሚያከብራቸው፤ የሚወዳቸው፤ ያገር ሽማግሌዎች የሞተን የሚቀብሩ፤ የታመመን የሚያስታምሙ፤ የተቸገረን የሚረዱ፤ አስራ ስድስት ነዋሪዎች ስም ዝርዝር እንዲገደሉ በቃለጉባኤ ተፈርሞበት ተቀምጧል። ለኦሮሞ ህዝብ ነጻነት እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ ነፍጠኞች ስምዝርዝር ይላል። የሚደንቀው ደግሞ ከነዚያ ሰዎች አራቱ ኦሮሞዎች ነበሩ።

ያቺ የኢሳ ብሄረሰብ ያስነሳት አጭር ጦርነት የነዚያን ንጹሀን ዜጎች ህይወት ለማትረፍ በቃች።ሕህቡንም ከመራር ሀዘን አዳነችው።

የኢትዮጵያ ህዝብ እንደነዚህ አይነት በሽተኞችን ይዞ ነው የሚጓዘው። ይህ የዘር ጥላቻ፤ ይህ የዘር ፖለቲካ፤ የወያኔን መሪዎችና መሰሎቻቸውን ለጊዜው ተጠቃሚ ሊያደርጋቸው ይችላል። በረጅም ጊዜ ጦሱ ግን የሚያጠፋቸው ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ለዘመናት ያካባተው፤ ያዳበረው አብሮ የመኖር የአንድነትና የመተሳሰብ መንፈስና ባህል ምንጊዜም በውስጡ ያለ በመሆኑ አንድ ቀን እነዚህን የዘር ልክፍተኞች በቃችሁ እንደሚላቸው ጥርጥር የለውም። የኢትዮጵያን ሀብት ዘርፈን የ ኢትዮጵያን ህዝብ በትነን የራሳችን መንግስት እናቆማለን ብለው ለሚቧችሩ ወዮ ለነሱ ይህ ሕዝብ አንድ ሆኖ በቃ ያለቀን።በመጨረሻዋ ሰአት ወዮ ለዘረኞች!

በስደት በምንኖርበት የባእድ አገር ጽንፈኛ የዘር ፖለቲካ አቀንቃኞች ለልጆቻቸው እንዴት ጥላቻን እንደሚያስተላልፉ የሚያመለክት አንድ ገጠመኝ ላክል።ይህንን ታሪክ ያጫወተኝ ሰው ነገሩ ለርሱ ብዙም ክብደት አልሰጠውም። የልጅ ነገር ብሎ እየሳቀ ነው የነገረኝ። እኔ ግን ከልጅ ነገርነቱ ባሻገር ነው የከፋ ነገር የታየኝ። ላንባቢያን ባካፍለው ሁላችንም እንማርበታለን ብየ አሰብኩ።

ሁለት ህጻናት ወንዶች ልጆች እድሜያቸው አስራ አንድ አመት የሆኑ ትምህርት ቤት ተከፍቶ አንድ ክፍል ይመደባሉ። ሁለቱም ኢትዮጵያውያን ናቸው። ያንኑ እለት በእፈፍት ሰአታቸው እግር ኳስ ሊጫወቱ እየተሯሯጡ ኳስ ሜዳ ገብተው ጥቂት እንደተጫወቱ ለማረፍ ወደሜዳው ጥግ ሄደው ሳር ላይ ቁጭ እንዳሉ ይተዋወቁና ጎን ለጎን ተንጋለው ወሬ ይጀምራሉ። ከየት እንደመጡ ይጠያየቃሉ። አንደኛው ከኢትዮጵያ አንደመጣ ሲነግረው ሌላኛው ከኦሮሚያ ነው የመጣሁት ይለዋል። ሁለቱም የኦሮሞ ብሄረሰብ ተወላጆች ናቸው። ይህ ከኢትዮጵያ ነው የመጣሁት የሚለው ልጅ “ ኦሮሚያ የት ነው” ይለዋል አዲሱ ጓደኛውን።

“ እሩቅ አፍሪካ ውስጥ ነው።” ይመልሳል የኦሮሚያው ልጅ
“ እዚህ አገር ከመጣህ ተመልሰህ ሄደሀል?”
“ አዎ ሰባት አመት የነበርኩ ጊዜ ሄጄ ነበር”
“ እኔም ስድስት አመት የነበርኩ ጊዜ አባቴ ወስዶኛል። ኢትዮጵያ ብዙ ደስ ብሎች አሳለፍኩ…ኦሮሚያ ከኢትዮጵያ በየት በኩል ነው?”
ተጠያቂው ህጻን ኦሮሚያ በየት በኩል ነው ለሚለው ጥያቄ መልስ ከመስጠቱ በፊት “አማራ ነህ?” ይለዋል። ከኢትዮጵያ መጣሁ የሚለው ልጅ ብሄሩንም አያውቅምና “ እኔ አንጃ “ ይላል።

ያም ቀበል ያደርግና “ ኢትዮጵያ የአማራዎች አገር ነው። ጥሩ አይደለም። ኦሮሚያ ጥሩ ነው። “ ይላል።
ብዙም አልተግባቡ ወደጨዋታቸው ይመለሳሉ። ይህ ከኢትዮጵያ ነው የመጣሁት የሚለው ልጅ ይህንን ታሪክ ለወላጆቹ ይነግርና “ኦሮሚያ የት ነው አዲስ ጓደኛ አገኘሁ” ይጠይቃል አባትን። አባትም ኦሮሚያ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ አንድ ክልል መሆኑን ያስረዳና የሚኖሩበት አገር ካናዳን እንደምሳሌ አድርጎ ፕሮቪንሶቹን እየጠራ እንደ አንዱ እንደማለት ነው ካለ በሗላ “ሁለታችሁም ኢትዮጵያውያን ናችሁ። ወንድማማቾች ናችሁ። ጥሩ ጓደኛ አግኝተሀል እንኳን ደስ ያለህ” ይለዋል።

ልጅ ይህንኑ ካባቱ የተነገረውን በሁለተኛው ቀን ትምህርት ቤት ሲሄድ ለአዲሱ ጓደኛው ያስረዳና በጓደኝነታቸው እንደሚቀጥሉ ይነግረዋል።

ያኛው ህጻን ግን ባልተጠበቀ መልኩ የሚያስከፋ መልስ ይሰጠዋል። “…ኖ!..ኖ! ከንግዲህ አንተ የኔ ጓደኛ አትሆንም አንተ….ነህ ..I hate …..” እያለ ጥሎት ይሄዳል።

በሁኔታው ግራ የተጋባው ልጅ እንደገና ይህንኑ ታሪክ ላባቱ ይወስድና አማራ ምንድነው? ብሎ ይጠይቃል። አባት ብዙ ዝርዝር ውስጥ ሊገባ አልፈለገም። “ ጓደኛ አልሆንህም ካለህ ምርጫውን አክብር። አትረብሸው። ሌላ ጊዜ በደንብ ስትተዋወቁ ጓደኛ ትሆናላችሁ “ በማለት ልጁን ያጽናናል።

ይህ ቡቃያ ከእናቱ ወይም ከአባቱ የዘር ፖለቲካ ልክፍተኛ እንዳለበት ምንም ጥርጥር የለውም። በዚህ መልኩ ነው የጥላቻ በሽታ ከቤተሰብ ወደ ልጆች የሚተላለፈው፤ የሚጋባው። አሁን በሀገራችን ስልጣኑን የተቆጣጠሩት የሕውሀት መሪዎች የዚህ አይነት አስተዳደግ ውጤቶች ናቸው ብየ ነው የማምነው። መልካሙ ነገር እነዚህ ህጻናት እኛ ካደግንበት ወይም ሀገርቤት ያሉት ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ከሚያድጉበት የተሻለ አለም ውስጥ ስለሆነያሉት፤ ነገ ጠዋት ሁላችንንም ወላጆችን እንደሚያርሙንና እንደሚተቹን የሚያጠራጥር ነገር የለውም፤ ምክንያቱም መንግስታቸው “በቆዳ ቀለምና በዘረኝነት አትታወር” እያለ ነውና የሚያሳድጋቸው።

በዛሬዪቱ ኢትዮጵያ በወያኔ ዘረኛ ገዢ ቡድን አስተዳደር ስር ያሉት ሕጻናቶቻችን አየሩ ሁሉ በዘር ፖለቲካ ሰበካ፤ በጥላቻ ወሬ፤ በልዩነት ፕሮፓጋንዳ ጩኸት በተወረረበት፤ ንጹህ አየር ተንፍሰው ለማደግ ፋታ ባጡበት ሁኔታ ሬዲዮ፤ ቴሌቪዥን ወያኔያዊ ሀሰተኛ የውንጀላ ድራማና ወሬ ብቻ በሆነበት ዘመን፤በሀሰት፤ በክህደት የሀገርን ታሪክ፤ የህዝብን አንድነት የሚያረክስ ሴጣናዊ ወያኔያዊ የቁራ ጩኸት ብቻ በሆነበት ምድራችን ለሚያድጉት ህጻናቶቻችን የወደፊት እጣፈንታ መጨነቅ ያስፈልገናል።

ባለፉተ ሀያ አመታት ውስጥ በሀገሪቱ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምናየው አንዳንድ ምልክት ወያኔ የዘራው በሽታ የሚፈልገውን ፍሬ እያፈራለት መሆኑን ያመለክታል። በዘር ተለያይተው የሚደባደቡ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን በታሪካችን ለመጀመሪያ ጊዜ ለማየት ችለናል። ነገ ሀገሪቱን የሚረከቡ ዜጎች ናቸው። ወያኔ እያሳየን ያለው ምን ያህል ትውልዱን እያዘቀጠልን እንዳለ ነው። ተበልጠናል። ልጆቻችንን ለወያኔ የዘረኝነት ፕሮፓጋንዳ ሰለባ ከመሆን ልናድናቸው አልቻልንም። አንድ ሆነው እንዲቆሙ ወላጆች ማስተማር አልቻልንም። ከህብረተሰብም ከትምህርትቤትም በፊት ሰው የሚቀረጸው በቤት ውስጥ ነው። ኢትዮጵያዊ ማንነታቸውን፤ ህብር ህዝብነታቸውን፤ የባህል የቋንቋ የስነልቡና ውህደታቸውን አያት ቅድም አያቶቻው ከባእዳን ወራሪዎች ጋር ተፋልመው ያቆዩአት አንዲት የጋራ ሀገር እንዳለቻቸው፤ ባለመጠራጠር እንዲያውቁ አላደረግንም። ለዚህም ነው ከአንድነታቸው ይልቅ ልዩነታቸው እየጎላ የታያቸው ልጆች ወያኔ መፍጠር የቻለው።ለዚህም ነው የወያኔን ሴራና ተንኮል መረዳት አቅቶአቸው አንዲህ ተባልን እንዲህ ሆን ብለው ሆብለው ለጅምላ ድብድብ መፍጠን የቻሉ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ማየት የቻልነው።
ለራሳችንም የዘር በሽታ ልክፍተኛ የሆን ወገኖች በሽታችንን፤ ህመማችንን፤ዋጥ አድርገን ለልጆቻችን ደግደጉን መንገር አልቻልንም።

የኢትዮጵያ ልጆች እጣ ፈንታ በኛ በወላጆቻቸው ትከሻ ላይ ነው ያለው አንጂ በመርዘኛው የወያኔ ገዢ ቡድን እጅ ውስጥ አይደለም። ወያኔ እየጋታቸው ያለውን የመጥፊያ መርዝ እንዳይውጡ ማድረግ የኛ ፋንታ ነው። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ወላጅ በቤቱ ውስጥ የኢትዮጵያዊያንን እኩልነት ብዛትና አይነት ባህላችንን ቋንቋችንን አንድነታችንን የምድራችንን ልክ ማስተማር ይጠበቅብናል።

ከውጭ ወራሪ ጠላት የከፋ ጠላት ከውስጥ ስለተቆጣጠረን፤ በዘር በሽታ የተለከፍን ሁሉ አማራውም፤ ኦሮሞውም፤ ትገሬውም፤ አፋሩም፤ ሶማሌውም…ሁሉም!.... ካባቶቻችን የወረስነው የመጠላላት በሽታ ካለ ዋጥ አድርገን፤ ነገ አብረው መኖር ስላለባቸው ልጆቻችን፤ ቡቃዮቻችን እናስብ።

የሚቀጥሉት ሰላሳና አርባ አመታት ነገሩ ሁሉ አሁን አንዳለው ከቀጠለ፤ልጆቻችን እርስበርስ ሲናቸፉ፤ ወያኔና ከውጭ በገፍ እያስገቡአቸው ያሉት ባእዳን ባለሀብቶች ይህችን ሀገር ይቆጣጠሯታል። ይቀራመቷቷል። እነዚህ ከውጭ እያስገቡ መሬት የሚያድሏቸው ባእዳን ሁሉም ሀብታምና ትልልቅ መንግስታት ከጀርባ አላቸው። ቻይና፤ ሳውዲአረቢያ፤ አሜሪካ፤ እንግሊዝ፤ ሕንድ፤ወዘተ…ለህዝባቸው የተትረፈረፈ ምግብ፤ ለኢንዱስትሪአቸው ጥሬ ሀብት፤ ለሸቀጣቸው ማራገፊያ ሰፊ ገበያ ኢትዮጵያ እየተበለተችላቸው ነው።

መሬትን ለማረስ መጀመሪያ ደኑን መመንጠር እንደሚገባ መሬቱን ለባእዳኑ ለመሸጥ መጀመሪያ ወያኔ ዜጎቻችንን በመግደል እየመነጠረ የሚሸጠውን ቦታ እያመቻቸላቸው ነው። በቅርቡ የሱሬ ብሄረሰቦች መቶ ሀምሳ የሚሆኑ ከመሬታቸው ከቀያቸው ውስጥ ተሰብስበው በመትረየስ ተጨፍጭፈው ተጥለዋል። አሁን መሬቱ ተመንጥሯል። ባእዳኑ ገንዘቡን ከፍለው መረከብ ይችላሉ።የኢትዮጵያ ህዝብ ምን አይነት የማደንዘዣ መርፌ እንደወጉት አይታወቅም፤ ተራ በተራ እየገደሉ እስኪጨርሱት ተቀምጦ እየጠበቃቸው ነው።

ዛሬ እንዲጠላሉ አድርገን ያሳደግናቸው ልጆቻችን ነገ ምድራቸውን የተቀራመቷት ባእዳንና ወያኔዎች በሚያቀርቡላቸው ጠመንጃ ስራቸው መዋጋት ይሆናል። የምድሪቱን ቱሩፋትና በረከት በብዙ ሺህ ማይልስ ርቀት ላይ ያሉ ህዝቦች ይኖሩበታል። በብዙ ሺህ ማይልስ ርቀት ላይ የሚገኙ የሀብታም ልጆች ይፋፉበታል ያድጉበታል። ይህችው ምድር ያበቀለቻቸው ዜጎቿ ያልታደሉቱ፤ ይራቡባታል። እርስበርስ እየተታኮሱ ይገዳደሉባታል።በወያኔና መሬቱን በተሸለሙት ሀብታም መንግስታት ወታደሮች ይገደሉባታል።

ልጆቻችንን ከመጠላላት ፖለቲካ እናድን። ለማናችንም አይበጅም። እኛም በሽታው ካለብን ዋጥ አናድርገው። ቀጠሮ የምንሰጠው ጉዳይ አይደለም። ዛሬ!..ዛሬ!..ዛሬ ነው ጊዜው። ፍቅርና አንድነት ያለው ህዝብ ያሸንፋል።የጋራ ጠላታችን ወያኔን አምርረን እንዋጋ።እርስበርስ መጠላለፉ እልቂታችንን ያቀርበዋል።ለመዳን አንድ እንሁን!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

Lkebede10@gmail.com

Monday, February 4, 2013

Ethiopia: ‘Judas of Wollayta’ shattered as pagan TPLF warlords cancelled his bizarre Sunday mass


The Horn Times breaking news, 3 Feb 2013.
by Getahune Bekele-South
Africa

Due to security concerns and the sectarian nature of Wollayta pastors, the TPLF has officially stopped the Sunday massweekly held at the grand palace and  those arrived today 3 Feb 2013,  including old as a hill self-made historian  Dr Lapeso Gedelebo are all turned away by federal police. The Ethiopian ruling minority junta instead appointed Tigray republic’s protestant high priest, Daniel Gebresilssie to conduct the service for one hour    with no outsiders allowed in except the immediate family members of PM Hailemariam Desalegn, unimpeachable sources told the Horn Times from Addis Ababa.
Since he moved to the official residence of the prime minister, Hailemariam Desalegn who claims to be an immaculate protestant Christian has been holding noisy and chaotic Sunday masses at the palace much to the irritation of his pagan masters, the TPLF warlords.
The deacons and deaconesses, the Netherlands ordained pastors-cum theologians and their prophetess wives from the emerging Wollyta bourgeoisie have been congregating every Sunday at the conspicuous palace, occupying it from Saturday night until the wee hours of Monday, some driving all the way from the rural town of Wollayta – Sodo, the birth place of  PM Hailemariam.
Nervously tolerated by Tigre palace guards and federal police commando units, the Wollyta crowd usually stays through the night reluctant to leave even after the 3pm scrumptious luncheon served by the first lady Roman Tesfaye, making the palace unavailable for state business.
According to our sources, the warning issued by palace authorities to the priestly Wollyta coterie to limit numbers of worshippers never been heeded but it was the attitude of the pastors that led to the total cancellation of the gathering.
On the pulpit decorated with TPLF flag and pictures of the dead tyrant Meles Zenawi, spurred on by the old curmudgeon Sibehat Nega’s anti-Amhara, anti Islam and anti Orthodox Church rhetoric, preacher after preacher prophesies the demise of Ethiopiawinet under the   “heavenly” rule of the puppet premier Hailemariam Desalegn.
Although such teachings were pleasing to the Tigre junta, Pastor Semaiat Toma Woldeselassie’s January 26 2013, vision of seeing the late Meles Zenawi walking in paradise with Jesus by his side was the most embarrassing appeasement which made the warlords blushed in shame while the first lady and the premier broke into song with the crowd shouting “halleluiah.”
“With all respect to protestant churches of Ethiopia, this one is of sectarian nature and their god is the dead colonizer Meles Zenawi. They are here to please their Tigre bosses and swear loyalty to the oppressive minority rule. They say unprintable things about other churches and religions in the name of prophesy.” Our source who requested anonymity said.
Nicknamed Judas of Wollyta by his own people, the prime minister has time and again showed that he is a man of very low intellect just like his murderous predecessor Meles Zenawi.
Reports are that Hailemariam is shattered by the decision to cancel the mass and from now, every Sunday, he has to spend an hour listening to the tiresome pedagogue Pastor Daniel as the warlords slowly taking control of all aspects of his life by isolating him from the people.
“It isn’t moral for a sitting prime minister to associate himself with a certain occult  powers and applaud them for hurling cheap insults on other churches and religions. Ethiopia is a secular state.” Our source added.
infohorntimes@gmail.com