Monday, September 1, 2014

ልማታዊ ዘርፎ አዘራፊ የጎሳ አንባ ገነነ መንግሰት

ልማታዊ ዘርፎ አዘራፊ የጎሳ አንባ ገነነ መንግሰት

“እውነትን የማያውቅ ሆናና ብቻ ነው። ግን እውነትን
እያወቀ ውሸት ነው የሚል ወነጀለኛ ነው።” ቤረተቶለት ብሬሽት

በዘር፣ በጎሳ ፣በሃይማኖት፣ በቛንቛ፣ በፆታ፣ በግብረሰዶም እየተመራ አገራችንን ኢተዮጵያን ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የሚገዙት ወንጀለኛ ለዛሙጥጤ የጎሳ አንባገነን ስብሰብ እየሠሩት ያለውን ዝብን አንገት አስደፊ ሀገርን ነፃነት ሰባሪ፣ አብሮነትን ሸርሻሪ ድርጊት... ሁሉ ጥርሱን ያገጠጠ፣ ድፍን ዓለም በሰፊው በግልጽ የሚያውቀው ሃቅ መሆኑ እየታወቀ፤ መሲሕ፣ ሃሳዊ ድረሳናትን እየደረሱ፤ ለሕዝብና ለሃገር የማይጠቅም፤ ሃገር ገዳይ ፍሬከርስኪ ሥራዎችን በማቅረብ ሰረበተ (Sychopatic Statement) ዲሰኩር መፈብርክ

የሕዝብን ስነልቦና በዘር፣ በጎሳ፣ በሃይማኖት፣ ቛንቛ በፆታ፣ በግብረሰዶም አየከፋፈሉ፣ አነዱን ካነዱ እያባሉ ጥላቻን እየፈጠሩ ጥላቻን እያነገሱ፤ የሕዝብን ጭንቅላት መቆጣጠር፤ ከጌቶቻቸው በምጽዋት በተሰጠ፤ የፕሮፓጋነዳ ዜና ማሰራጫ  መሣሪያዎች ተጠቅመው፤ በሆድ አደር ምንደኞች ወነጀል ሰሪ፣ የናት ጡት ነካሽ ጋዜጠኛ ተብየዎች ጠዋት፣ ማታ የሃሰት ዜናዎችን አየር ላይ አውለው በማሰለቸት የተጠመዱ ሕዝብንም ከሰሜን አሜሪካ፣ ከአውሮፓ፣ ከኤዝያን ፓሲፊክ ሀገራት በአገር ስም በተገኘ የምጽዋት የብድር ገንዘብ የግላቸው አድርገው፤ በንቅዘት/በሙስና፣ በጎሳ ኪራይ ሰብሳቢነት በወነጀል ተጨማልቀው፤ ሰለሕግ የበላይነት ሰለፍተሕ፣ ስለ ሰርአተ መድሎዋዊ አልቦነት፤ ቆበራቸውነ ሞልተው እየፎለሉ፤  በልማት ስም፤ ሕዘቡን ከሚኖርበት ቤት መኖሪያው አላነዳች በቂ ካሳ በማበረር የሚታወቁ፤ በርካሽ የቻይና ሰራሽ መስትዋት የአጊጡ ጥራት የሌላቸው ሰማይ ጠቀስ ፎቆችን ሕዝብንም ከቦታው እያፈናቀሉ በመገንባት፤ ለውጭ ባላሃብት የሃብት ትርፍ አካባች፤ በባርነት አገልጋይ ሠራተኛን ማጓጓዣ በሚል፤ የእውነተኛ ብርቅዬ ኢትዮጵያዊ ቅዱስ ሰማእታትን ሀውልት እያነሱ የባቡር ሃዲድ በመስራት፤ ክረምት በመጣ ቁጥር በውሃ እየተሸረሸረ የሚበላሽ ቁጥራቸው ይሄ ነው የማይባሉ፤ ሕዝብን ለመደለል፤ ባለሶስት፣ ባለ አራት፣ ባለ አምስት መስመር አስፋልት መንገድ ለናሙና ሠራን ብለው በኳኳቴ ዲስኩር የሕዝብን ጆሮ ያሰለቹ፣ በቅጡ ያልተጠኑ በየጊዜው የሚደረሰሱ፤ ከጥቅማቸው ጉዳታቸው የበዛ፤  የከባቢ የተፈጥሮ ሁኔታን አዛቢ፤ ለሙስና ለንቅዘት ለጎሳ ኪራይ ሰብሳቢነት የተጋለጡ ግድቦችን ከሕዝብ አፍ አስገድደው በመዋጮ በግዳጅ የቦነድ ግዥ ሕዝብን ደልሎ፤ በማወናበድ፣ በጠራራ ፀሐይ ኪስ የሚያወልቁ፤ እነዲሁም ትላልቅ ለጎሳ ክራይ ሰብሳቢነት የተጋለጡ ፐሮጀክቶችንም መገንቢያ በአገርና፣ በሕዝብ ስም በብድረ ስም የተገኘን፤ ገንዘብ ሲሶውን በመገልገ፤ ሶስት ሲሶውን በንቀዘት፤ ካባሪ ተባባሪዎቻቸው ጋር ሆነው፤ ዘርፈው የሚያዘርፉ፤ ይባስም ብለው፤ በእንግሊዝና በአሜሪካ መዋለ ፈሰስ ብድር አቅራቢነት፤ (Hedgefonds and Pension funds) የሚደረገውን፤ የእርሻ መሬት ቅረምት፤ በአገራችን በማስፋፋ፤ ቤልጅምን የሚያሕል ድነግል የእረሻ መሬት ከሕዝብ ቀምተው፤ ለጌቶቻቸው ለሰሜን አሜሪካ፣ ለአውሮፓ ለኤዝያና ለነዚሃ አገራት ተባባሪ አባታዊ አንባገነን የአረብ አገራት፣ በመዋለ ሀብት ፈሰስ ግኝት ስም፤ በነፃ፣ በወላግድ የሕዝብን ሀብት አስረክበው፤ [] ሰለቴክኖሎጅ ተጠቃሚነት፣ ስለ ሥራ ፈጠራ፤... በሚል ቱሪናፋ ዲስኩር ሕዝብን በማጭበርበር ወደር የማይገኘላቸው በአፍሪካም ሆነ በመላው ዓለም ብቸኛ የሆኑ ተወዳዳሪ የማይገኝላቸው ቆረጦ ቀጥል፤ ሸርክት፤ ዘረኛ የጎሳ ስርአትን አንጋሽ፤ ለባእዳን ጥቅም ያደሩ፤ በአሽከርነት ሕዝብንና አገርን አዋራጅ የወንጀል ሥራን፤ በአገርና በሕዝብ ላይ በመስራት የሚታወቁ፤ እደ ወያኔ-ሕውሃት/ኢሃድግ ተብዬ አይነት፤ ሰው-በላ ጉግ ማነጉግ ስብሰብ፤ የትም ዓለም ቢሆን፣ በዘመናችን ወደር የማይገኝለት፤ አገር ከሃዲ፣ ሕዝብን ጨቛኝ፣ ለውጭ ያደረ፣ አጎብዳጅ፣ እደማይገኝ፤ ያለፉት ሁለት አስረት ዓመታትን፤ የአገራችን የኢትዮጵያ እውነተኛ ድረሳነ ታሪክ የተከታተለ ሁሉ፤ በወያኔ የዘርኛ ልክፍት ተለከፎ ካላበደ ፀረ-ኢተዮጵያዊ ስብስብ፣ አልያም ለሆዱ ተገዝቶ፤ ለሆዱ ያደረ ካልሆነ በስተቀር፤ በአንክሮ መላው የአገራችን ሰፊው ሕዝብም ሆነ፤ ድፍን ዓለም በጠራራ ፀሀይ በሕዝብና በሃገር ላይ ትላነትም ሆነ ዛሬ በዲሞክራቲ በልማት ሽፋን ስም እየተፈጸሙ የነበሩ፤ አሁንም በመፈጸም ላይ ያሉ፤ ከላይ የተጠቀሱት፤ ወንጀሎችን እደሚያውቀው፤ እውን ነው። በማስረጃም ድጋፍ፤  በዝርዝር አነድ ባነድ ማቅረብ የሚቻል፤ መዝገብ የያዘው ሀቅ ነው።


ወያኔ-ሕውሃት/ኢሃድግ ካፈጣጠሩም የቅኝ ገዥ ተስፋፊ ቩልቃሽ አውሮፓ አንጋሽ ዘረኛ ርዮትን አነግብኦ አነዴ የግራ አለያም የቀኝ ርዮት ጭንብልን አጥልቆ፤ እደ አስፈላጊነቱ በግራ ሲመቱት ቀኙን በቀኝ ሲመቱት የግረውን አይዲዎሎጅ እየተከተለ እደ አስተማሪዎቹ እደ ናዚው አዶልፍ ሂትለር፤ እደ ፋሽስቱ ዱቼ ሞሶሎኒ አልያም እደ ሶቬዬቱ ሰታርሊን፤ሲያስፈልገውም እደ ቻይናው ማኦ ሴቱነግ እደ ካምፖዲያው ክሜር ሮዥም  የጎሳ አንባ ገነን ጥብቆውን አሰፍቶ፤ ባሰፋው ጥብቆ ልክ የሚያስብ የአጼ በጉልበቱ የመንደር ልጆች ስብሰብ እደነበረና፤ ንቃተ ሕሊናውም በቁመናው ተለክቶ ተስፍቶ በተሰጠው፤ ጥብቆ ልክ የሚያስብ ትላንትም ዛሬም እደነበረና እደሆነ፤ አያሌ የሱ አካል ያልሆኑ ወገኖች በመጽሃፍ ስለዚሁ ሊል ዘሊል ስብሰብ በመጽሃፍ በመጣጥፈ ጥናት የደረሱት መጣጥፍ አስረጅ ናቸው። ስልጣንም በአዲሱ  የቅኝ ገዥ ፈቃድ፤ ረዳትነት ባሜሪካው የደሕንነት ተቛም አባሪነት ስልጣን ላይ እደወጣ፤ አገርንም አዳስገነጠለ፣ በአምሳሉ በታዛዥነት የሚያገለግሉትን ቩልቃሽ የጎሳ ድረጅቶች  በመናጆነት ፈጥሮ ከላይ የተጠቀሱትን የወንጀል ሥራዎች እደሠራ እየሠራም እደሚገኝ የማይታበል ሃቅ ነው። በማን እየታገዘ እደሚሰራ እራሱ ወያኔ-ሕውሃት/ኢሃድግ የማይክደው ሀቅ ነው። እነዚህም ሀይሎች የአዲሱ የእጅ አዙር ቅኝ ገዥ የሰሜን አሜሪካ የአውሮፓና የኤዝያን ፓሲፊክ አገራት እደሆኑ አይካድም። እነዚህም ሀገራት የራሳቸው የሆነ ርዮትን አንግበው ጥቅማቸውንም ለማስጠበቅ መላውን ዓለም በተለይ የቀዝቃዛው ጦርነት ካበቃበት ዋዜማ ጀመሮ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥራቸው ውሰጥ እዳስገቡት አይታበልም። ቀደም ሲልም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በሗላም፤ እነዚሁ የሰሜን አሜሪካ አገራት፤ ማለትም አሜሪካ በአቛቛመችው፤ (Global finance and Corporate Capital) ዓለም አቀፋዊ የበላይ ኢኮኖሚ ጥምረ ተቛም እንዲሁም ዓለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ ተቆጣጣሪ (Multilaterial Institutions of Global Economic Surveillance, G7, IMF, WB, WTO, ...) ተቛማት አመካኝነት፤ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ የአፍሪካ፣ የኤዝያ፣ የላታይን አሜሪካ አገሮችን በኢኮኖሚ ጥገኝነት ውሰጥ አስገብተው፤ ተቀናጅተው እየሠሩ  እደሚገኙ፤ የአገራችን ሆነ፤ አፍሪካ፣ በኤዝይ፣ በላቲን አሜሪካን እየተሠሩ ያሉ ልማታዊ ተብየው ስራዎች የነዚህን ሕዝብና ሀገር ወደተሻለ የእድገት አቅጣጫ የሚያመራ ሳይሆን፤ በመሰረቱ የአዲሱን የእጅ አዙር የቅኝ ገዥዎች ርዮትን የበላይነትን አንጋሽ፤ እነዚሁ ሀይሎች ዓለም በትናንሽ እነሱ የሚቆጣጠሩዋቸው አገራትን ፈጥረው፤ ዓለምን ሙሉ በሙሉ አነድ በማድረግ፤ በቁጥጥር ውሰጥ አስገብተው በአንባገነንት ለመግዛት አልመው የሚሰሩት እነጅ፤ ዲሞክራቲን ለማስፋፋት፤ መድሎ አልባ የሕዝብ እድገትን፤ ብልጽግናን ለማምጣት፤ ድሕነትን ለማጥፋት፣ ቴክኖሎጅን ለማስፋፋት፤ እዳልሆነ፤ በዓለማችን ትላነትም ሆነ፣ ዛሬ በነዚሁ ሀይሎች፤ በቀጥታም ሆነ፤ በእጅ አዙር ተቀስቅሰው፤ በዓለማችን የምናያቸው ግጭቶች፣ ጦርነቶች፤ የሃብት የይገባኛል ቅርምት ትንንቆች ሁሉ አጉሊ ምስክሮች ናቸው። እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት የኢኮኖሚ ተቛማትም፤ ዓለም አቀፍ ስም ይስጣቸው እነጅ፤ ግልጋሎት ሰጭነታቸውም ሆነ፤ አፈጣጠራቸው፤ ለሰሜን አሜሪካ ለአውሮፓና ለኤዝያን ዓለም አቀፋዊ ባላሀብት እደሆነ፤ በዓለማችን ዛሬ በኢኮኖሚ መአቀብ፤ በፈቃደ ሕብረት ለፀረ-ሸብርተኝነት ቡድን ስም፤ በሰሜን አሜሪካ በአውሮፓና በኤዝያን ፓሲፊክ አገራት አጋርነት እየተደረጉ ያሉ በሀገራት ላይ የሚጣሉ ኢኮኖሚያዊ ማእቀቦችም ሆኑ ለሀገራት የሚሰጡ እርዳታዎች ሁሉ በማን ለምን እደሚደረጉ አጉሊ ምስክሮች ናቸው። በጣም የሚያሳዝነው ግን ትላንት የሶሻሊስት ሰርአት መስፋፋት አስግቶዋቸው፤ በየሃገሩ ደጋፊ ታዛዥ ድረጅቶች ፈጥረው የጥንት የስልጣኔ መሰረት የሆነትን አገራትን በዲሞክራሲ ማስፋፋት ስም በየአገሮቹ የውሰጥ ጉዳይ ጣልቃ እየገቡ፤ የአገራቸውንም ሕዝብ ጥቅምሕ ተነክቶዋል በሚል እያሰተባበሩ፤ በኢትዮጵያ፤ በኢራን፣ በኢራቅ፣ በሊቪያ፣ በግብጽ፣ በሱሪያ፤ በሱዳን፣... የሚሰሩት፤ አገርን የመበተን እኩይ ሥራም፤ መሰረቱ፤ በውነት ለነዚህ አገሮች ሕዝብ ዲሞክራሲ ለማምጣት በማሰብ ሳይሆን፤ አውሮፓ አንጋሽ የእጅ አዙር ቅኝ ገዥዎችን የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የመሐበራዊ የበላይነት ለማስፈን እደሆነ፤ አገሮቹንም በዘር፣ በጎሳ፣ በሃይማኖት፣ በቛንቛ ልዩነት አሽመድምዶ፣ በትናናሽ አገራት ከፋፍለው ቆራርጦ፤ ታዛዥ አባወራ እነሱ እደልባቸው የሚዘውሩዋቸው ምንደኞችን ስልጣን ላይ አውጥተው ዓለምን በበላይ አነድ አድረጎ ለመግዛት እደሆነ አያጠራጥርም። እነዚህም ከላይ የተጠቀሱት አገሮች አማራጭ፤  ከድጡ ወደማጡ ሆኖም ትላንት በአምባገነን ሥርአት ሲታመሱ ዛሬ ደግሞ ዘር፣ በጎሳ፣ በሃይማኖት፣ በቛንቛ ልዩነት ተሽመድምደው፤ እዲጠፉ የሚደረገው ሥራም ማን እያረመደው ያለ ሥራ እደሆነ ድፍን ዓለም የሚያውቀው ነው።

ለእጅ አዙር ቅኝ ገዥ ተባባሪነት

እንግዲህ  ያለው ሀቅ ይሄ ከሆነ፤ ባገራችን ላለፉት ሁለት አስረት ዓመታት አገርን የሚገዛው፤ ሊል ዘሊል የእጅ አዙር ቅኝ ገዥዎች መናጆ፣  የጎሳ አንባገነን መንግስት ተብዬው፤ ሰለ ልማታዊ መንግሰት ቢደሰኩር እደ ናዚ ሂትለር ወጣቶችንም አስገድዶ የረፍት ጊዜያቸው ከቤተሰቦቻቸው ጋር እዳያሳልፉና ቤተሰቦቻቸውን እዳይረዱ፤ ለመጭውም የትምሕርት ጊዜም መሰናዶ እዳያደረጉ አስገድዶ ከልክሎ፤ የወጣቱን  ጭንቅላት አጠባ፤ ሙከራ ሥራ ሁሉ፤ ስልጣን ካወጡት ሀይሎች የተሰጠው፤ አገርን ለጥገኝነት ጣይ፤ የቤት ሥራው ነውና፤ ሊገርምን አይገባም። ወጣቱም እራሱንና አገሩን ለባርነት እደመይጥል፤ እየታዬ ያለ፤ የቀን ተቀን የነፃነት ታሪካዊ ሥራው ምስክር ነው። ዋናው ጉዳይ ግን ፤የወያኔ-ሕውሃት/ኢአሀድግ እራሱን ልማታዊ መንግሰት ብሎ ሕዝብን ለማታለል የተነሳበትን ምክንያቱን ዳስሶ እውነቱን ለሕዝብ በመረጃ ማቅረቡ ላይ ነው ያለው ዋና ሚስጠሩ። ልማታዊ ምንግስት የሚለውም ሕሊናት በእጅ አዙር ቅኝ ገዥ ተስፋፊ ርዮት ተኮር ተቀንቅኖ  መሰራቱንም ዝርዝር ጉደይ ውሰጥ ከመግባታችን በፊት ማወቁ ሰርአቱ የማን አገልጋይ እደሆነ ቀደምት ግነዛቤን ያስጨብጣል።     
     

ልማታዊ መንግሰት ለማን?


ልማታዊ የሚለውም ቃል በአገራችን፤ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አነጻር ተያያዥ ሆኖ የሚቀርበው፤ ለጥቂት ዘረኛ የጎሳ ጽንፈኛ አሸባሪ፤ የባእድ ቅጥረኛ፤ የሕዝብን ደም በሰሪነጋ እየማጉ፤ የአገሪቷን መዋለ ሀብት አዘርፎ በመዝረፍ የሚታወቁ፤ አገረን ለባእዳን፣ የአዲሱ ቅኝ ገዥ ጥገኝነት ተግተው ጠዋት ማታ የሚያገለግሉ፤ አነዴ አብዮታዊ ዲሞክራቲ፣ ሌላግዜ ደግሞ ትራንፎረሜሽን፣ ሲአሰኛቸውም፣ ልማታዊ መንግሰት እያሉ፤ ራሳቸው ሆንነው፤ ሌላውን ሆናና አዲሆን የሚጥሩ፤ ጭንቅላታቸው የሰባ፤ በጎሳ፣ በጎጥ፣ በቤተሰብ፣ በጓደኝነት፣ በአብሮ አደግነት ተቧድነው፤ አገሪቱን  በፋሸስቱ የዱቼ ሞሶሎኒ ሕሊናት የጎሳ ክልሎች በቛንቛ ስም ደልድለው፤ አነዱን ካነዱ እያባሉ፤ በሚዘውሯቸው፤ አባሪ ተባባሪ አሸበሪ፤ የጎሳ አባወራዎችን በአስተዳዳሪነት፤ መድበው፣ በጎሳ ኪራይ ሰብሳቢነት፤ ተጨማልቀው፤ የአገርን ሀብት እዳስፈለጋቸው፤ በሚያዙበትና፣ ሲያስፈልጋቸውም፤ ወደውጭ በማሽሽ የሚታወቁትን፤  የወያኔ/ሕውሃት-ኢሃድግና አባሪ ተባባሪ ቡድን እነጅ፤ ከሃገርና ከሕዝብ ጥቅም ጋር ተያያዥነት ኖሮዋቸው ከቶም የሚቀርቡ  አይደሉም። ይሕን አውቆ እውነት አይደለም በሎ የሚክድ ካለ አነድም ሆናና ነው አልያም ወንጀለኛ ነው።

ልማታዊ መንግሰት ለምን?

እንግዲህ እነዚህ ቡድኖች ናቸው ከንቱ ሕዝብን መደለያ ቱሪናፋ ዲሰኩሮች እየፈጠሩ ላለፉት ሁለት አስረት አመታትም ሆነ፤ ዛሬም መንግስታዊ የሆኑ ዋና ዋና  ተቛማትን ተቆጣጥረው ከላይ አስከታች ባለው እርከን ውሰጥ ተሰግሰገው፤ ስልጣናቸውን ተገን አድርገው በዘር ማጥፋት፣ በዘር ማጽዳት፣ በስነልቦና የዘርማጥፋት፣ በአገር ክሕደት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በልዩ ልዩ ዘርፍ ብዙ ወነጀሎች ተሰማርተው፤ በሕዝብና በአገር ላይ የበቀል ወንጀል እረምጃ በመውሰድ ሕዝብና አገርን የሚበቀሉት። ይሕም የሠሩት ዛሬም የሚሰሩት ወነጅል፤ ተደብቆ አዳይታይ፣ ሕዝብም ተነሳስቶ ትግል አነስቶ ከስልጣናቸው እዳያወርዳቸው፤ በቀጣይነትም ስልጣናቸው ይዞ ለመቀጠል እዲያሰችላቸው ላም ባለዋለችበት ኩበት ለቀማ ተምሳሌትንት ያለውን መላ መፍጠር ግድ ስለሆነ ኤተኖ ፋሽታዊ ርዮታቸው በልማታዊ መንግስት ጭንብል ሸፋን ተከናንበው ለመታየት በመወሰን፤ ያው ትላንት እደለመዱት የመንደር ብልጣብልጥ አገርና ሕዝብ አያውቅብንም አባዜ የተከየነ የዘርፎ አዘራፊ ድራማቸውን በአዲስ ማቅረብ ግድ ሆነ። እደቅዱስ፤ ፈሪሃ እግዚአብሔር እዳደረበት፤ ሰውም በእጁ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በንጹሃን ደም የጨቀዬ የባእድ ቅጥር፤ ጨካኝ፤ የወሮበላ አለቃ የነበረውን፤ የወንጀለኞች አባወራን፤ ቅዱስ መንፈስ በርአይ ተገልጾ የአገር ልማትን እዳሳያው ተደረጎ፤ በአዲሱ የእጅ አዙር ቅኝ ገዥ ርዮት ላይ የተደነገገ ልማታዊ ዘርፎ አዘረፊ፤ እኩይ አቻ የማይገኝለትን ስነስርአት ተብሎ በአዋጅ  በዚሁ ፈላጭ ቆራጭ ወነጀለኛ ትእዛዝ፤ በሀገሪቱ አዋጅ ሆኖ በባለ ርአዩ ተብዬውና በአበሮቹ  እዲሰራበት ተብሎ ሥራ ላይ ዋለ ተብሎ የተለፈፈው። ዛሬ ዛሬ ደግሞ በቆሌቢስ በቅጽል ስሞ ሾተላይ ተብሎ በሚጠራው የበለይ ካደሬ፤ ተልእኮው እዳልተሟላ ተገልጾዋል። ጅራፍ እራሱ ገረፎ እራሱ ይጮሀል ነውና፤ ሰብ አሰባብ ፈጥሮ፤ ሌላው ላይ ማላከክ፤ አላያም ሕዝብን አወናብዶ መደለል ስርአቱ የተካነበት እኩይ ሥራ ስለሆነ ሊደንቀን አይገባም። የሚደንቀው የማወናበድ ሥራውን ነው።   

ይህ ሁሉ የማወናበድ ሥራም ልማታዊ መንግሰት ከሚለው መስፈረት ጋር አያይዞ ያው ሕዝብን ለመደለል እሳቤን ያደረገ ፀረ-ኢተዮጵያዊ፤ ፀረ-ነፃነት አንጋሽ፤ ከዚህ ቀደም ይህው እኩይ ስብስብ በሁሉም ዘርፍ የአገር አነድነት የሕዝቡ አብሮነት አቆራኝ እሴቶችን ተንደው እዲጠፉ ማድረግ ሥራን በቀጣይነት እዲገፋበት የሚያደርግ መሆኑን በመገንዘብ፤ ዘርፎ ማዘርፍ ተልእኮ ሥራውንም አነግሶ ለማከናውን እሳቤን በማድረግ እሰቤ እደሆነ አይጠረጠርም። እደሚታወቀው ሕዝብ አብሮ ካበረ እንቢኝን አነግቦ ይታገላል። ከተከፋፈል ግን ለቁጥጥረ አመች ከመሆኑም፣ እሰከዛሬ ወያኔ-ሕውሃት/ኢሀድግ፤ ሰበበ አሰባባትን እየፈጠረ፤ እደተለመደው፤ ሕዝብ ለሕዝብ እዲናቆር፤ እዲጣላ፤ እዳይተማመን ያደረገዋል። ለዚህም ነው ላለፉት ዓመታት የልብ ወለድ ተረት ተረት ፈጥሮ በታሪክ መልክ በጎሰኝነት ሰክርው ባበዱ ኤትኖ ፋሽስት ልሂቆቹ አመካኝነት፤ ፀረ-ኢትዮጵያ ታሪክ በመጽሃፍ ተደረሰው እዲወጡ የተደረገው። ለዚህም ነው፤ የአዲሱ የእጅ አዙር ቅኝ ገዥ ባሕልን አንጋሽ፤ ሥራን ለማስፈጸም፤ አይምሮዋቸው በጎሳ ጽነፈኝነት የተጎዱ ስብስቦች፣ የአገር ጡት ነካሽ፤ ደፋር ከሃዲ የበረት ልጆችን አሰልፈው፤ እ.ኤ.አ በ1889 በቤልጅሙ ንጉስ በንጉስ ሊዎፖልድ ሁለተኛው በኮንጎ የተደረገውን የሴቶች ጡት መቁረጥ ወንጀልን የአገር ታሪክ አድረጎ በሀሰት በማቅረብ፤ ሃውልት ስርቶ፤ በሃሰት የሃገርንም ሆነ የአፍሪካን ሕዝብን ታሪክ አኮሳሽ፤ አዋራጅ ወነጀልን መፈጸምም፤...  እዲሁ ከልማታዊ ዘርፎ ማዘረፍ የእጅ አዙር ርዮት ጋር ተያያዥነት ያለው በመሆኖ የሚታየው። (ለዚህም ነው ከጥነት ከጠዋቱ የወያኔ/ሕውሃት-ኢሃድግ የጋራ ታሪክን ማጥፋት ዋና አላማው አድረጎ የተነሳው። የጋራ ታሪክ ሕዝብን አነድ ሰለሚያድረግ፣ የሕዝብ አነድነት ለወያኔ ተልእኮ እንቅፋት ስለሆነ የሚጠፋበት ምሱ በመሆኑ አጥብቆ ይጠለዋል። )

በመሆኑም ልማታዊ ዘርፎ አዘረፊ ወይንም ልማታዊ መንግሰት ማን እደፈጠረው፤ ምን እደሆነ እነዴት እደተፈጠረ በሃሪውም ምነ እደሆነ መዳሰሱ ከላይ የተሰነዘሩትን ገለጻዎች አጠናካሪ ጭብጥን ያሰገኛል።

የእጅ አዙር ቅኝ ገዥ ቡድን ትላንት፤ በአፍሪካ በአዝያ በላቲን አሜሪካ፤ እደ ድንገንተኛ ውሃ የሶሻሊስት ርዮት መላውን አህጉሪቱን ያጥለቀልቃል ብሎ በመስጋት የፈጠሩት ርዮት ላይ የተመሰረተ፤ ያጋብሶ አደር የኢኮኖሚ ሕልዮ እደሆነ፤ ከላይ እደተጠቀሰው ልማታዊ ዲሞክራቲ የእጅ አዙር ቅኝ ገዥ ተስፋፊ ርዮት እደሆነ፤ ሕልዮቱም የዚሁ ተስፋፊ ይልን የፖለቲካ፣ የመሃበራዊና (አውሮፓን አንጋሽ ባህል ማስፋፊያ) ጥቅም ለማሰጠበቅ እደሆነ በግልጽ ይታወቃል። በመሆኑም፤ የልማተዊ ዲሞክራቲ ሕልዮ መሰረቱ ትናንት ከቀዝቃዛው ጦርነት ማለቂያ በሗላ ሳይሆን ቀደም ሲል ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በፊት ሶሻሊዝም በዓለም ዙሪያ የነበረው ተቀባይነት ያሰጋው አሜሪካ በልሂቃናቱ አማካኝነት በዓለም ዙሪያ የአጣውን የርዮት ተቀባይነት እደገና ተንሰራርቶ እዲነግስ ታስቦ ተቀንቅኖ የተፈጠረ ለመሆኑን በመረጃ ይታወቃል። እሰከ  ቀዝቃዛው ጦርነት ማለቂያ ድረስ የምዕራብ ሀገራት ርዮት በአፍሪካ ይህ ነው የሚባል ተቀባይነት እዳልነበረውም፤ በዘመኑ የነበረው የኃይል አሰላለፍ ምስክር በመሆን ይጠቀሳል። የልማታዊ ዲሞክራሲ እናት ተብላ የምትጠራውም ጃፓንም ሆነች፤ የምስራቀ ኤዝያን በመባል የሚታወቁትን አገራት እድገተ ታሪክ መዳሰሱ ጉዳዩን በቅጡ ለማወቅ ግድ ይሏል።
  
ጃፓን ከናዚ ሂትለር ጀርመን እና ከፋሽሰቷ የቬኒቶ ሞሶሎኒ ጣልያን ጋር በመወግን በፈጠረቸው የሁለተኛ የዓለም ጦርነት ምክንያት አሉ የሚባሉ ኢነዱሰትሪዎቿ ሆሉ፤ ተንኮታኩተው፤ በአሜሪክን የሃይል ቁጥጥረ ውስጥ እድትወድቅ ተደረገ። በመሆኑም ጃፓን ከኮሚኒስት አገራት ጋር ባላት የምድረ ፀፋዊ ድነበረተኝነት አማክኝነት፤  እደ ምእራብ ጀረመን ሁሉ የቀዝቃዛው ጦርነት መአከል ሆነች። በመሆኗም፤ የአገሪቱ የኢኮኖሚ መዋቅሮች መልሶ መስራት፤ ከምእራቡና ከምስራቁ የርዮት ትንቅንቅ አንጻር አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ ባጭር ጊዚያት በአሜሪካን ረዳትነት አገሪቱን መልሶ ለመገንባት እቅድ ተይዞ፤ መላው የአገሪቱ ኢኮኖሚ ተሽመድምዶ ወድቆ የነበረው፤ ባጭር ጊዜ ውሰጥ አገግሞ ለእድገት እዲበቃ ላካባቢውም ሞዴልነት ሆኖ ኢዲያገለግል ተደረገ። ጃፓንን በተመለከተ ሀቁ ይ ሆኖ ሳለ ያው እደተለመደው በምስራቅ ኤዝያ የምዕራቡን ርዮትን የበላይነት ለማሳየት ልበ ወለድ ስንክሳሮችን በኢኮኖሚ ሕልዮ ስም ጃፓንን በሞዴልነት ያስቀመጠ ሕልዮ መፍጠር ግድ ሆነ። 
     ("The post-1945 industrial and export-led expansions were associated with Cold War structures and were state-directed and -controlled. The Korean and Vietnam Wars each gave an economic boost to many of the nations in the region. Also, the anticommunist East Asian Newly Industrialized Countries (NICs) were supported by the United States, and dictatorships and authoritarian regimes, with strong militaries and secret police forces, were installed to sustain anticommunism. These regimes maintained local political conditions that allowed for the security of U.S. military bases. Thailand also provided bases for “rest and relaxation” for U.S. troops—that is, the origins of today’s regional sex trade".) (Stephen Gill teaches in the Department of Political Science at York University in Toronto. He is the author of a number of books, including Gramsci, Historical Materialism and International. Relations (Cambridge: Cambridge University Press, 1993) and, with David Law, The Global Political Economy: Perspectives, Problems and Policies (Baltimore: Johns Hopkins University Press, 1988. Mystification and the East Asian Model ).

የጃፓን ፈጣን እድገት መብቃት (ልማታዊ ዲሞክራቲ) ዋናው ምክንያት፤ እደሚባለው  ከምእራቡ በተለይም ከቢስማርክ ጀርምን (Prussian development state) የፐሮዚያን ሰፍነ ልማታዊ መንግሰት ተብየው የቅኝ ገዥ ተስፋፊ ልማታዊ መርሆ ተቀድቶ በተወሰዱ ትውፊቶች አማካኝነት እደሆነ የሚነገረውም (The East Asian capitalist development state was borrowed from the West, most immediately from Bismarck’s Germany. ((For a thorough discussion of the Prussian development state and the parallels with Japan, cf. David Landes “Japan and Europe” in W. Lockwood, The State and Economic Enterprise in Japan, Princeton UP, 1965.) But such borrowing of course intersects institutions and practices in the borrowing countries, and it led to different results in Japan, South Korea and most recently in China.) ግማሽ እውነትነቱ እደተጠበቀ ሆኖ፤ በርግጥም ጃፓን አነድ በአነድ የፐሮዚያን ሰፍነ ልማታዊ መንግሰት ተብየው የቅኝ ገዥ ተስፋፊ የገንዘብ ተቛማትን አሰራር አነድ ላነድ ገልብጣ መወሰዷን የሚያሰይ እውነታ አያጣጥለውም። በርግጥም ጉዳዩም ማን ምን ከማን ወሰደ ሳይሆን፤ ለልማቱ ሞቶር በመሆን በዋናናት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ የሆኑ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ መዳሰሱ ላይ ነው። እርግጥነው ከላይ በተቀመጠው ታሪካዊ ማስረጃ መሰረት፤ እ.ኤ.አ ከ1945  በሗላ የውጭ ኢክሰፖረት ንግድ መስፋፋት ከቀዝቃዛው ጦርነት ጋር በቀጥታ በቁጥጥር ውሰጥ ገብቶ ይሰራበት እደነበር ይታወቃል። በኮሪያና በቤትናም የነበሩት የጦርነት ግጭቶች ለከባቢው አገራት የኢኮኖሚ እድገትን ማትረፉ የማይካድ ሃቅ ነው። በፀረ/ኮሚኒሰትነት የሚታወቁት በምስራቅ ኤዝያ ያሉ ዛሬ በኢንዱስትሪ ያደጉ  የምስራቅ ኤዝያን (Taiwan and South Korea...) (ታይዋን፤ ሰሜን ኮረያ...) አገራት በአሜሪካን የሚደገፉ አንባገነንና ፈላጭ ቆራጭ የሆኑ፤ ጠንካራ የሆነ የወታደራዊ፣ የመከላካያ ሰራዊት፣ ጨካኝ የደሕንነትና የፖሊስ ሐይል ያላቸው እደሆኑ፤ እነዚህም ሀይሎች፤ ከምዕራቡ ርዮት በስተቀር ሌላ ርዮት ቦታ እዳይኖረው  ሙሉ በሙሉ በታማኝነት በቁጥጥር ግዳጃቸውን ሥራ ተሰማርተው አደሚሰሩ መረጃው ይጠቁማል። በማከልም ለአሜሪካ የወታደራዊ የጦር ቤዝ አመች የሆነ በአገሬው ተቀባይነት የሚገኝበትን የፖለቲካ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ሥራም ተሰልፈው የሰሩ እደነበር። አለፈው ተረፈውም ለአሜሪካ ወታደሮች መዝናኛ ታይላነድን መርጠው ወታደሩ እዲዝናና መዝናኛ የፍቶተ ሥጋ መናሕሪያ መአከል ፈጥረው ትብብር በማድረግ ለ አሜሪካ በሁሉም ዘርፍ አመች ሁኔታን አደፈጠሩ ይታወቃል። 

ለዚህመ ውለታ አፀፋ ይሆን ዘንድ፤ አሜሪካና የአሜሪካን ሸሪክ  የሆኑት የምዕራቡ ሀገሮች ምድረ ፀፋዊ ፖለቲካዊ (Geopolitical) እሳቤን መሰረት በማድረግ፤ ለነዚሁ ለምሰራቅ ኤዝያን አገራት ገበያቸውን እደከፈቱላቸው፤ ይህም ሁኔታ ለምስራቅ ኤዝያን አገራት የፈጣን የኢነዲሰትሪ እድገት በሌላም አጠራር dependent capitalist development.” “ልማታዊ ጥገኛ አጋብሶ አደር” ስርአት ፈር ቀዳች በመሆን አደተፈጠረ፤ በመረጃው ተጠቅሶ ይገኛል። እንግዲህ እነዚህ ጭብጥ ሁኔታዎች አልፈው ተረፈው፤ በአሜሪካንን የበላይነት በጃፓንን ሁለተኛ ቀደምትነት፤ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጥምረ ሀይል ሊፈጠር እደቻለ፤ ጃፓንም ካሜሪካን በተለገሳት የበላይነት፤ የምስራቅ ኤዝያ የፖለቲካ ሀይል አነዷ ሆና አደነገሰች መረጃው በአጽንኦት ይጠቁማሉ።

ሆኖም ባጠቃላይ ዋናው የምስራቅ አዝያ ሞዴል ቁልፍ ዝንባሌ፤ በፋይናንስ ቁጥጥር የተደገፈ መንግሰታዊ የንግድ ተቛማትን "ቁልፍ የሆኑ ኢኮኖሚ ዘርፎችን"  ወይንም የግል  "አገራዊ ትላልቅ" በኤክሰፖርት የውጭ ገበያ እድገትና ከፍተኛ ሀብትን ያሰገኛሉ ተብሎ በታመኑ፤ መንግሰት እደፍለግው፣ እደአሻው በሚያሽከረክረውና በሚዘውረው (Dirigisme) ኢኮኖመያዊ፣ ፖለቲካዊና መሐበራዊ (አነባገነናዊ) ስርአት መሆኑ መረጃዎች ያሰዩናል። (State-sponsored capitalism or the East Asian model is an economic system where the government invests in certain sectors of the economy in order to stimulate the growth of new (or specific) industries in the private sector. It generally refers to the model of development pursued in East Asian economies like SingaporeJapanTaiwan and South Korea. (An East Asian Model of Economic Development: Japan, Taiwan and South Korea, by Paul W. Kuznets. April 1988. Economic Development and Cultural Change, Vol. 36, No. 3, April 1988.) In recent decades it has also been used to classify the contemporary economic system in the People's Republic of China. ( Does China follow the 'East Asian Development Model'?, by Seung-Wook Baek. 2005. Journal of Contemporary Asia, Vol. 35, No. 4, 2005.)

የልማታዊ ዲሞክራቲ ርዮት በግራውም ሆነ በቀኙ የፖሊቲካ አቀንቃኞች ሂስ እደቀረበበት በጥናቶች ቢታወቁም ጽንሰሀሳቡ ግን የአዲሱን የእጅ አዙር ቅኝ ገዥ ተስፋፋ (ideology of neocolonialism) እርአይ ለማስፈጸም እደሆነ፤ ርዮቱም  አውሮፓን አንጋሽ በሆነ እይታ ላይ መሰረትን ያደረገ (Western dominance over such underdeveloped nations, in a neocolonialist fashion) የምዕራቡን አገራት በአገራዊ የልማት ስም ሸፋፍነው የፈጠሩት በልማት ወደሗላ በቀሩት የአፍሪካ የአዚያና የላቲን አሜሪካ አገራት አገራዊ ልማት ላይ ተጽእኖ ፈጣሪ መሆኑን አነዳነድ ለሂቃናት "disaster capitalism.” Disaster capitalism አደጋ ፈጣሪ ያጋብሶ አደር ስነስርአት በሚል ቃልም እደሚገልጹት፤ በቀኝም አመለካከታቸው የሚታወቁት የሙያው ልሂቃናት፤ ያዲሱ የእጅ አዙር ቅኝ ገዥ ተስፋፊ ስነስርአት ቀጥሮ ያሰቀመጧቸው፤ እደፍላጎታቸው የሚያዞራቸው አንባ ገነኖች የነጻ ገብያን ስነስርአትን ያዳክማሉ፤ የሚልም ሲሆን በቀኙ ፖለቲካም ጠርዝ አመለካከት የተመረዙ ለሂቃናትም የአውሮፓን አንጋሽ ስነስርአትን ሸርሻሪ ነው በሚል... እደሚተቹ ጥናቶች የመለክታሉ[11]-[15]                                                                                                                                                                                                     ይቀጥላል
                                                                                                            ነፃነት ፈረደ

Thursday, August 7, 2014

Obama Gets “Into” Africa: An Ugly Scramble for Oil, Minerals, and Markets

Unfortunately US policy towards Africa have largely translated into holding the door open for U.S. multinationals to do what outsiders have done for centuries: extract the continent’s wealth.


President Obama is definitely “into” Africa. As much as possible in a world riven by multiple crises, the president has made the continent a focus of his policymaking. Turning his own Kenyan heritage into a personal bridge to the region, he has visited Africa three times as president – in 2009, 2011, and 2013. He has touted his administration’s multi-billion initiatives such as Power Africa to bring electricity to millions of homes, a fellowship program for young African leaders, and the continuation of efforts to fight HIV-AIDS and other infectious diseases.

At a time when criticism is mounting about the way the president is handling the rest of the world, Africa is shaping up to be Obama’s major play for a legacy.

This week, to better position this effort, Obama welcomed delegations from 51 African countries to Washington for an unprecedented summit. As part of its press blitz, the White House released a fact sheet that detailed all the State Department’s high-profile programs including support for democracy in Nigeria, an expansion of civil society activity in Liberia, and an open government initiative in Sierra Leone. Many of these initiatives are indeed admirable, and I can imagine State Department staffers grumbling that the media focus on Ebola and Boko Haram has left no space for these more upbeat stories.

But don’t be fooled by all the talk of Obama’s special relationship with the continent or all the snazzy new entrepreneurial initiatives or the commitment to democracy reflected in his statement in Ghana a few years ago that “Africa doesn’t need strongmen, it needs strong institutions.” Most of U.S. policy toward Africa, alas, is business as usual. Yes, the President is “into Africa.” But more often that has translate into facilitating the entry of U.S. businesses into Africa so that they can do what outsiders have done for centuries: extract the continent’s wealth.

Strip away all the modern PR and prettified palaver and it’s an ugly scramble for oil, minerals, and markets for U.S. goods. Everyone wants a piece of Africa: drooling outsiders, corrupt insiders, cynical middle men. “We kind of gave Africa to the Europeans first and to the Chinese later, but today it’s wide open for us,” General Electric chief executive Jeffrey Immelt said at the summit, inadvertently providing a compact definition of neo-colonialism. And for all the talk of good governance and transparency, the political status quo of “guided democracy” with a sprinkling of genuine dictators provides the presumed stability and secure access to resources that the U.S. government, the Pentagon’s Africa Command, and businesses like General Electric value.

First, let’s dispense with the nonsense that China is the only country that behaves with no scruples when siphoning everything of value from Africa. The State Department’s Johnnie Carson provided an unvarnished U.S. perspective in a Wikileaks cable: “China is a very aggressive and pernicious economic competitor with no morals.” Well, It’s true that China has developed a reputation for dealing with dictators like Robert Mugabe in Zimbabwe, failing to hire local workers or purchasing local materials, and engaging in horrendous labor rights abuses in the mines it runs.

But China’s relationship is evolving. It is Africa’s leading trade partner, and a million Chinese are living in Africa. “A growing number of Africans say the Chinese create jobs, transfer skills and spend money in local economies,” writes the rarely China-friendlyEconomist. “African democracy has so far not been damaged. China turns a blind eye to human-rights abuses, but it has not undermined democratic institutions or conventions.”
The United States, meanwhile, presents itself as Africa’s ethical friend. It likes to point to the Dodd-Frank Act to prove that U.S. businesses are scrubbing their supply chains of unethical purchasing. The Act requires companies to disclose their payments to governments and contains specific provisions requiring producers to make sure that they’re not buying “conflict minerals” from armed groups in Congo.

But the first requirement hasn’t been implemented, and the second provision has produced decidedly mixed results. “The first round of conflict mineral investigations was due June 2, but only 6 percent of audited companies satisfied adequate compliance standards,” reports one watchdog organization. “Worst of all, of the nearly 1,000 enterprises that submitted reports pertaining to conflict minerals, 94 percent failed to validate their suppliers’ sourcing tactics.”
Dodd-Frank, in any case, affects only a small fraction of U.S. business dealings with Africa. Let’s look at the larger category of foreign direct investment (FDI). For all the high-minded talk, the United States and China have exactly the same record when it comes to FDI and governance. Both receive a score of -.1 in a Brookings index that puts Japan on top in terms of directing FDI toward more accountable governments (.5) and France at the bottom (-.3) for basically not giving a merde. In other words, both the United States and China basically go where the return on investments is most promising, regardless of political environment.

Then there’s the question of arms sales. No doubt China’s deliveries to Sudan and Zimbabwe are unacceptable, and its sales of small arms definitely fuel conflicts in the region. But according to a Norwegian study of the period 1989 and 2008, the United States provided more military assistance in dollar value to dictators in Africa than China did. In the last few years, the United States has made sales to the following unsavory governments in Africa: Algeria, Cameroon, Chad, Egypt, Equatorial Guinea, Niger, and Nigeria.

Since 2001, writes Nick Turse this week in China, America, and the New Cold War in Africa, “the United States has steadily increased its military footprint, its troop levels, and its missions on the continent — from night raids in Somalia and kidnap operations in Libya to the construction of a string of bases devoted to surveillance activities across the northern tier of Africa.” The State Department alone devoted $15 billion to security operations in Africa from 2005 to 2012, while the Pentagon has lavished a larger but unknown sum on its counter-terrorism operations in Mali, Niger, Nigeria, and elsewhere. The results have been less than inspiring: coups, collapsed states, and burgeoning terrorist organizations. China, meanwhile, has built roads, made friends on all sides of conflicts, and positioned itself for the long game.

The Obama administration wants us to understand that, like China, it is transforming relations with Africa. “We do believe we bring something unique to the table,” national security advisor Ben Rhodes said last week. “We are less focused on resources from Africa and more focused on deepening trade and investment relationships.”

That sounds nice. But it’s not actually true. The leading trade partner for the United States in Africa is Nigeria, and the leading U.S. import is oil. In 2013, the United States imported from Africa $26.3 billion in crude oil, $3.2 billion in precious stones, and nearly $1 billion in ores like titanium. That represents 77 percent of all imports. The remainder is largely raw materials such as cocoa beans, rubber, and unroasted coffee beans.

Of course, trade is a two-way relationship. As the U.S. Trade Representative Michael Froman said at the summit, “The United States has benefitted from AGOA [the Africa Growth and Opportunity Act] as well, not just from the stability that comes with increased global prosperity, but also from the market opportunities that accompany Africa’s rise. Since 2000, U.S. exports to sub-Saharan Africa have increased fourfold, from $6 billion to $24 billion. Last year, these exports helped support nearly 120,000 American jobs.” In an ideal world what’s good for Africa is also good for America. But too often, these economic deals preserve the same old inequitable relationship.
Consider the new agricultural initiatives. At the summit, the United States announced billions of dollars more in agricultural assistance to Africa. Although some of the funds will go to support local farmers growing food for domestic consumption, like sorghum, most of the money comes in the form of pledges by corporations like Coca Cola to source from Africa. Farmers make up two-thirds of the workforce in Africa. The challenge is to make their farming more sustainable. Tying farmers into volatile market relationships with immense multinationals is a spin of the roulette wheel, not a sure way of lifting Africa out of its dependency on the outside world.

Because of its “resource curse,” Africa’s oil and minerals and coffee beans have profited a narrow elite that has served as the middlemen to outsiders. This curse has undermined democracy and embedded corruption into the very circulatory system of the continent. If we were really “into Africa,” we would work to ensure that these resources benefit the largest number of Africans possible.

Some of what the Obama administration has done points in the right direction. But it is overwhelmed by the more powerful plays of the Pentagon and the multinationals. The president should be reining in these powerful players rather than opening the door wider for them to get into Africa. Only if this happens can the resource curse become a resource blessing. It’s the rare country like Norway that has accomplished this feat. But if Obama can help make this happen for Africa, his legacy would indeed be secure.



by John Feffer

Thursday, July 31, 2014

" ስንቅህን በአህያ ፤ ምሥጢርህን በጉያ "

ኢትዮጵያ ነጻ ሀገር ሆና የራሷን መንግሥት በመመስረት ከታወቀችበት ዘመን አንስቶ፤ መሪዎቿ በቀናዒነት ሀገሪቱን ከውጭ ወራሪ ኃይሎች ሲከላከሏት ቆይተዋል። በየዘመናቱ ወረራው ቢመጣባትም፤ ሁሉንም ከሕዝቡ ጋር በመሆን እየተዋጉ መልሰውታል። የዚህም ዋና አብነት፤ መሪዎችና ዜጎች መተባበራቸው ነበር። በገዥዎቹና በመሪዎቹ መካከል የነበረው ግንኝነት ፍጹም ዕጹብ- ደንቅ ነበር ማለት ባይቻልም፤ በሀገር ነጻነትና ሉዋላዊነት ረገድ ግን፤ ነፋስ የማይገባበት ውኅድትና ትብብር ነበረ ማለት ያስደፍራል። የጋራ ሀገራቸውን ለማዳን ኃይላቸውን አስተባብረው መቆም አማራጭ እንደ ሌለው አበክረው አውቀውና ተረድተውት ነበር ማለትም ያስችላል። የሕዝብና የመሪዎች በአንድ መንፈስ መቆም ደግሞ፤ ሀገሪቱ ከቅኝ ገዥዎች ወረራ እራሷን ተከላክላ እንድትቆይ አስችሏታል።

የውጭ ወራሪዎች ከተባረሩ በኋላ ግን ገዥዎች ሕዝቡን እየጨቆኑ መግዛታቸውን ይቀጥሉበታል። ሕዝቡም የመከራ ቀንበሩን እንደተሸከመ መራራ ኑሮውን ይገፋል። ለሀገር መሥዋዕት ለመቆም፤ በቤተ መንግሥት ውስጥ ጮማ እየቆረጠ ጠጅ እያንቆረቆረ በሚቀማጠለው ልዑልና የእለት ጉርሱ የዓመት ልብሱ ባረረበት ገበሬ መካከል፤ ብዙም ልዩነት ባየካሰትም የመሥዋዕቱ ክብደት የሚመዝነው ግን በአርሶ-አደሩና በተራው ሕዝብ ህይወት ላይ ነበር ማለት ይቻላል።

ኢትዮጵያ በዘመናት ነጻ ሀገር ሆና እንድትኖር ካበቋት ዐበይትና መሠርታዊ ነገሮች አንዱ፤ ዜጎቿ የሀገራቸውን የውስጥ ምሥጢር መጠበቃቸው ዋናው አብነት ነበር። " ምሥጢርክን በጉያ ስንቅህን በአህያ ! " የሚለው ግንዛቤ፤ የዚያን ጊዜ ነዋሪዎች፤ሀገራዊ ባኅልና ጠበይ ነበር። የሀገርን መሥጢርና የውስጥ ገመና እንኳንስ ለውጭ ጠላት አሳልፎ መስጠት ቀርቶ፤ እርስ በእርሱም ቢሆን በአደባባይ አውጥቶ መውያየት ብልኅነት አልነበረም። ጸያፍና እንደ ነውረኝነትም ያስቆጥር ስለነበር፤ ሁሉም ዜጋ የየራሱን ክብርና ስበዕና ለመጠበቅ ሲልም ጭምር፤ በአደባባይ ላለመዝረክረክ ብርቱ ጥንቅቄ ያደርጋል። ይህ ብሄራዊ / ኢትዮጵያዊ ባኅርይና ሥነሥርዓት፤ ለባዕዳን ወራሪዎችና ለሌሎቹም የሀገሪቱ ባላንጣዎች እንዲሁም፤ በጠቅላላው፤ የኢትዮጵያን ውስጠ- ምሥጢር ለማወቅ ሲያፈነፍኑ ለነበሩ ሁሉ አስችጋሪ ሆኖ ቆይቷል። የሀገርን ውስጠ- ምሥጢር መጠበቅ፤ የውጭ ጠላት ሰርስሮ እንዳይገባ ለመከላከል የሚያስችል ፍቱን መድህኒት ሆኖ ቆይቷል። የዛሬውን አያደርገውና !

አርበኛው በዝቶ፤ ሀገር ወዳድ ሞልቶ- ተርፎ በነበረበት በዚያን ታሪካዊና አስደናቂ ዘመን፤ የሀገር ውስጠ- ምሥጢር ተጠብቆ ቆይቷል። ያም ሲባል፤ ቁጥራቸው ግምት ውስጥ የማይገባ ጥቂት ከሃዲያንና ለሆዳቸው ብቻ ያደሩ ሰዎች እንደነበሩ ደግሞ መዘንጋት አይገባም። የዚህ ክስተት መኖሩ ደግሞ አያስደንቅም። ለምን ቢባል ? በማንኛውም ኅብረተ ስብ ውስጥ "በያንዳንዱ 12 ሐዋርያት ውስጥ፤ አንዳንድ ይሁዳ ስለማይጠፋ" ነው። እጅግ የሚያስደንቀው ግን፤ በአሁኑ በወያኔ ዘመን፤ የከሃዲያንና የሀገር ሻጩ ቁጥር እየበረከተ መምጣቱ ነው። ታዲያ " እያንዳንዱ ኅብረተሰብ የሚገባውን መንግሥት ያገኛል" የሚለውን ስላቅ ሙሉ ለሙሉ ለመቀበል ባይቻልም፤ ለአላፊ- ጠፊ ጥቅም ሲባል፤ ከሃዲውን ወያኔን የሚደግፉ ውህዳን ግብረ- ይሁዳ መብቅላቸው፤ ለስላቁ ማጠየቂያና መደላድል መሆናቸው ይበልጡኑ ያስገርመናል።

የአንድነት ኃይሉ፤ ከነኝህ አይነቶቹ ምሥጢር ዘክዛኪዎችና ጥብቋቸውን በየጊዜው ከሚለዋውጡ ክፍሎች ራሱን ካላጸዳ፤ ዉጤት ያስመዘግባል ተብሎ መጠበቅ፤ የኅልም እንጀራ ነው። በተለይም ደግሞ፤ ለመጣው መንግሥት ሁሉ ታማኝ አገልጋይ ለመሆን የሚገለባበጠው ሁሉ፤ ሀገርን ለማዳን በሚደረግው ትግል ውስጥ ዕምነት ሊጣልበት የሚገባ ሆኖ አልተገኘም። " ምሥጢር የባቄላ ወፍጮ አይደለም " እንዲሉ፤ ለወሬ ማጣፈጫ እንዲጠቅም ታስቦና ሁሉን ያውቃል እባላለሁ ከሚል ከንቱ ውዳሴ በመነሳት ብቻ መነኛውንም ነገር እንደ ቀዳዳ ስልቻ ማዝረክረክ የሚጠቅመው፤ የወያኔን ሥርዓት እንጅ ለማንም አይረዳም። በሀገርና በሕዝብ ላይ ከባድ ጥፋት ከፈጸሙ በኋላ፤ የንሰሀ ጸጸት ቢያደርጉ፤ የጠፋችው ሀገር ልትመለስ አትችልም። ይሁዳ፤ በክኅደቱ ተጸጽቶ ራሱን በዛፍ ላይ ቢሰቅልም ቅሉ፤ ጌታውን ክርስቶስን፤ ከሮማውያን ስቅላት ሊያድነው አልተቻለውም። " ልመና ሳሉ በቁመና ! " በመሆኑ፤ ኢትዮጵያን ከዘረኞች ጥፋት ማዳን የሚቻለው፤ ቀኑ ሳይመሽ ዛሬ ሁሉም በቁሙ ተባብሮ በመቆም መሆኑን፤ ልቡ በክኅደት ያልተሰለበ ዜጋ ሁሉ ያምንበታል

የወያኔ አገዛዝ፤ እንኳንስ ከወዶ- ገባዎች በነጻ የሚጎርፍለትን ኢንፎርሜሽን አግኝቶ ይቅርና፤ እንዲያውም በተጠናከረውና በሰላው የመረጃ መዋቅሩና አሰራሩ ጠላቶቹን እያጠቃ፤ ደጋፊዎቹን እያነቃ የሚርበተበት ዘረኛ ደርጅት ነው። የመረጃ ተቋሙን ለማደራጀት የቻለው ደግሞ፤ በራሱ ክኅሎትና ብቃት፤ ችሎታና ጭንቅላት እንዳልሆነ የሚያውቅ ያውቀዋል። የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም፤ ለባዕዳን አለቆቹ አሳልፎ የሰጠ በመሆኑ፤ የራሳቸውን ጥቅም እንዲጠብቅላቸው ሲሉ፤ ባዕዳን ኃይሎች፤ በሥልጣኑ እንዲቆይ የሚያስችለውን ነገር ሁሉ በመፈጸም ላይ ናቸው።

ባዕዳን አለቆቹ ከሚረዱት ሁሉ ዓይነተኛው ጉዳይ ደግሞ፤ የኢንተሊጀንስ ወይም የስለላ ተቋማቱን በሁለንተናዊ ረገድ ማደራጀት ነው፡፡ የስለላ ተቋማቱን ከማደራጀት አልፈው ተርፈው፤ በሥልጣና፤ በስለላ መሳሪያዎች ግንባታ፤ በኤሌክትሮኒክስ ሳይንስና አሰራር ደረጃ ይተባበሩታል። ከራሳቸው የኢንተለጀንስ ወይም ስለላ ድርጅቶች ጋርም ያስተባብሩለታል። ተቃዋሚ ድርጅቶችንና ግለሰቦችንም እየተከታተሉ ይይዙለታል። ፡የተቃዋሚዎቹንም እንቅስቃሴ ሁሉ የጠልፉለታል። የስለላ መርቦችንም በመዘርጋት፤በሁሉም የኢትዮጵያ ኅብረተስብ ውስጥ ሰርስረው እንዲገቡ አድርገውለታል። ሰላዮችንም በሙያው የተራቀቀ ችሎታ እንዲያገኙ ያሰለጥኑለታል። ኢትዮጵያን በማጥፋት ላይ የሚገኘው ወያኔ፤ ኢንተለጀንስን/ ስለላን አስመልከቶ ከባዕዳን የሚያገኘው ርዳታና ትብብር፤ የሚያስርገም ሆኗል።

የተቃዋሚ ድርጅቶች አለመተባበርና ያሰራራቸው ዝርክርክነት ተጨምሮ፤ ለወያኔ የስለላ ሰራተኞች ሰርስሮ ለመግባት አመች ሆኔታን አመቻችቶላቸዋል። የሚያስገርመው ደግሞ፤ ይህንን የስለላ ጥቃት አሁንም ቢሆን፤ ተቃዋሚ ነኝ የሚለው ክፍል ሁሉ፤ የቱን ያህል እንደተገነዘበውና ምንስ ያህል ጥንቃቄ እንደሚያደርግ በእርግጠኝነት ማወቅ አለመቻሉ ነው። ሰኔና ሰኞ የተገጣጠመለት ወያኔ ግን ሁኔታዎቹን ሁሉ ለመጠቀም እንቅፋት አላጋጠመውም።

ሁኔታዎቹ ሁሉ አሁን ባሉበት ደረጃ ይቀጥላሉ ማለት ግን አይደለም በዕርግጥም ይቀየራሉ ሁኔታዎቹን የሚቀይራቸው ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ የተባበረ ትግል እንደሚሆን ደረትን ነፍቶ መናገር ይቻላል። የወያኔ የበላይ ጠባቂዎቹ ሁሉ፤ የማይበገረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል መፋፋሙን ሲገነዘቡ፤ ወያኔን አጋልጠው እንደ ነጋበት ጅብ እንደሚፈረጥጡ፤ በሌሎች ሀገሮች ተደጋግሞ የታየ ሀቅ ነው።


ለዚህም፤ የሶቪየት ኅብረትንና ደርግን፤ የግብጹን ሆስኒ ሙባረክና አሜሬካንን፤ የኢራኑን ሻህ ባሃላቢንና አሜሪካንን እንደ ታሪክ ማስረጃ ጠቅሶ ማለፍ ይቻላል። ባዕዳኑ፤ ዘለዓለማዊ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ ደግሞ፤ ከሚመጣው አዲስ አገዛዝ ጋር ሰልፋችውን እንደሚያስተካክሉ ልንጠራጠር አንችልም። ዋናው ጥያቄ ግን፤ እረ ለመሆኑ፤ የኢትዮጵያን ዘላቂ ጥቅም የሚያስጠብቅላት ማን ሊሆን ይችላል ? የሚለው ነው። ይህንን ጥያቄ መመለስ የሚገባው፤ ማንኛውም የሀገሪቱ ዜጋ መሆን እንዳለበት እናምናለን የራስን ሀገር ጥቅም ለውጭ ባዕዳን አሳልፎ የሚሰጥ ቡድን፤ ኢትዮጵያ በታሪኳ ሲገጥማት ይኽ የአሁኑ የከፋ ሆኗል። እንደ እግር እሳት የሚያንገበግበው ግን፤ ሁሉ መሥዋዕት ተከፍሎ፤ ዛሬ ሀገራችን በአስከፊ ሁኔታ ሆና ማየቱ ነው።

ይህ ሀቅ እንዳለ ሆኖ እነኝህ የውጭ ኃይሎች፤ ከወያኔ ጋር እየተባበሩ፤ ይኽንን ተግባር የሚያከናውኑት፤ ሆን ብለው አስበውበት የኢትዮጵያን ሕዝብ ለመጎዳት ሲሉ ብቻ ነው ብሎ ለማለት ባያስደፍርም፤ ዛሬ ወያኔን የሚደግፉትና የድርጊቱም አባሪ-ተባባሪ ለመሆን የወሰኑት ግን የራሳቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ መሆኑ ደግሞ የሚካድ አይደለም።

ዘላቂ ጥቅማቸውን የሚያስጠብቅላቸውን ሁሉ በዘላቂ ወዳጅነት ደረጃ ያስተናግዳሉ ባይባልም፤ ወያኔን ግን በጊዚያዊ አገልጋይነቱ ይጠቀሙበታል እንጅ፤ አለቅነታቸውንና ሽርክናቸውን እስከ ዘለቄታው ድረስ እንደማይዘልቁበት እናውቃለን። ይህንን ለማለት የሚያስችለውም፤ " ዘላቂ ጥቅም እንጅ፤ ዘላቂ ወዳጅም ይሁን ዘላቂ ጠላት ብሎ ነገር የለም " የሚለውን የምዕራባውያን የዲፕሎማቲክ ይትብሃል ስለምንገነዘብ ነው። ያም እንዳለ ሆኖ፤ ወያኔ፤ ታማኝነቱን እያረጋገጠ ታዛዥነቱን እስከቀጠለላቸው ድረስ፤ የበላይ ጠባቂዎቹ ሆነው እንደሚሰነብቱ መዘንጋት አይገባም። በወያኔና በባዕዳን ኃይሎች መካከል ያለው ግንኙነት የአለቃና ጭፍራ ቁርኝነት ነው ጌቶቹ ሲጠሩትና ሲያዝዙት፤ አቤት- ወዴት ብሎ ያሉትን መቀበል ነው። ይህ ባኅርይ ደግሞ ለማንኛውም ሀገር-ወዳድ ኢትዮጵያዊ የሚዋጥለት አይሆንም። ለዚህም እኮ ነው፤ ሀገር ወዳድ መሪዎች በባዕዳን ኃይሎች የማይወደዱት።

በኢትዮጵያ፤ ሀገር ወዳዶ መሪዎች እስካልበቀሉ ደርስ ደግሞ፤ ሀገራችን ያልፍላታል ተብሎ የሚታሰብ አይሆንም።

ይህንን ሀቅ የተገነዘበ ዜጋ ሁሉ፤ ሀገር ወዳድ ዜጎችን እያበቀለ ማፍራትን አበክሮ ሊያስብበት ይገባል። በዚህ ረገድ ተስፋ የሚደረገውም በየዘመናቱ፤ ኢትዮጵያ ሀገራችን ዕውነተኞቹ ሀገር ወዳዶች የሚፈልቁባት ሀገር በመሆኗ ነው።

እነርሱ ደግሞ፤ ወደ መድረኩና ወደ ፖለቲካው ምኅዳር ሊመጡ የሚችሉት፤ እንደ "ዲዮጋን፤ በጠራራ ፀሀይ በፋኑስ ተፈልገው" ሳይሆን፤ እያንዳንዳቸው፤ ምግባራቸውንና ተግባራቸውን የሞራል ልዕልናቸውንና ታማኝነታቸውን በድርጊት ያስመሰከሩ እንዲሆኑ ይጠበቅባቸዋል እነኝህ ደግሞ ወላዲቷ ኢትዮጵያ በድባብ ትሂድ እንጅ ሞልተው ተርፈዋል ብለን ማመን እንፈልጋለን። ባንጻሩ ግን፤ ሰው ያላወጣ ትውልድ፤ " የሰው ያለህ!" እያለ በመጮሁ ብቻ ሰው ሊወጣለት የማይችል መሆኑን መገንዘብ ይገባል። አርበኛንና ሀገር ወዳድ ዜጎችን እያጠፉ አዲስ አርበኛን ማግኘት ያስቸግራል ምክንያቱም፤ እስካሁን እንደታየው ከሆነ፤ " የፊት ወዳጅህን ከፍነው በሻሽ፤ የኋለኛው እንዳይሸሽ !" ብለው እያዘኑ ያለፉትን ታላላቅ አርበኞች ታሪክ እየሰማን በማደጋችን ነው።

አርበኞች እየበቀሉ በመሰዋት፤ የነርሱን ፈለግ የሚከተል ትውልድ እያፈሩ ካለፉ፤ የነርሱ መሥዋዕትነት ከንቱ ሆኖ አይቀርም። የመሥዋዕቶቹና የሰማዕታቱ ገድል ዉጤት አስመዝግቧል ለማለት የሚቻለውም፤ ተተኪው ትውልድ  የነርሱን ዓርማ በማንሳት ሀገሩን ከጥፋት ለማዳን ሲችል ነው። ለዚህ ውጤት ዓብነት ከሚሆኑት መካከል ዋነኛው የራስን ምሥጢር እየጠበቁ የጠላት ሰላዮችን እየተከላከሉ ማምከን ወይም ከጥቅም ውጪ ማድረግ ይሆናል። ምሥጢርህን በጉያህ ይባላል እንጅ አዝረክርክው አልተባለም! በማንም ቀለምና ካባ የሚመጣ አምባገነን ለሥልጣኑ መሠረት አድርጎ የሚጠቀምባቸውና ሕዝብንም ለመጨቆን የሚገለገልባቸው ልዩ ልዩ የመጨቆኛ ማሳሪያዎች ይኖሩታል። በሕዝብ የተጠላ በመሆኑም፤ የሕዝብን ተቃዉሞ ይፈራል። ሥልጣኑን እየጠበቀ ዕድሜዉን ለማራዘም የመጨቆኛ መሳሪያዎቹን አዘጋጅቶ ማጠናከር የቅድሚያ አጀንዳው ወይም ተልኮው ይሆናል። የሕዝብ አመፅ በማንኛውም ወቅትና ሁኔታ ይነሳብኛል ብሎ ስለሚሰጋ፤አመፁን ለማዳፈን ማንኛውንም የኃይል ርምጃ ከመውሰድ አይቆጠብም። ይህን ለማሳካት ሲልም፤ እራሱ ያወጣውንም ህግ ቢሆን እንኳ ከመጣስ ወደ ኋላ አይልም።

ዛሬ በኢትዮጵያ የተዘረጋው ዘረኛ ሥርዓት አራማጆች የሚፈፅሙትም ይህንኑ ነው። ለኅልውናቸው አስጊ የመሰላቸውን ሁሉ ለማጥፋት የዓለም አቅፍ ህጎችን ሁሉ በመጣስ ድንበር -ዘለል ውንብድናን ሳይቀር ያካሂዳሉ።

የስለላ ተቋሞቻቸውን የሚቆጣጠሩት ከራሳቸው ብሄር የተውጣጡ አባሎች ናቸው። ዛሬ፤ በኢትዮጵያ የመንግሥት ታሪክ ተወዳዳሪ የማይገኝለትን ጸረ ሕዝብ የኢንተለጀንስ ተቋምና የስለላ ድርጅቶችን የገነባው ወያኔ ሆኗል። ለዐብነት የሚከተሉትን የኢንተለጀንስ አገልግሎት ልዩ ልዩ ተቋማትን እንመልከት

1.   በሕዝብ ደኅንነት ስም የተዋቀረው የወያኔ መረጃና ስለላ ድርጅት፤

2.   በናዚ ጀርመን ጌስታፖ አምሳያ የተደራጀው የፖሊስ /አጋዚ፤ፊዲራል...// ድርጅት
3.   ወያኔ የጻፋቸውን የመጨቆኛና የመቅጫ ህጎችን እየተረጎሙ የሚበይኑ "ዳኛች" የወያኔ ጠበቆችና "አቃቢ- ህጎች"
4.   ለምርመራና ማሰቃያ የተሰናዱ ዘመናዊ መሳሪያዎችና የስቃይ እስር ቢቶች......
  1. የሕዝብን አመፅ ለመቋቋምና ለማፈን ሲባል የሠለጠነ፤ የተደራጀና የታጠቀ ሠራዊትና ልዩ ምሥጢራዊ አፋኝ ቡድኖች፤
  2. ፕሮፓጋንዳቸውን የሚያዘንቡበት መገናኛ ብዙሃንና የኅትመት አገልግሎቶችን የሚጠቀሙባቸው ተቋማት ሁሉ፤
  3. ኤሌክትሮኒክስ ሰርቬላንስ ወይም ክትትል-ጠለፋ (የስልክ፤ የኮምፒውተር፤ የሴል ፎን መገናኛንና ራዲዮ ጠለፋ፤ ወዘተ.)
  4. በኅብረትስቡ ውስጥ ተሰግስጎ በመግባትና በብዛት ሰርስረው በስውር የተቀመጡ ሰላዮችና ወሬ አቀባዮች፤ ለነኝህ ሁሉ ማንቀሳቀሻ የሚሆነው ገንዘብ፤ ምን ያህል እንደሚሆን ትክክለኛውን አሃዝ በዕርግጠኝነት ቀርቶ በግምት እንኳን ቢሆን ለመናገር የሚችል አይኖርም። ምክንያቱም፤ ባጃቱ ወይም ወጪው በብርቱ ምሥጢር ስለሚያዝ ነው።

ያም ሆኖ፤ በበርካታ መቶዎች ሚሊዮን ብር እንደሚሆን፤ የምሁር ግምቶች አሉ። ይህ ሁሉ የሀገር ሀብት የሚፈሰው ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ታጥቆ ለተነሳ ዘረኛ ሥርዓት መጠበቂያ መሆኑ ታሪክ በሀገራችን ላይ በሚያሳየው ምፀት ላይ እንገረማለን።

ይህንን ሁኔታ ባጭሩ ለመገንዘብ ከቻልን፤ ምን መደረግ አለበት ? በሚለው ላይ ትኩረት ሊደረግበት ይገባል እንላለን። በበኩላችን የሚከተሉት ነጥቦች ቅድሚያና ትኩረት እንዲያገኙ ለሕዝብ እናሳስባለን። ለተቃዋሚ ኃይላትም ጥሪ እናስተላልፋለን

1.    የወያኔን የስለላ መረቦችን ለመከታተልና ለመበጣጠስ፦

. በመሀከላችን ሰርስረውና አድፍጠው የሚገኙትን ሰላዮቹ ማጋለጥና መንጥሮ ማውጣት፤
. በሁሉም የኅበረተስብ ውስጥ በተለያዩ ሽፋኖች ተመድበው የመረጃ ሥራ የሚሰሩትን ጠንቅቆ ማውቅና መለየት፤ እነኝህ ግለሰቦች ከየትኛውም ጎሳና ሙያ የተውጣጡ እንደሚሆኑ መረዳትና፤ ወያኔንን ከልብ ሊደግፉ ባይችሉም፤ ለጥቅም ብቻ ሲሉ ሀገርን ለመጉዳት እንደሚችሉ አለመዝንጋት፤

2.   የተቃዋሚ ክፍሎች ከወያኔ ሰላዮች ነጻ ያልሆኑ መሆናቸውን አውቀው አስፈላጊዉን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል። የጓዳ ምሥጢር የሚያቀብሉ ውስጥ- አዋቂዎች የሚያስከትሉት ከባድ ጉዳት መሆኑን መረዳት እንዝኅላል ከመሆንያድናል።

3.   ከወያኔ ጉዳትና ጥቃት፤ የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ወይም የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪ ወይም የሃይማኖት ተቋማት ወዘተርፈ ይጮሁልናል ብሎ ማሰብ ከንቱ ምኞት መሆኑን ተረድቶ ራስን ጠብቆና በራስ ኃይል ብቻ ተማምኖ መታገልና ሀገሪቱን ከጥፋት ማዳን። ሰሞኑን ወያኔ፤ በአንድ ስደተኛ ታጋይ ላይ የወሰደውን ድንበር -ዘለል ውንብድና ያጢኗል።

4.   የሕዝብን የተባበረ የአመፅ ትግል የትኛውም የስለላና ድርጅትና የመረጃ ስምሪት እንደማያቆም መረዳት ይገባል።

ይህንን ሀቅ አውቆ ተባብሮ መታገልና ሀገርንም ከጥፋት ማዳን አማራጭ የለውም! አሁን በሚታየው ዝርክርክነት፤ ሀገሪቱን ማዳን ይቅርና፤ ራስንም መከላከል አልተቻለም። ይህ ጥቃትና ጉዳት በየአንዳንዱ ቤት እያንኳኳ መምጣቱን የስሞኑ ድርጊት ተጨማሪ የማስጠንቀቂያ ደወል ሆኗል

" ያልጠረጠረ ተመነጠረ " ነውና፤ ሰላዮችን እየጠረጠሩ፤
ጠላትን እየመነጠሩ መታገል ለድል ያበቃል !


 ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኖራለች !