Sunday, March 17, 2013

‹ተመራማሪው ዶክተር› ዓለምሰገድ አባይ


ወልደማርያም ዘገዬ

ከሰደበኝ ስድቤን አምጥቶ የነገረኝእያልክ ኋላ እንዳታማርረኛ አማራ ነኝ ብለህ የምታምን ይህችን ብሶት ወለድ ወረቀት አታንብብ፤ ይብስ ትቃጠላለህ፡፡ ምድረ ኮምፕሌክሳም እየተነሣ የጭቃ ጅራፉን በአማራ ላይ መለጠፍ ተያይዞታልናዘመኑ ነው፤ ሳያውቅ የተኛን አንበሣ ዐውቆ በንቃት የቆመ ነብር ይጫወትበታልብለህ ቻል ማድረግ ነው፡፡ ይሄ አሁን ብዕር ያስነሳኝ ቆሻሻና ደደብ ሰውዬ - ዓለምሰገድ አባይ - የሚሉት ደግሞ ከመለስም የባሰ የመጨረሻው ፀረ-አማራና ፀረ-ኢትዮጵያ ሳይሆን አይቀርም፡፡ በሕይወትም ይኑር በሞትም ይለይ በነጻነት ማግሥት ከመለስ ዜናዊ ቀጥሎ ፍርድ ቤት ከምገትራቸውሰዎችመካከል አንዱ ነው - የሞተን ሰው መክሰስ በኔ አልተጀመረም - ይሄውና ራሽያም ሰሞኑን አንዱን ሟች የቀድሞ ጠበቃ በግብር ሽቀባ ምክንያት የሙት መንፈሱን ፍርድ ቤት ገትራ ዓለምን በሣቅ እያንከተከተችው ናት - እኔም ለዚያ ያብቃኝ እንጂ መለስን ጨምሮ ፍርድ ቤት የምገትራቸው ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ የዕለቱ አዝማች መፈክሬ፡- [ከጠባብ ጎስኛ የባእድ ቅጥረኛ ጠላት ይሠውራችሁ!]
  “ይሄ ባለጌ ሰውዬ ግን እንዴት እንዴት ነው አማራን በስድብ የሚሞልጨው እባካችሁን? ይሄ ንፍጣም የውሻ ልጅ! ‹የወደቀ ግንድ ምሣር ይበዛበታልአሉ? አሁንም ድረስ አማራነቴን አለማወቄ በጄ እንጂ እንደርሱ ቢሆን ይህ ጠብ ጫሪነቱ ክተት የሚያሳውጅ ነበር፡፡ ብሎ ብሎ ከኦሮሞ ቀጥሎ በምልዓቱ በኢትዮጵያ ሁለተኛ የሆነን የሕዝብ ክፍል ‹Minority Amhara› ይበል? ይህስ ባልከፋ - አለ እንጂ የሰማይ ስባሪ የሚያካክል የውሸት ቁልል ጥናታዊ ጽሑፉውስጥ ያጨቀው!”አለኝ አንድ ይህን ምሥጢር ሹክ ያልኩት ወዳጄ፡፡ እኔምእንደዚህ የሚሰማህ መሆንክን ባውቅ አልነግርህም ነበርአልኩት፡፡ ለዝርዝሩ ወረድ እንበልማ፡፡ [ከጠባብ ጎስኛ የባእድ ቅጥረኛ ጠላት ይሠውራችሁ!]
“Identity Jilted or Identity Re-imagined” በሚል ርዕስ ቀደም ሲል ያሣተመውንመጽሐፍሌላ ጽሑፍ ሳነብ በዋቢነት ገብቶ አገኘሁና ያን መጽሐፍ ከመደርደሪያየ አውጥቼ አቧራውን አራገፍኩና ማንበብ ቀጠልኩ፡፡ ከመነሻው የፊት ሽፋን ገጽ ጀምሮ እስከመጨረሻ ስዘልቅ ከሞላ ጎደል ሁሉም ይዘቱ እንትን እንትን የሚልና ክፉኛ የሚገማ ሆኖ አገኘሁት፡፡ አማራ ብሆን ኖሮ ገመዴን ይዤ ወደሚቀርበኝ ዛፍ እሄድ ነበር - ደግነቱ ኢትዮጵያዊ እንጂ አማራ አይደለሁም - ከፍ ሲልም ሰው ነኝ፡፡እንደዚህ ጨምላቃ ሰውዬ በዘረኝነትና በዘውገኝነት አረንቋ ሰምጬ በጥላቻና በበቀል ደዌያትም ተመርዤ ሥነ ልቦናዊ ሥቃይ ውስጥ ባለመግባቴ ፈጣሪየን አመሰግናለሁ፡፡ልል አሰብኩና መታፈር በከንፈር ብዬ ተውኩት፡፡ ይሁንና ምንም እንኳን በአስተዳደጌ የዚህ ወይ የዚያ ዘውግ አባል መሆኔ በወላጆቼ ተገልጾልኝ ወደፈፋና ሸጥ እንድሸጎጥ ባለመደረጌ ምክንያት በአማራነት የተፈረጀ አንድ ታላቅ ሕዝብ ሲሰደብ ያን ያህል ባይሰማኝም የሰዎችን ከንቱነትና ሰይጣናዊ ተፈጥሮ ይበልጥ ለመረዳት እነዚህን መሰል ጽሑፎች ማንበቡ መጥፎ እንዳልሆነ በማመን በሰዎች የተንሸዋረረ ግንዛቤና በጠሉት ላይ እስከምን ድረስ ሊዋሹ ሊጨክኑም እንደሚችሉ እያሰብኩ ያን እንደገማ ዕንቁላል የሚጠነባውን የዓለምሰገድ አባይን ከኢትዮጵያ ጠላቶች በተወሰዱ እጅግ በርካታ ጥቅሶች የታጨቀ ጽሑፍ እየተገረምኩም በሰው ልጅ ከንቱነት እያዘንኩም አነበብኩ፡፡ለካንስ ፊደል መቁጠር በራሱና ብቻውን ምንም ማለት አይደለምብዬምተፈላሰፍኩ፡፡ ተማረ የተባለ ሰው ይህን ያህል ወርዶ ከተጨመላለቀ ያልተማረውማ እንዴቱን ከዚህ አይብስ? ለዚህ ለዚህማ በአዲስ አበባና አካባቢዋ የሚርመሰመሱ ይሉኝታቸውን ቸርችረው በልተው የጨረሱ የወያኔ ጅቦችና ዓሣሞች ምን አጠፉ? በሀገርህ ሲወረር አብረህ ውረር የማይማን ፈሊጥ ከታሪካዊ ጠላቶቿ ጋር ተባብረው ኢትዮጵያን የሚግጡ ሌሎች ዜጎችስ ምን አጠፉ? ዶክተር ተብዬው እንዲህ ጆሮውና ዐይኑ ተመሳጥረውና ኅብረት ፈጥረው በአንዴ ከጠፉ፡- በሰውነት ሳይሆን በመወለድ፣ በእውነት ሳይሆን በሀሰት፣ በሣይንሳዊ መክሊት ሳይሆን በዘረኝነት ቅኝት የተሳሳተና ወገንን ከወገን የሚያናክስ ጥናት ተብዬ ካሰራጨ ከእንግዲህ ለኅሊናስ ሆነ ለሰብኣዊነት ማን ይታመን? ያላነበባችሁት በሞቴ አንብቡትና ፍረዱ፡፡ ከዚያ በኋላ ጥናት እንዲህ ከሆነ ባፍንጫዬ ይውጣ!› ብላችሁ እርግፍ አድርጋችሁ ትተዋላችሁ፡፡ [ከጠባብ ጎስኛ የባእድ ቅጥረኛ ጠላት ይሠውራችሁ!]
  ግሩም ነው፡፡ሪሰርችማለት ለካንስ እንዳማርኛ እንዳበጁት ሊበጅ የሚችል ነገር ኖሯል! ከስሜታዊ ቃለ መጠይቆች ባሻገር እዚህ ግባ የሚባል የምርምርና ጥናት ውጤት ሳይዝ በሪሰርች ስም እየቀለደ አንድን ሕዝብ መሳደብ የማያስቀጣ መስሎ ስላገኘው ብቻ እንደዚያ ሲሞላፈጥ ስታዩት አንዳች ነገር ይሰማችኋል፡፡ አማራን የማይወርፍ፣ የማያንቋሽሽ፣ የማይሳደብ፣ በሀሰት የማይወነጅል ዐረፍተ ነገር በየአንቀጹ አታገኙም፡፡ አማራን እያሳዩ የገረፉት ነው እሚመስል፡፡ የአሁኑ ትውልድ ኢትዮጵያዊ እንኳን፣ የወያኔን ሁልአቀፍ ሀገራዊና ትውልዳዊ ጥፋት በዐይኑ በብረቱ እያዬ ዓለምሰገድ በአማራ ላይ ያለውን ጥላቻ ያህል በወያኔ ላይ የለውም፡፡ የሚገርም ሰው ነው ይሄ ዓለምሰገድ የተባለ ውልቀሰብ፡፡ [ከጠባብ ጎስኛ የባእድ ቅጥረኛ ጠላት ይሠውራችሁ!]
  ይህ ትግሬ ነኝ የሚል ሰው - ግን ልክ እንደነመለስ ሁሉ ከኤርትራ በላይ ለኤርትራ የሚጨነቅ ሰው - ብዙ ቁጭት ያለበት ለመሆኑ መጽሐፉ አፍ አውጥቶ ይናገራል፡፡ትግራይ ትግሪኝለምን አልተመሠረተችም የሚል ትልቅ ፀፀት አለበት፡፡ ኤርትራና ትግራይ ለምን አንድ መንግሥት አልፈጠሩም፣ ትግራይ የጎንደርን ለም የእርሻ መሬቶች ይዛ ከአላውሃ መልስታላቋ ኤርትራወይምታላቋ ትግራይወይምታላቋ ትግራይ ትግሪኝበሚል የትግርኛ ተናጋሪ ሕዝብና መንግሥት ለምን አልመሠረተችም የሚል ታላቅ ቁጭት አለበት፡፡ ወያኔና ሻዕቢያ እፊታቸው ላይ ያልተጠበቀና ትልቅ የክፍለ ዘመን የሎተሪ ዕድል ተጎልቶላቸው ሳለ የወዲህኞቹ ሃሳባቸውን ቀይረው ለምን ኢትዮጵያዊነታቸው ጸኑ የሚል የእግር እሣት አለበት፡፡ አማራ ባላገር ነው፣ አማራ እንኳን ሌላ ሕዝብ ራሱን ማስተዳደር የማይችል ቀርፋፋና ኋላ ቀር ሕዝብ ነው፣ አማራ ደደብ ነው፣ አማራምን የማይለው ነገር አለ - በደምሳሳው አማራ የሁሉም ክፉና -ሥልጡን ነገሮች መገለጫ ነው የሚል ጭፍን አቋም አለው፡፡ ጥናቱና አጥኚው በውነቱ ከሂትለር የአርያን ዘር በባሕርይ የሚወራረሱ፣ ከዚሁ ዘውግ የናዚ ቅኝት የሚዛመዱ፣ ከፋሺዝም የሙሶሎኒ ሥነ ፍጥረት የሚጋሩ በዓለም የመጀመሪያዎቹ በቀል ወለድ የአጋንንት አካላዊና ቁሣዊ መከሰቻ ናቸው፡፡ ይህን መሰል ሰው በዚህኛው 21ኛ መቶ ክፍለ ዘመን ማየት ለሰው ልጅ ዘር በአጠቃላይ ሀፍረት ነው፤ ውሸት እግር አውጥቶ ሲራመድ ማየት ለሚፈልግ ሰው ይህን መጽሐፍ በማንበብ ሊያረጋግጥ ይችላል፡፡ የወያኔን ተፈጥሮም ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡ በመሠረቱ በዚህ ረገድ ብዙም ባላውቅ ካለኝ ጥራዝ ነጠቅ ግንዛቤ በመነሣት ስገምተው ጥናትና ምርምር የራሱ አካሄድ ያለው ይመስለኛል - እንደ አቶ ዓለምሰገድ የራስን ሸፍጥ በጥናት ስም ማቅረብ በፍጹም የሚቻል አይመስለኝም - በዘመናችን ዕድሜ ለኮፒ-ፔስት ጥናት እንደቀልድ ከመታየቱና ብዙውን ጊዜም ለፈንድና ለዕቅድ አፈጻጸም ማወራረጃነት የሚውል መሆኑን የሚጠቁሙሰነፎችና ምቀኞችባይጠፉም፡፡ ሲሉ እንደሰማሁት ጥናታዊ ዘገባ በሦስትዮሽ የማጣሪያ መንገድ ተበዝቆ(triangulation) በዘመናዊ የምርምር መንሽና ላይዳ ተበጥሮ (‹qualitative and/or quantitative የአቀራረብ ዘዴ) የተደረሰበት በኩር ሥራ ወይም ከቀድሞ መሰል ሥራ የተሻሻለ ተጓዳኝ ግኝት የሚቀርብበት እንጂ በየመሸታ ቤቱ የተቃረመ የጥላቻና የበቀል ስሜት የሚናፈስበት - እንደሎሬቱ አገላለጽ - የወሬ ማንፈሻ ጋሻ አይደለም - ጥናትና ምርምር፡፡ እንደዚያ ከሆነ እኔን ብዙ ጊዜ የሚገጥመኝን የሞልፋጣ ወያኔዎችን ስንክሳር በጥናት ስም ባቀርብ ተቀባይ ይኖረኛል ማለት ነው - ይህ የኔና የዓለምሰገድ ዓይነቱ አቀራረብ ጥናታዊ ሳይሆን መሸታዊ ነው ሊባል የሚችል፡፡ የዓለምሰገድጥናትመነሻውም መድረሻውም አሉቧልታና ፀረ-ኢትዮጵያ የውስጥና የውጭ ኃይሎች በንግግር ወይም በጽሑፍ ያስቀመጧቸው ሃሳቦች ናቸው፤ በተጨማሪም የጥንት የዋሃን ወደተንኮል ይዞርብኛል ብለው ያልተናገሩት ገራገር የግል አስተያየትና ሃሳብም እንደጥናት ግብኣት ተካትቷል፡፡ በጥናት ጽሑፍ ውስጥ ሊጠቀስ የሚገባው እንደአፈወርቅ /የሱስ ያለው ግላዊ አስተያየት አይደለም - ለተለዬ ዓላማ ካልሆነ በስተቀር፡፡ እዚህ ቦታ እገሌ እንደነገረኝ ተብሎም ጥናታዊ ጽሑፍ አይቀርብም፡፡ ነውር ነው፡፡ የምሁራዊነትን ይዘት ያወርደዋል፡፡ለምሳሌ የዛሬ 17 ዓመታት ገደማ ከአንድ የአንድ መሥሪያ ቤት የግዥ ሠራተኛ የነበረ ትግሬ ወያኔ ጋር (! በዘውጋዊ ቀመሩና በሥራው አጋጣሚ በጣም ብዙ ገንዘብ ዘርፎ እጅግ የከበረና ቢጠሩት የማይሰማ ቀጭን ጌታ ነው! አሁን፡፡ ) ሊፍት ሰጥቶኝ አብሬው ስሄድ ፕሮፌሰሮች አሥራትንና መስፍንን አንስቶአነ እንተሆንኩ ለነዚሁን ሰዎቹ እንኳዕ የፕሮሶፌርነት ማዕርግ የ12 ካርድም አልሰጣቸውም ነበረ!” በማለት በንዴት እየፎገላ የተናገረውን ካለዛሬ ለማንም አልተናገርኩም - እውነቴን ነው፤ የዚህ ዓይነቶቹን እውነተኛ ገጠመኞቼን ብጽፋቸው ወረቀትና ቀለም አይበቃኝም - ሰውዬው ያን ያለው ጭልጥ ካለ ወገናዊኑ እንጂ ሰዎቹንና አቋማቸውን ተረድቶ አይደለም፤ በብዙ መቶ ሺዎች - ምናልባትም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ - ተጋሩ አኅዋትና ከምዙይ ሰብዓይ ከምዝሰምዖን አነ ብወገነይ እፈልጥ እየ - ምክንያቱም የአሊየት ጉዳይ ከእንስሳዊነት ባሕርያችን የምንጋራው በምክንያት ሳይሆን በደምና በአጥንት እየተፈላለግን የምንቧደንበት ጥንታዊ የትስስር ገመድ ነው፤ መሠረቱም ማይምነትና ኋላቀርነት እንዲሁም የመኖር ዋስትና ሥጋት (insecurity)ነው፡፡ [recommended read on this issue:- The virtue of Selfishness, Ayn Rand] ፡፡ ይህ ከፍ ሲል የገለጽኩት የዛሬ 17 ዓመቱ ገጠመኜ በጣም ግለሰባዊ ነው፡፡ መላ ትግሬን አይወክልም - ከዚህም በላይ ሊሉ የሚችሉ ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ መብታቸውም ነው - እኛስ እነሱን ስንትና ስንት እንላቸው የለም - ዕድሜ ለዚህ እነሱእኛመለሳዊ ከፋፋይ ፈሊጥ፡፡ ነገር ግን በጥናት ስም ይህን አሉቧልታ ሁሉ አጠረቃቅሜጥናታዊ ጽሑፍብዬ ባቀርብ ያሳፍራል፡፡ ዓለምሰገድም ማፈር አለበት፡፡ አማራን መጥላት ሌላ - በጥናት ስም ይህን የተከበረ የሣይንስ ዘርፍ - ጥናትና ምርምርን አቧራና ጭቃ ላይ ጥሎ ማርመጥመጥ ሌላ፡፡ ቢያንስ ቢያንስ - የለውም እንጂ ቢኖረው ኖሮ የራሱ ኅሊና እየቆዬ በቆጠቆጠው ነበር፡፡ አብሮ ኗሪ በሆነ ሕዝብ መሀል ይህን የመሰለ ግፍና በደል መሥራት ታሪክ ይቅር የማይለው የግፍ ግፍ ነው - “አያልፍ የለም አለፈና፤ ይሏችኋል እቡናመባባል የማይቀር ከሆነ አሁን የምንለውና የምናደርገው ሁሉ ለነገው የአብሮነት ሕይወታችን እንቅፋትና የሆድ መቀያየምን የማይፈጥር መሆን ይገባዋል - የዱባን ጥጋብ መቆጣጠር ካለስንቅ መዝመትን ያስቀራልና ማስተዋልን ከአሁኑ እንለማመድ፡፡ አሁን እየተደረገ ያለውን ሰማይና ምድር ሊቋቋሙት የማይችሉትን የወያኔ ትግሬ ግፍ ዓለምሰገድ ቢመለከት - አሁንም ዐይን የለውም እንጂ - ምን ሊል ይችል ይሆን? ለነገሩአውቆ የተደበቀእንዲሉ የነሱ ጥፋት ለርሱ የፅድቅ መንገድ ነው፡፡ ሰዎች እንግዲህ እንዲህ ነን፡፡ ለራስ ስንቆርስ የማናሳንስ - ለሰው ስንቆርስ የምንቀናንስ፡፡  የዚህን ውሸታምና ዘረኛ ሰውዬ አርቲ ቡርቲ ጽሑፍ በስፋት ለመቃኘት ጊዜውም ሆነ ፍላጎቱ የለኝም፡፡ደግሞም በወቅቱ ልክ ልኩን የነገረው ሰው ሊኖር ይችላል ብዬ አስባለሁ፡፡ እኔም መጽሐፉ ከታተመ 14 ዓመታት በኋላ እንዲህ እየተንጨረጨርኩ ልወርፈው የዳዳኝ ገና አሁን ስላነበብኩት ነው - ያላነበብከው ነገር ምንጊዜም አዲስ ነው የሚል እምነት አለኝ - “ብለነው ብለነው የተውነውን ነገር፤ ሚስቱ ዛሬ ሰምታ ልትታነቅ ነበርየሚለውን የኔ ቢጤዋን ሞኝ ሚስት አስታውሱና በነገሮች መመሳሰል ዘና በሉ፡፡ የትኛው ሞልፋጣ ምን እንዳለ ማስታወሱ በራሱም መጥፎ አይመስለኝም፡፡ ይሄ አማራ የሚባል ፍጡር ግን ፈርዶበት! ምን ይሆን ጥፋቱ ምድረ ወያኔ እንዲህ የሚረባረብበት? ምድረ ማይም የሚቀረሽበት ይሄ አማራ የሚባል ነገር አንድ ተፈጥሯዊ መስህብ ሳይኖረው አይቀርም ግዴላችሁም፤ ሙት አሉት ሞተላቸው - ተሰደድ አሉት ተሰደደላቸው - ድሃ ሁን አሉት ደኸየላቸው - ታመም አሉት ታመመላቸው - አትብላ አሉት ተራበላቸው - አትናገር አሉት ዱዳ ሆነላቸው - አትመልከት አሉት ታወረላቸው፤ በተዘረፈ ገንዘብ ከየትም ባሰባሰቡት ትብታብና ደንቃራ፣ አንደርብና አፍዝ አደንግዛቸው ሰመመን ውስጥ ግባ አሉት ሰማይ ምድሩ ዞሮበት አንቀላፋላቸው፡፡ ከዚህ በኋላ የምን አትርሱኝ ነው? ለአቡሻክሩ መዞር፣ ለአበቅቴው መጥባት ደግሞ የዘመን ዑደቱን መጠበቅ እንጂ የወደቀን መቀጥቀጥ፣የተሸነፈንመነረት ሃይማኖታዊም ሞራላዊም ሰብኣዊም አይደለምና ወያኔዎች እባካችሁን በአቡነ አረጋዊ ይሁንባችሁ በምንም ይሁን በምን - በገደሉም ይሁን በባህሩ ጂኒማሸነፋችሁን›  ተገንዝባችሁ አሁን በመጨረሻው ዘመን ላይም ቢሆን በቅጡ ግዙ()፡፡ ሞቶም አጥንቱ እንዳያርፍ ያስደንግጥ ያለበት ይመስል ዘወትር በእውንም በህልምም የሚበረግጉ ወገኖች መብዛታቸው ይገርማል፡፡ ነገሩ የበሽታ ነው - ነጫጭባዎቹ psychosis ይሉታል - የአእምሮ በሽታ ስሙና ዓይነቱ ብዙ ነው፡፡ ህክምናም የለውም - መፍትሄው የአመለካከትና የአስተሳሰብ ለውጥ ወይም አካላዊ ሞት ነው - አንዱን መምረጥ ነው፡፡ ሆድ እንደሆነ አይሞላም - የድሎት ኑሮም አይጠገብም - ጥላቻም ገደብ የለውም፡፡ ከሁሉም ይልቅስ ያንቀላፋ ኅሊናን ቀስቅሶ ነፍስ እንዲዘራና ተጨባጩን እውነታ እንዲገነዘብ ማድረግ ለሁሉም የሚበጅ መልካም ነገር ነው - ወርቃማ አጋጣሚዎች ዕድሜያቸው አጭርና ባልተጠበቀ ሰዓት አሟልጨው ከእጅ የሚወጡ መሆናቸውን መረዳት በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ የሥነ አእምሮ ህመም መድሓኒት ቢኖረው ኖሮ ወያኔ በኢትዮጵያ እያደረገ ያለውን ነገር ሁሉ እየተመለከተ ያለ ዓለምሰገድን እሚያህል ትልቁን ምድራዊ የትምህርት ደረጃ የተጎናጸፈ ሰው ይህን ገሃድ የወጣ የከተማ መንግሥት-ለበስ ውንብድና ለመሸፈን በሚመስል ሁኔታ እንዲህ ባልተወራጨ ነበር - ‹ድንቄም ጥናታዊ ጽሑፍ! መድበለ ቅሌት ወውርደትበሉት ይህን ጽሑፍ የምታነቡለት ወዳጆቹ፡፡ [ከጠባብ ጎስኛ የባእድ ቅጥረኛ ጠላት ይሠውራችሁ!]
  ቀጣዩን ተመልከቱና በዱሮው የደርግ ቋንቋ የአማራን አናሳነት ወይም ንዑስነት ተመልከቱ - ከዋሹ አይቀር እንዲህ ነው፡፡አዲዮስ ሪሰርች!
Even as Tigray enetered the armed struggle in 1975, … elites of both sides of Mereb retained separate political identities. Notwithstanding the difference in visions and self perceptions, they managed to coordinate their struggles against the Amhara minority regime. (p. 7, emphasis added)
  የኛ ማለትም የነሱ ምሁር እንግዲህ ይሄ ነው(የነሱ ስል የወያኔዎች ማለቴ እንጂ የሰፊው የትግራይም ሆነ የኤርትራ ሕዝብ ማለቴ አይደለም - ከእነሱ ጋር ጊዜው ሲደርስ በመለሳዊ የፈግጠው ፈግጪው ስድ አንደበት ሳይሆን በጨዋ አንደበት እንነጋገራለን! ያኔ ማን ያውቃል ቋንቋም ሳያስፈልገን እንዲሁ በረቂቁ አውታረ ልቦና ወኅሊና ልንግባባም እንችል ይሆናል - ለርሱ የሚሳነው ነገር የለምና!) - አማራ አናሳጎሣሲሆን ይታያችሁ - የአቶ ስንሻው ቤተሰብ ዓይነት የአንድ አካባቢ ነገድ፡፡ ጥናት ማለት እንግዲህ ይዘኸው የምትነሳውን የሪሰርች ጥያቄ የሚመልስልህን ግሳንግስ ዐረፍተ ነገር መኝታህ ላይ ቁጭ ብለህ እየጠፈጠፍክ መጋገር ብቻ ነው ማለት ነው ፡፡ ይህን ሰውየኛየነሱፈሊጥ ከተወገደ በኋላ አግኝቼ ብንወቃቀስና ምናልባትም እስከዚያን ጊዜ ድረስየሕክምና ሣይንስ አጥንቼየጄኔቲክ ዲኤንኤ ቀመሩን ብመረምረው ደስ ይለኛል፡፡ አብዛኛው ጽሑፉ የጥናትና ምርምርን ፈለግ ካለመከተሉም በላይ ጭልጥ ያለ ውሸት ነው፡፡ በክህደትም የተሞላ ነው፡፡ ለምሳሌ ጣሊያኖችን ያሸነፈው ኃይል ከመላዋ ኢትዮጵያ የተውጣጣ መሆኑን ላለማመን ሲፈልግጣሊያን በአፍሪካ ጦር መሸነፍን እንደውርደት ስለቆጠረችው …› በማለት የኢትዮጵያን - እርሱየአማራው ዘረኛ መንግሥትበሚል የሚጠራትን የኢትዮጵያ ሕዝብ ተጋድሎ በማንኳሰስ ድሉን ለሌላ አሳልፎ ይሰጣል፡፡ ለነገሩ ደባው እንጂ የሚያናድድ ድሉ በርግጥም የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የመላው ጥቁር ሕዝብ ድል መሆኑ ተወስቶ የማይጠገብ ታሪካዊ ኹነት ነው፡፡ ኢትዮጵያን ማንሳቱ የሚጠቅመው ከሆነ ያነሳል፤ አለበለዚያ የአማራው ዘውግ የገዢ መደብ›  እያለ ነው ከኢትዮጵያ ጋር በተመሳስሎ (synonymously) አማራውን አላግባብ የሚያነሳ የሚጥል - ያባቴ አምላክ የሥራውን ይስጠውና፡፡ [ከጠባብ ጎስኛ የባእድ ቅጥረኛ ጠላት ይሠውራችሁ!]
  ቀጣዩን ደግሞ ተመልከቱልኝ፡- …The failure of the shared commonalities and war against a common enemy [Dergue/Ethiopiawinet] to shape a single trans-Mereb political identity is puzzling. (ibid)
እንደዚህ የሚለው - ነገሩም ዕንቆቅልሽ የሆነበት - ወያኔና ሻዕቢያ ድል ካደረጉ በኋላ አንድ ሆነው ያቺን ማርና ወተት እንደመና ከሰማይ የሚዘንብባትንየቃል ኪዳንምድርትግራይ ትግርኝ ለምን አልመሠረቱም? የሚል ቁጭት እያንገበገበው ነው - ( በቀላል የሚቀየም ሰው አይኑር፡- ኢትዮጵያ ሁሉም ነገር አላት - ሁሉም ነገር ግን በግድ በአንድ አካባቢ ይገኝ አይባልም - አያስኬድምም፤ እዚህ ወርቅ እዚያ ጤፍ፤ እዚህ ነዳጅ እዚያ ቡናእንጂ በግድ ትግራይ እንደደቡብ ወይም ምዕራብ እንደ ምሥራቅ ይሁኑ አይባልም፤ ከሆኑልንም እሰዬው)፡፡ ይህን ሰውዬ ግን ወገኛ በሉት፡፡ አንዱ አቀባይ ሌላው ተቀባይ፣ አንዱ አምራችና አስመራች ሌላው በላተኛ፣ አንዱ ሎሌ ሌላው ጌታ ሆነው እየተቀማጠሉ ከመኖር ለማን ጀቴ ብለው ነው ከአላውሃ ወዲያ በደረቁቻ መሬት - ለብዙ ዘመናት አገልግሎት ከመስጠት አኳያ አፈሩ ወደድንጋይነት ዛፉም ወደቁጥቋጦነት በተለወጠ መሬት ላይ ተወስነው የሚኖሩ? በሞኝ ደጅ ሞፈር መቁረጥ እየተቻለ የሌለን ጠባይ የምን ግድርድርነት ነው? ትግራይ ትግሪኝ ጥንቅር ብሎ ይቅር እንጂ የምን በችጋር መቆራመድ? ትክለ ሰውነትን ሳይቀር የሚቀይርና የተላጠ ሙዝ የሚያስመሰል ባለቤት የሌለው የመሀል አገር ሀብትና ጥሪት እያለ የምን መረብ ምላሽ ነው? ይሉኝታ ዱሮ ቀረ፡፡ ዓለምሰገድ ግን ጅልነትም አለበት ልበል? አላህ ከላይ ፈረደባቸውና የኋላ ኋላ ለይምሰልም ቢሆን - ከላይ ሣይሆን ባልጠበቁት ሁኔታ ከግርጌ ተመነቃቀሩ እንጂ እንደመነሻውማ ዕቅዳቸው ሌልኛ ነበር - ‹አላህ ሲቆጣ ሽመል አይቆርጥም ያደርጋል እንጂ ነገር እንዳይጥም›  እንዲሉ ሆኖባቸው፡፡ ይህን መሠሪ የሁለትዮሽ ሸፍጥ ብፃይ ዓለምሰገድ አያውቀውም ማለት ይከብደኛል፡፡ መንገብገቡ ግን እንደአካሄድ ትክክል ነው - ይንገብገብ ይቆላጭም፡፡ ግን ግን ሁለቱ የዲያብሎስ ውላጆች በጋራ የሠሩትንና አሁንም ድረስ እየሠሩት
የሚገኙትን ኢትዮጵያንና ኢትጵያዊነትን የማጥፋት ዘመቻ መርሳት አይገባንም - እርሱም እኛም፤ በቂያማ ቀን የምናወራርዳት ሒሳብ ልትኖረን ስለምትችልንቁም በበኅላዌነ በዐቢይ ትጋህ ወአርምሞ፣ እስከንረክብ ነጻነት በከዊነ ወልደአብ ወእሞእንድንል በጥራዝ ነጠቁቅኔ ዘረፋ፡፡ የጎጃምንና የወሎን ገበሬ በፎርጅድ ብር ስንትና ስንት መኪና ሙሉ እህል በተለይም ጤፍ እኒያኞቹ ከገዙና እኒህኞቹም እኒያኞቹን በጠራራ ፀሐይ ከሸኙ በኋላ ምሥኪኑ ገበሬ ብሩን ሊጠቀምበት ወደባንክ ሲሄድ እኒህኞቹ የሠሩትን ተንኮል እያወቁ ገበሬውን በወንጀለኝነት አላሰሩትም? በዚህች በኢትዮጵያ ምድር ላይ እጅግ የሚዘገንን ግፍ ተሠርቷል! ክፍያውንም የሚችለው እንደሌለ ብዙ ጊዜ ተገልፆኣል፡፡ በትዕግሥት መጠበቅ ብቻ ነው፡፡ አስታውሱ - የነዚህወገኖቻችንን ወንጀል እንኳን ሌላው የዓለም ዜጋ ሰይጣን ራሱስ ሊሠራው ይችላልን?... ስንቱን በጋራ አሠሩ - ገደሉ - አሰደዱ - አሳደዱ(በጠፍ ጨረቃ ወስደው ደብዛዋን ያጠፉት ማርታ መኮንን ትዝ አለችኝ፤ ከጨካኙ የባሕር አውሬ ከሻርክ የባሱ እነዚህን አውሬዎች የሚሊዮኖች ደምና ዕንባ በሠልፍ እየጠበቃቸው ነው!)፡፡ አዲስ አበባ የሻዕቢያ መንቦራቦሪያ አልነበረችምን(አሁንስ ቢሆን ማን ያቃል አይደለች ትሆን ይሆን?) ግን አይዞን ወንድሞችና እህቶች፣ እናቶችና አባቶች ጓዶች፣ ይህም ያልፋል፡፡ (በድርበቡ መንጌን መሰልኩባችሁ ልበል? ሆን ብዬ ላስታውሳችሁ ፈልጌ ነው፡፡ሰው ካልመሄድ ወይ ካልሞተ አይመሰገንም፡፡ በስንት ስለት የተገላገልኩትን ደርግን መናፈቄ ይገርመኛል - የዕድላችን ጥመቱም እንዲሁ፡፡)  [ከጠባብ ጎስኛ የባእድ ቅጥረኛ ጠላት ይሠውራችሁ!]
  በነገራችን ላይ የቫቲካንን የጥቁርና የነጭ ጪስ የሞኞች የሚመስል ትዕምርታዊ የሊቀ ጳጳስ የምርጫ ሂደት ተከታትዬ አሁን በዚህ አንቀጽ መመለሴ ነው፡፡ ይቺ የሌጋሲ ነገር ታዲያ በእግረ መንገድ ሰሞኑን ከምንጊዜውም በላይ እየገረመችኝ መጥታለች፡፡ በፍራንሲስ አንደኛ›(Francis I) የጵጵስና ስም እንዲጠራ የወደደው አዲሱ አርጀንቲናዊው የጣሊያን ዝርያ ተመራጭ ሊቀ ጳጳስም በመጀመሪያ ንግግሩ የቤኔዲክት 16ኛን ሌጋሲ እጠብቃለሁ ሲል ብሰማ ጊዜ ቅንጭላቴ በአንዴ ሰሜን ኮሪያ ደርሶ ኢትዮጵያንም በበረራ ክልሉ አጣልፎ ወደጳጳሱ አህጉር ወደላቲን አሜሪካ ቬንዝዌላ ውስጥ ቆይታ አድርጎ ተመለሰ፡፡ ግሩም ነው! ነገሮች እንዴት ነው እየተመሳሰሉ የሚሄዱ ያለ? የሻቬዝና የመለስማ በሚገርም ሁኔታ አንድ ሆነው አረፉት፡፡ ልዩነታቸው ግን መለስ የደረቅ ጣቢያ ወኪልና የችጋር አምባሳደር - የጥቂቶች ቀፈት ገልባጭ - የብዙዎች አንጀት ቆራጭ ሲሆን ሁጎ ሻቬዝ - ምንም እንኳን በአምባገነንነትና እልኸኛነት ዝንባሌው ክፉኛ ቢታማና ሄንሪክ ካፒሪሌስን የመሰሉ ሣተና ጠላቶችን ቢያፈራም - የድሆች አባትና የሀገር ዕድገት መሠረት በዚያውም የብዙኃንን የፍቅር ልብ የገዛ፣ ለባዕዳን የተፈጥሮ ሀብት ብዝበዛ ሀገሩንና ሕዝቡን አጋልጦ ያልሰጠ በዚህ ሥራውም ውድ ክፍያ ከፍሎ ሲያበቃ ያለውን ሕዝባዊና ሀገራዊ ፍቅር በደሙ ዋዥቶ ያወራረደበት መሆኑ ነው፡፡የኤርትራንም ቲቪ ጎብኘት አድርጌ ነበር - ከመመለሴ በፊት፡፡የሞኝ ልቅሶ ሁልጊዜ አበባየእንዲሉ ሰዎች የትና የት በደረሱበት በዚህ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘመን የሻዕቢያ ቲቪ አሁንም የሚያላዝነው ስለትግሉ ዘመን የደርግና የኤርትራ አማፂያን ጦርነት ነው፡፡ ድብልቅልቅ ያለ የበረሃ ጦርነት እያሳዩ - የሆሊውድ ፊልም ይመስል - ተመልካቾቻቸውንእያስተማሩ ያዝናናሉ፡፡ ባለንበት የምንረግጥ የአፍሪካ ቀንድ ደናቁርት ሆነን መቅረታችን ሆድ ሆዳችሁን አልበላውም? ሰው የምንሆን መቼ ይሆን?
  ስለዚያ ብሽቅ ትግሬ-ርትራዊ ዶክተር ተብዬ ይህንንም በነካ ዐይናችን እንመልከት፡- The 1974 anti-feudal Ethiopian popular revolution,… actually ended up unleashing ethno-regional forces that, in 1991, brought the Amhara hegemony into its demise. (op. cit, p. 12 emphasis added)
የዘሬን ብለቅ ያንዘርዝረኝ ያለው(ችው) እነማን ነበሩ? እንዲያው ይህ ጥጋበኛና ጠባብነት ለካንስ አፍንና መላ ሰውነትን መደዴ ነው እሚያደርጉ! በከልቻ የጣር መንፈስ አማራን አርቀን ቀብረናል፤ እንኳንስ ለባንክ የቦርድ አባልነት ለዘበኛም ቢሆን እሱን አታንሱብን፣ በሽታችን ይመጣብንና ያንቀጠቅጠናል እያለ ይወራጫል - ደደቡጄኔራል› - ለነገሩ ለካንስ እርሱም ባጃቢው አጥኚነት በርሱተማሪነትበርቀት ኤምኤውን ይዟል አሉ - ተስፋየ /አብ ነው በመጽሐፉ የነገረን፡፡ ገንዘብ ካለ እንኳንስ ዲግሪና ሕንፃ ቤት መንገድም በሰማይ አለ አይደል? ችግሩ ተንጋለው የተፉት ተመልሶ ሊያውም ወዳፍ መምጣቱ ነው፡፡ ምን አለ ትሉኛላችሁ! [ከጠባብ ጎስኛ የባእድ ቅጥረኛ ጠላት ይሠውራችሁ!]
  ይህ በሽተኛ ሰውዬ - ዓለምሰገድ - በመጥሐፉ ላይ ዳር እስከዳር እሚለውየአማራ ገዢ መደብ ጨቋኝና ጨካኝ ነውነው፡፡ በአማራ ጥላቻ ሁለመናው ፍጹም ታውሯል፡፡ አማራን እንደ እባብ ነው የሚቀጠቅጠው - ሌሎች ኢትዮጵያውያን ብሄር/ብሔረሰቦችንማ ከነመፈጠራቸውም ዘንግቷል - አማራ ላይ ብቻ ነው ፊጥ ያለውና እርሱን በየአጋጣሚው የሚጨፈጭፈው - ኢትዮጵያ ውስጥ ካለ አማራ አንድም የሌላ ብሔር ዜጋ ያለም አልመሰለው፡፡ ስለወያኔ ትግሬ ደግሞ ትንፍሽ አይልም፡፡ ኢትዮጵያን ለአማራ ሰጥቶ ሌሎችን ፎሪ አውጥቷቸዋል፡፡ ከቤተ መንግሥት ዘበኛ እስከ መከላከያ ተራ ወታደር ድረስ በትግሬ ስለታጨቀው የወያኔ መንግሥትና የግፍ አገዛዝ አንዲትም ቃል አይተነፍስም- እንዲተነፍስ መጠበቁም ቂልነት ነው - በመሠረቱ፡፡ የለየለት የሻዕቢያና ወያኔ ጉዳይ አስፈጻሚ ቡችላ ኢትዮጵያዊ እንዲሆን አንጠብቅም፡፡ በጥናት ስም የሠራው ዕኩይ ተግባር ግን መቼም ቢሆን የሚረሳ አይደለም፡፡ አሁንም የኢትዮጵያ አምላክ የሥራውን ይክፈለው፡፡ [ከጠባብ ጎስኛ የባእድ ቅጥረኛ ጠላት ይሠውራችሁ!]
  ለመሆኑ አፄ ምኒልክ አማራ ብቻ ነበሩ? አፄ /ሥላሴ አማራ ብቻ ነበሩ? መንግሥቱ /ማርያም አማራ ብቻ ነበር? የጥንቱ አፄ ገላውዴዎስ አማራ ነበሩ? በእውኑ ኢትዮጵያን ያስታዳደረ ሁሉ አማራ ብቻ ነበር? ኢትዮጵያ 1983. ወዲህ ካልሆነ በስተቀር በአንድ ዘር ፍጹማዊ የበላይነት እንዲህ እንዳሁኑ አበሳዋን አይታ ታውቅ ይሆን? አማርኛስ 80 ብሔር/ብሔረሰብ መገናኛ ድልድይ ሆኖ ማገልገሉ ያሸልመው ነበር እንጂ እንደጋለ ብረት ሊያስቀጠቅጠው ይገባ ነበርን? ይሄ ነገር የበሉበትን ወጪት መስበር አይሆንምን? አሁን አማርኛ ባይኖር ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ በምልክት ቋንቋ ሊገዛ ነበረ ወይ? ምን ዓይነት የሚመር ቀልድ ነው? ምሥጋናው ፅድቁ ቀርቶ ዕልቂቱ ኩነኔው ቢቀር ምናለበት? ለምን ግፍ ለልጆቻቸው ያቆያሉ? ለምን ያናግሩናል? ለምን መገፋታችንን ተቋቁመን፣ ችግራችንን ችለን ለፈጣሪያችን እየጮህን የመከራ ሕይወታችንን እርሱ እስከፈቀደ ድረስ እንድንገፋ አይተውንም? ወይንስ የጊዮርጊስስ ግብር የበላ ሳይነኩት ይለፈልፋል እንደሚባለው ሆኖ ይሆን? አማርኛ እየተናገረ አራት ኪሎን የተቆጣጠረ ሁሉ አማራ ነው እየተባለ ይህ ምሥኪን ሕዝብ ላይ ማንም እንዲያስታውክ የፈቀደለት ማን ይሆን? ጊዜ? ፈጣሪዕድል? የታሪክ አጋጣሚ? ጉልበት? ገንዘብ ወይንስ የነዚህና የመሰል ቅንብሮች ውሁድ? በዚህ ዓይነት አማርኛን የመጀመሪያ ቋንቋው ያህል አጣርቶ እየተናገረ አማሮችን ሙሉ በሙሉ ለመጨረስ ተነስቶ የነበረው ግን ልቡን አይቶ እግሩን እንደነሳው እባብ የዕቅዱን እኩሌታ እንኳን ሳያከናውን በአጭር የተቀጨው መለስ ዜናዊስ ለምን የአማራው ገዢ መደብ አልተባለም? ከዋሹ አይቀር እንዲያ ማለትም ይቻል ነበር፡፡ ታዋቂው ገጣሚ - ገሞራው - ምን አለ? “ምን ያለ ዘመን ነው ዘመነ ግርምቢጥ፤ ውሻ ወደ ግጦሽ አህያ ወደ ሊጥ፡፡ቀን የሰጠው ዓለምሰገድ ቅሉ በውሸት ቱማታ ጥናት ተብዬ የጠላ ቤት ወሬው የአማራን አከርካሪ ሊሰብር የገማ ብዕሩን ማንሳቱ ማንን ቢንቅ ይሆን? ለነገሩ ከራሱ ሌላ ማንንም ሊንቅ አይችልም - ናቂ ተናቂ ነውና፡፡ በዕብሪተኛው አባቱ ቃል - ‹ወራዳ ነው › - እደግመዋለሁ - ‹ወራዳ ነው› - እንዳልለው ከጨዋነት አንጻር ትዝብት ውስጥ ሊጥለኝ ይችላልና ለፈጣሪ ብቻ እተወዋለሁ፡፡ [ከጠባብ ጎስኛ የባእድ ቅጥረኛ ጠላት ይሠውራችሁ!]
  ለአንዱ ጓደኛየ ይህን ጉዳይ ስነግረውይህ የውሻ ልጅ ያላለው ነገር የለም በለኛቢለኝ ጊዜአይ፣ ተው ስድብን ለሰዳቢ መተው እንጂ ሲሳደቡ አብሮ መሳደብ ከትሁት ሰው አይጠበቅምብዬ አበረድኩት፡፡ለዚህ የሳዋ ቤት ቱሪናፋው ደግሞ ታሪካዊ ጠላቶቻችን የገንዘብ ድጋፍ አድርገውለት እኮ ይሆናል›  አለኝና በማከልምስሜትና የቡና ቤት ቃርሚያ መሆኑን እያወቁ እንዲያ አድርገው ከሆነየጠላትህ ጠላት ወዳጅህ ነውከሚለው እሳቤ በመነሳት መሆን አለበት፡፡ አለበለዚያ ቃለ መጠይቅና የቡና ላይ ጨዋታ ተይዞ ወይም አንድ ሰው በራሱ ተነሳሽነት በጽሑፍም ይሁን በቃል፣ በጠባብ መድረክም ይሁን በሰፊ አደባባይ ያንጸባረቀውን ሃሳብ በዋቢነት እየጠቀሱ ከደንብ ውጪ ሰውን ማሳሳት ተገቢ አይደለም ብቻ ሳይሆን ሪሰርችን መግደልና ተኣማኒነቱን ማሳጣት ነው፡፡አለኝ፡፡ እኔም ሌላ ሃሳብ አስከተልኩ፡- እገሌ እንዳጫወተኝአፄ / ሥላሴ አሥመራ ላይ በሕዝብ ፊትኤርትራ መሬቷን እንጂ ሕዝቧን አንፈልግምብለው ተናግረዋል፣ ወዘተ. የሚል ከአሉቧልታ ውጪ የሚጨበጥ ነገር የሌለው ነገር በጥናት ስም ማውጣት ወንጀል ብቻ ሳይሆን ሥርየት የሌለው ኃጢኣትም ነው፡፡ ጊዜ ሰጠኝ ብሎ ያለ የሌለ ዕድፍን በሕዝብ ላይ መለደፍ አይነጋ መስሏት ቋቷ ውስጥ የዓለምሰገድን የሚመሰል ቆሻሻዋን እንዳስቀመጠችው ሴት መሆን ነው፡፡ ነውርን ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ ዝንታለሙን ይሉኝታቢስ መሆን ከሰውነት ተራ መውጣት ይመስለኛል፡፡ ሁሉም ነገር ያልፋል፡፡ መጽሐፍ የያዘው ነገር ግን በቀላሉ አያልፍም፡፡ እስከወዲያኛው ያስተዛዝባል ከዚያ ያለፈ መዘዝም ሊያስከትል ይችላል፡፡ አንዴ ከመናገርህ ሁለቴ አስብ የሚባለውም ለዚህ ነው፡፡ የጭቃ ጅራፍን ከማንጓት በፊት የምንለው ነገር ሊያመጣ የሚችለውን የዞረ ድምር መመልከት ተገቢ ነው፡፡አልኩት፡፡ [ከጠባብ ጎስኛ የባእድ ቅጥረኛ ጠላት ይሠውራችሁ!]
  ይህን ቆሻሻ መጽሐፍ ሳነብ ጎን ለጎን እያየሁ የነበረው በስሙ እየተነገደበት ያለውን ምሥኪን አማራ ሳይሆን የአሁኑን የትገሬውን የገዢ መደብ ነበር፡፡ የውሻ ልጅ ያላጤነው እንግዲህ ይህን ነውአለና ጓደኛየ ነገር ጀመረኝ፡፡የኔ ዘመዶች ምን እያደረጉ ነው? ይህን ነገር ስለአማሮች ስናገር እነሱንስ አያስወቅስብኝ ይሆን ወይ? ማለት ሲገባ ዐወቀች ዐወቀች ሲሏት የባሏን መጽሐፍ እንዳጠበችው ሴት የራሱን ጉድ ነው የዘከዘከው፤ ትዕቢት ደግሞ ኅሊናን በዕብሪት ሞራ ይሸፍናል፡፡ እንጂ አማራስ ይህ ጭንጋፍ የዘበዘበውን ያህል ኃጢኣት በማንም ላይ ይሠራል ብዬ አላምንም፤ ጥፋት ነበረበት ቢባልም እንኳን በንጽጽራዊ ዕይታ ኢምንት ጥፋትን በብዙ ሺህ ዕጥፍ በሚገመት የጥፋት ቁልል አጠፌታውን በመመለስ አማራን እንደክርስቶስ ይህን ያህል መውገር የፈሪ ዱላ ያስብላል፤ ይህ ነገር ደግሞ ከባህልም ከሃይማኖትም አብሮ ከመኖር የቆዬ ትውፊትም አንጻር ለወደፊቱ አያቀባብርም፡፡ አማራ በአማራነት ተደራጅቶ የማንንም ንብረት አልዘረፈም፡፡ ጥፋት አልነበረም ማለት ግን አይደለም፡፡ አማራ በአማራነት ተሳስቦ ቡድናዊ ጥፋት በማንም ላይ ለማድረስ የሚያስችል ማኅበራዊና ሥነ ልቦናዊ ዝግጅት ባይኖረውም በተናጠል ደረጃ ጥፋት ያጠፉ አማርኛ ተናጋሪዎች መኖራቸው አያጠያይቅም፡፡ ሆኖም ጥፋትን በጥፋት መመለስ ሌላ ሦስተኛ ጥፋት እንዲጸነስ በር መክፈትና በቀለኝነትን ማበረታታትም ነው…” እያለ ያወርደው ገባ - ብሶቱን፡፡ ባላቋርጠው ማቆሚያ ባልኖረው፡፡ ይህ ሰውዬ ብዙ የሀሰት ውንጀላዎችን በአማራው ላይ ደፍድፏል፡፡አማሮች የኤርትራን ንብረት ዘርፈዋል፤ ከጣሊያን መውጣት በኋላ የአየር ላይ በገመድ መንሸራተቻ የትራንሰፖርት መሣሪያዎችን ነቅለው ሸጠዋል…› ብሏል፡፡ እውነት መሆን አለመሆኑን የሚያጣራ ያጣራው - እኔ ግን እንዲህ ዓይነት ነገር ተፈጽሞ እንኳን ቢሆን አማራ ብቻ ተነጥሎ ያን አይሠራም ባይ ነኝ፡፡ ይህ ሰው በዚህ ብቻ አይገታም፡፡ አማራን ለማዋረድ ካለው ያልተገራ ስድ ፍላጎት የተነሳ የኤርትራ ክፍለ ሀገር ሰዎችን እጅግ የሰለጠኑ አድርጎ ሲያቀርብ አማሮችን በዚያው አንጻር እጅግ ኋላ ቀርና ከፍ ሲል እንደተገለጸውእንኳንስ ሌላ ሕዝብ ሊያስተዳድሩ ራሳቸውንም ማስተዳደር አይችሉምበማለት በማይማዊ ድፍረቱ አንጓጧል፡፡ በሌላ ምዕራፍ ደግሞ ኤርትራውያን በጣሊያኖች ሸረኛ አገዛዝ ከአምስተኛ ክፍል በላይ እንዳይማሩ የተደረጉ ማይማን፣ ከተራ የጥበቃና አትክልተኛ ሥራዎች በስተቀር ከፍ ባሉ ቅጥሮች እንዳይመደቡ የሚከለከሉ አላዋቂና የተዘነጉ ዜጎች እንደነበሩ ያወሳል፡፡ ሰውዬው የሚለውን የሚያውቅም አይመስልም፡፡ እዚህ የሚለውን እዚያ ያፈርሰዋል፡፡ በሌላም በኩል አማራውን ገዢ መደብለማንኳሰስ የአፄው ወታደሮች በሸበጥ ጫማ ወደኤርትራ እንደሄዱ ይናገራል፡፡ ቀጥሎም ከመሀል ሀገር ለማስተማር ወደኤርትራ የሄዱ አማሮች በባዶ እግራቸው ክፍል ውስጥ እንደሚገቡና እንደሚያስተምሩ በዚያም ምክንያት የዚያች ግዛት ዜጎች በአማሮች እንደሚያፍሩ ይናገራል፡፡ የሚገርም ነው፡፡ የሁለት ብር የዘመኑን የቻይና ፍራቢ ጫማ አጥተው ባዶ እግራቸውን ወደ ክፍል ገብተው አስተምረው ከሆነ የዚያን ጊዜዎቹ አስተዳደሮች - አሁን በሕይወት ያሉቱ - ሊጠየቁ ይገባል፡፡ ነገር ግን እንደኔ እንደኔ ይህ ዓይነቱ ወሬ ተራ የተርቲብ ወሬ እንጂ በፍጹም እውነትነት ያለው አይመስለኝም፡፡ ያኔ መምህራን ንጉሥ ነበሩ፡፡ እንኳን ያኔ አሁን በባዶ እግራቸው አልሄዱም፡፡ የሚገርም ዓለምሰገድ ነው እባካችሁን፡፡ ይህንን ለይቶለት ያበደን ሰው ጠበል መውሰድና የተሣፈረበት በሚሊዮን የሚቆጠር አጋንንት እንዲወጣለት ማድረግ ከጨዋ አንባቢና ከቅን ቤተዘመድ ይጠበቃልና ሰውዬው በሕይወት ካለ እባካችሁን አትጨክኑበት፡፡ መለስ የአማራ ጥላቻው አናቱ ላይ ወጥቶ በአጭር ተቀጨብን፡፡ የዚሁ ዋልጌ ሟች ጓደኞችም በአብዛኛው ገሣ ለብሶ ከብት ከመጠበቅ ውጪ ሌላው ቀርቶ ከአድማስ ባሻገር ሌላ አገር ያለ በማይመስለው በዚሁ የአማራ ሕዝብ ላይ ጦራቸውን ሰብቀው በምናብም በተግባርም ሊጨርሱት ቢቋምጡም የነሱም የአሁንና የወደፊት ዕጣ የሚያምር አይመስልም፤ አንዱ የአንዱን የቀብር ጉድጓድ መቆፈሩ በእስካሁኑ ሁኔታ የማያዋጣ መሆኑን ያላወቁ ጅሎች ለጊዜው በሚያብለጨልጭ ዓለማዊ ሀብትና ንብረት እየተታለሉ ወንድማቸውን መቅበሩን ተያይዘውታል - እነሱም ተራቸው ሲደርስ የማይቀርላቸው መሆናቸውን ግን ረስተውታል፡፡ ባለጌ ባልጎ ያባልጋል፡፡ ኤዲያ! ሊያልፍ ያለፋል አሉ? ለማንኛውም - [ከጠባብ ጎስኛ የባእድ ቅጥረኛ ጠላት ይሠውራችሁ!]

Wednesday, March 13, 2013

What Is Courage?


Courage is an indispensable yet--even in psychotherapy--surprisingly underrated commodity. Life requires courage. Yet we tend to lose sight of its vital meaning, power and importance. I am not speaking solely here of the obvious physical courage of the daredevil, boxer, soldier or superhero, or the selfless courage of those willing to risk their own skin to rescue others, but of the extraordinary, heroic courage demanded of each of us every day.
Consider the courage it takes to live on this undeniably dangerous planet of ours, where earthquakes, tsunamis, epidemics, volcanic eruptions, tornadoes, hurricanes or a random meteor strike can, at any moment, destroy our dwellings and kill us or our loved ones, Or savagely murdered by some rival tribe or gang, be the innocent victim of a street shooting, school massacre or violent home invasion, or brutally mugged in the park or street. Where routine commercial airplane flights can be hijacked by religious or political fanatics and deliberately crashed into some building or blown out of the sky. Where, as in Japan most recently nuclear reactors catastrophically fail, contaminating our air, food and water. And where a hydrogen bomb in the hands of terrorists or during wartime could instantly vaporize entire cities and precipitate a devastating "nuclear winter" across the planet. A world where, on any given day, we or those we care for could be killed or crippled in a car crash, hit by a bus, or suffer a massive heart attack or debilitating stroke. Or where a fascistic government can for little or no reason have citizens arrested and secretly executed for speaking out, seeking freedom, or simply being of a certain ethnic background. A world, in which famine, drought, rampant unemployment or global economic crisis can profoundly exists threaten not only our way of life, but our fundamental ability to feed our families. Given these terrifying facts of life, how do we muster the courage each day to get out of bed and face such stark, existential reality? Yet, most of us do just that. We get up, get dressed, go to school or work, face the speeding two-ton hunks of shiny steel hurtling down the freeway, the abusive spouse, parent or boss, and the ever-present dangers of participating in this extraordinarily perilous postmodern place. How? Well, for most, the solution is unconsciousness Denial.
The easiest way is to block out our awareness of these ubiquitous existential threats. Then, no courage is really necessary. For where there is no perceived risk, nothing to fear, no threat, who needs courage? But there is definitely a high cost to this strategic unconsciousness: We sacrifice our vitality, self-awareness, sensitivity and capacity to fully experience our environment in all its volatile terror, beauty and wonder. Of course, we all need some sense of comfort, safety and security in life. Such self-deception serves this defensive purpose, and is, to some extent, psychologically sound. Too much reality can be overwhelming for the fragile human psyche. Yet, this universal tendency toward rendering ourselves oblivious or blind to life's inherent, riskier ness can itself be seen as a failure of courage.
What is courage? Courage is a kind of strength, power or resolves to meet a scary circumstance head on. Courage is called upon whenever we confront a difficult, frightening, painful or disturbing situation. When our resources are challenged or pushed to the absolute limit. When we have been felled threatened weak, vulnerable, intimidated or terrified. When our first instinctive reaction is to flee at such times, life is begging an existential question of us: Can we find the courage to face and defeat our fear, or will we be defeated by it? Can we call forth what theologian Paul Tillich called our "courage to be“? Or will we cowardly choose instead, as Shakespeare's Hamlet deliberates, "not to be"?
Courage is of course, synonymous with bravery and fortitude. But today, we have lost the true essence of courage. The word courage comes from the French root cour or coeur, which means heart. So courage has to do with the heart, that vital muscle that keeps our blood flowing and sustains life. Symbolically, the heart represents the spiritual core or innermost center of feelings, especially eros. Many centuries ago, the concept of courage referred to the emotions, feelings or daimonic passions in general, including lust, love, anger or rage. Love and sexual passion can be the catalyst for courageous action. A mother's love for her children can lead to courageously laying her life down to save her offspring. Falling in love and sexual lust encourage us to reach out to one another and risk relationship. And platonic love and compassion encourages us to selflessly help those less fortunate than ourselves, say, as in the case of Mother Teresa.
The connection between anger, rage and courage (cou-rage) is especially key: Courage often requires the energizing, fortifying daimonic affects of anger or rage to precipitate fuel or sustain it. As Rollo May (1981) explains, "Encountering one's destiny requires strength, whether the encounter takes the form of embracing, accepting, or attacking. . . . Constructive anger is one way of encountering destiny." And, I would add, of generating courage. As well as countering apathy, depression and despair. Today, this more complex understanding of courage persists when we refer to someone very brave as "having a lot of heart," i.e., being intensely passionate. Mel Gibson's character, hot-tempered Scottish freedom fighter William Wallace in Braveheart (1995) is a fine example of such raging courage.
Courage is required in almost every basic human activity or endeavor. For instance, to allow oneself to love and commit to another person takes immense courage. Separating from our parents and forging an independent life for ourselves is a courageous act. To survive an abusive, traumatic or neglected childhood with some sense of dignity and integrity intact demonstrates tremendous courage and resilience. Getting old demands courage (“Staring at Sixty.") It takes courage to authentically be oneself in the world, and, as May (1976) points out in The Courage to Create, to dare to be truly creative, to artistically express and expose one's innermost self. Career or relationship changes require courage as is pursuing one's fondest dreams, or, as Joseph Campbell put it, to "follow your bliss." Indeed, it takes terrific courage to live, and to do so creatively, lovingly, meaningfully and productively.
Courage also comes into play when morality and spirituality are at stake. Moral or spiritual courage is what motivates us to do the right thing, to right or wrong, to take a stand for some dearly held moral principle or spiritual value despite the personal pride or public opinion. This kind of courage is exemplified by Jesus of Nazareth's crisis of courage in the Garden of Gethsemane ("O my Father, if it is possible, let this cup pass from Me.") and Mahatma Gandhi's or Martin Luther King's commitment to passive, non-violent resistance. Standing up to evil and fighting for what we truly believe in takes moral courage, especially when it places one's own physical safety or that of one's family at risk. Spiritual or moral courage is what allows us to acknowledge our human failings, weakness and fears, and accept rather than conceal them behind a facade of macho bravado or spiritual pretension. Paradoxically, it can be a courageous and encouraging act to confess our vulnerability, sensitivity, anxiety or despair to others Evil deeds, such as mass murders or serial killings, may seem to some to take courage. But such courage is pathologically displaced and perverted. These cowardly violent perpetrators failed or refused to muster the courage to establish a place in and constructively contribute to society. Theirs is a wicked rage for recognition. Suicide can, in some extreme situations, take courage, but, more often than not, is more a manifestation of cowardice than courage. The same may be said of nihilism, a deeply discouraged, sweeping negation and devaluation of life as meaningless. "Courage," writes Tillich (1952), "is the power of life to affirm itself in spite of . . . ambiguity, while the negation of life because of its negativity is an expression of cowardice." Courage is needed to tolerate and, as much as possible without pathologically distorting reality, transform meaninglessness into meaning. For, as C.G. Jung concludes, "Man cannot stand a meaningless life."
We need courage to constructively encounter fates, defeat despair, and to heroically find and fulfill our destiny. For example, when composer Ludwig van Beethoven discovered he was losing his hearing at the age of twenty-eight, he became understandably depressed about his unfortunate fate. He fell into despair. Then rage. And eventually, his anger gave him the courage needed to encounter his fate and fulfil his musical destiny, resolving to "raise superior to every obstacle" and "take Fate by the throat." Despite total deafness, Beethoven bravely went on to compose his most heroic and beautiful music right up until his death at fifty-seven.
Courage learns the "Cowardly Lion" in the classic film The Wizard of Oz (1939), is something without which we can have no real self-esteem, pride or power, and must ultimately come from within rather than without. He is so guilt-ridden and ashamed of his own fear, anxiety and perceived cowardice that he cannot recognize his innate courage as he bravely accompanies Dorothy and Toto to see the Wizard of Oz. As he is finally wisely counseled by the Wizard, fear, fleeing and inaction is not necessary to be equated with cowardice. For, as the saying goes, "Discretion can often be the better part of Val our."  Sometimes it takes more courage to tactically back away from a confrontation than to mindlessly attack to stand down rather than further escalate a treacherous crisis. The part of wisdom is, knowing when to do, which to be able to consciously pick and choose our battles rather than unconsciously or impulsively reacting.
Courage is not the absence of fear, but moving ahead despite fear. For if there is no fear, which needs courage? Of course, encouragement--the supportive provision of exhortation-- can, as in the movie, be sought and received, and much of psychotherapy consists of such clinical encouragement to face, accept and fight to become one's self in the world. Indeed, Alfred Adler recognized that one of the most common underlying conditions in patients seeking psychotherapy is discouragement. In this sense, the "great and powerful" Wizard of Oz is an archetypal representation of the psychotherapist, upon who much power and wisdom is projected by the patient. And, as the timeless story makes clear, seeking such professional assistance is itself an act of courage, a bold and decisive step toward healing and wholeness.
Fascinatingly, in L. Frank Baum's book (1900), upon which the film was based, the Wonderful Wizard of Oz prescribes a potion to bolster the Cowardly Lion's courage. Alcohol has traditionally been referred to as "liquid courage," but, of course, its fortifying effects last only as long as intoxication. Psychiatric medications many of which, whether recognized or not by physicians, are external sources of "biochemical courage"-- are widely prescribed today for depression, phobias, anxiety disorders, psychosis and other fundamentally discouragement-related symptoms and syndromes. In the positive sense, these drugs can, for many, temporarily provide the courage to survive devastating traumas and deal with reality rather than escaping from it. But ultimately, courage must be discovered internally, and seems to spring from a place in us we previously never knew existed, some secret reservoir or inner source of strength, sustenance and steeliness in the face of life's inevitable catastrophes, frustrations and disappointments.
In the final analysis, courage is essentially an existential choice. Courage is the empowering experience of a decision to stand up and withstand the "slings and arrows of outrageous fortune." And, when wounded or knocked down, to pick oneself up, dust oneself off, and "keep on keep in' on." A choice to stand and fight when appropriate, rather than run to tolerate or attack rather than cower and withdraw, to persevere rather than quit, to act with integrity rather than expedience, to take responsibility rather than slough it off, to embrace reality rather than retreat from it, to move forward in life rather than regress or stagnate, to create rather than destroy, to love rather than hate, to deal with one's demons rather than not to consciously face the existential facts of suffering, infirmity and death rather than denying them. If truth be told, the archetypal virtue of courage--true courage rather than mere bravado--is a prime determinant of what we do with life. And what we don't do with it. And of how we feel about ourselves. Like the Cowardly Lion, who constantly looks for courage outside himself, we may already be more courageous, more heroic, than we imagine. Acknowledging our past acts of courage, tapping into our innate capacity to be courageous, and seeking professional encouragement, when needed is a constructive means of marshaling the requisite courage to face the sometimes daunting past, present and future, whatever it may bring. 


Thursday, March 7, 2013

ዲግማዊ አፄ ሚኒሉክ በታላቁ የጃን ሜዲ ጉባኤ ሊይ ያስተላለፉት መልእክት


ከአፈወርቅ ዘብሄረ ዘጌ 1906 .
በሮማ ከተማ ከታተመ
ዳግማዊ አጤ ሚኒሌክመፅሀፍ የተወሰደ

አፈውርቅ ይህን የዳግማዊ አጤ ሚኒሊክን የምክር አዋጂ ያገኙት መፅሃፋቸዉን ከመጨ ረሳቸዉ በፊት ከእንድ ጃንሆይንና ኢትዮጵያን ከሚውድ ወዳጃቸዉ እንደሆነ ይገልጡና

ኢትዮጵያን የወደደ የኢትዮጵያን መልማት የኢትዮጵያን ደስታ የኢትዮጵያን ትልቅነት የወደደደ ሰዉ ይሄን የጃንሆይን ቃል አዝኖ ተክዞ መቀበል ይገባዋል እዝኖ ተክዞ ማለቴ እንዲህ ያለ እናት ንጉስ የሞቱን ነገር አስቦ ለኢትዮጵያ የሚበጀዉን አዉቆ እንዱህ ያለ የተገባ የጣፈጠ ከልብ ጠልቆ የሚገባ ምክር ለህዝቡ መስጠቱ ተሞቱም በሁዋላ ለኢትዮጵያ የሚሆነዉን ላገር የሚጠቅመውን ለህዝቡ የሚያከብረዉን ነገር ማሰቡና መምከሩ እጅግ ያሳዝናል ማለቴ ነዉ

ይሉና ሙሉውን የጃንሆይን መልእክት እንዲህ አስቀምጠዉታል::

የጃንሆይ የዳግማዊ ሚኒሊክ ቃል::

1906 ዓመተ ምህረት ግንቦት 10 ቀን አዲስ አበባ ጃን ሜዲ ከሚባል ሥፍራ ጉባኤ ተደርጎ ዲግማዊ ምኒሊክ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ያዘዙት ቃል ይህ ነዉ::

ያገሬ የኢትዮጵያ ሰዎች ልጆች ወዳጆች እግዚአብሔር የገለፀልኝን ምክር ልምከራችሁ ምክሬንም እግዚአብሔር በልባችሁ እንዲያሳድርባችሁ ተስፋ አደርጋለሁ::

አፄ ቴወዴሮስ የሞቱ ጊዜ ከሳቸዉ ጋር የነበርው ሰዉ ሁለ ያንዱን አገር አንዱ እደርባለሁ አንዱን ገድዬ እኔ ጌታ እሆናለሁ እያለ ሁለም ላይረባ ተላል ቀረ::

ከዚህም በኁዋላ ያፄ ዮሃንስ ሰዉ የሆነዉን የምታዉቁት ነዉ ባገር በሽታ ሳይገባበት ሌላ የባእድ ጦር ሳይነሳበት በምቀኝነት እርስ በርሱ አንደተላለቀ አይታችሁታል::

አሁንም ልጆቸ ወዳጆቸ አንዱ ባንዱ ምቀኝነት ይቅር ያንዱን አገር አንዱ እኔ እደርባለሁ እንዳትባባሉ እኔ እስካሁን በፍቅር እንዳኖርኩዋችሁ እናንተም ተስማምታችሁ በፍቅር እንዴትኖሩ እለምናችኁዋለሁ::

እናንተ አንድ ልብ ከሆናችሁ በምቀኝነት እርስ በርስ ተዋግታችሁ ካላለቃችሁ በቀር አገራችን ኢትዮጵያን ለሌላ ለባእድ አትሰጥዋትም ክፉም ነገር አገራችን አያገኛትም ነፋስ እንዲይገባባችሁ አገራችሁን በያልችሁበት በርትታችሁ ጠብቁ ወንድሜ ወንድሜ እየተባባላችሁ ተደጋገፉ የኢትዮጵያን ጠላት ተጋግዛችሁ ተድንበር መልሱ:: የኢትዮጵያ ጠላት ባንደ ወገን ትቶ ባንደ ወገን ቢሄድና ድምበር ቢጋፋ በኔ ወገን ታልመጣ ምን ቸገረኝ ብላችሁ ዝም አትበሉ ጠላት በመጣበት በኩል ኁላችሁም ሂዳችሁ አንድነት ተጋግዛችሁ ጠላታችሁን መልሱ እስከ እየቤታችሁ እስቲመጣ ዝም ብላችሁ አትቆዩ

ይህነን ምክር መስጠቴ እኔማ በእግዚአብሔር ቸርነት ይህን ያህል ዘመን ገዝቸ የለምን ነገር ግን ሰዉ ነኝና እንግዲህ እስንት ያህል ዘመን እቆያለሁ ስል ነዉ አሁንም እኔ እንደተምኘሁት እግዚአብሔር የትጨ መረበትና ፈቃደ ሆኖ ልጀን ቢያቆምላችሁ ከልጀ ጋር ሁናችሁ አገራችሁን ጠብቁ አደራ ብያችኁአለሁ አደራ የሚያኖሩበት ሰዉ የታመነ ስለሆነ ነዉ አሁንም እኔ እናንተን አምኘ ልጀን አደራ ብየ እሰጣችሁአለሁና አሳድጉት በብልሀት ምከሩት በጉልበት እገዙት በምክር ደግፉት ልጀን አደራ መስጠቴ ከልጀ ጋር ኢትዮጵያን አደራ ጠብቁ ማለቴ ነዉ እኔም ይኽዉ በገዥዎች አለማወቀ በሕዝቡ አለመስማማት የተነሳ ተብዙ ዘመን ጀምራ ተከፋፍላ የነበረችዉን አገራችነን ኢትዮጵያን ማስኘ ተጣጥሬ ይኽዉ አስፍቻታለሁ እናንተም ከልጀ ጋራ ሁናችሁ ተስማምታችሁ የኢትዮጵያ ድንበር እንዲሰፋ እንጅ አንድም ጋት መሬት እንዲይጠብ አድርጉ ጠብቁ አልሙየደጊቱ አገራችን የኢትዮጵያ እምላክ ይገዛችሁ  ይጠብቃችሁ::

ከዚሕ ቃል የወጣ በሰማይም ነፍሱ በምድርም ስጋዉ ልጅ እስከ ልጅ ልጁ የትርገመ ይሁን የኢትዮጵያ ወቃቢ ያጥፋው እኔም ሳለሁ ከፈቃዴ የወጣውን እረግሜአለሁ::

ማስታወሻ
አቤት ታላቅነት አቤት አርቆ አስተዋይነት አቤት የሐገርና የወገን ፍቅር እንዴት
መታደል ነዉ እንደነብይም ያደርጋል ለነገሩ እግዚአብሔር የገለፅልኝን ምክር ብለው የል
ብቻ ምን ያደርጋል ከምክራቸዉ ስለወጣን የተረፈን እርግማኑ ነዉ::

ወንዴማገኝ