(በ ይታያል እውነቱ) ሆላንድ
....ምንይልክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ
ግብሩ
እንቁላል ነበር ይሄን ግዜ አበሻ.......
..........በግዜው ይህንና ይህንን የመሳሰሉ ልዩ መልዕክት ያላቸው የግጥም
ቋጠሮዎች የተደረደሩት ወራሪው የኢጣልያ ሰራዊት ከነበረው የቅኝ ግዛት ፍላጎት መስፋፋት በመነሳት በኢትዮጵያ ላይ አካሂዶት በነበረው
ወረራ የደረሰበትን ሽንፈት ለመግለፅ፤ በዘመኑ የነበሩ ነገስታትና ሰራዊታቸው ያሳዩትን ጀግንነት ለማወደስ፤ በአጠቃላይ ባርነትን
ፍፁም ሊቀበሉ ያልቻሉ ጀግኖች አባቶቻችን በከፈሉት መስዋዕትነት ዛሬ ላይ ሆነን የነፃነትን አየር ለመተንፈስ መብቃታችንን ለመመስከር
ነው። በእርግጥ ከዚያ ቀደም ይሁን ከዛ በሗላ የነበሩ አባቶቻችንም ቢሆኑ በየወቅቱ ግዜ እየጠበቀ በተለያየ አቅጣጫ የመጣብንን ባእዳን
ወራሪ በተደጋጋሚ አሳፍረው መመለሳቸው ባይካድም፤ በአድዋ ጦርነት ግዜ የተገኘው ውጤት ግን፤ ለኛ ኢትዮጵያኖች ብቻ ሳይሆን ለዓለም
ጥቁር ህዝቦች እንደ ነፃነት ተምሳሌት ሆኖ ይጠቀሳል። በዚህም ድል መላው የጥቁር ህዝቦች እጅግ ከፍ ያለ ኩራት ሲሰማቸው ይኖራል።
ከዚህ በተፃራሪው በዚያ ቀውጢ ዘመን ራሳቸውን በጥቅማጥቅም ለማኖር ሲሉ ባርነትን አሜን ብለው በመቀበል ሀገርን ለጠላት አሳልፈው
የሰጡና በራሳቸው ወገን ላይ ፊታቸውን አዙረው የዘመቱ ጥቂጥ ባንዳዎች እንደነበሩ አይዘነጋም። ዛሬም እነዚያ የሞሰለኒ አሽከሮች
ካደረሱብን በደል በላይ በከፋ መልኩ ሀገርና ታሪክን እያጠፉ ያሉት፤ የኢጣልያ ባንዳ ከነበሩት ከአቶ አስረስ ተሰማ የልጅ ልጅ ሟቹ
መለስ ዜናዊ ጀምሮ በርካታዎቹ የወያኔ ባለስልጣናት የባንዳ ልጆች (ሰላቶዎች) መሆናቸውን መገንዘብ ይኖርብናል።
ወራሪው
የኢጣሊያ ጦር እንደሌሎቹ ሀገራት ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ለመያዝ ሲያስብ ቀደም ብሎ እራሱን ዘመናዊ በሆነ መሳሪያና ሰራዊት ቢያደረጅም፤
የሚከፍለው መሰዋዕትነት ቀላል አለመሆኑን በመረዳት በቀደምትነት የህዝቡን ነባራዊ አንድነት መናድ ሲል የኦርቶዶክስ እምነትን ማጥፋትና
እንዲሁም አማራ የተሰኘውን ብሄረሰብ መምታት እንደ ዋና አማራጭ አድርጎ ተነሳ። በእርግጥ ፋሽስቱ ጣሊያን ይህንን ለማድረግ መነሳቱ
ስሜታዊ ሳይሆን ትርጉም ያለው ሥራ ለመስራት አስቦ እንደነበር ያሳያል። ይኸውም በዚያን ዘመን የ.ኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ በመንግስት አስተዳደር
ውስጥ ያላት ተደማጭነትና በሀገር ጉዳይ ላይ የነበራት ጠንካራ አቋም ጉልህ በመሆኑና እንዲሁም አማረኛ ተናጋሪ የሆነው ህብረተሰብ
የሀገሩን ዳር ድንበር ለማስከበር በተደጋጋሚ የከፈለውና የሚከፍለው መሰዋዕትነት ድንበር የሚያግደው ባለመሆኑ ለወራሪው የኢጣሊያ
ሰራዊት ታላቅ ፈተና ነበር። ስለሆነም ኢትዮጵያ የምትባለዋን ሀገር ለመያዝ
እነዚህን
ወሳኝ ፈተናዎቹ ማለፍ ግድ ስለሆነበት የኦርቶዶክስ እምነትንና አማራ የሆነውን ትውልድ ማጥፋት በዋነኛነት እቅድ ውስጥ ያስቀመጠው
ጉዳይ እንደነበረ ታሪክ ራሱ ያወሳናል።
ውድ
አንባቢያን ዘረኛው ወያኔ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ያለ አንዳች የሕዝብ ይሁንታ የመንግስትነቱን ሥልጣን ከያዘ ሁለት ዓስርት አመታት ወዲህ
የሥልጣን እድሜውን ለማራዘም ሲል የጥፋት እጁን የተለያዩ ሀይማኖታዊ ተቋማት ላይ እንዳሳረፈ፤ ቀይ ሽብር፣ ግምገማ፣ ሽብርተኛ፣
ሙስና ወዘተ.... በማለት ስም እየለጠፈ ከሥራ እንዳፈናቀለ፤
በፕላንና በሰፈራ ስም የብዙሀኑን ቤት ንብረት እንዲሁም ድንግል መሬት ነጥቆ ለባእዳን እንደቸበቸበና በርካታውን ሕዝብ የበይ ተመልካች
እንዳረገው ባሳለፍነው የመከራ ዘመን ሁላችንም የተገነዘብነው ሀቅ ነው። በዚህ ሰሞን ደሞ እንደ ስብዐት ነጋ አይነቱ አንጋፋ የወያኔ
መስራች በይፋ የሚናገረውና እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ ድብቅ የነበረው
በጫካ የረቀቀው የወያኔ ማኒፌስቶ፤ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያንን በጎሳና በብሄር ከፋፍሎ እስከወዲያኛው ረግጦ ለመያዝ እንዲያመች ሆኖ
የተቀረፀ፣ የኦርቶዶከስ እምነትና አማራ የሆነውን ብሄር አስቀድሞ የሚመታ መርሀግብር ያለው መሆኑን ከተለያዩ ማህበራዊ ድሕረ-ገፆች
ጋር ባደረጋቸው ምልልሶች ቁልጭ አድርጎ አስቀምጦታል። አቦይ ስብአት ነጋ ቃል በቃል """"ከእንግዲህ
አማራና ኦርቶዶክስን ኦርቶዶክስን ኦርቶዶክስን መተነዋል ሊያንሰራራ አይችልም!!!"""" ሲል በንቀት
መልክ አስረግጦ ተናግሯል። ይህ አባባል በቀጥታ ከፋሽስት ጣልያን የተቀዳ፣ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ላይ የተከፈተ የጥቃት ዘመቻ
ነው። አባባሉም ሲመነዘር "ከእንግዲህ የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድነትና ህብረትን ገለነዋል" ማለት ነው። ከዚህ በመነሳት ነው
ከዚያ ቀደም በአርባ ጉጉ፤ በበደኖ፤ በጉራ ፈርዳ ያካሄዱትን የዘር ማጥፋት ወንጀል ዛሬም በከፋ መልኩ ቀጥለውበት በቤሻንጉል ጉምዝ
የሚኖሩ አማራና አማርኛ ተናጋሪ የሆኑ ዜጎችን በግፍ እያፈናቀሉ የሚገኙት። ይህም በመሆኑ የችግሩ ሰለባ የሆኑ በርካታ ህፃናት ይጮሀሉ፣
ሴት ልጅ በዋርካ ሥር የመከራ ልጅ ተገላግላ እሚያርሳት አጥታ ትሰቃያለች፣
አባቶች እጆቻቸውን ለፈጣሪያቸው ዘርግተዋል፣ እናቶች የወንድ ያለህ ይላሉ፣ ይህ የአማራና የአማርኛ ተናጋሪ ድምፅ ብቻ አይደለም፤
ይህ የአፋር ልጆች ድምፅ ብቻ አይደለም፣ ይህ የኦሮሞው ድምፅ ብቻ አይደለም፣ ይህ የጌራጌው፣ የትግሬው፣ የከንባታው፣ የሲናሻው፣
የወላይታው፣ የጋናቤላው ወዘተ..... ድምፅ ብቻ አይደለም፤ ይህ የመላው ኢትዮጵያን ጥሪ ነው። ይህ የነፃነት፣ የሞት የሽረት፣
የመኖር ያለመኖር ጥሪ ነው። ሀገርን ከጣልያን ባንዳ የልጅ ልጆች (ከሰላቶዎች) እጅ ፈልቅቆ የማውጣት ጥሪ ነው። እናም ማንኛውም
ሀገርና ወገን ወዳድ ዜጋ በአንድ ላይ ሆኖ የሚመክርበት ግዜው አሁን ነው።
(ልኡል
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይታደግ)
""""እውነትም ሰላቶ""""
ከቶ እንዴት ይሆናል መለስ የኛ Hero ለስ
በጥፋት ላይ ጥፋት ጥፋትን ደምሮ?
ስሙን አትደርድረው ከጀግኖቹ ጎራ፣
ከዘርዐይ፣ ከአብዲሳ፣ ከባልቻ አባነፍሶ.... ........ ....
.......................................... ከገበየሁ
ጋራ።
ጀግና ነው አትበለን ቴዎድሮስን ይመስል፣ ዎድሮስን
እድፍ ነው ታሪኩ ልብን የሚያቆስል።
ጀግና ነው አትበለን ልክ እንደ ዮሃንስ፣
እሱ የሞተለትን ድንበርን የሚያፈልስ።
እንደ ዐፄ ምኒልክ Hero ነው አትበለን፣
በጎሳና በዘር መለስ ነው የከፈለን።
መሪ ነው አትበለን ልክ እንደ ተፈሪ፣
ሰንደቅን አዋራጅ ትውልድ አሳፋሪ።
ጭራሽ አትቀላቅለው ከጥቁር ሰው ጎራ፣
..................................ወደብን በመሸጥ፣
...............................ድንበርን በመቁረስ፣
....................................በዘር በማፋጀት፣
...............................ወዘተ....ወዘተ...........
.....""""መለስ ሰላቶ ነው!""""
ቂም ይዞ የሰራ።
No comments:
Post a Comment