Monday, October 14, 2013

ነፃነት በምጽዋት የሚገኝ አይደለም

ነፃነት በምጽዋት የሚገኝ አይደለም

የኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃነቱን ከወያኔ (ኢህአዳግ) በምጽዋት የሚቀበለ፤ አካለ ስንኩል ፍጡር: ወይም ዜጋ ሳይሆን፤ በትግለ ውጤት ከወያኔ እጅ በግድ ፈልቅቆ የሚጎናጸፈው የጀግንነት ምሱ መሆን አለበት :: ምንደኛ ቅጥረኛ አምባ ገነኖች ምንጊዜም ነፃነትን  ለሕዝብ በፈቃዳቸው ያስረከቡበት ጊዜ ስለሌለ፤ ነፃነትን በምጽዋት መልክ ከወያኔ የሚጠብቅ ግለሰብ፤ ወይም ቡድን፤ ወይም ማህረሰብ፤ ወይም የፖለቲካ ድርጅት፤…….. ወዘተ ካለ እሱ በታሪክ ገለባ ውስጥ ተደብቆ: ገለባው ሲቃጠል አብሮ የሚነድ ስነፍ ፍጡር ነው።

“Blinding ignorance does mislead us. O! Wretched mortals, open your eyes!”
(Leonardo da Vinci)

ከዋያኔው አንባ ገነን መሪ ኅልፈት በኋላ በስልጣን ክፍተት ሽግሽግ እየታመስ ያለው ወያኔ፤ የ “ከየተም አምጭው ግን ዱቄቱን ፍጭው” አስተምህሮ ተከታይ ፋሪዚያን ደቀመዛሙርቶችና ከሻቪያ ጋር የወገኑ አለያም የስልጣን ጉዳይ እንጅ ከወያኔ የጎሳ ፖለቲካ ርዮት ጋር ቁርኝት የነበራቸው ያላቸው ቡድኖችና ኩሳ ኩስ ሆደአደር ምንደኞች፤ ላለፉት ሁለት አስር ዓመታት የነጻነት ትግል ተቀጣጥሎ በሁሉም አቅጣጫ ተቀባይነትን ሲያገኝ፤ እንደ እርጎ ዝንብ ባገር ውስጥም ይሁን ከአገር ውጭ እዚህ እዛ ጥልቅ እያሉ፤ ጊዜና ሰዓትን እየመረጡ፤ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያነት፤ የነጻነት ትግል በምያብበት በሚቀጣጠልበት ወቅት፤ፍሬውን ለማምከን  ቅን አሳቢ መስለው የሚፈታተኑን፤ ጭለምተኛ በታታኝ ኃይሎች፤ በተለያዬ ወቅት አውዛጋቢ አጄንዳን እየቀርጹ፤ በበረቱ ውስጥ መንጋውን እንደሚያምስ አምጸኛ በሬ፤ አተካሮ በመፍጠር ለአገሩ ለውገኑ የተነሳውን ሕዝበ ትግል ለማደናቀፍ፤ አንድነቱን ለመናድ፤ ለማናጋት፤ አዳዲስ አነታሪኪ ውዥንብር በመጫር፤ አፍራሽ የፈጠራ ቯልትን በማሰራጨት፤ ትግልን ለማዳከም፤ሕዝብን ለማታለል፤ እንደተለመደው ውሃ የማያንሳ ቱሪናፋ ዲስኩርን በመፍጠር በመሐበርስብ የኢንተርኔት ቴክኖሎጅ መውያያ መድረኮች፣ ድኅረ ግጾች ላይ በመለጠፍ በራዲዮና በቴለበዥን በመጽሄትና በጋዜጦች በማሰራጨት፤ የእገሌ ቡድን የበላይነቱን ተቆጣጠረ፤ የእገሌ ቡድን ተሽነፈ በሙስናም ተከሶ ዘብጥያ ጸጉሩን ተላጭቶ ወረደ፤ ቀንደኛው የወያኔ የደሕንነት ዋና ስው ዘብጥያ አልወርደም ወርዷል ፤  ወያኔ የትግራይ አባይ አገር ሊመስረት ተነሳ፤ የነጻነት ትግሉ አለ ሻአቪያ ደጋፊነት ከቶ የማይታስብ ነው፤የጎሳ ማንነቴን ማንም ጠፍጥፎ በሌላ ማንነት ሊጭንብኝ አይችልም፤ የኔ ጎጥ ታሪክ ትክክል ነው አይደለም ፤ ይህ የሃይማኖት ድርጅት አክራሪ ነው፤ እገሊት የምትባል የወያኔ ቁጭበሉ ጠቅላይሚኒስተር ባልተቤት ከፀረ ማሪያሙ ክፓስተር ጉግማንጉግ ጋር ጠሎት አደርገች፤ የአገሪቱ ያየር ኃይል አባላት  “እኛ አናቀውም” የተባለውን አዲሱን የነጻነት ቡድን በጅምላ እንዳሉ ተቀላቀሉ፤ እገሌ የሚባለው አርቲስት ከገሌ አርቲስት ጋር አይዋደድም፤ እክሌ የሚባለው ጋዜጠኛ ወደር የሌለው ባልተሟል ነው አይደለም  ወ.ዘ.ተ በሚል አሉታዊ የቡና ስኒ አተላ ዝቅዘቃ ጥንቆላ እንደተጠመዱ እንደተካኑ ሥራፈት የመንደር ባልቴቶች ተምሳሌታዊ ተራ ተውኔት የወሬ ድራማ ፤  የትግል አቅጣጫ አሞኝቶ ለማስለወጥ መሞከር እራስን ከማሞኝነት በስተቀር፤ ዜጋ ይህና ይህን በመስሉ ተራ የተንኮላዊ ቯልት የሚፈታ አይኖርም።

“Love does not dominate; it cultivates.” (Johan Wolfgang von Goethe)
ፍቅር ተጽኖ አድራጊ ሳትሆን አለምላሚ ናት። ” በመሆኑም

ወጣቱ ሳተናው አዲስ ትውልድ ለአገሩና ለሕዝቡ ያለው ፍቅርና ወገንተኝነት መሰረት ያደረገ ሁሉ ገብ እልህ አስጨራሽ ከታች እስከላይ ባሉት የወያኔ  የመጨቆኝ መስተዳደር አካል ወስጥ ተስግስገው የአገርንና የሕዝብን ነጻነት ገፈው አዋርደው ኢትዮጵያዊ አብሮነትን ስብረው በዘር በጎሳ በጎጥ ሕዝብን በክልል ከልለው የጥፋት ወንጀላቸውን ሌብነታቸውን ሕዝብ እንዳያውቅ ከሚያደርጉ፤ ከአገሩ ጠላቶች ከሆኑት፤ የወያኔ የትግሬ ነጻነት ግንባርና ተላላኪ ድርጀቱ ኢሃድግ ጋር፤ በስልት በብልሕነት፤  ሕዝብን ከጎን ያደረገ፤ ትግልን በአዲስ ነድፎ፣ አጎልብቶ፤ በክፊል እንደሚንቀሳቀስና፤ የውደፊት መስናዶዎችን፤ በሕቡም ይሁን በይፋ፤ እንደ ሽረሪት ድር በተደራ ሕዋስም ይሁን በውሉ በማይታወቅ፤ ሁሉ ገብ ሕዋስ ወ.ዘ.ተ እየተረዳ፤ የሕዝብ የነጻነት መታገያ፤ ደጀኖችን ገንብቶ፤ ሰላማዊ ትግሉን፤ አቀጣጥሎ፤ በቆራጥ መስዋትነት፤ የወያኔ የትግሬ ነጻአውጭ ግንባርና አበር ግንባሮችን ከሥልጣን ወንበራቸው አባሮ፤ አባቶች ደማቸውን አፍስሰው፤ አጥንታቸውን ከስክስው፤ ያቆዩትን አገር መልሶ፤ የወያኔን ባንዲራ አውርዶ ለጥቁር ሕዝቦች ሁሉ የነጻነት ተምሳሌት ምልክት የሆነችውን ሰንደቃላማውን ስቅሎ፤ ነጻነትን እንዲያውጅ፤ ታሪካዊ  ግዳጁንም፤ በድል አድራጊነት እንዲወጣ፤ ከአለፉትና ከዘመኑ ትግል  በመማር፤ አዲስ  የትግል አመላካች፤ ስትራቴጅዎችን፣ ታክቲኮችን፣ ተጨባጩን፣ አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ የአገሪቱን የፖለቲካ የመሃበርስባዊ የኢኮኖም ጭብጦች እየመረመረ፤ እየፈተሽ ፤ አስፈላጊም መስሎ ከታየው፤ አዲስ  የራሱ የሆነ የትግል ስልት በመፍጠር መጛዝ ግድ እንደሚል የብዙዎቻችን እምነትና ፣ግንዛቢያዊ ጭብጥ  ነው።

“Make your work to be in keeping with your purpose” (Leonardo da Vinci)

ከስንዴ እንክርዳድ እንደማይጠፋ ሁሉ አንዳንድ የኔ ቢጠ የዋህ በተቃዋሚ ወገን የተሰልፉ ልሂቃን አልፎም የወያኔ ሆድአደር ልሂቃን  መርምረውም ይሁን ሳይመረምሩ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ በመርዝ የተለወሰ አሉታዊ የመሃበራዊ ሳይንስ እውቀትን ሳያላምጡ በመጉረስ እንደ ጋማ ከብት ከሆዳቸው ገፍተው ወደ አፋቸው እየሳቡ አምጥተው መልስው መላልሰው ከሚአመነዥኩ ፤የጎሮሮ ስንጥር ሆነው ትግልን ከሚያውኩ፤ መስሪ ልዩነትን እያጎሉ፤ ካንድነት ይልቅ መበታተንን፤ ከፍቅር ይልቅ ጥላቻን የሚስብኩ፤ ታሪክን ባሕልን አገራዊ ማንነትን፤ ሕዝባዊ አብሮነትን፤ አገራዊ አንድነትና እድገትን የሚሽረሽሩ፤ የሚንዱ እሳቤዎችን በጎ አስቢ በመምሰል፤ የሚረጩ የሕዝብ ጠላቶች እንዳሉ በመገንዘብ፤ በምያነሱትም አፍራሽ የስነ ልቦናዊ ጥቃት ስላባን መሰርት ያደርጉ በውዝግብ ሴራ ተቀንቅነው ተረቀው በሚቀርቡልን የውሸት እንቶፈንቶ መጣጥፎችም ሆኑ ዲስኩሮች ሳንደናገጥና ሳንሸበር ፤በስነ ጽሁፍ ጌጠው በተዋቡ፤ በማር በተለውሰ መርዝ ተከትበው በተጻፉ  ጽሁፎችና በመሳሰሉት አጀንዳዎች ሳንታለል፤ አንድም አጀንዳዎቹ አደገኝነታቸውን በዝርዝር ጭብጥ በሆኑ መረጃዎች ለሕዝብ አቅርቦ በማሳያት፤ሕዝብ እንዲያውቀው በማድረግ፤ አልያም ሕዝብ ደግሞ ደጋግሞ የሚያውቃቸውና ደግሞ ደጋግሞ ያለተቀበላቸው ከሆኑ አውቆ እንዳላወቁ በማለፍ ግዜን በንትርክ ባለማጥፋት፤ በተለይ አገር ወስጥ ያለው ወጣት ትውልድ ከወገኖቹ ጋር አብሮ እየመከረ፤  ለአገርና ለሕዝብ ነጻነት የሚበጅ፤ ታግሎ የሚያታግል፤ አዲስ ታሪካዊ መርሕ ነድፎ፤ ያግሩን መሬት በአገሩ በሬ ብለው አበው እንደቀለጹት፤ ትግልም በአገርና በአገር ልጅ ነውና፤ ስጋዊ ሞትም ለስውልጅ የተሰጠው የማይቀር ጽዋ ነውና፤ የአገርና የሕዝብን ባርነት ሞት ከማየት በነጻነት ለነጻነት ታግሎ ማለፍ የተቀደስ ተግባር መሆኑን ካባቶቻችን ካያቶቻችን ከቅደመአያቶቻችን ከቅመአያቶቻችን የታሪክ ገድለ አስትምህሮ የነጻነት ቀንአኢ መገለጫችን የሆነውን ምርሕ አንግቦ ለነጻነት በጽኑ ከሕዝብ ጋር ወግኖ ከሕዝብ ጋር አብሮ ሆኖ በመታገል የውጭ ጥገኝነትን ሳያማልለው የውጭ እርዳታ ድጋፍም ሳይሻ ሕዝብ የበላውን በልቶ ሕዝብ የሚጠጣውን ጠጥቶ፤ ሕዝብ  ጛስን ጎዝ ጉዞ ቁርበቱን አንጥፎ ሌቱን እንደሚያሳልፍ ሁሉ እሱም እንደሕዝብ ሌቱን አርፎ፤ ሕዝብን የነጻነት ጋሻና ጦር አድርጎ በሚንቀሳቀስበት፤ ሁሉ የወገን ድጋፈ ማድረግ  ማበርታታት ኢትዮጵያዊ ግዴታችን መሆኑን በመገንዘብ፤ ትግሉም በምጽዋት ከወያኔም ሆነ ከሻቢያ ይመጣል ብሎ በታሪክ ገለባ ውስጥ ተደብቆ: ገለባው ሲቃጠል አብሮ የሚነድ ስነፍ ፍጡር እንዳንሆን ቆም ብለን እራሳችንን እንመርምር ትግሉንም ተግላችን እናድረገው።                                       ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!
 
ኢትዮጵያ በተባበሩ ልጆቿ ክንድ ተከብራ ለዘላለም ትኑር !!

No comments:

Post a Comment