ከአፈወርቅ ዘብሄረ ዘጌ በ 1906 ዓ.ም
በሮማ ከተማ ከታተመ
„ዳግማዊ አጤ ሚኒሌክ “ መፅሀፍ የተወሰደ
አፈውርቅ ይህን የዳግማዊ አጤ ሚኒሊክን የምክር አዋጂ ያገኙት መፅሃፋቸዉን ከመጨ ረሳቸዉ በፊት ከእንድ ጃንሆይንና ኢትዮጵያን ከሚውድ ወዳጃቸዉ እንደሆነ ይገልጡና
“ኢትዮጵያን የወደደ የኢትዮጵያን መልማት የኢትዮጵያን ደስታ የኢትዮጵያን ትልቅነት የወደደደ ሰዉ ይሄን የጃንሆይን ቃል አዝኖ ተክዞ መቀበል ይገባዋል እዝኖ ተክዞ ማለቴ እንዲህ ያለ እናት ንጉስ የሞቱን ነገር አስቦ ለኢትዮጵያ የሚበጀዉን አዉቆ እንዱህ ያለ የተገባ የጣፈጠ ከልብ ጠልቆ የሚገባ ምክር ለህዝቡ መስጠቱ ተሞቱም በሁዋላ ለኢትዮጵያ የሚሆነዉን ላገር የሚጠቅመውን ለህዝቡ የሚያከብረዉን ነገር ማሰቡና መምከሩ እጅግ ያሳዝናል ማለቴ ነዉ”
ይሉና ሙሉውን የጃንሆይን መልእክት እንዲህ አስቀምጠዉታል::
የጃንሆይ የዳግማዊ ሚኒሊክ ቃል::
በ1906 ዓመተ ምህረት ግንቦት 10 ቀን አዲስ አበባ ጃን ሜዲ ከሚባል ሥፍራ ጉባኤ ተደርጎ ዲግማዊ ምኒሊክ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ያዘዙት ቃል ይህ ነዉ::
ያገሬ የኢትዮጵያ ሰዎች ልጆች ወዳጆች እግዚአብሔር የገለፀልኝን ምክር
ልምከራችሁ ምክሬንም እግዚአብሔር በልባችሁ እንዲያሳድርባችሁ ተስፋ አደርጋለሁ::
አፄ ቴወዴሮስ የሞቱ ጊዜ ከሳቸዉ ጋር የነበርው ሰዉ ሁለ ያንዱን አገር አንዱ
እደርባለሁ አንዱን ገድዬ እኔ ጌታ እሆናለሁ እያለ ሁለም ላይረባ ተላል ቀረ::
ከዚህም በኁዋላ ያፄ ዮሃንስ ሰዉ የሆነዉን የምታዉቁት ነዉ ባገር በሽታ ሳይገባበት ሌላ የባእድ ጦር ሳይነሳበት በምቀኝነት እርስ በርሱ አንደተላለቀ አይታችሁታል::
አሁንም ልጆቸ ወዳጆቸ አንዱ ባንዱ ምቀኝነት ይቅር ያንዱን አገር አንዱ እኔ እደርባለሁ
እንዳትባባሉ እኔ እስካሁን በፍቅር እንዳኖርኩዋችሁ እናንተም ተስማምታችሁ በፍቅር
እንዴትኖሩ እለምናችኁዋለሁ::
እናንተ አንድ ልብ ከሆናችሁ በምቀኝነት እርስ በርስ ተዋግታችሁ ካላለቃችሁ በቀር
አገራችን ኢትዮጵያን ለሌላ ለባእድ አትሰጥዋትም ክፉም ነገር አገራችን አያገኛትም ነፋስ እንዲይገባባችሁ አገራችሁን በያልችሁበት በርትታችሁ ጠብቁ ወንድሜ ወንድሜ እየተባባላችሁ ተደጋገፉ የኢትዮጵያን ጠላት ተጋግዛችሁ ተድንበር መልሱ:: የኢትዮጵያ
ጠላት ባንደ ወገን ትቶ ባንደ ወገን ቢሄድና ድምበር ቢጋፋ በኔ ወገን ታልመጣ ምን
ቸገረኝ ብላችሁ ዝም አትበሉ ያ ጠላት በመጣበት በኩል ኁላችሁም ሂዳችሁ አንድነት ተጋግዛችሁ ጠላታችሁን መልሱ እስከ እየቤታችሁ እስቲመጣ ዝም ብላችሁ አትቆዩ
ይህነን ምክር መስጠቴ እኔማ በእግዚአብሔር ቸርነት ይህን ያህል ዘመን ገዝቸ
የለምን ነገር ግን ሰዉ ነኝና እንግዲህ እስንት ያህል ዘመን እቆያለሁ ስል ነዉ አሁንም እኔ እንደተምኘሁት እግዚአብሔር የትጨ መረበትና ፈቃደ ሆኖ ልጀን ቢያቆምላችሁ ከልጀ ጋር ሁናችሁ አገራችሁን ጠብቁ አደራ ብያችኁአለሁ አደራ የሚያኖሩበት ሰዉ የታመነ
ስለሆነ ነዉ አሁንም እኔ እናንተን አምኘ ልጀን አደራ ብየ
እሰጣችሁአለሁና አሳድጉት በብልሀት ምከሩት በጉልበት እገዙት በምክር ደግፉት ልጀን አደራ መስጠቴ ከልጀ ጋር
ኢትዮጵያን አደራ ጠብቁ ማለቴ ነዉ እኔም ይኽዉ በገዥዎች አለማወቀ በሕዝቡ አለመስማማት የተነሳ ተብዙ ዘመን ጀምራ ተከፋፍላ የነበረችዉን አገራችነን ኢትዮጵያን ማስኘ ተጣጥሬ ይኽዉ አስፍቻታለሁ እናንተም ከልጀ ጋራ ሁናችሁ ተስማምታችሁ የኢትዮጵያ
ድንበር እንዲሰፋ እንጅ አንድም ጋት መሬት እንዲይጠብ አድርጉ ጠብቁ አልሙየደጊቱ አገራችን የኢትዮጵያ እምላክ ይገዛችሁ ይጠብቃችሁ::
ከዚሕ ቃል የወጣ በሰማይም ነፍሱ በምድርም ስጋዉ ልጅ እስከ ልጅ ልጁ የትርገመ ይሁን የኢትዮጵያ ወቃቢ ያጥፋው እኔም ሳለሁ ከፈቃዴ የወጣውን እረግሜአለሁ::
ማስታወሻ
አቤት ታላቅነት አቤት አርቆ አስተዋይነት አቤት የሐገርና የወገን ፍቅር እንዴት
መታደል ነዉ እንደነብይም ያደርጋል ለነገሩ እግዚአብሔር የገለፅልኝን ምክር ብለው የል
ብቻ ምን ያደርጋል ከምክራቸዉ ስለወጣን የተረፈን እርግማኑ ነዉ::
ወንዴማገኝ
No comments:
Post a Comment