Wednesday, October 16, 2013

ለአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ፍትሕ አይቀሬ ናት

ለአፍሪካ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ፍትሕ አይቀሬ ናት

 ማስታወሻ ለአንባቢው፡፡ ባለፈው ሳምንት ሐተታዬ ‹‹የዘር አደን›› በሚል አሉባልታዊ ክስ  የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ላይ በአፍሪካ ያንባገነኖች ስብስብ የተሰነዘረበት ክስ በመቃወም  የዓለም ወንጀለኛ ፍርድ ቤት ትክክለኛነት አድልዎ ነጻ መሆን ደግፌ ተሟግቼለሁ፡፡ በዚህም ሳምንት ለዚሁ ለዓለም አቀፍ የሕግ ተቛም ያለኝን ድጋፍ በመቀጠል፤ ፈላጭ ቆራጭ የአፍሪካ ገዢዎች የፈጸሙትን ግፍና በደል ጭቆና በመዘርዘር ራሳቸውን ነጻ በማድረግ፤ የአይ ሲን (የዓለም ወንጀለኛ ፍርድ ቤት) ስም በማብጠልጠልና የቆመለትን ዓላማ የሳተ በማስመሰል፤ ገዢዎችና ምንደኞቻቸው ያነሱዋቸውን ማስረጃ ቢስንጀላዎች፤ በተጨባጭ ማስረጃ ዋቢ አድርጎ በማቅረብ፤ ሸፍጣቸውን ይፋ አድርጎ ለማቅረብ በመውሰን ይህን ጽሁፍ አቅርቤአለሁ፡፡

የኦክቶበር 11-12, 2013 የአፍሪካ አንድነት ‹‹መሪዎች›› የጨረባ ስብሰባ የተጠራውም ቴአትራዊ የልብ ወለድ ሴራ ለማካሄድና ነጻ ለመምሰል የሚያስችላቸውን ቅጥፈት ለማናፈስ መሆኑ ግልጽ ሆኖ ቢታይም፡፡

በኔ እምነት የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ሕግጋት አንግቦ ሥራውን በትክክል እንደሚሰራ፤ በአምባ ገነኖች የሃሰት ውንጀላ ሳይፈታ ሕጉ በሚፈቅደው መሰረት፤ የፍትሕ አስከባሪነት ሥራውን እየሠራ እንዳለ የሚያሳይ ተስፋ ስጭ ጠንካራው ምልክት ነው፡፡ ምንም እንኳ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ላለፉት ጥቂት ዓመታትራውን በማከናወን  ላይ መገኘቱ ቢጠቀስም፤ ያስመዘገባቸው ውጤቶችም ጥቂት ቢሆኑም፤ ለወደፊቱ ግን ያሻቸውን በደልና ግፍ ፈጥመው ግድያና አስገድዶ መድፈርን ሰብአዊ መብት በደልን አዘው በማስፈጸም በሥልጣናቸውም አላግባብ ባልገውና ተጠቅመው፤ ሃገርንራቁተው፤ ሕዝብን በበደልና ግፍ ጫና አጉብጠውና አንበርክከው፤ በነጻ ሲቀመጡና ሲንደላቀቁ የነበሩትን እያጋለጠ ለፍርድ ለማቅረብ የሚችል ጠንካራ ተቋም እንደሚሆን እምነቴ ነው፡፡  የአፍሪካ ጨቋኝና የግፍ በደል ባለቤት የሆኑት ገዢዎች በሕዝቡ ላይ ሊኩራሩና ሊደነፉ፤ የሕግ የበላይነትን በመጨፍለቅ ሊቀጥሉ ይጥሩ ይሆናል፤ አሁን ግን አይ ስለመጣባቸውና ለሕዝቡ ወግኖ ስለቆመ ስሙ በተጠራ ጊዜ እየተርበደበዱና መግቢያ እያጡ በመሄዳቸው የአይ ሲን ስም በማጉደፍ ነጻ ለመሆን ቢጥሩ መንገድ ሁሉ፤ በደላቸው ሁሉ፤ ግፋቸው ሁሉ አይ ሲን እየቀሰቀሰባቸው በመሆኑ ኦክቶበር 13 2013 የቁም ተዝካራቸው ማውጫ አድርገው እንደተስበስቡ የሚታወቅ  ነው፡፡

በኦክቶበር 11-12,  2013 አድመኞቹ የአፍሪካ ‹‹መሪዎች›› አስተጋቢው የእንግዳ መቀበያ የአፍሪካ አዳራሽ በመሰባሰብ አብዛኛዎቹ በሮም ከጸደቀው ደንብ (አለም ኣቀፍ ዉል) በመውጣት በደስታ ተሞልተው የዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤትን የሞት ውሳኔ ቢያስተላልፉም፤ ቀብሩንም ለማስፈጸም የኢትዮጵያ የይስሙላ ጠቅላይ ሚኒስትርና የአፍሪካ  አንድነት ተዘዋዋሪ 2013 ሊቀመንበር ሃይለማርያም ደሳለኝ ስብሰባውንም ሲከፍት ‹‹ዛሬ በዚህ የምጽዋት አዳራሻችን የተሰባሰብነው አይ ሲን ለማወደስ ሳይሀሆን ልንቀብረው ነው….›› በማለት እንደነበር፤ የዚህ የቀብር ጥድፍም ሰበቡ የኬንያው ፕሬዜዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በኬንያ በተካሄደው 2007 ምርጫ ወቅት በፈጸመው የሰብአዊ መብት ግፍ ለመጠየቅ ኖቬምበር 12 2013 ለፍርድ ሊቀርብ በመሆኑ፤ በተመሳሳይ ወንጀልም ምክትሉ ዊሊያም ሩቶ ፍርዱ በሄይግ የዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ መታየት ከጀመረ ሁለተኛ ወሩ ማስቆጠሩ፤ የአፍሪካ አንድነት በኬንያታ እና በሩቶ ላይ የተመሰረተውን ክስ ዘዴ ፈልጎ ካላነሳ በስተቀር ‹‹የኑክሊየር ፈንጂ መቃወሚያውን›› በመጠቀም ከአይ አባልነት ለመውጣት እንደሚችልም በማስፈራራት ላይ እሳቤ በማድረግ ነበር፡፡

ላለፉት ጥቂት ወራት ሃይለማርያም በአይ ላይ የቃል ጦርነት ሲያካሂድ ነበር፡፡ ባለፈው ግንቦት የጃጀዉና በቅዠት ዓለም ያለው ሮበርት ሙጋቤን በመደገፍ በአይ ላይ ውንጀላ አካሂዷል፡፡ ግልጽና ማስረጃው ከመጠን ያለፈውን ግፍ ለፈጸመ የአፍሪካ ገዢ ጥብቅና መቆምና ሕዝብን ለባሰ ግፍ ማብቃት የሃይለማርያም የአፍሪካ ወቅታዊ ሊቀመንበርነት ተግባር ሆኗል፡፡ ሃይለማርያም ቃላትን በማሰባሰብና ከጀርባ ባሉት ሽነቋጭ አለቆቹ በመመራት ግራ የገባውን አባባል በመጠቀም አይ ‹‹99 በመቶ›› የሆኑት በደለኛ ተከሳሾች አፍሪካውያን በመሆናቸው  የዘር አደን ላይ ነው የሚል መሰረተ ቢስ ወሬ እየነዛ ነው፡፡

ባለፈው ሳምንት በተካሄደው 68ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ስብሰባ ላይ ባሰማው ወሬው፤ አይ የኬንያታንና የሩቶን ክስ በማንሳት ጉዳዩ በኬንያ ባለስልጣናት እንዲታይ ማድረግ አለበት በማለት የማይገባ  የድፍረት ጥያቄ አንስቷል፡፡ ሆኖም ኬንያታ ከተሰነዘረበት ወንጀል ነጻ ሳያደርገው፤ ማድረግ ያሰበው ግን ኬንያታ ራሱ በሚያዘውና መመርያ በሚሰጠው ችሎት ይዳኝ ለማለት ነው፡፡ አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ ይላሉ አበው ሲተርቱ፡፡ ባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያና ናይጄርያ  ለአይ ይጋባኝ ሰሚ የኬንያው ክስ እንዲነሳ ያቀረቡትን የጽሁፍ ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል፡፡

ሃይለማርያም የዚህ ተቀባይነት የሌለው አሳፋሪ ጉዳይ አፈጉባኤ ሆኖ የመገኘቱ ምጸታዊ መነሾ አስገራሚ ነው፡፡ 34 የአፍሪካ ሃገራት የሮምን ደንብ/ዉል የፈረሙበት ሲሆን (አይ ሰን በማቋቋም ወንጀሎችን በመመርመር ሰብአዊ መብት ጥሰትን የዘር ጭፍጨፋን ግፍ በማጥራት ለፍርድ እንዲያቀርብ ውክልናና ስልጣን ሰጥቶታል):: እስከሁንም ኢትዮጵያ የዚህ ሕግ አባል ለመሆን ፊርማዋን ነፍጋ ቆይታለች፡፡ የሃይለማርያም የሥላጣን አባት ይህን ሕገ ደምብ ላለመፈረም ወስኖ ያቆየው ምናልባትስ አይ እንደማይለቀውና ወንጀሉን አጥርቶ እንደሚፋረደው ተገንዝቦ ይሆን? ለፊርማውም ችግር የሆነበት ሰበብ ሕጉን ፈርሞ ከተቀበለው የፊርማው ቀለም ሳይደረቅ በሰራቸው ሕገ ወጥ ተግባራት በፈጃቸውና ባስፈጃቸው ንጹኃን ዜጎች ሳቢያ አይ በሩን እንደሚያንኳኳና ለሕግ እንደሚያቀርበው ጠንቅቆ በመረዳቱ ነው?  እነዚያስ 34 ሃገራት ሕጉን አጽድቀው አይ ሲን ሲያቋቁሙ አይ የአፍሪካ ጋሻ መከታ ሆኖ ወንጀለኞችን አላንዳች አድልዎ እያደነ ለፍርድ እንደሚያቀርባቸው አልተገነዘቡትም ነበር?

አይ ሲን በአፍሪካ አለሳልሶ የመግደል ጥበብ የሃይለማርያም ተንኳሽና የሚያስቆጣው ክሱ የሚያሳየው፤ አይ ሲን ከአፍሪካ በድል በማስወጣት እራሱን ‹‹ጭራቅ ገዳዩ ጀግና›› ላመሰኘት የተነሳሳ መስላል፡፡ (የሱ ቀደምት የሥልጣን አባቱም ‹‹የአዲሱ ትውልድ አፍሪካዊ መሪ›› በሚል መጠርያ ለራሱ የፈረስ ስም ሰጥቶ፤ ታላቅ በመሆን በሽታ ተለክፎ ለማይለቅና ለማይድን እጀሰብ ተዳርጎ ነበር::) የነገሩ እውነታ መሰርት ግን በዚህ አካሄድ የሃይለማርያምና የጸረመስቀል ተዋጊዎቹ አካሄድ በኬንያዊያን ባለስልጣናት ላይ የተመሰረተውን ክስ ለማስነሳት፤ በብዛት ከአይሲ አባልነት መውጣትን እንደማስፈራሪያና ማገቻ በማድረግ ወንድሞቹን ኬንያታንና ሩቶን ከአይ ማነቆ በማላቀቅ፤ ወደፊት በእነሱ ላይ ሊደርስ የማይችለውን አይቀሬውን ህጋዊ የክስ እርምጃ አስቀድሞ ለመዝጋት የሚያደርገው የአልሞት ባይ ተጋዳይ የሕልም ሩጫ ነው፡፡ አፍሪካን በሚገባት ከፍተኛ የአመራር ስልጣን ላይ ላመስቀመጥ የሚጥረውን አይ ሲን ለማጥፋት ከንቱ ጥረት ከማድረግ ይልቅ ሃይለማርያምና መሰል ግፈኛ ገዢዎች ራሳቸውን ከግፍ ባህሪና ልምዳቸው በመመለስ እንደሰው በማሰብ ለሰብአዊ ፍጡራን ተገቢውን አገልግሎት ለማከናወን ቢተጉ ይበጃቸዋል፡፡

በኦክቶበር 11-12 2013 በአፈሪካ አንድነት ስለ አይ   ቀብርስለሚደረገው ንግግር ቅድመ ትርኢት

የአፍሪካ ‹‹ገዢዎች›› በኦክቶበር 11-12 2013 በአፍሪካ አንድነት በሚሰባሰቡበት ጊዜ ስለሚያካሂዱት እብደት ቀረሽ ጸረ አይ  ዘመቻ በቂ ግንዛቤ አለን፡፡ የንግግራቸው መነሾና አካሄድየ አይ ሲን ወኔ ለመገድልና ተግባሩን ለማገድ አስቀድሞ ንድፉ በአምባሳደር ቋሚ ተወካይ ማቻሪያ ካማው፤ በኬንያ በተባበሩት መንግስታታ ቋሚ ሚሲዮን በኩል ለአምባሳደር ሜናንካዶ (የሴኪውሪቲ ካውንስል የሜይ ወር 2013 ሊቀመንበር) በተዘጋጀው ባለ 13 ገጽ ሚስጥራዊ ሰነድ ተዘርዝሯል፡፡

መላ የሌለውና ቅጥ ያጣ እርማት የተካሄደበት የካማው ሚስጥራዊ ሰነድ፤

  1. ኬንያታን ሩቶ ከአይ ማነቆ ሊላቀቁ ይገባል ምክንያቱም እነሱን ለክስ ማቅረብ የኬንያንልኡላዊነት ነጻነት የሚጥስ ነው፡፡ እንደ ካማው አባባል ‹‹የኬንያታና የሩቶ ክስ ራሱን ለሚያስተዳድረው መንግስታችን በውስጥ ጉዳያችንና በሃገራችን ኬንያና በልኡላዊነታችን ላይ የተቃጣ ውርደት ነው በማለት ይከራከራል፡፡ የኬንያ ልኡላዊነት ከኬንያ ውስጥና ውጭ የተለያዩ ተዋንያንን በመጠቀም ለወቀሳ እየተዳረግን ነው፡፡እንዳለፈውና እንደተለመደው የሲቪሉን ማህበረሰብ በማነሳሳት የራሱን ፖሊሲ እንዲቃወም በመደረግ የሮምን ስምምነት ሰበብ በማድረግ አይሲሲን በአስፈጻሚነት እየተጠቀሙበት ነው፡፡›› ነጻነት ለአፍሪካውያን ጨካኝና አረመኔ ገዢዎች የመጀመርያው ስደተኛ ነው፡፡ አሁን የአፍሪካን ነጻነት ለማስከበር በማለት የሚንደፋደፉት አስመሳይ የአፍሪካ ጨቋኞች በኖቬምበር 2010 ምርጫ ወቅት ፈረንሳይ በቀጥታ በአይቮሪኮስት ግጭት ጣልቃ በገባችበት ወቅት፤ ገዳም እንደገባች አይጥ ተሸጉጠው ትንፍሽ ሳይሉ ፈረንሳይ የቀድሞ ቅኝ ግዛቷን መልሳ ስተወር አንዲት ቃል አልተነፈሱም፡፡ የአፍሪካ አንድነትም ቢሆን በዝምታ ተቀምጦ ጠበይ ተመልካች በመሆን ከጎን ሆኖ ከመመልከት አላለፈም፡፡ በጃንዋሪ 2013 ፈረንሳይ የሰሜን ማሊን ከሽብርተኞች ወረራ ነጻ ለማውጣት ጣልቃ ሲገባ የአፍሪካ መሪዎች የፈረንሳይን ጦር ለማስወጣት የነጻነትንና የልእልና ማስከበርን ጉዳይ አላነሱም፡፡ አሁንም እንደገና የአፍሪካ አንድነት ከተመልካችነት አላለፈም፡፡

በወንጀል በሰብአዊ መብት ጥሰት፤በጦር ወንጀለኛነት፤በዘር ማጥፋት ለሚሰነዘር ክስ ሉአላዊነት ሕጋዊ መከላከያ አለያም የፖለቲካ ውይይት ሁኖ አይቆምም፡፡ አሁን በአፍሪካ ፈላጭ ቆርጫ ገዢዎች የሚነሳው የሉአላዊነት ጥያቄ አይ የተጣለበትን አደራ ላማዘናገት ሆን ተብሎ የተነሳና ቀድሞ ከነበሩት የንጉሳዊ ገዢዎች በምድራዊ ዳኝነት እንጠየቅም ሥዩመ እግዚአብሔር ነን እንደሚሉት ለመሆን የታቀደ ዘዴ ነው፡፡ ሕገ ወጥ የሆነውን የአፍሪቃ ፈላጭ ቆራጭ ገዢ ሊዳኘው የሚገባውና የሚችለው ሌላው ሕገወጥ አፍሪካዊ ገዢ መሆን አለበት ነው የሚሉት፡፡

  1. ኬንያታና ሩቶ ከክስ ነጻ የመሆን መብት አላቸው ምክንያቱም በማርች 2013 ምርጫ ‹‹ንጹህ›› ናቸው ስለተባሉ፤ካማው ኬንያታና ሩቶን በተመለከተ ሁለቱ ሰዎች ንጹሃን ብቻ ሳይሆኑ በክፍተኛው የመንግስት ስልጣን ላይ ስለተቀመጡ ሃለፊነትም አለባቸውና ክሱ ሊሰረዝላቸው ይገባል በማለት ይሞግታል፡፡ አይ የከፈተው የክስ
    መዝገብ የሚዘጋበት ምክንያት ኬንታና ሩቶ የፈጸሙት የሰብአዊ መብት ድፍረትና ጥሰት በፍትህ አደባባይ ቆሞ ስለሚመሰክርባቸውና ለፍርድ ሊያቀርባቸው ስለሚችል የንጹሃን ግፍና በደል በነሱ የስልጣን ወንበር መያዝ ተቻችሎ ነጻ ሊሆኑ ይገባል ነው፡፡  እነዚህ ሁለት ዋናና ምክትል ገዢዎች የኬንያውያን ሁሉ መተሳሰርያ በመሆናቸውና ሕዝቡም በፍቅር ስለመረጣቸው፤ 86 በመቶ ድምጹን ሰጥቶ መንበራቸው ላይ ስላስቀመጣቸው ክሱ ሊሰረዝላቸው ግድ ነው፡፡ ካሙ ክርክሩን በመቀጠል፤ የሮሙ
    ስምምነት ኬንያታንና ሩቶ ሊያካትት አይገባም፤ምክንያቱም በአሁኑ ጊዜ ከፍተኛውን የሃገሪቱን አመራር በዋናነትና በምክትልነት የያዙ በመሆናቸውና የኬንያ ሪፑብሊክ የመከላከያ አዘዦች በመሆናቸው፤ነው ይለናል፡፡ ካሙንን ግራ ያጋበው ነገር ኬንያታና ሩቶ ንፁህነታቸውን ለማረጋገጥ መመረጥ አያስፈልጋቸውም፡፡ ማንም ሰው ቢሆን በፍርድ ሸንጎ ወንጀለኛ እስካልተባለ ድረስ ንጹህ ነውና፡፡ ስለዚህም በተጠረጠሩበት ወንጀል ኣይ የሚለው ችሎት ፊት ቀርበው ንጸህናቸውን በነጻ የፍትሕ ስርአት ያረጋግጡ ነው እንጂ ወንጀለኞች ናቸው ብሎ አልደመደመም፡፡ የሁለቱ ባለስልጣናት በአጥጋቢ ውጤት ከመመረጣቸው ጋር የተሰነዘረባቸው ተጠርጣሪነት አንዳችም ግንኙነት የለውም፡፡ ጥያቄው 2007-08 በስልጣን ላይ በነበሩበት ግዜ ተፈፀሙ በተባሉ ወንጀሎች ነው፡፡ ኬንያታና ሩቶ የሃገሪቱ መሪዎች መሆናቸው ከሕጉ ጋር የሚያገናኘው ሰበብ የለውም፡፡ የሮም ስምምነት አንቀጽ 27 ማንኛውም ተጠርጣሪ አይሲሲ ችሎት ቀርቦ ንጽህናውን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል ይላል፡፡ ስምምነቱ ማንንም በእኩል ደረጃ ይመለከታል፡፡ ማንንም ከማንም በስልጣን ደረጃ አያመዛዝንም ለአይ ምንኛውም ተጠርጣሪ እኩል ነው፡፡ ተመራጭ ፕሬዝዳንትም ይሁን የፓርላማ አባል የመግስት ባለስልጣንም ሆነ ተራ ዜጋ ለአይ ችሎትና መመርያ ሁሉም እኩል ናቸው፡፡

  1. በኬንያታና በሩቶ ላይ የተመሰረተው ስንኩል ክስ (የተባበሩት መንግሥታት ሴኩሪቲ ካውንስልና በኬንያም መንግሥት ወንጀል መስራታቸው ሳይተላለፍለት ነው) በአግባቡ ምርመራና ማጣራት ሳይካሄድበት ነው ይላሉ፡፡ የአይ ክስ ተቀባይነት የሌለው ምስክሮቹንም አስጠንተው ያቀረቧቸው ናቸው፡፡ ተጠቂ ነን ብለው የቀረቡትም ሃሰተኞች አለያም ተመርጠው የተሰየሙ ናችው፡፡ የምስክርነት ቃላቸውም ደካማና የማያሳምን ነው፡ በማለት ካሙ ይከራከርላቸዋል፡፡ ምስክሮች  በመደለያ የተገዙ ያንንም ነው አይደለም ብሎ የሚወስነው የአይ ችሎት ነው፡፡ ምናልባትም ምስክሮቹ ተአማኒነት የሌላቸው በጥቅማ ጥቅም የተገዙ ናቸው የሚባልም ከሆነ የካሙስ መንግስት ማስረጃውን በማቅረብ ሊቃወም ይችላል፡፡


  1. የአቃቤ ሕግ ቢሮ ሚዛናዊ ባልሆነ መልኩ በኬንያታና በሩቶ ላይ የክስ ምስረታውን ተከሳሾቹን በሚጎዳ መልኩ እያካሄድ ነው ለፍትሕ በእኩል መልኩ የተከናወነ አይደለም በማለት ተጠርጣሪዎቹን ተከሳሾች ፍትሕ በአግባቡ ነጻ ናቸው አይደሉም ከማለቱ ይልቅ አይ ሲንና የአቃቤሕግ ቢሮን በሃሰት በመወንጀልና ፍትሕ ገደል ይግባ ለኛ በሚመቸን መልኩ የማይሰራም አይ ፍርስርሱ ይውጣ የሚል ነው የካማው ቅጥ ያጣ ሙግት፡፡ ፍትሕ ለመዛባቱ የካማው መንግስት ማስረጃ ካለውና በፊትም ሆነ አሁን ኬንያታንና ሩቶን ፍትሕ ይነፍጋቸዋል ብሎ ካሰበ ወደ ፍርዱ መድረክ በማቅረብ ሕዝብ እንዲያውቀው ሊያደርግ ይገባዋል፡፡ በተቃራኒው ካማውና የአፍሪካ መሪዎች ሊያደርጉና ለማድረግም በመጣር ላይ ያሉት አንዳችም እውነትነት የሌለው የክስ ዳውላ በመዘርገፍና እርፍት የለሽ የድረሱልን ጥሪ በማሰማት ዓለምን ሊያሳምኑ በመጣር ላይ ናቸው፡፡ እውነት ካላቸው እነካማው አለን የሚሉትን የፍትህ ግድፈት አደባባይ ያውጡት፡፡

  1. አይ ሲና የአቃቤው ሕግ ቢሮ ማንም የማይቆጣጠረውና ከሕግ ውጪ ለማንም ተጠያቂ ያልሆነ ባለሥልጣን ነው ለመጀመርያ ጊዜ ቋሚ ዓለም አቀፋዊ ተቋም የሃገራትንና የዜጎቿን ሕጋዊ ግዴታ ለመመልከትና ለመወሰን ወንጀልም ሲያገኝባቸው በአግባቡና በስርአት ቅጣት ለመጣል ተመስርቷል፡፡ አይ ብቃቱን በተመለከተ በማንኛውም መልኩ ለዓለም አቀፍ ሕግጋት ምን እንደሚያስፈልገው ሲረዳ የመከራከሪያው የመጨረሻ ቃላት አይ ሲወስን በማንኛውም መንግስት ቁጥጥር ስር አለያም ትእዛዝ ሳይሆን ዓለም አቀፍ ሕግጋት በሚመሩበት ስርአት ብቻ መሆኑን ነው፡፡ ካሙ የሚያውቀውና የሚለውም ሆነ አይ ያድርግ የሚለው አለቆቹ በሚወነጀሉበት ጥፋታቸው ሁሉ አስቀድሞ እነሱ የሚያዙት ችሎታቸው ጉዳዩን ይመርምር ነው፡፡ የሚያውቀውና የሚከተለው አሁን ምርመር ይደረግባቸው የተባሉት አለቆቹ ሲያስሩ ሲገድሉ ሲያሰቃዩ ፍርድ አልነካቸውምና አሁን እንዳይነካቸው ይደረግ ነው፡፡ ካሙ ችግሩና በሽታው አለቆቹ የሚመሩበት ያልተጻፈ ሕግና ያልተሰጣቸውን ስልጣን መጠቀም ስለሆነ በዚያው መሰረት ይዳኙ ነው፡፡ አይ የሚታዘዘውም ሆነ የሚመራው በዓለም አቀፉ የፍትሕ ስርአት ነውና ማንንም አይጠላም ማንንም ከማንም አስበልጦ አያፈቅርም፡፡ ካሙ ለምን አንድ አቃቤ ሕግ ብቻውን ያጣራው ጉዳይ ተቀባይነት ያገኛል ነው፡፡ አይ ደግሞ አቃቤ ሕግ ግድፈት አለበት የሚል ማንኛውም ተጠርጣሪ አለያም ዜጋ መስረጃውን አቅርቦ ሊሞግተው ይችላል ነው፡፡


የአፍሪካን ዲክታተሮችና ጭፍሮቻቸው ስለ ‹‹ቁጥጥር አልባ ሥልጣን›› ሲያወሩ ማዳመጥ የአዞ እንባ እንዲሉ አይነት ነው፡፡ የኬንያን ባለስልጣነት መጠን የለሽ የስልጣን ክልል በመጠኑም ቢሆን ለመቆጣጠር ያስቻለው 2010 የወጣው ሕገመንግስት ነው፡፡ በኬንያ ስርአት አልበኝነትን ሕገወጥነትን ለመከላከል ሲባል የወጣው አዲሱ ሕገመንግስት  ነው መሰረት የጣለው፡፡ ማንም ሊረዳው የሚገባው አዲሱ የኬንያ ሕገመንግስት 2007 በተከሰተው የምርጫ ውዝግብ ሳቢያ በተካሄደው ውይይት ላይ ተመስርቶ መረቀቁና መጽደቁ ነው፡፡ ኬንያታና ሩቶ በዚያው ሕገመንስት ደንብና ስርአት  ውስጥ በተካተተው መመርያ መሰረት ነው ለፍርድም ሊቀርቡ ማዘዣ የወጣባቸው፡፡

በአፍሪካ የሕግ የበላይነት እነ ካማው መሰረተ ቢስ የሆኑ በርካታ ጥያቄዎችን በማንሳት ሕዝብንና መንግስታትን በማታለልና መንገድ በማሳት አለቆቻቸውን ነጣ ለማድረግ ይጥራሉ፡፡ እነ ሃይለማርያም ደሳለኝ የአይ አካሄድ ማንም ግፈኛና ወንጀለኛ ከነጉድፉ ተሸሽጎ እነዳይኖርና ግፍና በደሉን በማር ቀብቶ ለማስመሰያነት እንዳዋለ እንዳይኖር  የማድረግ ስልጣኑ ማነህ ባለሳምንት ይለናል በማለት አስቀድመው ለራሳቸው የሚጠቅም ከለላ ለመፍጠር ነው ጥረታቸው፡፡ የዓለም ሕግ ተፋለሰ ሲሉ እስከ ዛሬ ድረስ እነዚህ የኡኡታ አሰሚዎች የፈጸሙትን የሕግ መፋለስ በመዘንጋት ሳይሆን አውቀው ትክክለኛ መስለው ለመታየት እንጂ በአይ አካሄድ የተፋለሰ አንዳችም ሕግ የለም፡፡ አለ ከተባለ ደግሞ ከነማስረጃው ማቅረብ እንጂ ከንቱ የጋጋኖ ጨኸት የትም አያደርስም፡፡ የአፍሪካ አንድነት ደንብም ቢሆን በአፍሪካ ውስጥ ሰብአዊ መብት ሊከበርና ሊጠበቅ እንደሚገባው ይደንግጋል፡፡ ስለመልካም አስተዳደርም በደንቡ ላይ አስፈሯል፡፡ ማንም ከወንጀል ነጻ ሊሆን እንደማይችል ደንቡ ያናገራል፡፡

በኦክቶበር 13 ለቁጥር የሚጣክቱት መሪዎች ከሮሙ ስምምነት ለመውጣት ማሴር ማለት ሕግ አልበኝነትና የራሳቸው የአፍሪካ አንድነት የሚተዳደርበትን ደንብ መጣስ መሆኑን መዘንጋት ነው፡፡ ተጠያቂነትን ያወጁ ሃገራት ተጠየቁ ሲባሉ ሕጉን ያወጣነው ሕዝብን ለመቅጣት እንጂ እኛ ልንጠየቅበት አይደለም ማለት ምን የሚሉት፡፡ በጣም ቀላል የሆነና የማይቀር ምርጫ አለን፡፡እነዚህን በአፍሪካ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ሆነው ግፍን በመፈጸምና ሃላፊነትን አላግባብ በሚጠቀሙ ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ከሮም ውልና ስምምነት የመውጣት አድማቸው ላይ አቋም በመያዝ መመጎት ቢያንስ  የነዚህን እኩዮች አድማ የሚቃወሙትን ተቆርቋሪ ወገኖች ማገዝ ነው፡፡ ለዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት መቆምና መወገን ማለት አፍሪካ ውስጥ በመግዛትና ግፍ በመፈጸም ያሉትና ባለስልጣናት መሞገት ነውና አብረን ሆነን ከአፍሪካ ጫንቃ ላይ እንዚህን ጋሬጣዎች እንንቀስ! አይ ሲን የመደገፊያው ወቅት አሁን ነው::


ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም



Monday, October 14, 2013

ነፃነት በምጽዋት የሚገኝ አይደለም

ነፃነት በምጽዋት የሚገኝ አይደለም

የኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃነቱን ከወያኔ (ኢህአዳግ) በምጽዋት የሚቀበለ፤ አካለ ስንኩል ፍጡር: ወይም ዜጋ ሳይሆን፤ በትግለ ውጤት ከወያኔ እጅ በግድ ፈልቅቆ የሚጎናጸፈው የጀግንነት ምሱ መሆን አለበት :: ምንደኛ ቅጥረኛ አምባ ገነኖች ምንጊዜም ነፃነትን  ለሕዝብ በፈቃዳቸው ያስረከቡበት ጊዜ ስለሌለ፤ ነፃነትን በምጽዋት መልክ ከወያኔ የሚጠብቅ ግለሰብ፤ ወይም ቡድን፤ ወይም ማህረሰብ፤ ወይም የፖለቲካ ድርጅት፤…….. ወዘተ ካለ እሱ በታሪክ ገለባ ውስጥ ተደብቆ: ገለባው ሲቃጠል አብሮ የሚነድ ስነፍ ፍጡር ነው።

“Blinding ignorance does mislead us. O! Wretched mortals, open your eyes!”
(Leonardo da Vinci)

ከዋያኔው አንባ ገነን መሪ ኅልፈት በኋላ በስልጣን ክፍተት ሽግሽግ እየታመስ ያለው ወያኔ፤ የ “ከየተም አምጭው ግን ዱቄቱን ፍጭው” አስተምህሮ ተከታይ ፋሪዚያን ደቀመዛሙርቶችና ከሻቪያ ጋር የወገኑ አለያም የስልጣን ጉዳይ እንጅ ከወያኔ የጎሳ ፖለቲካ ርዮት ጋር ቁርኝት የነበራቸው ያላቸው ቡድኖችና ኩሳ ኩስ ሆደአደር ምንደኞች፤ ላለፉት ሁለት አስር ዓመታት የነጻነት ትግል ተቀጣጥሎ በሁሉም አቅጣጫ ተቀባይነትን ሲያገኝ፤ እንደ እርጎ ዝንብ ባገር ውስጥም ይሁን ከአገር ውጭ እዚህ እዛ ጥልቅ እያሉ፤ ጊዜና ሰዓትን እየመረጡ፤ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያነት፤ የነጻነት ትግል በምያብበት በሚቀጣጠልበት ወቅት፤ፍሬውን ለማምከን  ቅን አሳቢ መስለው የሚፈታተኑን፤ ጭለምተኛ በታታኝ ኃይሎች፤ በተለያዬ ወቅት አውዛጋቢ አጄንዳን እየቀርጹ፤ በበረቱ ውስጥ መንጋውን እንደሚያምስ አምጸኛ በሬ፤ አተካሮ በመፍጠር ለአገሩ ለውገኑ የተነሳውን ሕዝበ ትግል ለማደናቀፍ፤ አንድነቱን ለመናድ፤ ለማናጋት፤ አዳዲስ አነታሪኪ ውዥንብር በመጫር፤ አፍራሽ የፈጠራ ቯልትን በማሰራጨት፤ ትግልን ለማዳከም፤ሕዝብን ለማታለል፤ እንደተለመደው ውሃ የማያንሳ ቱሪናፋ ዲስኩርን በመፍጠር በመሐበርስብ የኢንተርኔት ቴክኖሎጅ መውያያ መድረኮች፣ ድኅረ ግጾች ላይ በመለጠፍ በራዲዮና በቴለበዥን በመጽሄትና በጋዜጦች በማሰራጨት፤ የእገሌ ቡድን የበላይነቱን ተቆጣጠረ፤ የእገሌ ቡድን ተሽነፈ በሙስናም ተከሶ ዘብጥያ ጸጉሩን ተላጭቶ ወረደ፤ ቀንደኛው የወያኔ የደሕንነት ዋና ስው ዘብጥያ አልወርደም ወርዷል ፤  ወያኔ የትግራይ አባይ አገር ሊመስረት ተነሳ፤ የነጻነት ትግሉ አለ ሻአቪያ ደጋፊነት ከቶ የማይታስብ ነው፤የጎሳ ማንነቴን ማንም ጠፍጥፎ በሌላ ማንነት ሊጭንብኝ አይችልም፤ የኔ ጎጥ ታሪክ ትክክል ነው አይደለም ፤ ይህ የሃይማኖት ድርጅት አክራሪ ነው፤ እገሊት የምትባል የወያኔ ቁጭበሉ ጠቅላይሚኒስተር ባልተቤት ከፀረ ማሪያሙ ክፓስተር ጉግማንጉግ ጋር ጠሎት አደርገች፤ የአገሪቱ ያየር ኃይል አባላት  “እኛ አናቀውም” የተባለውን አዲሱን የነጻነት ቡድን በጅምላ እንዳሉ ተቀላቀሉ፤ እገሌ የሚባለው አርቲስት ከገሌ አርቲስት ጋር አይዋደድም፤ እክሌ የሚባለው ጋዜጠኛ ወደር የሌለው ባልተሟል ነው አይደለም  ወ.ዘ.ተ በሚል አሉታዊ የቡና ስኒ አተላ ዝቅዘቃ ጥንቆላ እንደተጠመዱ እንደተካኑ ሥራፈት የመንደር ባልቴቶች ተምሳሌታዊ ተራ ተውኔት የወሬ ድራማ ፤  የትግል አቅጣጫ አሞኝቶ ለማስለወጥ መሞከር እራስን ከማሞኝነት በስተቀር፤ ዜጋ ይህና ይህን በመስሉ ተራ የተንኮላዊ ቯልት የሚፈታ አይኖርም።

“Love does not dominate; it cultivates.” (Johan Wolfgang von Goethe)
ፍቅር ተጽኖ አድራጊ ሳትሆን አለምላሚ ናት። ” በመሆኑም

ወጣቱ ሳተናው አዲስ ትውልድ ለአገሩና ለሕዝቡ ያለው ፍቅርና ወገንተኝነት መሰረት ያደረገ ሁሉ ገብ እልህ አስጨራሽ ከታች እስከላይ ባሉት የወያኔ  የመጨቆኝ መስተዳደር አካል ወስጥ ተስግስገው የአገርንና የሕዝብን ነጻነት ገፈው አዋርደው ኢትዮጵያዊ አብሮነትን ስብረው በዘር በጎሳ በጎጥ ሕዝብን በክልል ከልለው የጥፋት ወንጀላቸውን ሌብነታቸውን ሕዝብ እንዳያውቅ ከሚያደርጉ፤ ከአገሩ ጠላቶች ከሆኑት፤ የወያኔ የትግሬ ነጻነት ግንባርና ተላላኪ ድርጀቱ ኢሃድግ ጋር፤ በስልት በብልሕነት፤  ሕዝብን ከጎን ያደረገ፤ ትግልን በአዲስ ነድፎ፣ አጎልብቶ፤ በክፊል እንደሚንቀሳቀስና፤ የውደፊት መስናዶዎችን፤ በሕቡም ይሁን በይፋ፤ እንደ ሽረሪት ድር በተደራ ሕዋስም ይሁን በውሉ በማይታወቅ፤ ሁሉ ገብ ሕዋስ ወ.ዘ.ተ እየተረዳ፤ የሕዝብ የነጻነት መታገያ፤ ደጀኖችን ገንብቶ፤ ሰላማዊ ትግሉን፤ አቀጣጥሎ፤ በቆራጥ መስዋትነት፤ የወያኔ የትግሬ ነጻአውጭ ግንባርና አበር ግንባሮችን ከሥልጣን ወንበራቸው አባሮ፤ አባቶች ደማቸውን አፍስሰው፤ አጥንታቸውን ከስክስው፤ ያቆዩትን አገር መልሶ፤ የወያኔን ባንዲራ አውርዶ ለጥቁር ሕዝቦች ሁሉ የነጻነት ተምሳሌት ምልክት የሆነችውን ሰንደቃላማውን ስቅሎ፤ ነጻነትን እንዲያውጅ፤ ታሪካዊ  ግዳጁንም፤ በድል አድራጊነት እንዲወጣ፤ ከአለፉትና ከዘመኑ ትግል  በመማር፤ አዲስ  የትግል አመላካች፤ ስትራቴጅዎችን፣ ታክቲኮችን፣ ተጨባጩን፣ አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ የአገሪቱን የፖለቲካ የመሃበርስባዊ የኢኮኖም ጭብጦች እየመረመረ፤ እየፈተሽ ፤ አስፈላጊም መስሎ ከታየው፤ አዲስ  የራሱ የሆነ የትግል ስልት በመፍጠር መጛዝ ግድ እንደሚል የብዙዎቻችን እምነትና ፣ግንዛቢያዊ ጭብጥ  ነው።

“Make your work to be in keeping with your purpose” (Leonardo da Vinci)

ከስንዴ እንክርዳድ እንደማይጠፋ ሁሉ አንዳንድ የኔ ቢጠ የዋህ በተቃዋሚ ወገን የተሰልፉ ልሂቃን አልፎም የወያኔ ሆድአደር ልሂቃን  መርምረውም ይሁን ሳይመረምሩ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ በመርዝ የተለወሰ አሉታዊ የመሃበራዊ ሳይንስ እውቀትን ሳያላምጡ በመጉረስ እንደ ጋማ ከብት ከሆዳቸው ገፍተው ወደ አፋቸው እየሳቡ አምጥተው መልስው መላልሰው ከሚአመነዥኩ ፤የጎሮሮ ስንጥር ሆነው ትግልን ከሚያውኩ፤ መስሪ ልዩነትን እያጎሉ፤ ካንድነት ይልቅ መበታተንን፤ ከፍቅር ይልቅ ጥላቻን የሚስብኩ፤ ታሪክን ባሕልን አገራዊ ማንነትን፤ ሕዝባዊ አብሮነትን፤ አገራዊ አንድነትና እድገትን የሚሽረሽሩ፤ የሚንዱ እሳቤዎችን በጎ አስቢ በመምሰል፤ የሚረጩ የሕዝብ ጠላቶች እንዳሉ በመገንዘብ፤ በምያነሱትም አፍራሽ የስነ ልቦናዊ ጥቃት ስላባን መሰርት ያደርጉ በውዝግብ ሴራ ተቀንቅነው ተረቀው በሚቀርቡልን የውሸት እንቶፈንቶ መጣጥፎችም ሆኑ ዲስኩሮች ሳንደናገጥና ሳንሸበር ፤በስነ ጽሁፍ ጌጠው በተዋቡ፤ በማር በተለውሰ መርዝ ተከትበው በተጻፉ  ጽሁፎችና በመሳሰሉት አጀንዳዎች ሳንታለል፤ አንድም አጀንዳዎቹ አደገኝነታቸውን በዝርዝር ጭብጥ በሆኑ መረጃዎች ለሕዝብ አቅርቦ በማሳያት፤ሕዝብ እንዲያውቀው በማድረግ፤ አልያም ሕዝብ ደግሞ ደጋግሞ የሚያውቃቸውና ደግሞ ደጋግሞ ያለተቀበላቸው ከሆኑ አውቆ እንዳላወቁ በማለፍ ግዜን በንትርክ ባለማጥፋት፤ በተለይ አገር ወስጥ ያለው ወጣት ትውልድ ከወገኖቹ ጋር አብሮ እየመከረ፤  ለአገርና ለሕዝብ ነጻነት የሚበጅ፤ ታግሎ የሚያታግል፤ አዲስ ታሪካዊ መርሕ ነድፎ፤ ያግሩን መሬት በአገሩ በሬ ብለው አበው እንደቀለጹት፤ ትግልም በአገርና በአገር ልጅ ነውና፤ ስጋዊ ሞትም ለስውልጅ የተሰጠው የማይቀር ጽዋ ነውና፤ የአገርና የሕዝብን ባርነት ሞት ከማየት በነጻነት ለነጻነት ታግሎ ማለፍ የተቀደስ ተግባር መሆኑን ካባቶቻችን ካያቶቻችን ከቅደመአያቶቻችን ከቅመአያቶቻችን የታሪክ ገድለ አስትምህሮ የነጻነት ቀንአኢ መገለጫችን የሆነውን ምርሕ አንግቦ ለነጻነት በጽኑ ከሕዝብ ጋር ወግኖ ከሕዝብ ጋር አብሮ ሆኖ በመታገል የውጭ ጥገኝነትን ሳያማልለው የውጭ እርዳታ ድጋፍም ሳይሻ ሕዝብ የበላውን በልቶ ሕዝብ የሚጠጣውን ጠጥቶ፤ ሕዝብ  ጛስን ጎዝ ጉዞ ቁርበቱን አንጥፎ ሌቱን እንደሚያሳልፍ ሁሉ እሱም እንደሕዝብ ሌቱን አርፎ፤ ሕዝብን የነጻነት ጋሻና ጦር አድርጎ በሚንቀሳቀስበት፤ ሁሉ የወገን ድጋፈ ማድረግ  ማበርታታት ኢትዮጵያዊ ግዴታችን መሆኑን በመገንዘብ፤ ትግሉም በምጽዋት ከወያኔም ሆነ ከሻቢያ ይመጣል ብሎ በታሪክ ገለባ ውስጥ ተደብቆ: ገለባው ሲቃጠል አብሮ የሚነድ ስነፍ ፍጡር እንዳንሆን ቆም ብለን እራሳችንን እንመርምር ትግሉንም ተግላችን እናድረገው።                                       ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!
 
ኢትዮጵያ በተባበሩ ልጆቿ ክንድ ተከብራ ለዘላለም ትኑር !!